Thursday, December 3, 2015

በጎንደር ከተማ በሚገኘው የህወሓት ወህኒ ቤት ዛሬም በርካታ እስረኞች በጥይት ተጨፈጨፉ፤


በጎንደር ከተማ የሚገኘው የህወሓት ግዙፍ ወህኒ ቤት በእሳት ከነደደ በኋላ ከጥይት እና ከእሳት ቃጠሎ የተረፉት እንዲሁም በተጨማሪ ማምለጥ ያልቻሉት እስረኞች ከከተማው ውጭ በአንገረብ ወንዝ ግድብ አቅራቢያ ወደሚገኝ ሌላ አዲስ ወህኒ ቤት የተዛወሩ ሲሆን እስረኞቹ ቃጠሎው ከተነሳበት ማክሰኞ እለት ጀምሮ ምግብና ውሃ ፈፅሞ አልተሰጣቸውም፡፡
በዛሬው ዕለት የእስረኞች ቤተሰቦች እንዳይጠይቁ በመከልከላቸው ምክንያት በአዲሱ ወህኒ ውስጥ ከፍተኛ አመፅ ተነስቶ ከአስር በላይ እስረኞች ተገድለዋል፤ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፤ ወህኒውን ሰብረው ያመለጡም እንዳሉም ታውቋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በክልሉ አስተዳደር ላይ ምንም አይነት እምነት በማጣቱ ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ያሉበት ጦር ከሁመራና ከሌሎች የትግራይ አካባቢዎች አጓጉዞ ጎንደር ከተማን ወሯታል፡፡ በመሆኑም በጎንደር ከተማ ሊፈነዳ የተቃረበ የህዝባዊ አመፅ ውጥረት ነግሷል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ተበጥብጦ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ አጥሩ ዙሪያውን በህወሓት ታማኝ ጦር ተከቧል፡፡
የጎንደር ከተማ በየደቂቃው የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ድምፅ የሚደመጥባት ታላቅ ጦር ሜዳ ሆና ትገኛለች፡፡

No comments:

Post a Comment