Monday, October 19, 2015

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግብጽና የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን አስጠነቀቁ


ግብጽና ኢትዮጵያ ሊዋጉ ነው እንዴ? ይሄ መግለጫ አላማረኝም
“በሰላም የመኖር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ግብጽ የተለያየ መስርያ ስለገዛች በመሳርያ ኃይል ኢትዮጵያን አታንበረክክም:: ነው እንጂ ግብጽን አንፈራም:: ግብጽ ጠቅላላ አገር ምድሩን መሳርያ ማድረግ ትችላለች ከፈለገች:: የሚዋጋው ግን መሳርያ አይደለም:: እኛም ራሳችንን የመከላከል መብት አለን:: እንከላከላለንም” ኃይለማርያም ደሳለኝ
“ግብጽ ከካይሮ ተነስታ ኢትዮጵያን አታጠቃም:: እኩይ ዓላማ ያላቸው ጎረቤቶቻችን ለዚህ አላማ ድጋፍ ከሰጡ ግን እናስጠነቅቃለን:: ጣታቸውን ካንቀሳቀሱ አስቀድመን እንጨርሳቸዋለን” ኃይለማርያም ደሳለኝ
ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲህ አይነት መራር መግለጫ ሲሰጡ ብዙም አይሰሙም:: ዛሬ ግን ግብጽንም ለግብጽ ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ የኢትዮጵያን ጎረቤቶች መራር ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::
“አስቀድመን እንጨርሳቸዋለን” እስከማለት የደረሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብጽንም አልማሯትም:: ” ግብጽ አገር ምድሩን መሳርያ ብታደርገው መሳርያ ብቻውን አይዋጋም” እስከማለት ያደረሳቸው ምን ይሆን?
የኢትዮጵያ ደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ሰው የሆኑትን አቶ ጌታቸው አሰፋም ያለወትሯቸው እዚህ አሜሪካ መሆናቸው ተወስቷል::ኢሳትንም ከራሺያ ሳተላይት ለማውረድ ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እንዳካሄደች ኢሳት ዘግቧል:: በተመሳሳይ ዜናም ኢትዮጵያ ሰራዊት ምልመላ መጀመሯ ተዘግቧል::
ስምንትና ዘጠኝ ሚሊዮን ሰው በረሃብ ውስጥ ባለበት ሰዓት የወቅቱ ዜና ረሀቡና እርዳታ መሆን ሲገባው ይሄን ጦርነት መሰል መግለጫ በዚህ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒትሩ የሰጡት ምን ችግር ቢኖር ይሆን?

No comments:

Post a Comment