
በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት አማኑኤል መንግስቴ ይባላል። ድምፃዊ ሲሆን “የቋራዉ አንበሳ” በሚለዉ ተወዳጅ ስራዉ በህዝብ ዘንድ በስፋት ይታወቃል። አማኑኤል የወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ልጅ ሲሆን እናቱ ወ/ሮ እማዋይሽ የመፈቅለ መንግስት ሙከራ አድርጋችኋል በሚል በሕወሓት አገዛዝ የፈጠራ ክስ ሰለባ ሆነው የእድሜ ልክ እስር ከተፈረደባቸው ፍርደኞች አንዷ ናት። ዛሬ የአማኑኤል ታሪክ ተቀይሯል። የሕወሓት የግፍ አገዛዝ ከሚወዳት እናቱና ከሚወደው ሞያው ነጥሎታል። የሙዚቃ ህይዎቱን ትቶ የሕወሓት አገዛዝን ለመፋለም በረሀ የወረዱ አርበኞችን ተቀላቅሏል። ጨቋኙን የሕወሓት አገዛዝ ማስወገድ የሚቻለው በትጥቅ ትግል ብቻ መሆኑን በማመኑ ለዚህ ውሳኔ መብቃቱን ተናግሯል። አማኑኤል መንግስቴ በርካታ ወጣቶችን አስከትሎ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን መቀላቀሉ ታውቋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር በጥምረት ከሚሰሩ ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment