
የግብጽ የወሬ ምንጮች የሀገሪቱን የውሀና መስኖ ሚኒስትርን ሆሳም ሞጋዚን ጠቅሰው እንደዘገቡት ከሆነ ሀገሪቱ ከነገ ማለትም ከፈረንጆቹ ኦክቶበር 4-5 ለሁለት ቀናት ከሱዳንና ኢትዮጵያ ጋር በዛው በግብጽ ንግግር ታደርጋለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ሶስቱ ሀገራት በግድቡ የጎንዮሽ ተጽእኖ ላይ ጥናት እንዲያካሂዱ ሁለት የውጪ ድርጅቶችን የመረጡ ቢሆንም ድርጅቶቹ ባለመስማማታቸው ጥናቱ አለመካሄዱና ይባስ ብሎም ዴልታሬ የተባለው የደች ኩባኒያ ከዚሁ ስራ ራሱን ማግለሉ ሲዘገብ ነው የሰነበተው፡፡ በዚሁ በአሁኑ የንግግር መርሀ ግብር ላይ በሁለቱ ድርጅቶች መሀል የተፈጠረው ክፍተት ዳግመኛ በሚጠብበትና ስራው ድጋሚ በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ምክክር ይደረጋል ነው የተባለው፡፡ በውይይቱ ላይ ከዚህ በተጨማሪም የሶስቱ ሀገራት ባለስልጣናትና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እንደሚካፈሉ ነው የተነገረው፡፡
No comments:
Post a Comment