ስለ ንፁህ ውሃ ለመወያየት የሁሉም ክልሎች የውሃ መስርያቤት ኃላፊዎች አድዋ ድረስ እንዲሄዱ ከተደረገ በኃላ ”ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት አቶ አባይ ወልዱ” ”ስለ ውሃ ለመነጋገር እዚህ ድረስ በመምጣታችሁ ተሞክሮ ስለምናገኝ ደስ ይለናል” ካሉ በኃላ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ገርባ ንግግር ሲያደርጉ እንዲህ አሉ ”ባለፉት 5 አመታት ብቻ 41 ሚልዮን ሕዝብ ንፁህ ውሃ ማድረስ በመቻላችን ከሣሃራ በታች ካሉ አገሮች ቀዳሚ ሆነናል።አሁን የንፁህ ውሃ ሽፋናችን 80% ደርሷል” ሲሉ ተናገሩ።ውሸት በቁሙ ሲሄድ ማለት ይህኔ ነው።አቶ ኃይለማርያም አዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ውሃ እያገኘ አይደለም ካሉ ገና ሁለት ዓመት አልሞላውም። እና አቶ ከበደ ምነው ቁጥሩን አከበዱት? እና ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር፣ከሐረር እስከ ባህርዳር ንፁህ ውሃ አጥተው ቢጫ ጀርካል ይዘው የሚንከራተቱት ኢትዮጵያውያን 20% ውስጥ ብቻ ያሉ ናቸው ማለት ነው?
የአድዋ ውሃና ፍሳሽ መስርያቤት የእናት ልጅ ወይንስ የእንጀራ ልጅ?
========================================
ከላይ እንደጠቀስኩት የውሃ ፎረም እየተደረገ ያለው አድዋ ላይ መሆኑን ስሙን በእንግሊዝኛ ብቻ የምፅፈው የአማርኛ መሃይም የሆነው EBC ገልጧል።ማታም ይደግመው ይሆናል።የእኔ ጥያቄ የአንዲት ከተማ የውሃ ፍሳሽ መስርያቤት በምን በጀቱ ነው እንደ ዜናው የ 9ክልሎች የውሃ መስርያቤቶችን ኃላፊዎች ባለሙያዎች ወዘተ የትራንስፖርት ወጪ፣የሆቴል እና ሌሎችም ወጪዎችን ችሎ ማዘጋጀት የቻለው? በዜናው ላይ ዋናው መስርያ ቤት ሳይሆን የአድዋ ውሃና ፍሳሽ ቢሮ የጠራው እና ያዘጋጀው ይላል።።የውሃ ፍሳሽ የአንዲት ከተማ ቢሮ ቀርቶ ዋና መስርያ ቤቱ የረባ ወንበር እንደሌለው እናውቃለን።እና ከቢሮ ቢሮም የእናት ልጅ እና የእንጀራ ልጅ አለው እንዴ?
(በነገራች ላይ ከላይ ያወጋሁት በሙሉ የዛሬ ጥቅምት 12/2008 ዓም የቀትር ኢቲቪ ቀዳሚ ዜና ነበር።መንገድ ላይ ስሄድ ሞባይሌን ስነካካት ያሰማችኝ ጉድ ነው)

No comments:
Post a Comment