የሰሞኑ የስልጣን ቅርጫ ላይ ያልታዩት አቶ ሼምየለሽ ከማል የትገቡ ? በኢትዮዽያ ህዝብ ላይ ዳማ ሲቆሙሩ ቆይተው በተለይም በሙስሊሞቹ ህዝብ ላይ የዶክመንተሪ ፊልሞችን በማቀነባበር የተካኑ የነበሩት አቶ ሼምየለሽ ከማል ዛሬ ምን ዋጣቸው በህይወት ከሌሉ ነብሳቸውን አይማረው አገር ጥለው ወተውም ከሆነ በተሰደዱበት ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልጠራጠርም. አቶ ሼምየለሽ ኡስታዝ አቡበከርን ‹‹አጥፍቶ ጠፊ›› ብለው መዝለፋቸውን ሰምተዋል?
አቶ ሼምየለሽ በቃለ መጠይቃቸው ሌላ ቦታ ላይ የተናገሩት ንግግር ደግሞ መንግስት እስልምናን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን የሚያረጋግጥ ይመስላል፡ በየሲዲው ፀብ ቆስቋሽ ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያስፈፅሙት፣ በኢቲቪ አፍሪካ የተለያዩ ቻናሎችን በመጠቀም የሚያሰራጩት እነዚሁ አክራሪዎችና ሽብርተኞች ናቸው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በካቴና ተጠፍሮ መታየቱን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ደግሞ አቶ ሼምየለሽ ከማል ክፋት የተሞላበት ንግግር ተናግረዋል፡፡ ‹ራሴን አጥፍቼ እጠፋለሁ፣ ወደ ጥፋትና ወደ ሽብር ሥራ እገባለው ያለ ሰው በማለት ምንም ሳይሰቀጥጣቸው አፋቸውን ሞልተው ተናግረዋል
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለንድም ቀን እንኳን እንዲህ ያለ ንግግር ተናግሮ አያውቅም፡፡ እጅግ ሰላማዊና ሰላምን ሲሰብክ የቆየ ሰው ነው፡፡
ሁልጊዜም ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው አስተዋይ የሙስሊሙ ህዝብ መሪ ነው ፡፡ መንግስት የሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪዎችን ለማሰር ባሰበበት ወቅት እንኳ እኛ ብንታሰር ከስሜታዊነት ራቁ! ሲል ነው ህዝበ ሙስሊሙን ቃል ያስገባው፡፡ ይህን ለሚሊዮኖች ተምሳሌት የሆነ ሰው ‹‹አጥፍቶ ጠፊ›› ሲሉ መሳደብ ወንጀል ነው – ምን ያደርጋል! ይህን እንኳ የሚያርም የአስተዳደርም ሆነ የፍትህ ስርአት የለም እንጂ፡
አቶ ሼምየለሽ ከማል እንደው በደፈናው ለማስታወስ ያክል ነው እንጂ የሰሩት ስራ ወንጀል ተነግሮ አያልቅም ወያኔ ኢሀዴግ በግዜያዊ መገልገያነት የሚጠቀምብሽ ባለስልጣናት ሁሉ እንደማስቲካ እያላመጠ እንደሚተፋሽ አትጠራጠሪ ህዝብ ከፈጣሪ በታች ፈራጅ ነውና ፍርድህን ከህዝቡ ትቀበላለህ ብዙም ሳንጎአዝ የሌሎችንም ባለስልጣናት ታኝኮ መትፋት እናያለን የአቶ ሼምየለሽ ከማል ምንጩ ሳይታወቅ ተስፈንጥሮ ከስልጣን መወገድ ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር ባልነበራቸው የስራ አለምግባባት እንደነበር ምንጮች ይጠቅሳሉ
በአንድ ወቅት አቶ ሼምየለሽ ከማል በተሰጣቸው ወንበር ላይ በመኮፈስ በማን አለብኝነት ከሳሹም ፈራጁም እሳቸው ነበሩ የ አንድነት የፍተህ ፓርቲ በጠራውም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ምንም ሳይዘገንናቸው በሽብር ተግባር ላይ የተሰማሩ በማለት ሰልፈኞችን ፈርጀዋል

..ወያኔ ኤሀዴግ አብዛኛውን ግዜ ተገልግሎባቸው ሊጥላቸው የሚፈልጋቸውን ባለስልጣናት ከህዝብ ጋር በደንብ አርጎ ያናክሳቸዋል ህዝብን እንዲያሰቃዩ እንዲሳደቡ በማን አለብኝነት እንዲንቀሳቀሱ ካደረገ በውኃላ ከቅርብ የስራ ባልደርባቸው ጋር የማናቆር ስራውን ይሰራል ይህን አሰራር ወያኔ ኤሀዴግ ከጫካ ጀምሮ የተካነዉ የስራ ልምዱ ነው የኛዎቹ ሆድ አደሮች ግን መቼም አይረዱትም እንደዚ እያደረገ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ይገለገልባቸዋል ዘመነኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ
አሁን ደሞ ተረኛው አቶ ሬድዋን ሁሴን የምክትል ጠቅላይ ሚንስቴርነት ቦታ ለማግኘት መቀመጫቸውን ሲያሰፉ ቆይተው ያልታሰበ ዱብዳ ወርዶባቸዋል. አቶ ሬድዋን ሁሴን ከመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትርነት በመነሳታቸውም በጣም ደስ ብሎኛል፤ ተግባሩን ለተከታታለ፣ ለዚህ ትልቅ ቦታ የሚመጥን ሰው አልነበረምና፡ሬድዋን ሥልጣኑን ፖለቲካ ማራመጃ አድርጎት ነበር ያውም በወሳኝ ህዝባዊ ጉዳዮች ላይ ! አሸባሪው ISIS ውድ የሀገር ልጆችን አንገት በአደባባይ ሲቀላና አናታቸውን በጥይት ብሎ ሲደፋ፤ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ገና አልተረጋጋጠም›› ብሎ በዜና ያስነገረ ሰው ነበር
ሬድዋን በሚሰጣቸው መግለጫዎቹ፣ በ‹ምርጫ ክርክር›› ወቅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚጣረስ ነገር ሲገልጽ እንደነበረ በስፋት ዘርዝሮ መግለጽ ቢቻልም ፡፡

የሬድዋንን ቦታ የተካው አቶ ጌታቸው ረዳም ቢሆን በአደባባይ ሲዋሽ እናውቀዋለን፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በበየመን የፀጥታ ሀይሎች ተይዞ ለኢትዮጵያ መንግሥት መሰጠቱን ተከትሎ ከሀገር ውጪ ከሚገኝ አንድ የሚዲያ ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ መረጃው እንደሌለውና ጉዳዩንም እንደማንኛውም ሰው በማኅበራዊ ድረ-ገጽ መስማቱን ነበር በወቅቱ የገለጸው፡፡
በባለፈው ዓመት ‹‹የምርጫ ክርክር›› ወቅትም ከዶ/ር ቴዎድሮስ ጎን ሆኖ፣ ለተቃዋሚዎች ብሽሽቅ የሚመስል መልስ ሲሰጥ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ …
ጊዜያዊ ስልጣንን ምርኩዝ በማድረግ በማንአለብኝነት ዜጎችን በንግግር ማናደድ እና ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሃይላትን ማብሸቅ ለቀድሞ ሟች በዘረኝነት መንፈስ ለተለከፉት ጠቅላይም አልበጀም፡፡ …
ለማንኛውም ሬድዋንም ሄደ ጌታቸው ተተካ ለህሊና፣ ለእውነትና ለመርህ መኖር፣ ብሎም ሕዝብን ማገልገል እስካልተጀመረ ድረስ አዲስ ሚኒስትር እንጂ ለውጥ አይመጣም ! የዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚቀልድባት ሳይሆን ለእውነት የሚሰራላት ሰው ነው የምትሻው!!!
ለሃገራችን ነፃነት እንታገል በኃገር እና በህዝብ ትከሻላይ ሲደንሱ ቆይተው እርስበርስ በመናቆር ስልጣናቸውን ሲለቁ መንግስት ወንጀላቸውን ሸፍኖ ከለላ ቢሰጣቸውም እኛ ዝም ልንላቸው አይገባም በሰሩት ስራ ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ባገኘነው አጋጣሚ ልንረባረብ ይገባል

በኢሳ አብድሰመድ
No comments:
Post a Comment