Friday, December 18, 2015

የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት ጦር ኃይል ላይ ባደረሰው ጉዳት የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና በርካታ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

pow-and-medic-3_xlarge
የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት መተማ አካባቢ በአንድ ግንባር ላይ ብቻ በህወሓት ጦር ኃይል ላይ በፈፀመው ጥቃት የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና በርካታ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ከማክሰኞ ዕለቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃት በኋላ የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኛ ወታደሮች ተሞልቶ ሲቪሎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ 
የሆስፒታሉ ምንጮቻችን እንደገለፁት እስከ ትናንትና ድረስ ከ40 በላይ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና የቁስለኞች ቁጥር ቢያንስ በየአንድ ሰዓት ልዩነት እየጨመረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አንድ የሸዲ ነዋሪ ከየቦታው የተለቃቀሙ ከ26 በላይ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከቱን መስክሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት ጦር ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ 36 አውቶብስ ሙሉ ፌደራል ፖሊስ በመተማና በዙሪያዋ ተራግፏል፡፡

No comments:

Post a Comment