ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ ም ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ዓካባቢ በሚኖርበት ቀበሌ ከጓደኛው ጋር ባመሹበት የተገደለው እውቅ ባለጸጋ ገበሬ፥ በሰሜን ጎንደር በተለይም በዓርማጭሆና በጠገዴ ወረዳዎች በመልካምነቱ ከፍ ያለ ዝናን ያተረፈ፥ በብዙዎች የተከበረ ደህና ጎበዝ እንደነበረ በሰፊው ይነገራል፥ ኃይሌ ገብረመድህን ዓለሙ ነብስ ይማር!
በተለይም ባለፈው ዓመት ተቀስቅሶ በነበረው የክልል ዓንድና የክልል ሶስት የድንበር ውዝግብ ላይ፥ ዓካባቢውን ወክለው ከሕዝብ ጎን በመቆም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ካደረጉ የሰሜን ጎንደር ተወላጆች ጋር ስሙ ይጠራ እንደነበር ይታወቃል፥እሄን የድንበር ግርግር ተከትሎ በማህበረሰቡ ያገኘው ተደማጭነትና ተወዳጅነቱ በወያኔዎች ጥርስ እንዳስነከሰበት በዋናነት ይጠቀሳል፥ በብዙ የወገን ተቆርቋሪ ኢትዮጵያን ላይ ሲፈጸም የኖረው የሞት እጣ ደርሶበት፥ ዛሬ እሄን ጀግና ገበሬ፣ የዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የግፍ ሰለባ ዓድርጎታል፥
ይህ ዓይን ያወጣ በዓደባባይ የተፈጸመ የግድያ ወንጀል፥ የክልሉ የምክር ቤት ዓባል ወንድም እጂ ይፈጸም እንጂ ግድያው ላይ ዓብረው የነበሩት የምክር ቤት ዓባል፥ ዓቶ ቻሌ ዓለሙ እራሳቸው ከጓዶቻቸው ጋር በመሆን ያደረጉት የተቀነባበረ ወያኒያዊ ተግባር መሆኑን የሚያሳብቁ ብዙ መረጃዎች እየተጠቀሱ ነው፥ ወጣቱ ገበሬ ዓቶ ኃይሌ፥ ዓገሩንና ሕዝቡን የሚወድ፥ ለተበደለ ሰው ተቆርቋሪ፥ ለተቸገረ ወገን ደራሽ፥ የተጣላ ዓስታራቂ፥ ዋስ ጠበቃ የሚሆንና፥ በሕብረተሰቡ ተወዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ወደ ዓርባ ዓመት የሚጠጋና የሶስት ታዳጊ ልጆች ዓባት መሆኑም ተገልጿል፥ኃይሌ ገብረመድህን ዓለሙ / Haile Gebremedhin Alemu
ለግድያ የሚያደርስ ምንም ምክንያት በሌለበት የመዝናኛ ቤት ውስጥ፥ የተቀነባበረ እርምጃ በሚመስል መልኩ ባለተጠበቀ ሁኔታ የተፈጸመውን ግድያ፥ በቅርበት የታዘቡ የዓካባቢው ነዋሪዎችና፥ የዓቶ ኃይሌን ማንነት ለሚያውቁ ሁሉ፥ በዚህ ወንጀል ላይ የመንግሥት እጂ ያለበት ያስመስለዋል ሲሉ ግምታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፥ ብቻውን ሳይሆን 8 እራሱን ገብቶ ነፍስ ያጠፋው፥ ገዳይ ማንነት ቢታወቅም በብዙ ሰዎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ዓሰቃቂ ወንጀል ፈጽሞ ያለምንም ጠያቂ መኪናውን ዓስነስቶ ማምለጡና፥ በሰዓቱ የዓካባው መብራት እንዲጠፋ መደረጉ፥ከገዳዩ ጋር ዓብረውት የነበሩ ግለሰቦች በጥይት ተመቶ የወደቀውን ቁስለኛ ለመርዳት ምንም ሳይሞክሩ ጨለማን ተገን ዓድርገው መሸሸታቸው፥ የገዥውን ሥርዓት ዓራማጅ ማንነታቸውና፥ ከገዳይ ጋር ያላቸው የዝምድና ትስስር ሲጨመርበት፥ ዓጥምደው እንዳጠፉት ጥርጣሬውን ዓጠናክሮታል፥ ዓብሮት ከነበረው የምክር ቤት ዓባል ወንድሙ ጋር፥ ለማምለጫ የተጠቀሙባት የገዳይ መኪና መለያ ሰሌዳዋ ተነቅሎ ጎንደር ዓየር ማረፊያ ቆማ መገኘቷ ደግሞ ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ያደርገዋል፥የዓቶ ኃይሌ ነፍስ በእጇ ላይ ማለፉን ዘግየት ብላ በስፍራው ከደረሰችው የሟች ሚስት የተረዱ፥ በዓካባቢው የነበሩ ሰዎች በሰዓቱ የጸጥታ ዓስከባሪ ፖሊስ ወይም ወደ ህክምና የሚወስድ ሌላ ዓካል ደርሶለት ቢሆን ኖሮ ሕይቱ ሊተርፍ ይችል እንደነበረ ዓስተያየታቸውን ይሰጣሉ፥

No comments:
Post a Comment