Wednesday, December 30, 2015

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወጣቶቸ እያደኑ ማሰራቸውን ቀጥለዋል።


ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ እንደገና ባገረሸበት ማግስት አመጹን ደግፈዋል በሚል በክልሎች እና በአዲስ አበባ የተለያዩ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። በአንቦና ወለጋ ዩኒቨርስቲዎች በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያው የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ ከሚታወቁት መካከል ደግሞ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ዮናታን ተስፋየ በደህንነት ሃይሎች ታፍኖ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስዶ ታስሯል።
ዮናታን ባለፈው ግንቦት ተደርጎ በነበረው ምርጫ ሰማያዊውን በመወከል ባደረገው የምርጫ ክርክር ብዙዎች ድጋፋቸውን ሰጥተውት ነበር። ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋውና ፍቅረማርያም አስማማው ሰላማዊ ትግል ታጋዮችን ከማስበላት በስተቀር ለውጥ አያመጣም በሚል ሰማያዊ ፓርቲን ከለቀቁ በሁዋላ አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ሲሄዱ መንገድ ላይ መያዛቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ጓደኛቸው ዮናታን ተስፋየ ግን በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት ይቻላል በሚል በፓርቲው ውስጥ ታቅፎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ወጣት ዮናታን፣ የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ማንሳታቸው ተከትሎ በሚሰጣቸው አስተያየቶች ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ሲደርሱት ቆይቷል።
ከወጣት ዮናታን በፊት በማህበራዊ ሚዲያዎች የጎላ ተሳትፎ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ተይዞ ታስሯል።
መንግስት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ የኦፌኮ አመራር የሆኑትን እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ከ5 ሺ በላይ የኦሮሞ ወጣቶችን አስሯል። ከ124 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ በጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል።

የዞን 9 ጦማርያን ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ በጠቅላይ ፍ/ቤት ተቀባይነት በማግኘቱ ጦማሪያኑ ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ




የከፍተኛው ፍ/ቤት የዛሬ 3 ወር ገደማ በነፃ ያሰናበታቸው የዞን 9 ጦማርያን ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ በጠቅላይ ፍ/ቤት ተቀባይነት በማግኘቱ ጦማሪያኑ ለታህሣሥ 20 እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በጦማሪያኑ ላይ የሰጠውን ብይን በመቃወም አቃቤ ህግ ይግባኝ የጠየቀባቸው ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፉ በርሄና ክሱ ከሽብር ወደ ወንጀል የዞረለት በፍቃዱ ኃይሉ በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት ከጠዋቱ 2፡30 ለቃል ክርክር ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የከፍተኛው ፍ/ቤት ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጦማርያኑ በአቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ማሰናበቱ የሚታወስ ሲሆነ አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ ጥቅምት 8 ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባለ 11 ገፅ የይግባኝ ማመልከቻ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡
ለ17 ወራት በእስር ላይ የቆዩት ጦማርያኑ፤ ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም ከማረሚያ ቤት መውጣታቸው ይታወሳል።
ጦማርያኑ የተከሰሱት የፀረ ሽብር አዋጁን በመተላለፍ፣ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም በማቀድ፣ በመዘጋጀትና የሽብር ተሳትፎ በማድረግ በአሸባሪነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ተሳትፈዋል፤ ስልጠናም ወስደዋል በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል ጦማርያኑ ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ ቢሞክሩም መ/ቤታቸው ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልፀዋል፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በኬሚካል ኢንጅነርነት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው አቤል ዋበላ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ ወደ ስራ ገበታው ለመመለስ ቢፈልግም አየር መንገዱ ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡
ፍ/ቤቱም አየር መንገዱ ታህሣሥ 22 ቀርቦ ምላሽ እንዲሰጥ አዟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ CPJ አስታወቀ


ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቀሶ የነበረዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ መቀመጫዉን በዚህ በአሜሪካ ያደረገዉ CPJ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሰኞ አስታወቀ. በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለእስር የተዳረገዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራው በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ተቋሙ ጥሪዉን አቅርቧል. በአንድ ሳምንት ዉስጥ ለእስር ሲዳረግ ሁለተኛ ጋዜጠኛ የሆነዉ ጌታቸዉ ሽፈራዉ, ባሳለፍነዉ አርብ ወደ ቢሮዉ በማምራት ላይ እንዳለ በጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን, ጋዜጠኛዉ በነገረ-ኢትዮጵያ ላይ በዋና አዘጋጅነት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል. ጋዜጠኛዉ ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ምርመራዉን አልጨረስኩም በሚል የ 28 ቀን የተጨማሪ የምርመራን ጊዜ ጠይቆ ፍርድ ቤት ይሁንታን ሰጥቷል. የጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፍራዉ እስር ግልጽ አለመሆኑን ያስታወቀዉ CPJ ጋዜጠኛዉ የበረካታ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን የፍርድ ሒደት እንዲሁም በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰዉን ተቃዉሞ ሲዘግብ መቆየቱን አዉስቷል. ይኸዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ጋዜጠኛዉ ለእስር የተዳረገበትን ምክንያት ለማወቅ ለመንግስት ባለስልጣናት ጥያቄን ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን አስታዉቋል. በአዲስ አበባ ማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት ምርመራ እየተካሄደበት የሚገኘዉ የነገር-ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ምርመራዉ ከተጠናቀቀ በኋላ በተለመደዉ የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችል CPJ ባወጣው መግለጫው አመልክቷል. ሰማያዊ ፓርቲ ለንባብ በሚያበቃዉ ነገር-ኢትዮጵያ ላይ በዋና አዘጋጅነት ሲያገለግል የነበረዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ በአሁኑ ወቅት በማንም እንዳይጎበኝ ተደረጎ እንደሚገኝምታውቋል. ባለፈዉ ሳምንት በኦሮሚያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያ በማገልገል ላይ የነበረዉ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ምርቃና ለእስር መዳረጉ ይታወሳል. ይህ በእንዲህ እንዳለ ከወራት በፊት ከተመሰረተባቸዉ ክስ በነጻ የተሰናበቱት አምስት ጦማርያን ከነገ-በስትያ ረቡዕ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መጠራታቸዉን አሳስቦት እንደሚገኝ CPJ ሰኞ አክሎ ገለጿል. ከሳሽ አቃቤ ህግ ጦማሪያኑ በነጻ እንዲሰናበቱ የተላለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ እንደሚያቀርብ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን የጦማሪያኑ ክስም በድጋሚ ሊታይ ይችላል ተብሎ መጠበቁን ከሀገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል. በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በሶስተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘዉ ኢትዮጵያ 10 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል.

Tuesday, December 29, 2015

ኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ500 በላይ አባላት ታስረውብኛል፣ ግጭቱን ተከትሎ እስከ 4ሺ ሰዎች ታስረዋል አለ


ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ እንደዘገበው:-
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባና 6 ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ500 በላይ አባላት ሰሞኑን እንደታሠሩበት ፓርቲው ገለፀ፡፡ የኦፌኮ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ ጉርሜሣ አያኖ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር፣ አዲሱ ቡላላ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ደረጀ መርጋ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ፣ መ/ር አለሙ አብዲሳ ፀሐፊ፣ መ/ር ታሪኩ ኦዲተር፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ ም/ዋና ፀሐፊ እንዲሁም አቶ በቀለ ገርባ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሰሞኑን በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡
ከፓርቲው አማካሪ ም/ቤት አባላት መካከልም የታሠሩ እንዳሉ የገለፁት ዋና ፀሐፊው፤ ከዞን አመራሮች የቄለም ወለጋ ዞን አመራር አቶ መሠረት ዳባ፣ የምስራቅ አርሲ ዶዶላ አመራር አህመድ ኢቦ፣ የባሌ አመራር አቶ ሁሴን አምዳ፣ የሆሮ ጉዱሩ አቶ ደገባስ ዋቀዩ፣ የኢሊባቡር አመራር አቶ እስማኤል ሁሴንና አቶ ያዛቸው አብዲሣ ታስረዋል ብለዋል፡፡
የወረዳ አመራሮችና ባለፈው ግንቦት በምርጫ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጨምሮ እስከ 500 የሚደርሱ የፓርቲው አባላት በተለያዩ አካባቢዎች መታሠራቸውን አቶ በቀለ ገልፀው፤ ፓርቲው ባለው መረጃ መሰረት በአጠቃላይ ተቃውሞውን ተከትሎ የታሠረው ሰው ብዛት እስከ 4ሺ ይደርሳል ብለዋል፡፡
ከ300 በላይ የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች እንዳሉ የተናገሩት ዋና ፀሐፊው፤ በግጭቱ የቆሰሉ ከ1500 በላይ ተጎጂዎች በወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በሚኒልክና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል

በጎንደሩ የህወሓት አገዛዝ ግዙፍ ወህኒ ቃጠሎ ምክንያት ያመለጡ እስረኞችን በማደን ላይ የነበሩት ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ጥቃት ተፈፀመባቸው፡፡


የህወሓት አገዛዝ ፖሊሶችና ታጣቂዎች በአምባ ጊዮርጊስ ጀጀሆ ከፍተኛ አሰሳና የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪ ሲያስጨንቁ የሰነበቱ ሲሆን በመጨረሻም አንድን የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ ግለሰቡ ድንገት በከፈተባቸው ተኩስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ግለሰቡም ገድሎና አቁስሎ ለመሰወር ችሏል፡፡
በግለሰቡ ከተገደሉት ታጣቂዎች መካከል አስማማው ሀብቴ የተባለው ሲገኝበት አስከሬኑ በጭልፎ ወንዝ ባለእግዚአብሄር ተቀብሯል፡፡ መኩሪያው የተሰኘው ፖሊስ ደግሞ በጠና ቆስለው የመዳን ተስፋ ከሌላቸው መካከል አንዱ ነው፡፡
በህዳር ወር መገባደጃ ላይ በጎንደሩ የህወሓት ወህኒ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት በርካታ እስረኞች ማምለጣቸውና በጥይት መጨፍጨፋቸው አይዘነጋም፡፡

ሱዳን ፣ግብፅና ኢትዮጵያ በካርቱም ሲያደርጉ የቆዩትን የሶስትዮሽ ውይይት በስምምነት ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል


ሱዳን ፣ግብፅና ኢትዮጵያ በካርቱም ሲያደርጉ የቆዩትን የሶስትዮሽ ውይይት በስምምነት ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል ።የውይይይቱን ማዕቀፉችን ስምምነት ያረፈባቸውን ነጥቦች ሳይጠቅሱ አንዳንድ ኮካዎች የባድመን ተወሰነችልን ሊደግሙብን ዳር ዳር እያሉ ነው ።
ከካርቱም የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ከሆነ ስምምነት የተደረሱባቸው ነጥቦች በአብዛኛው ግብፃውያንን ጮቤ ያስረገጡ ሆነዋል ።
1)በማርች ወር የሶስቱ አገራት ፕሬዝዳንቶች ያፀደቁትን ደንብ በስራ ላይ ለማዋልናአስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ደንቡን ለመሰረዝ ተስማምተዋል ።ግብፅ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ደንብ እያከበረች አይደለም በማለት ስሞታ ስታቀርብ መቆየቷ አይዘነጋም ።
2) በግድቡ ዙሪያ የሚደረገው ጥናት በስምንት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።ይህም በቅርብ ግዜ ውስጥ ግድቡ በተወሰነ ደረጃ ውሃ ተሞልቶ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ይጀምራል ሲሉ ለነበሩ መልካም ዜና አይደለም ።
3) አጨቃጫቂ ሆኖ የቆየው አዲስ አጥኚ ቡድን መቅጠር የግብፅ ተደራዳሪዎችን ባስደሰተ መልኩ እልባት በማግኘቱ በሆላንዳዊው ካምፓኒ ቦታ ሌላኛው የፈረንሳይ አጥኚ ካምፓኒ አርቴርሊያ ተተክቷል ።በሆላንዳዊው ካምፓኒ ደስተኛ ያልነበሩት ግብፁች እሰይ ስለቴ ሰመረ ማለት ጀምረዋል ።
የግብፁ አቡ ዛኢድ ስለዛሬው ስምምነት ለአገራቸው ሚዲያ “የዛሬው ሁኔታ ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ነው “ብለዋል ።
4) ግብፅ ለታችኛዎቹ የተፋሰስ አገራት ከግድቡ የሚወጣው ውሃ የቀድሞ መጠኑን ሳይቀንስ እንዲወርድ የግድቡ በሮች ብዛት እንዲኖራቸው መጠየቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሳምንት የቴክኒክ ምክክር ለማድረግ ተስማምታለች ።
5)የውይይቱ ዋነኛ መከራከሪያ የነበረውም ኢትዮጵያ ለአምስት ተከታታይ አመታት ግድቡን በውሃ ለመሙላት መዘጋጀቷን መናገሯ ነበር ።ግብፅ ውሃ መሙላቱ ቢያንስ ለስምንት ወራት የተቀጠረው የጥናት ቡድኖቹ ሪፖርት እስኪቀርብ እንዲዘገይ በመጠየቅዋ ውሃ መሙላቱ ይዘግይ ተብሏል ።

በድርቁ ምክንያት 400ሺ ህጻናት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው፣ አንድ ሚሊዮን ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከ 400ሺ የሚበልጡ ህጻናትን ለአሳሳቢ የጤናና የአካል ችግር አጋልጦ እንደሚገኝና ጉዳት የሚደርስባቸው ህጻናት ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።
ለተረጂዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ በመቅረብ ላይ አለመሆኑ ችግሩን እያባባሰው እንደሆነም ድርጅቱ ገልጿል። ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ወደ ግማሽ የሚጠጉት ህጻናት መሆናቸውን ያስታወቀው ዩኒሴፍ ከእነዚሁ መካከል ከ 400ሺ የሚበልጡት ለከፋ የጤናና የአካል ጉዳይት ተዳርገው እንደሚገኙ አመልክቷል።
የህጻናቱ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ሲገልፅ የቆየው ይኸው ተቋም፥ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የህጻናቱን ህይወት ለመታደግ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በቀጣዩ ጥቂት ወራቶች ውስጥ የተረጂዎች ቁጥር ወደ15 ሚሊዮን ያሻቅባል ተብሎ በመጠበቁም ለጉዳት የሚጋለጡ ህጻናት ቁጥርም አብሮ እንደሚጨምር ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በድርቁ ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ መድረሱን ያወሳው ድርጅቱ በሀገሪቱ ያለዉ የድርቅ አደጋ ከተገመተዉ በላይ መሆኑንም አመልክቷል።
የህጻናት አድን ድርጅቶች ጥምረት በበኩሉም ልዩ ድጋፍና ክትትልን የሚፈልጉ ህጻናት በቂ ድጋፍ እያገኙ አለመሆኑ ስጋት መፍጠሩን ገልጿል።
ይኸዉ ከ180 በሚሆኑ ወረዳዎች ዉስጥ ተከስቶ ያለዉ የድርቅ አደጋ እስከቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድርስ ቀጣይ በመሆኑም አስከፊ የጤናና የአካል ጉዳት የሚደርስባቸዉ ህጻናት ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጥምረቱ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የአለም አቀፉ ማህብረሰብ የገባዉን ቃል ባለመጠበቁ ሳቢያ ቸግሩ እየተባባሰና የተረጂዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን በደጋሚ አስታዉቋል።

Monday, December 28, 2015

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች ተቀጣጥሎ ይገኛል


ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል :: ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡
Tigest Tesgaye's photo.
Tigest Tesgaye's photo.Tigest Tesgaye's photo.

በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::


ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል :: ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡

ከኦሮሚያ ቴሌቪዥን 17 ጋዜጠኞች በዘላለም ጀማነህ ፊርማ ተባረሩ


ከኦሮሚያ ቴሌቪዥን 17 ጋዜጠኞች በዘላለም ጀማነህ ፊርማ ተባረሩ
ከኦሮሚያ ቴሌቪዥን 17 ጋዜጠኞች በዘላለም ጀማነህ ፊርማ ተባረሩ
ከሁለት ዓመት በፊት 20 ጋዜጠኞችን ያሰናበተው መንግስታዊው የኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ 17 የድርጅቱን ጋዜጠኞች አባርሯል ።
የድርጅቱ ዜና ዘጋቢ የነበረው ፍቃዱ መርከና ለእስር ከተዳረገ በኋላ ቀጣይ ተረኛ እንሆናለን በሚል ስጋት ተወጥረው የነበሩት ጋዜጠኞች በኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት ደረጃ የግብርና ኃላፊ በሆኑት አቶ ዘላለም ጀማነህ ፊርማ ከስራቸው መባረራቸው ተነግሯቸዋል ።
Adjama Dejene's photo.

የዓርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት ያቀጣጠለው የነፃነት እሳት አሁንም በሰሜን ተራሮች እየጨሰ ነው፥


ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው፣
ጀግናው የዓርማጭሆ ልጅ ትግሉን ከጀግናው ሠራዊታችን በሲቃ እንደተረከበው የሚያሳዩ ድሎች በየመንደሩ እየተመዘገቡ ነው፥ የዓርማጭሆና የወልቃይት ጠገዴ ጀግና እስከ ትግራይ ድንበር እየተሻገረ በጠላት መንደር ስጋት መፍጠሩን ዓጠናክሮ ቀጥሏል፥
ባለፈው ዓርብ ለቅዳሜ ዓጥቢያ ሃምሌ 3፣ 2007 ዓ.ም ታች አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ልዩ ኃይል እና ፀረ-ሽምቅ ጎራ ለይተው በመሰለፍ ግራ በተጋባ ሁኔታ እርስበርሳቸው በጥይት ተጠዛጥዘዋል፡፡ በሁለቱ የወያኔ ታጣቂዎች በተደረገው ለሰዓታት የዘለቀ ውግያ በትንሹ ስድስት አባላት ሲሞቱ በርከት ያሉ ቁስለኞች መሆናቸው ተገልጧል፡፡
ዘረኛውንና ፋሽስቱን የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቡድን በጠመንጃ አምበርክኮ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት የማድረጉ የትጥቅ ትግል ከኤርትራ በርሃዎች አልፎ በኢትዮጵያ መሬት ላይ በአስተማማኝ ሁኔታ እግሩን በመትከሉ፥ ህወሓት ወያኔ ከአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ብቻ ሳይሆን ከወልቃይትና ከአርማጭሆ ህዝብ በእያቅጣጫው የተከፈተበትን ፋታ የሌለውና ጠንከር ያለ የተኩስ ናዳ ፈፅሞ መቋቋም አልቻለም፡፡

Sunday, December 27, 2015

ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ነው


ambo
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰማ::
ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት መደፈራቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል::
ፖሊሶች ሴት ተማሪዎችን መድፈራቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:

ዜና ወልቃይት: የህወሓት ካድሬዎች የወልቃይትን አማሮች በየከተማው እየሰበሰቡ የማስፈራራት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ


ኮሚቴዎቻችን ቅስቀሳቸውን አጠናቀው ወደ ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ በእነሱ እግር
ተተክተው የህወሓት ካድሬዎች የወልቃይትን አማሮች በየከተማው እየሰበሰቡ
የማስፈራራት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።ኮሚቴዎች ያሏችሁን ነገር እንዳትሰሙ ፣መከራ
ሊያመጡባችሁ ነው፣ በሰላም መኖር ይሻለናል… የመሳሰሉት አይነት ማስፈራሪያ መሰል
ስብሰባዎች እዬተካሄዱ ነው።
ዛሬ በዳንሻ ከተማ በምዕራባዊ ዞን አስተዳዳሪ ተብየ በአቶ ኢሣያስ መሪነት የማስፈራርያ
ስብሰባ ሲደረግ ውሏል። ነገር ግን ስብሰባው በከፍተኛ ተቃውሞ እና በወልቃይት
አይበገሬነት ተጠናቋል። የወልቃይት አማሮች ደጋግመው እንደተናገሩት ለአማራነታቸው
አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል በሚገባ ተዘጋጅተው ጨርሰዋል። ከእንግዲህ ወደ
ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስ የለም ብለዋል። ጠገዴ ጠለምት እና አርማጭሆ የወልቃይት
ወገኖቹን ጥያቄ በንቃት እዬተከታተለ ነው። በወገኖቹ ላይ አንዲት ክፉ ነገር ብትፈፀም
አፀፋ ለመመለስ ወደ ኋላ አይልም። እንዲሁም ቀሪው የአማራ ህዝበ ከመቸውም ጊዜ
በበለጠ የወልቃይትን የአማራነት ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለ ይገኛል።
የወልቃይት አማራነት ይለምልም!!
ድል ለመላው አማራ!!

ሰበር ዜና!! . . . ሐገር መስጠቱ ለሶማሌም ሊቀጥል ነዉ


ወንበዴዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን መስጠቱን በፓርላማዉ ላይ በአሻንጉሊቱ ጠ/ ሚኒስቴር ተብዬ ባረጋገጠ ማግስት አሳዛኙ ኢትይጵያን የማጥፋት ዘመሻዉ ወደ ሶማሌያ መዛመቱን ታማኝ ምንጮች በቁጭት እየገለጹ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ በ 1977 እና 1978 አመተ ምሀረት ኢትዮጵያን ተሻግሮ ወረራ ፈጽሞ የነበረዉን በሲያድ ባሬ የተመራዉን ሰላሳ አምስት ሺ 35.000 ጦር ሰራዊት እይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የመለሰዉ ጀግናዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አየር ሐይላችን ዛሬ ባላወቀዉና ባልገመተዉ መልኩ ያ የወገኖቻችን ደም የፈሰሰበትንና የተከበረዉን ዳር ድንበር መልሶ ለሶማሌ ለመስጠት ዉስጣዊ ደባ እየተደረገበት ይገኛል።
ምንጮች እነደጠቆሙት ከሰሞኑ ከሶማሌያ ፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የመከረዉ በሰላም ማስከበር ስም በዚያዉ የሚገኘዉ ክንፍ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ስለተባሉት ቦታዎች የተወያየ ሲሆን የሰላም ማስከበሩ ስራ በማጠናቀቁ በኩል የሚፈለገዉን መሰዋትነት ከፍሎ ሶማሌን ወደ ቀድሞዋ ጠንካራነቷ መመለሱ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ነዉ ካለ ወዲህ ስለ ኦጋድንና ሶማሌያ የኔ ናቸዉ ብላ ስለምታስባቸዉ ቦታዎች መክሯል።
ኢትይጵያን የማጥፋት ዘመቻዉን አጥናክሮ የተያያዘዉ የትግራዩ ነጻ አዉጭ በዚህ ጉዳይ ላይ በዚያዉ በሶማሌያ ከሚገኙ ከአንዳንድ አመራሮች ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት ወታደሩን ያሳምጻሉ የተባሉትና ስብሰባዉ ላይ ጠንካራ ተቃዉሞ ያሰሙያ ተቆርቋሪዎችን በዝዉዉር ሰበብ በሄሊኮፍተር ጭኖ ወደ ኢትዮጵያ የመለሳቸዉ ሲሆን እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።
ድል ለኢትጵያ ህዝብ!!
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

Thursday, December 24, 2015

ሰበር ዜና በዛሪው እለት የሱዳኑ ፕሪዝዳት ሃሰን ኡመር አልበሸር መከላከያ ሰራዊቱን ወደ ኢትዮ ጠረፍ መሸኘታቸው ተሰማ።


ፕሪዝዳንቲ በተገኙበት በዛሪው እለት የነብዩ ሙሃመድን ልደት በማክበር ባዛውም መከላከያ ሰራዊታቸውን በተጠንቀቅ እንዲቆም ካሰረዱ በኋል ወደ ኢትዮ ሱዳን ጠረፍ በክብር ሸኝተዋል
ፕሪዝዳንቱ ሰሞኑን አዲሰ አበባ መሰንበታቸውን የተለያዩ ብዙሃን መገናኛውቸ ሲዘግቡት መቆየታቸውን አሰታውሰን የሱዳኑ አምባሳደርም ሰለመሪቱ የሰጡት አሰተያየት ነበር ይህውም የአማራ መንግሰት ነው
ማለቱ የሚታወሰ ነው በነገራችን ላይ የአማራ መንግሰት የምትለዋን ቃል ከማን የተማረው ይመሰላቹኋል?
መሪታችን አንሰጥም ያለ ሁሉ ማድረግ ያለበትን እሱ ያውቃል ተነሱ የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን ይህ ጥሪየ ነው
ወቅታዊ መረጃ የሚያደርሰን ሪፖርተራችን፡ነገ ሰለደንበሩ ጉዳይ አንዳንድ ሰውችን አነጋግሪ ሪፖርት አደርጋለው ብሎናል ጠብቁን
መሪታችን አይሸጥም
Gebrye Yegaynt Anbesa's photo.

ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን – ( ‪ሃብታሙ አያሌው‬ | ከቂሊንጦ እሥር ቤት)

ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ትግል፣ ኢትዮጵያ እንደ እናት ሆና የረዳቻቸዉ ፣ እንደ ጋና፣ ታንዛኒያና ሴኔጋል ያሉ የአፍሪካ አገሮች እንኩዋን ሳይቀሩ የትናየት በደረሱበት ዘመን፣ እንደ ደርግ ዘመን አሁንም በኢትዮጵያ፣ ረሃብና ችጋር የሚገድለን አልበቃ ብሎ፣ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያዉያን እጅ እየተገደሉ ነው።
በቅርቡ በጎንደር እና በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎቸ እንዳየነው፣ በዜጎች ላይ የደረሰው ግድያ፣ ድብደባና ግፍ እጅግ በጣም ልቤን እንዳደማው መግለጽ እወዳለሁ። ለሞቶት ነፍስ ይማር፣ ለቤተሰቦቻቸዉም መጽናናቱን ያብዛላቸው እላለሁ።
በወገኖቻችን ላይ የደረሰን ጭካኔ አጥብቄ እያወገዝኩ ፣ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተቃዉሞ ከሚሰማባቸው ቦታዎች በአስቸኩዋይ እንዲወጡ እጠይቃለህ። መንግስት ገዳዮችን፣ ትእዛዝ የሰጡትን ለፍርድ እንዲያቀርብና ጉዳት ለደረሰባቸው አስፈላጊውን ካሳ እንዲሰጥ እጠይቃለሁ። ገዢዎች የሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄ በማናናቅ፣ በሚቆጣጠሩት ሜዲያ በሕዝብ ላይ የሚያሰሙት ዛቻ፣ ማስፈራራት ፣ ስድብ አቁመው፣ ለሕዝብ መሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የፍትህና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እጠይቃለሁ።
እኔን ጨመሮ በርካታ ዜጎች በሰላም ሐሳባችንን በመግለጻችን ሽብርተኞች ተብለን፣ ፍትህ ተነፍገን በግፍ ታስረናል። ነጻ ጋዜጦች ተዘግተዋል። በሌሎች አገሮች የእንስሳት መብቶች ሲከበሩ፣ በኛ አገር ግን ለሰብእና ክብር አይሰጥም። ዜጎች በአገራቸው ፈርተዉና ተሸማቀው ነው የሚኖሩት። ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ስደትን መርጠዋል። በልማት ስም ጥቂቶችን ለመጥቀም፣ ገበሬዎች ከእርሻቸው ይፈናቀላሉ። “ከዚህ ብሄረሰብ ናችሁ፣ የናንተ መሬት አይደለም” ተብለው ብዙዎች የዘር ማጽዳት ወንጀል ይፈጸምባቸዋል። በጎንደር ለምለም የአገራችን መሬት፣ ሕዝብ ፓርላማው ሳያውቀው ሊሰጥ እንደሆነ እየሰማን ነው። አገር በ 11% አድጋለች እየተባለ፣ አሥር ሚሊዮኖች ለረሃብ ተጋልጠዋል። ይሄ ሁሉ መቆምና መስተካከል አለበት። “ኢሕአዴግ ልብ ይበል ፤ የጥፋት እጆቹን ይሰብሰብ ፣ ሕዝብን ያክብር፣መሰረታዊ የፖለቲካ ሪፎርም ያድርግ፣ ለብሄራዊ መግባባት ራሱን ያዘጋጅ” እላለሁ።
ነጻነትን ለተጠሙ፣ ፍትህን ለተራቡ ኢትዮጵያዊያን መልእክት አለኝ። ነጻነት፣ ፍትህ ከሌሎች በስጦታ የሚሰጠን አይደለም። ነጻነትና ፍትህ እኛው ራሳችን ታግለን የምናገኘው ነው። በመሆኑም የአገሪቱዋ ሕገ መንግስት እና አለም አቀፍ ሕጎች በሚፈቅዱት መሰረት፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻችንን እንድናሰማና ትግሉን እንድንቀላቀል ጥሪ አቀርባለሁ። ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን። የአንዱ ሕመም እኛንም ሊያመን ይገባል። እንተባበር፣ እንደራጅ፣ በጋራ፣ በማያዳግም ሁኔታ፣ “በኢትዮጵያችን ከዚህ በሁዋላ በግፍ ደም መፈሰስ የለበትም” እንበል። አሁንስ በቃን !!!!

ሰበር መረጃ የህዝብ ጠላት የሆነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ስብስብ ( ወያኔ ) በኢትዮጵያዊያን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ለማካሀድ የመጨረሻዉ ወቅት ላይ ይገኛል።


የኢትዮጵያን መሬት ከጎንደር ቆርሶ ለመስጠት የተዋዋለዉና ትግራይን ለማስገንጠል ቆርጦ የተነሳዉ የሕዝብ ጠላት ወያኔ በሱዳንና በኢትዮጵያ ወታደሮች የታገዘ የጅምላ ጭፍጨፋ የጎንደር ህዝብ ላይ ለመፈጸም የመጨረሻዉ ዳር ላይ እንደሚገኝ ከዉስጥ አርበኞች የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የወያኔ አቻ ባለስልጣን ተብዬ ወሮበሎች ከሱዳኑ ኦማር ሁሴን መሓመድ አል_በሽር ጋር የመሬት እርክክብ ለማድረግ ጫፍ በሚገኙበት በዚህ የመጨረሻዉ ወቅት የወያኔ ወታደሮች፣ የአጋዚ እንስሳዎች እንዲሁም በሱዳን በተለይም እ.ኤ.አ 2005 ዓ/ም ዳርፉር ላይ በተካሄደ የጅምላ ጭፍጨፋ ወደ 400.000 ያህል የሱዳን ህዝብ በጭካኔ የፈጀዉ የአል_ብሽር ሰራዊት ወደ ጎንደር ጠረፍ እንዲንቀሳቀሱ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን በሁለቱ ሰይጣናዊያን ወሮበሎች መካከል እንደ ዋና ጠላት ተደርጎ የተቀመጠዉን የአማራ ዘር ለማጥፋት አል_በሽር ከፊት ለፊት ወያኔ ከኍላ በመዉረር የአጼ ቴድሮስን ሐገር የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጥፋት ተነስተዋል።
ይህንን መረጃ የላኩልን የዉስጥ አርበኛ እንደገለጹት መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ነገ ዛሬ ሳትል በሐገርህና በህዝብህ ላይ የተነሳዉን ይህን የግፍ ድግስ መፋለምና ማኮላሸት ካልቻልክ ሐገር፣ ወገን፣ ታሪክ እንደሌለህ እወቅ በማለት ጥብቅ ማሳሰቢያቸዉን አስተላልፈዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጉድሽ ወያኔአ

Wednesday, December 23, 2015

ኢህኣዴግ እርስበርሱ እየተባላ ነው


ከህዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ድርጅቱ ውስጥ ብዙ መከፋፈል እንደተፈጠረ ከዛው ከድርጅቱ ኣባሎች ሚስጥር ማፈትለክ ጀምሯል።
1፡በስርቆትና በወገን ባብሮ ኣደግ ጠ/ሚ ከዚ በፊት በይፋ ባይሆንም ስብሰባን ኣግጣሚ ኣድርጎ የተናገራቸው ትግራይን ጨምሮ መላ ሃገሪትዋ ላይ ብልሽውና ላይ የተዘፈቁ ሌባነታቸውን ለመሸፋፈንና ስማቸውን ለማደስ በኦህዴድ ኣባላት ላይ ዘምተዋል። ይህም ኣልበቃ ብሏቸው መከላከያና ፖሊስ ውስጥ ብዙ ወሳኝ ባይሆንም ኣደጋ ሊጥሉ ይችላል ወይ በተዛማጅ ኣስጊ ናቸው የተባሉ የኦሮሞ የኣማራ ተወላጆች ገሚሱ በዝውውርና በእስራት ከቦታቸው እየተነሱ መሆኑን። ሊላው ግንባር ላይ ከሃይል በላይ ላሉ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ መሆኑንና ለስራ በሚል መቀሌ ተጠርተው ያልተመለሱ እንዳሉም ለማረጋገጥ ተችሏል።
2፥ጠ/ሚ የድርጅቱ ሊቀመንበር እሱን ከሚከተሉት ከደቡብና ከክልል ኣማራ ብኣዴን ተብዬው ኣንድ ራሱን የቻለ ቡድን ድርጅቱ ውስጥ ጎራ ፈጥሯል። ውጪ ሚገኙት ላይም ይሄ ክፍፍል ጥላውን ኣስርፎ ብዙ ኣምባሳደሮች እየተቀየሩ ነው።
………ብዙ ቁጥር የያዘውን የኦሮሞ ህዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው ኦህዴድ ተብሎ የተለጠፈው ብዙ ኣባላቱ ተቃውሞ ስላሰሙ ባንድ ላይ ሁሉንም ማሰር ለድርጅቱ ኢህኣዴግ ህልውናውን ኣደጋ ላይ እንደሚወድቅ ታውቆ ለጊዜው በግምገማ ልክ እንደበረዶ ማቅለጡን ጀምረውታል በቅርብ ውጤቱን ይጠብቁ።

አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ተገለፀ


የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ እጁ፣ እግሩና ጆሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እጁን ታስሮና ተሰቅሎ በተገረፈበት ወቅት የግራ እጁ አጥንት የተሰበረ ሲሆን የእግር ጥፍሮቹም ተነቅለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጆሮው ላይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
በተለይ እጁ ላይ ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ተነግሮት የነበር ቢሆንም ከክኒን ውጭ ሌላ ህክምና እንዳልተሰጠው ቤተሰቦቹ ገልፀዋል፡፡ የ17 አመት ፍርደኛ የሆነውና በዝዋይ እስር ቤት የታሰረው አቶ ዘሪሁን በአሁኑ ወቅት ለህክምና ቃሊቲ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ህክምና እንዳላገኘ ቤተቦቹ ገልፀዋል፡፡ የዝዋይ እስር ቤትን ህክምና እንዲያገኝ በጠየቀበት ወቅት ‹‹ከቃሊቲ እስር ቤት ጋር እየተነጋገርን ነው፣ መኪና የለም›› በሚሉ ሰበቦች ህክምና ሳያገኝ ቆይቷል ያሉት ቤተሰቦቹ ወደ ቃሊቲ ከመጣ በኋላም ፖሊስ ሆስፒታል ተመርምሮ መድሃኒት ቢታዘዝለትም የታዘዘለትን መድሃኒት ‹‹ሀኪም አላየውም፡፡ ሀኪም ያረጋግጠው›› እየተባለ ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን የፀረ ሽብር አዋጁ በወጣ በወራት ውስጥ ከታሰሩት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡
Netsanet Beqalu Mannet's photo.

ኢትዮጵያ መሬት ጠቧት ወደሱዳን ግዛት ለመስፋፋት እየሞከረች ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አላገጡ


በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ኦስማን ናፊ Assayha ለተሰኘ አረብኛ ጋዜጣ የሰጡት ቃለመጠይቅ አስገራሚ ነው። ኢትዮጵያ መሬት ጠቧት ወደሱዳን ግዛት ለመስፋፋት እየሞከረች ናት ሲሉ ከሰዋል። የጉዌንን መስመር ተግባራዊ እንዲሆን ከንጉስ ሃይለስላሴ ጋር ስምምነት መደረሱን: ሱዳን በቅንነት መሬቷን ለኢትዮጵያውያን ገበሬዎች መፍቀዷን: በምላሹ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የራሳቸው አድርገው በመስፋፋት ከዚያም ባለፈ የሱዳንን ዜጎች በመግደል ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ይሄን የሚያደርገው ማእከላዊውን መንግስት የተቆጣጠረው የትግራይ ገዢ ሳይሆን የአማራ ክልል መንግስት ነው ብለው ተናገሩ። የዘር ክፍፍል ጨዋታውን እንደ ህወሀት ይችሉበታል። ከሁሉ የገረመኝ የህወሀትን አፈጣጠር የገለጹበት መንገድ ነው። ኢትዮጵያን የሚመራው ገዢ ቡድን ከካርቱም ማህጸን የወጣ ነው አሉና አረፉት ። እኛ ከትግራይ ማህጸን የወጣ ነው ብለን ይሄን ሁሉ ዘመን ቆይተን ከባእድ ማህጸን መፈጠሩ ሲነገረን አጃኢብ አልና ዝም ። ለነገሩ ህወሀት ከትግራይ ማህጸን ቢፈጠር ኖሮ እንደዚህ አረመኔ: ጸረ-ኢትዮጵያ አይሆንም ነበር። …የሱዳኑ አምባሳደር “የድንበሩ ጉዳይ የእኛ የትኩረት አጀንዳችንም አይደለም” ማለታቸውም አስገራሚ ነው። ህወሀት እንዲህ አጣድፎ መሬታችንን ለማስረከብ ለምን ፈለገ ይሆን?

የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ተሰማ


የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ስላለ የወሰደውን 100 ሺሕ ሔክታር፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ ቢያቀርብም እስካሁን በሃራጅ ተሽጦ ባንኩ ሊያገኘው የቻለው 2.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የካሩቱሪ ዳይሬክተር ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለ100 ሺህ ሔክታር ሊዝ መሬት አንድ ጊዜ የሚከፈል 5.6 ሚሊዮን ዶላር በባንክ እንዳይከፍል ታዞ በጥሬ ገንዘብ ጉዳዩ ለሚመለከተው ግለሰብ መክፈሉን መናገሩ ይታወሳል። መንግስትን የሚወክለው ግለሰብ መጀመሪያ 5.6 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሎ በኋላ ካሩቱሪ መክፈል የማይችለውን 55.8 ሚሊዮን ብር እንዲበደር ፈቅዶለታል።
Samuel Hailemikael's photo.

በታች አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ቀበሌ በስብሳባ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነዉ የተባሉ ግለሰቦች ህወሃት አድራሻቸዉን አጠፋዉ።

የቀበሌዎን ህዝብ አቶ አዲሱ ለገሰ እና አቶ አለምነዉ መኮነን ለማነጋር ከሰበሰቡ በሃላ በፀረ ሰላም ሃይሎች ጥቃት ሊፈፀም ነዉ በማለት ስብሰባዉ ተቆርጧል። የስብሰባዉን መቋረጥ
ተከትሎ ህወሃት በርካታ አርሶ አደሮችን ወዴት እንደወሰዳቸዉ አልታወቀም። የወያኔ ቡድን መገናኛ ብዙሃን ሰላም ነዉ እያሉ ቢለፉፉም አሁንም ድረስ አካባቢዉ ሙሉ በሙሉ የጦር ቀጠና እንደሆነ ነዉ።
በተያያዘ ዜና ወያኔ፣ በአማራው ክልል መስተዳደር ጣልቃ በመግባት፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከሃላፊነት በማንሳት የአማራው ክልል ህዝብን “ልፋጭ” ብለው የሰደቡትን. በሕዝብ የሚጠሉትን፣ አቶ አለምነህ መኮንን ለማስቀመጥ እየዶለቱ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አቶ ገዱ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ጠመንጃ አካባቢያቸውን ይጠብቁ ዘንድ ለገበሪዎች ማደላቸው በህወሃት አልተወደደላቸውም። ከትግራይ ክልል መሪ ጋር ብዙ ጊዜ እንደተጋጩ የሚነገርላቸው አቶ ገዱ በወያኒዎች ጥርስ ዉስጥ መግባታቸው ቢታወቅም፣ ታች ባለው እና ከጊዜ ወደጊዜ በሕወሃት ላይ ተቃዉሞ በሚያሰማው የብአዴን አባል ድጋፍ አላቸው።
ብአዴን በባህር ዳር ባደረገው ጉባኤ አባልቱ ከፍተኛ ተቃዉሞ በህወሃት ላይ ሲአይሰሙ እንደነበረ ይታወሳል። “እነርሱ ባለ ፎቅ እኛ ግን ሎተሪ ሻጮች ነው የሆነው” ሲሉ የነበሩት የብአዴን አባላት ሕወሃት በሚወስዳቸው አገር ጎጂ ፖሊሲዎች ከሕዝብ ጋር እነርሱ መጣላት እንደሌለባቸው ሲናገሩም ነበር።

Monday, December 21, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ


ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ መጥራታቸውን አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ የጠሩት ሰልፍ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ፤ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ላይ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግስት እየወሰደው ያለውን እፈና እና እርጃዎቸ እንደሚያወግዙ ምክትል ሊቀመንበሩ ተገልፆአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ የሚያደርጉት ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ መሆኑን ታውቋል፡፡ መንግስት እየወሰዳቸው ባሉ የተሳሳቱ እርምጃዎች ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መሆኗን የገለፁት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ሀገራችን ካለችበት ችግር ለማውጣት ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙና በሰልፉም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሰልፉ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

መድረሻ ያጡት 4500 ቅጥረኛ ወያኔዎች በአማራው ሀይል ተከበቡ

ተደጋግሞ እደተዘገበው ወያኔ በቅማንት ስም ጎንደርን ለመረከብ ሴራ ሲያሴር ከርሞ ብጥብጥ ፈጥሮ ነበር፡፡ ወዲያው በወያኔው ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ አማራው “በሉ እንግዲህ ቋራ ላይ እንክተት” ብሎ ልክ አባቶቹና እናቶቹ በጥንት ዘመን ያደርጉ እንደነበረው ታጥቆ ተሰባስቦ ወደሽንፋ ሄደ፡፡ ወደቋራ ከዘመተው አማራም የደባርቅ፤ የበለሳ፤ የደብረታቦር፤ የጎጃም፤ የጎንደር አማራ ይገኝበታል፡፡ በመኪና እየተጫነ ሆ ብሎ ሽንፋ ገባ፡፡ በማሩ ቀመስ ደምቢያ በኩል ያለው አማራ ደግሞ ሆ ብሎ ወደዛው ወደሽንፋ ዘመቻ ሲያደርግ መንገድ ላይ ታቦት ከቤተ ክርስቲያን ወጥቶ በስንት ልመና ተመለሰ፡፡
. በዚህ ግርግር መድረሻ ያጡት 4500 ቅጥረኛ ወያኔዎች ወደጭልጋ (ሰራባ ወታደራዊ ካምፕ) ሸሽተው በመግባት ወደውጭ እንዳይወጡ በአማራው ሀይል ስለተከበቡ ታግተው ከርመው አሁን ተለቀዋል፡፡ የተለቀቁትም በሀገር ሽማግሌ በስንት ልመና እርቅ ተፈጽሞ ዳግም አማራውን እንዳያውኩ ቃል ገብተው ነው፡፡
 እነደመቀ፤ አባይ ጸሀየና የመሳሰሉት የወያኔ ባለስልጣናት የጎንደርን ወጣቶች በጎሀ ሆቴል ሰብስበው ነበር፡፡ ስብሰባው ለ10 ሰአት ሆኖ ጥሪ የተደረገላቸው ግን በ9 ሰአት ነበር፡፡ ስብሰባውም ላይ ወጣቶች “እኛ እኮ የራሳችንን ስራ ሰርተን የምንኖር፤ መንግስት የማይደግፈን ነን፡፡ ለምንድነው አስር ሰአት ስብሰባ ለማድረግ ዘጠኝ ሰአት ምትጠሩን? ምን መስለን ታየናችሁ? ደግሞ እያንዳንዷን የምታደርጓትን ነገር እናውቃለን፤ ማናውቅ እንዳይመስላችሁ፡፡ በቅማንት ስም እና በሱዳን ስም መሬታችንን ለራሳችሁ ለትግራይ ሪፑብሊክ ልትወስዱ ነው፤ ተነቃቅተናል” ብለው አፋጠጧቻው፡፡ ባለስልጣናቱም “አወ ጥፋት ተሰርቷል፤ እናውቃለን” አሉ፡፡ ወዲያው ግን ወጣቶቹ በጥያቄ ቀጥለው ያጣድፏቸው ጀመር፡፡ ባለስልጣናቱም ተደናግጠው አንገታቸውን ደፉ፡፡ የስብሰባው ሁኔታ አዝማሚያው አላምር ሲላቸውም ራሳቸው በትነውት ወዲያውኑ ብን ብለው ጠፉ፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ እንደታየው እንደዛ አይነት ድፍረት የተመላበት ንግግርና ማፋጠጥ ገጥሟቸው አያውቅም ተብሏል፡፡
4. የወልቃይት የአማራ ብሄረተኝነት ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ በይፋ ጎንደር ላይ ጽ/ቤት ከፍቷል፡፡ በዚህም አባይ ጸሀየ ለምን ተፈቀደላቸው የሚል አቲካራ ቢጤ ከፍቶ ተገቢ መልስ ተሰጥቶታል ተብሏል፡፡
5. የጎንደር አማራ በቅማንት ስም የሚደረገውን ሴራ፤ ለሱዳን በሚስጥር ስለተሰጠው መሬት፤ ስለወልቃይት ጉዳይ፤ አማራው ላይ ስለሚደረገው አጠቃላይ መድሎና የዘር ማጥፋት ወንጀል ውግዘት የሚያደርግ ሰልፍ እያዘጋጀ እንደሆነ ታውቋል፡፡ መላው አማራም ከጎናቸው እንዲቆም አሳስበዋል፡፡
መቸም መብታችንንም ሆነ ህልውናችንን በልመና አናገኝም፡፡ በቻልነው መንገድ ሁሉ መታገል አለብን፡፡ ህልውናችን ስጋት ላይ ከመውደቅ የከፋ ነገር ምንም አይደርስብንም፡፡ የህልውና አደጋ የሚፈታው ደግሞ በእልህ አስጨራሽ ትግል ነው፡፡
አሰግድ ታመነ

ሰበር ዜና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ከመቀሌ መልስ ሁመራ ላይ ባረፉት ሆቴል ማምሻውን በህዋሀት ታጣቂዎች መከበባቸው ታወቀ ።



ዛሬ ማምሻውን ሁመራ ጎንደር ከመናኸሪያ ወረድ ብሎ ከሚገኘው አዱ ገነት በሚባል ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው የምገኙ የወልቃይት አማራ ታጋዮች በወያኔ ፖሊስ መከበባቸው እና ቤቱን እዲከፍቱ በሚጠየቁበት ሰአት ይህ ዜና ከስፍራው በውስጥ መስመር ተልኮ ለናንተ አደርሰው ዘንድ ግድ ሆኗል። እነዚህ ታጣቂ ትግሮች ስለ ወልቃይት ሊመክሩ ወደ መቀሌ ሄደው ከ10 ቀን ቦኃላ መመለሳቸውንና ይህን እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ለመረዳት ችያለሁ።
ላልሰሙ አሰሙ!

Saturday, December 19, 2015

የነፃነት ትግሉን ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ ለምስገባት በሰሜን ኢትዮጵያ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እየተደረግ ነው፡፡


የኢትዮጵያ ልጆች በክብራ ለህዝባቸው ነፃነት እና ለሀገራችው አንድነት በክብር እየተሰው ነው፡፡በቅረብ ቀን ማንም ያልጠበቀው ድል ይመዘግባል፡፡ድረጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ከወህደት ወዲህ እዲስና ወቅቱን ያግናዘበ የትግል ስትራቴጅ በዚህ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ማፀደቁና ውሳኔ መሳለፉ ይታወቃል፡፡
“እኛ አርበኞች ግንቦት 7 ነን!”
“…እኛ ለነፃነትና ለፍትህ የቆምን፤ ለእኩልነትና ለአንድነት የተጋን፤ ለህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት እየደማንና እየሞትን የምንገኝ፤ የህዝብ ጭቆና እና ምሬት የወለደን አርበኞች ግንቦት 7 ነን…”
….ሰልፍ የጀግና ነው፡፡ድል የእግዚያብሔር ነው! እናት አገር ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

የአሜሪካ መንግስት የኦሮሚያ ተቃውሞና ቀውሱ አሳስቦኛል ሲል መግለጫ አወጣ፡፡


(Addis Ababa, Ethiopia) – United States government agencies and officials have begun openly reacting to the ongoing protests in many parts of the Oromia Region. On Friday night, the State Department said the United States is deeply concerned by the recent clashes in the Oromia region of Ethiopia that reportedly have resulted in the deaths of numerous protestors.
“We urge the government of Ethiopia to permit peaceful protest and commit to a constructive dialogue to address legitimate grievances. We also urge those protesting to refrain from violence and to be open to dialogue,” a statement by Mark C. Toner, Deputy Department Spokesman reads. “The government of Ethiopia has stated publicly that the disputed development plans will not be implemented without further public consultation. We support the government of Ethiopia’s stated commitment to those consultations and urge it to convene stakeholders to engage in dialogue as soon as possible.”
US Ambassador to the UN, Samantha Power, on her part tweeted Friday saying: “The Ethiopian government must use restraint in response to Oromo protests and take immediate steps to decrease the tension.”
Violent clashes between security forces and student protesters in Ethiopia has entered into its fourth week. The two sides began the confrontation, which opposition figures say has caused the death of more than 70 people so far, after Oromo students in various parts of the country began protesting against the government’s new master plan for Addis Ababa which they call will incorporate lands into the capital city and displace thousands of Oromo farmers.

የቤኒሻንጉል ህዝብ ጉሙዝ ተወላጆች ለከፋፋዮቹ እና ዘራፊዎቹ ወያኔዎች ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጡ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ / መተከል ዞን /አልመሃል ከተማ የጉሙዝ ተወላጆች በከፋፋዩ ወያኔ ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ፈጥረዉበታል:: የጉሙዝ ተወላጆች ለከፋፋዮቹ እና ዘራፊዎቹ ወያኔዎች ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: “በአባይ ግድብ ስም የምታደርጉትን ዝርፊያ አቁሙ እንዲሁም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በእርስ ለማጫረስ የምትሰሩትን ዘረኛና ከፋፋይ ስራችሁን በፍጥነት አቁሙ” የሚለዉ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::
-በተለዬም ሰሞኑን አንድ ወያኔ የአባይ ግድብ አካባቢን እመነጥራለሁ በሚል ሰበብ ኮንትራት በመዉስድ 46 ሚሊዮን ብር አለአግባብ በጥቂት ቀናት ዉስጥ እጁ እንዳስገባ ህዝቡ ስለሰማ ከፍተኛ ቁጣ ዉስጥ ገብቷል
-በአካባቢዉ ሁሉንም የንግድ ስራዎች ማለትም ለቅርጻ ቅርጽ የሚያመቹ ዉድ ዛፎችን፣ፎቅ መደገፊያ መስሪና ዉድ የሆኑ ወደ ዉጭ ሀገር ኤክስፖርት የሚደረጉ ሀብቶችን በሙሉ የወያኔ አባላት ብቻ ተቆጣጥረዉት መገኘታቸዉ ብሎም ሌሎች ማህበረሰቦች ወደዚህ ስራ ሊገቡ ሲሞክሩ በሩ ሁሉ መዘጋቱ ህዝቡን እያስቆጣ ነዉ:: በአካባቢዉ ማዕድን ለማዉጣት: ሌላዉ ቀርቶ የቡልዶዞር ማከራዬት ስራ እንኳን ለመስራት ወያኔ ያልሆነ ሰዉ አይችልም:: በመሆኑም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ከፍተኛ ምሬት ዉስጥ ገብቷል::
– የቤኒሻንጉል ህዝብ የአማራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ በማድረግ እራሳቸዉ ወያኔዎች የአማራን ህዝብ እየገደሉና እየጨፈጨፉ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነዉ አማራዉን እያፈናቀለና እየገደለ ያለዉ ብለዉ መግለጫ በእኛ ስም ማዉጣታቸዉ ለእኛ ያለቸዉን ንቀት ያሳያል ሲሉ የአካባቢዉ ተወላጆች ወያኔን በገሃድ እየተቃወሙ ነዉ::
– በመሆኑም የቤኒሻንጉ ተወላጆችል ከሌሎች ማህበረሰቦች ማለትም ከአማራዎች: ኦሮሞዎች: ሺናሻዎች: ጉሙዞች እና አገዎች ጋር በመሆን ጠላታችን በዝባዡና ከፋፋዩ ወያኔ ብቻ ነዉ:: እኛ ኢትዮጵያዊ ነን:: እርስ በእርሳችን አታባሉን በማለት በከተማዋ ያሉ የወያኔ ንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠሩ ነዉ::
-የቤኒሻንጉል ህዝብ “እኛ ኢትዮጵያዊ ነን: ለማንም ህዝብ ጥላቻ የለንም:ጠላታችን ኢትዮጵያዊነትን በእርስ በእርስ ጦርነት ሊያጠፋ የተነሳዉ ወያኔ ብቻ ነዉ” ሲል አቋሙን መግለጹ ወያኔዎችን ስላሰጋቸዉ ህዝቡን እንደለመዱት በዘር የመከፋፈል ስራ ለማከናወን እየተዘጋጁ መሆኑም ታዉቋል

የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ናቸው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል


የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል። እርምጃዎቹ ሁኔታውን ከማባባስ በስተቀር የሚፈይደው የለም ብሎታል፡፡
በጉዳዩ ውስጥ የተሣተፉ ወገኖች ሁሉ ከአመፃና ከሁከት አድራጎት መቆጠብና ድምፆቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ቢያሰሙ እንደሚበጅም ቡድኑ መክሯል፡፡
የዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ከትናንትና ወድያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የወሰደውን የሃል እምርጃ ኮንኗል። መንግስት የኢትዮጵያን ጸረ-ሽበር ህግን በመጥቀስ “ሰልፈኞቹ ከውጭ በሚያገኙት ድጋፍ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወክ የጀመሩት ሁከት ነው” ያለውን አምነስቲ መግለጫ አጣጥሎታል።
እስካሁን የመንግሥት ባለስልጣናት አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ በበኩላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው 4 ፓሊሶች መገደላቸውን ከዚህ በፊት መግለጻቸው ይታወሳል።

ኦህዴድ ኢህአዴግን ከዳ .በትግራይ ወጣቶች ለውትድርና እየተጠሩ ነው


በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ የኦህዴድን መክዳት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ከንቅናቄው ጋር በተያያዘ ህወሃት/ኢህአዴግ ጥቅሙን ለማስከበር የትግራይ ወጣቶችን ለ“ብሔራዊ” ውትድርና እየጠራ መሆኑ ተሰማ፡፡
ሳምንታት ያስቆጠረውና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በማድረግ የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ ልዩ እየሆነ መሄዱ ኦህዴድ ኢህአዴግን የመክዳቱ ማስረጃ ነው ሲሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ለጎልጉል መረጃ የሚያቀብሉ አመራር አስታውቀዋል፡፡
በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ፤ ስለላ፤ ሕዝባዊ አደረጃጀት፤ ቁጥጥር፤ … መዋቅሮችን ሁሉ አልፎ ይህንን ያህል ሕዝብ ያለአንዳች ከልካይ መውጣቱ አገዛዙ ሕዝቡን ለመጠርነፍ የተጠቀመበት አሠራር መልሶ ራሱን እየጠረነፈው እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ታማኝ ተብሎ የተቀመጠው ካድሬም ሆነ የጥርነፋው መዋቅር ሕዝቡን ሊያስቆም አለመቻሉ የኦህዴድ እምቢተኛነትና ለአገዛዙ ድጋፍና እገዛ ከማድረግ ይልቅ ከሕዝቡ ጋር ለመቆሙ እንደ ዓይነተኛ ማስረጃ ይጠቀሳል፡፡
በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የተዛባ አመራር እንዲሁም የኃይል (የሥልጣን) ሚዛን አለመስተካከል በኦሮሚያ ውስጥ ኢህአዴግን ተቀባይነት እያሳጣው ከመሄዱ ባሻገር ሕዝቡን “ኦነግ፤ አሸባሪ፤…” በማለት ህወሃት/ኢህአዴግ እስርቤቱን “ኦሮምኛ ተናጋሪ” እንዳደረገው በስፋት ሲነገር የቆየ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የቀረበውን ዕቅድ ከደገፉት ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞ በስተቀር የተቀረው የኦህዴድ አመራር በኢህአዴግ እምነት የሚጣልበት ባለመሆኑ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ኦህዴድ ኦሮሚያን የማስተዳደር ውክልናው ቆሞ ክልሉ ህወሃት በሚቆጣጠረው ደኅንነት እየተመራ መሆኑ አብሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
ኦህዴድ የሚታመን ባለመሆኑ ክልሉን የማረጋጋትም ሆነ የመምራት ኃላፊነት በመነፈጉ ኦህዴድ እና ኢህአዴግን የሚያስተሳስረው የመጨረሻ ገመድ ተበጥሷል፤ ከዚህ ሕዝባዊ ንቅናቄ ኢህአዴግ ማንሰራራት ቢችል እንኳን በአዲስ የሚፈጥረው ኦህዴድ ከቀድሞው ፍጹም የተለየ እንደሚሆን ይህንን ለማድረግ በራሱ ለህወሃት/ኢህአዴግ ፈታኝ እንደሆነ አብሮ ተጠቁሟል፡፡
ከኦህዴድ መክዳት ጋር በተያያዘ ህወሃት/ኢህአዴግ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተነሳውን ሕዝባዊ ንቅናቄ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚችል የሚያምነው ኃይል ባለመኖሩ የትግራይ ወጣቶች እንደ ብሔራዊ ውትድርና ዓይነት ግዳጅ መጠራታቸው ተሰምቷል፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በኢህአዴግ ውስጥ የህወሃት የጥቅም ተጽዕኖ ግልጽ በመሆኑ ይህንን ጥቅም ለማስጠበቅ የትግራይ ወጣቶች መስዋዕትነት የሚከፍሉበት ግዳጅ አሁን ነው በማለት ለአገልግሎት ተጠርተዋል፡፡
“አገርህን አድን” በሚል ዓይነት ጥሪ ወንድሟ ወደ ውትድርና መሄዱን በለቅሶ የተናገረች በአውሮጳ የምትገኝ እንዳለችው ከሆነ ይህ ዓይነቱ ግዳጅ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ምንም መረጃ እንደሌላት ተናግራለች፡፡ ወንድሟ በምን ዓይነት ለህይወት የሚያሰጋ ግዳጅ ላይ እንደሚሰማራም ካሁኑ ለማወቅ እንደማይቻል በማስረዳት እሷም ሆነች ቤተሰቧ በከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ በመረበሽ አስረድታለች፡፡ ከትግራይ የተገኙ መረጃዎች እንዳመለከቱትም ወጣቶች ለተመሳሳይ ወታደራዊ ግዳጅ እየተጠሩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በኦሮሚያ ሕዝቡ ያስነሳው የተቃውሞ ንቅናቄ ቀጥሎ በዛሬውም ዕለት በተለያዩ ቦታዎች በስፋት ቀጥሏል፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ የሚወሰደው እርምጃ የዚያኑ ያህል የቀጠለ ሲሆን በኦፊሺያል ከሚሰጠው ቁጥር በበለጠ መልኩ እስካሁን ከመቶ በላይ ሰዎች መገደላቸው በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይነገራል፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የተመረሩ ኃይሎች በሁሉም ክልሎች የሚኖረው ሕዝብ እንዲሁም በውጭ አገር ያለው በኅብረት መንቀሳቀስ እንዳለበት ያሳስባሉ፡

Friday, December 18, 2015

Demonstration agenst ethiopian dictator infront of weyane embassy stockholm

Demonstration agenst ethiopian dictator infront of weyane embassy stockholm

ከ6ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታፍነው ተወሰዱ


በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች የነበሩ ሁለት ሴቶች ምሽቱን በደህንነቶች ከዶርማቸው ታፍነው መወሰዳቸውና የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ስለተማሪዎቹ መሰወር ተጠይቀው “አያገባኝም “የሚል ምላሽ መስጠታቸው በግቢው ውስጥ ተቃውሞ አስነስቷል ።
ሁለቱ ተማሪዎች ሲቪል በለበሱ ሰዎች በተወሰዱበት ወቅት ከለሊት ልብስ በቀር ምንም አለመልበሳቸው ተነግሯል ።
በአሁኑ ሰዓትም ዩኒቨርሲቲው በፖሊሶች ዙሪያውን ተከቦ ይገኛል ።
Dawit Solomon Yemesgen's photo.

ሰበር ዜና!! አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዝምታውን ሰበረ!!፡፡


በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ የለውጥና የዘመናዊነት ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዝምታውን በመስበር በአሁኑ ሰዓት በመነቃነቅ ላይ ያገኛል። ከአራት ኪሎ ወደ ሽሮ ሜዳ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፓሊስና የመከላከያ ሰራዊት ይተራመሳል። የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነትና የአንድነት ችቦ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ተለኮሰ። ወያኔ የማይቀረውን የውርደት ካባ ሊከናነብ ሰዓቶች እየቸኮሉ ነው።
ወያኔ ህዝብን በመናቅ በየከተሞች አስገድዶ በመሰብሰብ በሆዳም ካድሬዎቹ አማካኝነት የሚያደርገው የከረፋ ወሬ መላውን ኢትዮጵያዊ ለለውጥ እየቀሰቀሰው ነው።
በስድስት ኪሎ ካምፓስ የተቀጣጠለው አሳት ወያኔን ሳያቃጥል አይጠፋም። በመሆኑም በመላው አገሪቱ የምትገኙ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም ለሁለንተናዊ ነፃነት ተነሱ። ከትምህርት በፊት ነፃነት በማለት መላው የአገራችን ወጣቶች ተነሱ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ሞት ለወያኔና ግብረ አበሮቹ!!

የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት ጦር ኃይል ላይ ባደረሰው ጉዳት የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና በርካታ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

pow-and-medic-3_xlarge
የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት መተማ አካባቢ በአንድ ግንባር ላይ ብቻ በህወሓት ጦር ኃይል ላይ በፈፀመው ጥቃት የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና በርካታ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ከማክሰኞ ዕለቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃት በኋላ የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኛ ወታደሮች ተሞልቶ ሲቪሎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ 
የሆስፒታሉ ምንጮቻችን እንደገለፁት እስከ ትናንትና ድረስ ከ40 በላይ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና የቁስለኞች ቁጥር ቢያንስ በየአንድ ሰዓት ልዩነት እየጨመረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አንድ የሸዲ ነዋሪ ከየቦታው የተለቃቀሙ ከ26 በላይ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከቱን መስክሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት ጦር ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ 36 አውቶብስ ሙሉ ፌደራል ፖሊስ በመተማና በዙሪያዋ ተራግፏል፡፡

በአዲስ አበባ እያንጃበበ ያለው ታቃውሞ ሊፈነዳ የደረሰ መሆኑ ከየአካባቢው ከሚመጡ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡


በአገሪቱ የሚታየው የህዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴ እየተንከባለለ ሸገር ሊገባ ነው፡፡ ወጣት አዛውንቱ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ እየተነጋገረ ነው፡፡በቃኝ ብሎ ሊነሳ መሆኑ ነገሩን አስፈሪ አድርጎታል፡፡ ህውሓት ተጨንቋል በአዲስ አበባ ወጣቱን በአበል ለመሰብሰብ በየሰፈሩ የቀበሌ ካድሬው ቢራወጥም የሚሳካ አልሆነም፡፡ በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ የአዲስ አበባ ወጣትን እያነቃቃው መሆኑ በዚህ ቀን ሳይባል ድንገት የሚፈነዳ የህዝብ ብሶት እንዳለ በተለያየ ቦታ ያሉ ወጣቶችን በማነጋገር ሁኔታውን በቅርብ ከሚከታተሉ ወገኖች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ሁሉ ነገር ጨልሟል የታክሲዎች እንቅስቃሴ በውጥረቱ ምክንያት ቀዝቅዟል፡፡አብዛኞዎቹ ሳይታሰብ የሚገነፍል ቁጣ ይመጣል በሚል አቁመዋል፡፡አዲስ አበባ የሚኖሩ የባለስልጣን መኖሪያ ቤት ከዚህ ቀደም ባልነበረ የወታደር ጋጋታ እየተጠበቀ ነው፡፡ የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ቦሌ 03-05 አካባቢ እንዲሁ(መካኒሳ አቦ ማዞሪያና ብስራተ ገብርኤል ብዛት ያለው ሰራዊት ፈሷል በሌላ በኩል ማረሚያ ቤቶችና ድርጅቶች በሚበዙበት አካባቢ በከባድ መሳሪያ ጭምር እየተጠበቀ መሆኑ ስጋቱ ምን እንደሚመስል ያሳያል ሲሉ የሚናገሩ ብዙ ናቸው፡፡በአዲስ አበባ እየመጣ ያለው ተቃውሞ ሳይታወቅ ሊፈነዳ የሚችል በመሆኑ ለታማኝ ካድሬዎች እራሳቸውን ህዝብ ከሚበዛበት እንዲርቁና ነቅተው እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል ከአለም ባንክ ወደ ጀሞ ጥቁር በመልበስ በድምጽ አልባ ተቃውሞ በመንገድ ሲሄዱ የነበሩ ወጣቶች እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መረጃውን ለማጠናከር እየፈለግን ነው፡፡
=
በሌላ በኩል በደብረ ማርቆስ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡ በደብረ ማርቆስ ቀበሌ03 ልዩ ስሙ አምረት በሚባል ሰፈር በቀበሌ ቤት የሚኖሩ ሰዎችን በማፈናቀል ቦታውን በሊዝ እየተሸጠ ነዋሪዎችን ከከተማው ዳር እያሶጡ መሆኑ ከነዋሪዎች በተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁን ሰዓት በደብረ ማርቆስ እንዲሁም በባህር ዳር በአማራ ህዝብ በጎንደር የሚደርሰው የህውሓት የማጋጨት ሴራ ለሱዳን በሚሰጠው መሬት በአማራው ላይ በሚደርሰው ጭቆና ህውሓትብአዴን)ህዝቡ በቃ ሊል ከጫፍ መድረሱ ከሚመጡ የህዝብ ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡
በመላው ኦሮሚያ እየተቀጣጠለ የመጣው ህዝባዊ ንቅናቄ)በአማራው ሊደገም እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉ ሁኔታውን በቅርብ ከሚያውቁ ሰዎች ለመስማት ተችሏል፡፡ የጎንደር ህዝብ ከስርዓቱ ጋር እየተናነቀ መሆኑ ተቃውሞ ወደ ጎጃም ሸዋ ወሎ እየተዛመተ ከሄደ እንዲሁ በመሀል አገር ከተጀመረ በቀናት ውስጥ ህውሓት)ሊያበቃለት እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡አሰግድ ታመነ

የህወሓት የደንነት ቢሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን አስጠነቀቀ፡


የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር ወስኖአል። የውሳኔውን ቅጅ ከ አንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ጋር በአቶ ካሳ ተክለብርሀን በኩል ለጠቅላይ ሚንስትሩ ልኳል።
የአቶ ሀይለማርያም አስተዳደር አመፁን ለመቆጣጠር መመሪያ ከአሜሪካ መንግስት መቀበሉን በአስቸኳይ አቁሞ የተነሳውን መጠነ ሰፊ አመፅ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የሚያስችል የኦፕሪሽን መርሀ ግብር አውጥቶ ለፊደራል ፓሊስና መከላከያ ማስረከብና ለተግባራዊነቱም ካልተንቀሳቀሰ ሙሉ ሰላም የማስከበሩን ስራ መከላከያ ይረከባል ይላል። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ይደረጋል ማለት እንደሆነ ምንጮቸ አረጋግጠዋለል።
Samuel Ali's photo.

Thursday, December 17, 2015

ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል:: ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::


ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል::
ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::
ወያኔ አንድም እርምጃ ቢወስድ ምላሹ የከፋና በቂም የታጀበ ይሆናል:: በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ያቀረበን መግደል ማቁሰል የከፋ ዉጤት አለዉ::
በወለጋም በርካታ ቦታወች ተቃዉሞዉ የመለስ ዜናዊይን ምስል የኦህዴድን አርማ እየለቀሙ በማጋየት የቀጠለ ሲሆን ወሳኝ ወሳኝ መንገዶችም በመዘጋት ላይ ናቸዉ::
አዲስ አበባ በኦሮሞ ተወላጆች መኖሪያ ቤት ፍተሻ ተጀምሯል:: ወያኔ ያቄመዉ ሰዉ ቤት ፈንጅና ጦር መሳሪያ አስቀምጦ ድራማ ሊሰራ አስቧል::
በህዝብ ባስ በሰላም ባስ ህዝቡ መሄድ አደገኛና የወያኔ ቀጢይ ድራማ ሰለባ መሆን ነዉ:: ቤተክርስትያን መስጊድ ገበያ ሲኒማ ቤት ወዘተ… ህዝብ የሚሰበሰብባቸዉ አካባቢ ህዝቡ ጥንቃቄ ያድርግ:: ወያኒ አሸባሪ ፀረ ሰላም አፈነዳዉ ብሎ ህዝብን ንብረትን ለማዉደም አስቧል::
ጎንደር ፍጥጫዉ ቀጥሏል:: ከተማዋ እስከ መተማ አገሪቱ ተወጥራለች:: ባህርዳርና የጎጃም ከተሞች ሊወልዱ ምጥ ላይ ናቸዉ::
አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔን ቁም ስቅሉን በማሳየትና የህዝብን ደም በመመለስና ተቃዉሞወችን በማቀናጀት የወያኔን ሴራ በማጋለጥ ተጠምዷል::

የህወሓት‬ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጀግናው የቋራ ህዝብ ውርደት ተከናንበው ተመለሱ፡፡


አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች በዛሬው ዕለት ወደ ቋራ አምርተው ህዝቡን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ህዝቡ በአንድነት አምፆ ከእነሱ ጋር ፈፅሞ መነጋገር እንደማይፈልግ ገልፆ የውርደትና ሀፍረት ጉንጉን አበባ አንገት አንገታቸው ላይ አስሮ መልሷቸዋል፡፡
የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ አጥንት ፍላጭ የሆነው ጀግናው የቋራ ህዝብ አሳፍሮ የመለሳቸው እነ አባይ ፀሐዬ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ የፀጥታ ኃይሎችን፣ የዞኑን አመራሮች፣ ወሬ ለማዳመጥና እግር ጥሎት የገባውን ህዝብ ለማወያየት ሞክረው ነበር፡፡ ባለስልጣናቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎች ያሏቸውን ጠብመንጃ ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ህዝቡ እንዳይደግፍ ሲያሳስቡ ህዝቡ “ቢመጣ ቢመጣ ከእናንተ የባሰ አይመጣ…” ሲል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስማቸው እየነገደ ከሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ጋር እንዳቆራረጣቸው በመግለፅ ህወሓትን ከሰውታል፡፡ ከዚህ በኋላ የህወሓት ደጋፊም እንዳልሆኑ የአቋም ለውጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ በበኩላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ወጡበት ህዝብ አፈሙዝ አዙረው ምላጭ መስበር እንደማይሹና አገዛዙ ወደ ወገናቸው ተኩሱ የሚላቸው ከሆነ አስቀድሞ የጦር መሳሪያቸውን እንዲረከባቸው ጠይቀዋል፡፡

ከታጋይ አረበኛ ተስፋሁን‬ የንፁሃን አንገት በከንቱ እየተቀላ ዝምታ የለም::

ነስ ተነስተዋል ጀግኖች አዋሳ አዲስ አበባ ጎጃም ባሌ አርባምንጭ ወሎ ___
ህዝብ ራሱን ከሞት የመከላከል ተፈጥሮዊ መብት አለዉ።በግልፅና በስዉር ጦረነት የታወጀበት ህዝብ አፀፋዊ
እርምጃ በገዳዮች ላይ መዉሰድ አለበት።ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ህዝብ ላይ ቃታ የሚስበዉን የወያኔ ማፍያ ቡድን ባገኘነዉ ነገር
ሁሉ እርምጃ እንዉሰድበት። በቅርብ ርቀት በቀላሉ በጠርሙስ ነዳጅ ሞልቷ በመወርወር ራሳችን እንከላከል። ገዳዮች ነፍስ
አላቸዉ:: በፍራት ይርዳሉ። ይበረከካሉ! በመጨረሻም እጅ ይሰጣሉ! ይቀጣጠል ይንደድ በታሪክ ህዝብ ተሸንፎ አያዉቅም።
እንደ ሰደድ እሳት በፍጥነት ይዳረስ። በአራቱም አቅጣጫ ፀረ ወያኔ ትግሉ ይቀጥል:: አለን ከጎናችሁ ነን ።የንፁሃን አንገት
በከንቱ እየተቀላ ዝምታ የለም:: አሁን ነዉ የአገሬ ሰዉ ጀምረናቸዋለን እንጨርሳቸዋለን ማለት:: በቃ የዘረኞችን እድሜ
ከዚሕ ላይ ያብቃ! በለዉ !በቃ በለዉ አገሬ
አገር አድን ንቅናቄ's photo.

Monday, December 14, 2015

ወያኔዎች ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖባቸዋል።


ላለፉት በርካታ አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየከረረ ነው፤ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል እያልን ስንጎተጉትና ስንጽፍ ነበር። ህዝብ ይሄንን መንግስት በጣም እንደሚጠላ፤ ሕዝብ ጨዋ ስለሆነ ታግሶ እንጂ የመረረው እለታ ጉድ እንደሚፈላ ስንናገርና ስናስጠነቅቅ ነበር። ሰዎቹ አልሰሙንም። ጭራሽ 100% አሸነፍን ብለው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት በገሃድ አሳዩ።
ከአንድ ሶስት ወራት በፊት በዲቪ የመጣ አንድ የመንግስት ሰራተኛ “ ነገሮች በጣም ታምቀዋል። ሰው በጣም ነው የጠላቸው። There is a gathering storm” ነበር ያለኝ። እንደውም ይሄ ሰው አሁን የስርዓቱ ተጠቃሚ የሆኑቱን ጥቂቶቹን “ዜጎች” ብሎ ነበር የሚጠራቸው። ለምን ብዬ ስጠየቅ “እነርሱ እንጂ እኛ እኮ ዜጎች አይደለንም”” ነበር ያለኝ። ያን ያህል ነበር ጥላቻዉን የገለጸልኝ።
ይኸው እንዳስጠነቀቅነው እየሆነ ነው። ሕዝቡ ተቃውሞዉን እያሰማ ነው። ወያኔዎች ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖባቸዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት አምቦን አረጋግተናል ብለው ነበር። ብዙ ሰው ገድለዉና አስረው። ሆኖም “ስንገድለው፣ ስንድበድበው አፉን ይዘጋል” ያሉት ሕዝብ እንደውም የበለጠ አምርሮ ወጣ።
አምቦ ብቻ አይደለም፤ በአምቦና በአዲስ መካከል ያለችው ቡራዮም የጦርነት አውድማ ሆናለች። የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ሱቆች በሙሉ ተዘግትተዋል። ከቡራይዪ አዲስ አበባ መንገድ የለም: እንግዲህ ቡራዮ ማለት ትንሽ ሄድ ካልን ፣ አስኮ፣ ከዚያም ጉለሌ ነው የምንደርሰው።
አዲስ አበባ አፋንጫ ላይ ያሉትን አገዛዙ ማረጋጋት ካልቻለ፣ እንደ ዶዶላ፣ ባኮ፣ ነጆ፣ ቆቦ..ያሉትን እንዴት ነው የሚያረጋጋው ?? በጉልበት፣ በኃይል ይሄን አይነት ፣ እኔ በእድሜዬ አይቼ የማላወቀዉን ተቃዉሞ ማስቆም የሚቻል አይመስለኝም።
ለጊዜው አሁን እያደረጉት እንዳለው ብዙዎችን በመድልና በማሰር ለጊዜው መረጋጋት ቢያመጡም፣ በከፋ ሁኔታ እንደገና አመጹ መቀስቀሱ አይቀርም። አሁን ህዝቡ በሰላም ነው እጆቹ እየዘረጋ ድምጹን የሚያሰማው። ግን እየከፋ ከሄደ፣ ጣሊያን ፋሺስትን ባለው መሳሪያ ሁሉ እንደመከተ ፣ መሳሪያዉን እና ጎራዴዉን መወልወል መጀመሩ አይቀሬ ነው። ያን ጊዜ የሰላም ሳይሆን የአመጽ እንቅስቅሴ ነው የሚሆነው። ያን ጊዜ በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን በሌላኛውም ወገን እልቂት ይጀመራል። አገሪቷ ወደ ሶሪያ አይነት የርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ትዘፈቃለች። በዙህ ሂድት ደግሞ 200% የሚከስሩት ሕወሃቶችና ደጋፊዎቻቸው ነው። ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው። ማን ምን እንደሆነ በሚገባ ይታወቃል።
በመሆኑም በአስቸኳይ የወያኔ ታጣቂዎች ተኩስ አቁመው፣ ተቃዉሞ ከሚሰማባቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ እጠይቃለሁ። እነርሱ ባሁኑ ጊዜ ለሕዝብቡ አለርጂክ ናቸው። የነርሱ ብቅ ማለት ህዝቡን የበለጠ ያስቆጣል።
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም። አሻንጉሊት መሆናቸው ሰሞኑን በገሃድ ታይቷል። እንደ አንድ መሪ በዚህ ወቅት በቴሌቭዥዝን ቀርበው ህዝቡን ፣ ባይሰማቸውም እንኳን፣ ለማረጋጋት መሞከር ነበረባቸው። ሆኖም ግን፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው፣ ቢያንስ በዚህ ወቅት ድፍረት አግኝተው፣ ቆራጥ ዉሳኔ ያሳለፉ ዘንድ እጠይቃለሁ። ስልጣኑ በሕግ አላቸውው። እርግጠኛ ነኝ ፓርላውንም ቢሰበስቡ፣ 5% ብቻ ሕወሃቶች ያሉበት ፓርላማ ከጎናቸው ይሰለፋል። እነ ሶምራ የነሱስ፣ እነ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢትዮጵያን አኬልዳም (የደም መሬት) ሲያደረጉ ዝም መባል የለባቸውም። አቶ ኃይለማሮያም ሊያስቆሟቸው ይገባል። በዚህ ወቅት አቶ ኃይለማሪያም ዝምታን ከመረጡ ግን ለሚፈሰው ደም ሁሉ እርሳቸውም ተጠያቂ ነው የሚሆኑት።
አጋዚ ሕዝብ ከሚኖርበት ከተማ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ፣ ለተፈጠሩት ችግሮች የፖለቲካ መፍትሄ መፈለግ አለበት። ሕዝብ አገዛዙን ተፍቶታል። ኢሕአዴግ የመግዛት ሞራል ብቅት የለዉም። አገዛዝን እንዳለ ስልጣን ላይ የሚያቆይ ኮስሜትክ ለዉጥን ህዝቡ አየቀበልም። በመሆኑም አቶ ኃይለማሪይም የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም በማድረግ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ቢያደረጉ ጥሩ ነው።
አሁን 11 ኛው ሰዓት፣ አምሳ ዘጠነኛው ደቂቃ ላይ ናቸው። በኦሮሚያን በጎንደር የተነሳው ተቃዉሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ወይንም የጎጃም ወሎ የመሳሰሉት ከተቀላቀሉት፣ ሁሉም ነበር አበቃ ማለት ነው። ህዝቡ ያኔ በሕይወታቸው ነው የሚዉጣቸው። ለርሳቸው የሚበጅ ነገር ማድረግ ካለናቸው ማድረግ ያለባቸው አሁን ነው።

ሕዝብን ከመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር –


በነሶሞራ የሚመራው እዝ፣ ህዝብን ለመጨረስና በሃይል አንገትን ለማስደፋት ሁለት ዲቪዝን ጦር ወደ ምራብ ሸዋና ወለጎ እየወሰደ ነው። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገዛዙ ሊወስደው የሚችለው የመጨረሻ ተግባር ነው። ጎንደር ላይ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ ወደ ኦሮሚያ እየተሰማራ ያለው ሲደመርበት በሌሎች ከተሞች የሚኖረው ጦር በጣም የተመናመነ ነው።
በመሆኑም በአዲስ አበባ. በጎጃም፣ በወለኦ፣ በሰሜን ሸዋ፣ እና በደቡብ ክልል ሕዝቡ ለነጻነትና ለመብት ድምጹን ማሰማት ቢጀመር ይሄ ስርዓትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመገርሰስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።
በመሆኑም ሌላው ማሀበረሰብ ድምጹን ያሰማ ዘንድና በኦሮሚያና በጎንደር ለመብታቸው ከቆሙ እየተገደሉ ካሉ ወገኖቻችን ጎን እንዲቆም ያስፈልጋል።
እስከአሁን በጎንደር ከ150 በላይ ዜጎንች የተገደሉ ሲሆን በኦሮሚያ የዛሬን ቀን ሳይጨመር ከሰባ በላይ ሕይወታቸው አልፏል።
የሚሊዮኖች ድምጽ
Millions of voices for freedom - UDJ's photo.

በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ


mekelakeya
በኦሮሚያ እና በ150 የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣን ለማብረድ መንግስት ወታደሮቹን አሰማርቶ ትናንት ብቻ በም ዕራብ ሸዋ እና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ሕዝቤ አልተኩስም ያሉ ሕወሓት የሚያዘው መከላከያ ሚ/ር ወታደሮች በየቦታው ዩኒፎርማቸውን በአደባባይ በማቃጠል ሕዝቡን እየተቀላቀሉ ነው::
በኦሮሚያ የተነሳው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ በም ዕራብ ሸዋ ባኮ እንዲሁም በም ዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ በወራ ጅሩ; አቹማ ጎሪ እና ጊዳ ከተሞች ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል;; ቡራዩ ከተማ የመለስተኛ ሁልተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወታደሮች እንዳይገቡ በድንጋይ መንግዱን አጥረውታል::

ተቃውሞው በኦሮሚያ ክልል ሳይወሰን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በመቀጣጠል ላይ ነው፡


በምራብ ሸዋ አንቦና ጊንጭ አካባቢ ያሉ የኦሮሞ ማህበረሰብና ሌሎችም ኗዋሪዎች ዛሬ በነቂስ በመውጣት ተቀውሞቸውን በማሰማት ላይ ናቸው ፣አዲስ አበባ ነጻ እስከምትዎጣ ድረስ ተቀዋማቸንን አናቆምም በማለት ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ነው
ተቃውሞው በመንግሥት የጸጥታ ኋይሎች የሚሰነዘርበትን ድብደባ አፈናና ግድያን ከመቋቋም በላይ፣ ቀን በወለደ ቁጥር አዳዲስ ከተሞችን እያሰለፈ በከፍተኛ ሕዝባዊ ኋይል እየገሰገሰ ነው፡፡
የወያኔ አጋዚ ጦር አደባባይ ወተው ጥያቄ እያቀረቡ ያሉ ንጹሀን ዜጎችን መግደሉን ቀጥሎበታል።
ዛሬ ጠዋት በውለጋ ዩንቪረስቲ በተነሳው ተቃውሞ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ወደመሀል ከተማው በማምራት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ጦሩ በከፈተው ተኩስ በርካቶች ቆስለዋል ሂወታቸውም ያለፊ ተማሪዎች እንዳለ የሚያሳይ መረጃ እየወጣ ነው,,,
በተያያዘ ዜና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ / መተከል ዞን /አልመሃል ከተማ ዛሬ ጠዋት የጉምዝ ተወላጆች የትግሬወችን መኖሬ ቤት እና ድርጅቶች አቃጠሉ ፡ በእሳቱ ሙሉ በሙሉ ከወደሙት ውስጥ አክሱም ሆቴል ተክለ ብርሃን አምባየ የወተት ከብት እርባታ እና ንብረትነቱ አቶ መርሃዊ ገ/ፃዲቅ የተባሉ ግለሰብ የሆነ የእጣን መጋዝን ይገኝበታል፡፡
ህዝባዊ አመጹ በየከተማው እየተቀጣጠለ ነው።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ጠረፍ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።


45 ሱዳናውያን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወሰዱብኝ ስትል ጸረ ሰላም ያለቻቸውን በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ዓውግዛለች፥ በተጨማሪም ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጠርፍ ተሻግረው ሸፈቱ ሲል እሄው የሱዳን አረብኛ ጋዜጣ ዘግቧል።
ጋዜጣው እንደዘገበው 45 ሱዳናውያን ዜጎቿ በታጣቂዎች ተይዘው፥ በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ በመተማ ዓካባቢ እንደሚገኙና የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዓሳውቋል ሲል ይገልጻል፥
የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ከሚሰጠው የድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሱዳን ተወልደው ያደጉና በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግረው በርሃ መግባታቸው ታውቋል።
በሰሜን ጎንደር የሱዳን ጠረፍ ዙሪያ ከፍተኛ የዓመጽ እንቅስቃሴ እንዳለና የሕዝቡ ቁጣ ግለቱ እየበረታ መሆኑ ከዓካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፥
ሞት ለወያኔ፥ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሰበር ዜና ! ! !ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ተከፈለ


ዛሬ ከወታደራዊ ደህንነት ቢሮ የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰራዊቱ የህወሐትና ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሚል ተከፍሏል።፣ በሰሜን በምስራቅ እዝ፤ በደቡብና በምእራብ እዝ ዉስጥ የሚገኙ የእግራኝና የሜካናይዝድ አባላቶች ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ ከጥያቄዎቹ በጥቂቱ
* በአሁኑ ወቅት በመላዉ ሐገሪቱ እየሆነ ስላለዉ ያለመረጋጋት ገለጻ ይደረግልን?
* እኛ ወደ በረሐ ወጥተን የምንንከራተተዉ ለዚህ ደሐና እንክርት እዝብ ሉአላዊነት ነዉ ለምንድን ነዉ ፌደራል ፖሊስና ፖሊስ ሰራዊት ላይ እርምጃ የማይወሰደዉ?
* ቤተሰቦቻችንን ጥለን ሐገር ስንጠብቅ እናነተ ከተማ መሐል ያሉ ቤተሰቦቻችንን ትገድላላችሁ ምን ማለት?
* አርበኞች ግንቦት 7፣ ኦነግ እያላችሁ አታጨቅጭቁን መጀመሪያ ህዝቡ የሚፈልገዉን አድርጉለት ከዚያ ወዲህ ስለ ዉጊያዉ እንነጋገራለን!!
* በጎንደርና በትግራይ በኦጋዴን በተለያዩ ስፍራዎች በጦርነት እየተመታን ነዉ እኛ እንኳን አማጺያንን ልንመክት ቀርቶ በቤተሰቦቻችን ሐሳብ አልቀናል!!
ሌሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነን ህዝባችን ላይ አንዘምትም በማለታቸዉ። በመንግስት ላይ መከላከያዉን አሳምጸዋል በሚል ዉንጀላ ከ20 በላይ አባላት የተከሰሱ ሲሆን የመቶ አለቃ ሪቁቱ ከምስራቅ እዝ በወታደራዊ ደህንነቱ በወጣ ትእዛዝ ትናንት ተወስደዉ የደረሱበት ባለመታወቁ ዉስጥ ለዉስጥ ዉጥረቱ ተባብሷል።
በተያያዘ መረጃ የብሐራዊ ደህንነት የተባለዉ ወንጀለኛ ክፍል ከ001 ቁጥር በወጣ ትእዛዝ መሰረት በመንግስት ጉያ ስር ተቀምጠዉ ከግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር በመሳጠር ሁከት ሊያስነሱ ይችላሉ ያላቸዉን 124 የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰራዊት አባላት እንዲያዙ ትእዛዝ ቢተላለፍም!!!~ 84 ቱን በቁጥጥር ስር እንዲያዉል የተላከዉ ሐይል ሁሉንም ሊያገኛቸዉ አለመቻሉን አሳዉቋል።
በተጨማሪአዲስ አበባ ዉስጥ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎችን በማከናወንና የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ ለማስቀልበስ ጌታቸዉ አሰፋ የተባለዉ የደህንነቱ ቢሮ ዳይሬክተር ክፉኛ እየተጋ እንደሆነ ያሳወቁን ግለሰብ እንደገለጹት ህዝቡ ከዚህ በኋላ ቦንብ አይደለም ምንም ቢፈነዳ የሚመለስ አይነት ባለመሆኑና በራሱ በደህንነት መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚገኙ ትግሬ ያልሆኑ የተለያየ ብሐረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያኖች እንዲህ ባለዉ ነገር ባለመስማማታቸዉና ልዩነት በመፈጠሩ የተነሳ ነዋሪነታቸዉ ጉለሌ አካባቢ የሆኑ አንድ የደህንነት ቢሮዉ ስርጭት ክፍል ( program facilitator ) ግለሰብ በዳይሬክተሩ ትእዛዝ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
ወያኔ ይዉደም! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

Sunday, December 13, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ


አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከህዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓም ድረስ ሰራዊቱ በሚገኝበት የትግል ቦታ የመጀመሪያውን የምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ በስኬት አጠናቋል::
ይህ ስብሰባ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከተሰኘ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያው የምክር ቤት ስብሰባ ነው::
ይህ ስብሰባ፦
1. ውህደት ከተደረገበት ከጥር 2 2007 ዓ.ም ወዲህ የስራ አስፈፃሚውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል፤
2. ከውህደት ወዲህ ንቅናቄው የፈጸማቸውን ተግባራት በጥልቀት መርምሯል፤
3. የንቅናቄውን ህገ-ደንብና አሰራሮችን መርምሮ ማሻሻያዎችን አድርጓል፤
4. የምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል
5. ተተኪና ወጣት የአመራር አባላት ምክር ቤቱ ውስጥ እንዲካተቱ አደርጓል፤
6. የሃገራችንን የወቅቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች በጥልቀት መርምሯል፤
7. በወቅቱ ሁኔታዎች ጥናት ላይ ተመርኩዞ የወደፊት የትግል አቅጣጫውን ቀይሷል፣ ግልጽ የሆነ የትግል ስትራቴጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፤
8. ከስብሰባው በኋላ መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት ቅደም ተከተል አውጥቶ ለስራ አስፈጻሚው መመሪያዎችን አስተላልፏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የህወሓትን አምባገነን አገዛዝ አስወግዶ በምትኩ ፍትህ የነገሰባት፣ የዜጎች እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ዴሞክራሲያዊት አገር ለመገንባት የሚያደርገውን ትግል በግንባር ቀደምትነት ለማስተባበርና ለመምራት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መነሳቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይገልጻል::
አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ወደ አዲስ ደረጃ ተሸጋግሯል ብሎ ያምናል:: ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችና ድርጅቶች በሙሉ በሚያመቻቸው መንገዶች እየተደራጁ ከንቅናቄያችን ጋር ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ትግል አምባገነኑን ወያኔ ከስልጣን እንድናስወግድና በምትኩ ፍትህ፣እኩልነትና የሃገርን አንድነት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ስርዓት እንድናቋቁም ጥሪ ያደርጋል::
ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ!