Wednesday, October 28, 2015

የአሜሪካ ኢምባሲ የመኢአድ ፕሬዝዳንት የአቶ ማሙሸት አማረን ቪዛ ከለከለ


በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ዉስጥ ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ዉስጥ ይሰፍን ዘንድ ከሃያ አራት አመታት በላይ ሲታገል የኖረዉ እዉቁ
የፖለቲካ ታጋይ አቶ ማሙሸት አማረ በወያኔ መንግስት ከአስር አመታታ በላይ በእስር ቤት ሲማቅቅ ኖሯል:: በቅርቡ እንኳን
ባልተጨበጠ ዉንጀላ አቶ ማሙሸት አማረ ለወራት በእስር ቤት ሲንገላታ ከርሞ ሁለት የተለያዩ ዳኞች በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ
ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም ብለዉ በመፍረዳቸዉ ነጻ መለቀቁ ይታወሳል::
እንዲያዉም የመጀመሪያዉ ዳኛ በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ ጥፋት አላገኘሁበትም ብሎ ግልጽ ፍትሃዊ ብይን ሲበይንለት
በፖሊስ እምቢተኝነት እና ፖሊስ አለቀዉም ስላለ እስር ቤት ሲማቅቅ መክረሙ ይታወሳል::በመጨረሻም ሁለተኛዉ ዳኛም
ተመሳሳይ ብይን በማስተላለፉ አቶ ማሙሸት አማረ ነጻ መዉጣቱ ይታወቃል::
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ደስታቸዉን ለመግለጽ እና የድርጅታዊ ድጋፋቸዉን ለማጠናከረ በማሰብ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት ( የመኢአድ) ደጋፊዎች እና አባላት ለአቶ ማሙሸት አማረ ግብዣ አድርገዉለት ነበር::
ለአሜሪካ ኢምባሲ በላኩትም የግብዣ ጥያቄ መሰረት ሁሉንም ወጭዉን ማለትም የአዉሮፕላን ጉዞዉን እንዲሁም
የሚቆይባቸዉን ቀናት ወጭዎች ሁሉ በመሸፈን በአምሳ አንዱ የአሜሪካ ግዛቶች እየተዘዋወረ ደጋፊዎችን እንዲያበረታታ
የመኢአድ አባላትን ደግሞ በርትተዉ የድርጅቱን ስራ እንዲሰሩ ለማበረታታን እንዲችል ለማድረግ አቅደዉ ግብዣ አደረጉለት::
በአዲስ አበባ የመሸገዉ የአሜሪካ ኢምባሲ ግን አስቂኝ ምክንያት በመፍጠር አቶ ማሙሸት አማረን ቪዛ ከልክሎታል::
ከሃያ አራት አመታት በላይ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ የፖለቲካ ትግል ዉስጥ የኖረን ሰዉ : ህይወቱን ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል
የሰጠን ሰዉ እንዲሁም ከአስር አመታት በላይ በአምባገነኑ የወያኔ በእስር ቤት ሲማቅቅ የኖረን ሰዉ ሀብት አላፈራህም :
ንብረት የለህም: ሚስት እና ልጆች የሉህም ስለሆነም ቪዛ አንሰጥህም በሚል ተልካሻ ምክንያት ወደ አሜሪካን ሀገር
በመሄድ ደጋፊዎችን እና አባላትን እንዳያነቃቃ ከልክሎታል:: ይሄ ዉሳኔ በአጠቃላይ አስቂኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ሰላማዊ
የዲሞክራሲ ሂደት ላይ ደግሞ የተሰነዘረ ተደጋጋሚ ጥቃትን ለማሳዬት አንዱ መገለጫ መሆኑ ግልጽ ነዉ::
የአሜሪካ መንግስት ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ አይናቸዉን በጨዉ ታጥበዉ የወያኔ መንግስት ያድረገዉን የ2007 ዓም
ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነዉ ሲሉ አዉጀዉ መሄዳቸዉ ሳያንስ አሁን የአሜሪካ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የሚያሳድረዉ ልዩ ልዩ
ተጽዕኖ እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል:: ይሄ በማሙሸት አማረ ላይም የተሰጠዉ ዉሳኔ አንዱ መገለጫዉ መሆኑን ያሳያል::
የአሜሪካ ኢምባሲ የመኢአድ ፕሬዝዳንት የአቶ ማሙሸት አማረን የአሜሪካ ጉዞ ዉድቅ ማድረጉ ከወያኔ መንግስት በተቀበለዉ ትዕዛዝ ሳይሆን አይቀርም የሚል እምነት አለኝ የሆነ ሆኖ አሜሪካኖቹም ሆኑ ሌሎች ምዕራባዉያን የወያኔ መንግስት ወዳጆች ጠንቅቀዉ ሊረዱት የሚገባዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በራሱ የሚያረጋግጥ ህዝብ እንደሆነ ነዉ:: ስለሆነም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱ እስኪረጋገጥለት ሰላማዊ ትግሉ ከመላዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እንዲሁም ሌሎች ዲሞክራሲያን ሀይሎች ጋር በመሆን ማጧጧፍ እንዳለበት የሚያሳይ ዉሳኔ እንጅ ትግሉን ወደኋላ የሚቀለብሰዉ አይደለም ስለሆነም በዉጭ ያለዉ ደጋፊና አባላት እንዲሁም በሀገር ዉስጥ ያለዉ ደጋፊና አባላት መኢአድን በማጠናከርና ዲሞክራሲያዊ ትግሉን በማጧጧፍ ለስራ መነቃቃት ይገባናል ብየ አምናለሁ ፡፡
Legese Weldehana's photo.

No comments:

Post a Comment