Wednesday, October 21, 2015

“እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል” ለአባይ ግድቡ? ለአባይ ወልዱ? ወይስ ለአባይ ጸሃዬ?


Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.Amdom Gebreslasie's photo.

ለ900ሺ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ሰሙኑን መቀሌ ከተማ ደርሰዋል።
አንድ ሚሊዮን ለሚጠጋ ተረጂ እስከ 350 መኪኖች እህል ጭነው በቀጥታ ከጅቡቲ ትግራይ ገብተዋል።
መንግስት እንዳለው የጫኑት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ሳይሆን ከውጭ በእርዳታ የገባ መሆኑ ጭነው የመጡት ሹፌሮች አውግተውኛል።
“ድርቁ በቁጥጥር ስር ኣውለነዋል” የሚል የትግራይ መንግስት መግለጫ ተደጋግሞ እየተሰማ ባለበት ቅፅበት “ለእርዳታ የመጣው እህል እየተሸጠ ነው” የሚል ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው።
እህሉ መቀሌ ከተማ ወደሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጠ መሆኑና ጥያቄ ላነሱ ሹፌሮች ደግሞ “ድርቁን በቀላሉ ስለተቆጣጠርነው ትርፉ ተሽጦ ለአባይ እንዲሆን ተወስኗል” ተብሎዋል።
ከእኔ ጋር ሁኖ ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት “… የትኛው አባይ ነው? አባይ ግድብ፣ አባይ ወልዱ፣ ወይስ አባይ ፀሃዬ …” ብሎ ጠይቋል።
የትግራይ ገዢዎች ድርቁም እህሉም በቁጥጥራቸው ስር ያዋሉ ይመስላሉ …!!! ድርቅ ካጠቃው፣ ህይወቱ በአደጋ ውስጥ ከገባ፣ ህይወቱን ለማቆየት የጎረሳት ማቆያ ምግብ ከጉሮሮው የሚቀሙ ሌቦች እንጠብቀው።
ኤፍ ኤም ፋና ትግርኛ ፕሮግራም ምስጋና ይድረሳቸውና ትንሽ ብትሆንም የድርቁ ሰለባ ወገኖች ድምፅ አሰምተውናል።
“ወጣቱ ስደት ከመሄድ ትንሽ ተረጋግቶ ነበር። ኣሁን በድርቁ ምክንያት ፈርቶ ባህር እየገባ ነው … ተማሪዎች በዚህ ሁኔታ መማር ኣንችልም ብለው ቤት እየዋሉ ነው … ከ8 ሺ በላይ የቀበሌያችን ከብቶች በምግብና ውሃ እጦት ክፉኛ ተደርቀውብናል … መንግስት ቶሎ ሊደርስልን ይገባል … ” ብለው ሲናገሩ ሰምተናል።

No comments:

Post a Comment