ራያ ቆቦ አካባቢ በኢትዮጵያ እጅግ ለም ከሚባሉ መሬቶች አንዱ ነው። ወያኔ በምስራቁ አቅጣጫ ከዓለታማ ክልላቸው ባሸገር ያሉትን ለም የወሎ ወረዳዎች ከወሰዱ ቆዩ ኮረም፣መሆኒ፣ራያ፣አዘቦ….ልጆቹም የአማርኛ መጻህፍቶች እየተቃጠሉ በትግርኛ እንዲማሩ ተደረገ።
አሁን ደግሞ ዓይን ባወጣ መልኩ ቆቦ ወረዳን ለመዋጥ አሰፍስፏል። ድንበራችን አለውሃ ድረስ ነው የሚለውን ትርክት በየቀኑ ከሊቅ እስከ ደቀቅ የሚያነበንቡት ነው። የህወሀት ማባበያ የሚሆኑ አሳሂ ስልቶችም ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። ለምሳሌ ቆቦ ወረዳ ባዛር ሲያካሂድ የአማራ ክልል መንግስት በጀት አልያዝኩም በሚል ሰበብ ገሸሽ ሲል እነ አባይ ወልዱ ስፖንሰር እና አጋፋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተደረገ። በሌላ ጊዜ ለአማራ ክልል የልማት ቴሌቶን ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሲዘጋጅ የትግራይ ክልል ቆቦ ወረዳ ላይ ት/ቤት ፣ጤና ጣቢያ ለመስራት ቃል ሲገባ አይተናል። ያለምንም ምክንያት ከመቀሌ ወደ ቦታው እየመጡ የሙዚቃ ኮንሰርትና ሰርከስ የሚያሳዩበት ጊዜም አለ።
አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉትም ትግራይ በቆቦ አይወሰንም። ይልቁንም ወልደያ ድረስ strategic interest እንዳለው ይናገራሉ። ከወልደያ ወጣ ብሎ የቆመው “እንኳን ወደ ትግራይ ደህና መጣችሁ” የሚለው ታፔላ ራሱ አመላካች ነገር አለው። የወደቅ ግንድ ምሳር ይበዛብታል እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከትግሬ ባሻገር ኦነግ ስንቱን ክ/ሀገር አቃራርጦ መጥቶ ራያ የኔነው ሲል እያየን ነው። ተቆርቋሪ ሞግዚት የሌለው ህዝብ መቼም እንዲህ ነው!
No comments:
Post a Comment