
አንዳንድ የአዲስ አበባ ወጣቶች የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም የተቃውሞ አጀንዳዎችን በመሳብ ችግር ሊፈጠር ይችላልበሚል ፖሊሶች ያለ እረፍት ስራቸውን እንዲሰሩ ታዘዋል፡፡ የአመት እረፍትና ፍቃድ ተከልክሏል፡፡ምናልባትም አደጋው ከእስካሁኑ የከፋ ሊሆን ስለሚችል በየወረዳው ያሉ የመንግስት ተቃዋሚ የሚባሉ ወጣቶች ላይ ልዩ ክትትልና ጥበቃ እንዲያደርጉ በስብሰባ መመሪያ ተላልፏል ሲል አንድ ቅርበት ካለው የፖሊስ ምንጭ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተለይ በጎንደር በሚሰጠው መሬትና በኦሮሚያ ክልል በሚወሰደው ሀይል የጉዳዩ አሳሳቢነት ጨምሯል ሲል የገለጸው ምንጫችን ይህንን የሚመሩት የተቃዋሚ ፓርቲ ሀይሎች ዋነኞቹን በየ ሰፈሩ የመለየት ስራ እንዲሰራ ጥብቅ ትህዛዝ ተነግሯል፡፡ በማለት ከፖሊስ ውስጥ በተገኘው ጥቆማ ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment