(ለገሰ ወ/ሃና )
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት( መኢአድ) ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ በመላው ሀገራችን እና በውጭ ሀገር የሚገኘው ህዝብ መኢአድ ይዞት የተነሳው ሠላማዊ ትግል ህዝብ የሚፈለገው የህግ የበላይነት : እኩልነት የሠፈነበት ስርአት እና የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ ምንግዜም ቢሆን ሠላማዊ ትግሉ የማይቋረጥ እንደሆነ ገለጹ:: ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ አቶ ማሙሸት አማረ የትግሉን ዉስብስብነት እና እልህ አስጨራሽነትም አጽንኦት ሰጥተዉ ገልጸዋል::
ይህንን በመገንዘብ አባሎቻችን : ደጋፊዎቻችን እንዲሁም መላው ህዝባችን ለምናደርገውን ትግል እንደ ሁልጊዜው ያልተቋረጠ ድጋፉን እንዲያደርግና አባላቱ በያሉበት ሠላማዊ ትግሉን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል:: እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶች የመኢአድ አባላት በመሆናቸው ብቻ እየተለቀሙ ወደ እስር ቤት የተወረወሩ አባላትን ከጎናቸው ቆመን አጋርነትችንን ማሳየትና የሚራቡትን ቤተሰቦቻቸውን ማገዝ እንደሚገባ እና ሠላማዊ ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል ትግሉን እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል::
መኢአድ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ቦርድን ከሶ በፍርድ ቤት እየተከራከረ መሆኑን እና በህገወጥ መንገድ የተነጠቀዉን ቢሮ ለማስመለስ እየሰራ መሆኑንም አያይዘዉ አብራርተዋል::
እስካሁን ድረስ ለተደረገዉ ትግል ያልተቋረጠ ድጋፍ ላደረጋችሁ ሁሉ በመኢአድ ሠማዕታት ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም አክብሮታቸዉን ገልጸዋል:: ለወደፊቱም መኢአድ እስከመጨረሻዉ ህቅታ ድረስ ለኢትዮጵያ ፍትህ እንደሚታገል ገልጸዉ ድጋፋችሁ እንደማይለየን እምነታችን የፀና ነው ሲሉ ንግግራቸዉን አሳርገዋል ::

No comments:
Post a Comment