Wednesday, October 7, 2015

ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም በአዲሱ ካቢኔ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር እዛም ሄዶ ይቁረጠው ነው ?


ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስትር በነበረበት ወቅት በዋናነት በሙስሊምና የኦርቶዶክስ ቤተ እምነቶች ውስጥ ዋነኛ ፈትፋች በመሆን ሙስሊሞቹን በአህባሽ አስተምህሮ ለማስጠመቅ ከሊባኖስ ጭምር መምህራንን በማስመጣት በአስተምህሮው ለማጥመቅ መሞከሩ በዚሁ ጣልቃ ገብነቱ የተነሳ ብዙዎች ለሞት፣ለእስራትና ለስደት መዳረጋቸው አይዘነጋም፡፡
በኦርቶዶክስ ማህበረ ቅዱሳንን ለማፍረስና በአክራሪነት ስም ማህበሩ እንዲበተን ያልፈነቀለው ደንጊያ አልነበረም፡፡ጳጳሱ የዶክተሩን ድጋፍ በማግኘታቸውም ጳጳሳቶቻቸውን ማስፈራራታቸውና የሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲቀለበስ ማድረጋቸውም የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው፡፡
ዶክተሩ አሁን በአዲሱ ካቢኔ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸውን ሰምተናል፡፡ሽፈራው ዶክትሬታቸውን የሰሩት ከአካባቢ ወይም ከደን ጋር በተያያዘ ባይሆንም እዚህ አገር ሜሪት ስለማይታይ ሹመቱ የጎሳ ስብጥር ለማሟላት የተደረገ ይሆናል፡፡የሆነስ ሆነና ሽፈራው በፌደራል ጉዳዩች ቆይታቸው የብዙዎችን ህይወት ነቅለዋል፡፡መትከል ማሳደግ የማያውቁትን ሰው ደን ጋር መውሰድ ደግሞ አገር ከማውደም ተለይቶ አይታይም፡፡ማነህ አንተ ይሄ በየቤተ ክርስቲያኑ የተተከለውን ዛፍ እየቆራረጥክ ጣልልኝ የአክራሪዎች ዋነኛ መደበቂያ መሆኑን በፌደራል ጉዳዩች ቆይታዬ አረጋግጫለሁ ››ላለማለታቸው ምንም ማረጋገጫ የለኝም፡፡

No comments:

Post a Comment