Saturday, October 31, 2015

በባህርዳር የባጃጅ ሾፌሮች አድማ መቱ




የባህርዳር ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በከተማው ባጃጆች ከአንድ መስመር ውጭ እንዳይሰሩ ከመከልከላቸው ባሻገር ኮንትራት ጭናችኋል በሚልና በሌሎችም ሰበቦች በየቀኑከፍተኛ ቅጣት ስለሚጣልባቸውና ቅጣቱ ከሚያገኙት ገቢ በላይ በመሆኑ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ መገደዳቸው ተናግረዋል፡፡ ታክሲዎች በማይደርሱበት አካባቢ ጭምር ኮንትራት ሲጭኑ 400 ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የገለፁት ሾፌሮቹ፣ በሌሎች አጋጣሚዎችም በየቀኑ ስለሚቀጡ ለኪሳራ እንደተጋለጡ ገልፀዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ለገዥው ፓርቲ ሰዎች ቅርበት ያላቸው የባጃጅ ሾፌሮች የተሻለ ገቢ በሚገኝበት አካባቢ ስምሪት ሲሰጣቸው ሌሎቹ ገቢ ወደሌለበት እንዲሰማሩ በመደረጋቸው፤ ይህም ቅሬታ አስነስቶ እንደቆየ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ሁሉም በተደጋጋሚ ከቅጣት ባለመዳናቸው ባለፈው ሳምንት ጀምሮ አብዛኛዎቹ የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ በዛሬው ቀን ሁሉም ስራ ማቆማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት በከተማው የትራንስፖርት ችግር አጋጥሟል ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment