Saturday, October 31, 2015

በሲዊድን ስቶኮሆንም አርበኞች ግንቦት 7 ያዘጋጀው የአገር አድንን የደጀንነት ጥሪ በደማቅ ሁኔታ በማከናወን የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች አቶ አበበ ቦጋለ እና አቶ ቸኮል ጌታሁን ለታዳሚው በረሀ ያለው ትግል እና በውስጥም በውጭም ያለው ትግል ለታዲሚው ሰፊ ማብራሪ የሰጡ ሲሆን በስዊድን በድምቀት የተካሄደ የአገር አድን ጥሪ ለጨረታ የቀረበው ፎቶ በ 100 ሺህ የስዊድን ክሮነር ተሽጧል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ – በአበበ ገላው


በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አምባሳደር ግርማ ብሩ በዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ በሌሊት በድብቅ በመግባት ሕጋዊ ስልጣኑ ሳይኖራቸው ስለስርጭቱ ለጥቂት የድርጅቱ ሠራተኞች የኢዲቶሪያል መመሪያ ከሰጡ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት (ቪኦኤ) እና በህወሀት የበላይነት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ስብሰባው በሚስጥር በተካሄደበት ጊዜ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች ለሬዲዮ ስርጭቱ ሰራተኞች ስለዜና አዘጋገብ፣ እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚተላለፈው የስርጭት ጥራት ሁኔታ መመሪያ የመስጠት ሙከራ ያደረጉ ለመሆናቸው ከታመኑ ምንጮች በተገኙ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡ ከቪኦኤ ባለስልጣኖች ዕውቅና ውጭ በሚስጥር እንዲከናወን የተደረገው ይህ ስብሰባ የተካሄደው በዋሽንግተን ዲ.ሲ 330 ኢንዲፔንደንስ አቬኑ በሚገኘው በቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል የኢዲቶሪያል የስብሰባ ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ድብቅ ስብሰባ እንዲካሄድ የተደረገው ባልተለመደ እና እንግዳ በሆነ መልኩ በሰንበት፣ እ.ኤ.አ መስከረም 26 ቅዳሜ ዕለት ከስራ ሰዓት ውጭ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ ነበር፡፡ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በሰለሞን አባተ ግንባር ቀደም አደራጅ እና አስተባባሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድምጽ የትግርኛው ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በበትረ ስልጣን ተባባሪነት  በዲፕሎማቶቹን  እና ሁለት ቴክኒሸኖችን ጨምሮ ሰባት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦችን ባካተተው ቡድን መካከል የተካሄደው ስብሰባ ተገቢነት የሌለው እና አግባብ ያልሆነ ተብሎ ተፈርጇል፡፡ አገዛዙ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡትን ብዙሀን መገናኛዎች ጸጥ ለማድረግ እና የስርጭት አድማሳቸውን ለመገደብ እያራመደ ካለው አውን ያወጣ ስልት አንጻር ከፍተኛ በሆኑ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች እንደዚህ ያለ ስብሰባ መካሄዱ እና ስለቪኦኤ እያራገቡት ያለው የጥላቻ አጀንዳ በሕጋዊ መልኩ ስልጣን የተሰጠውን የመተዳደሪያ ደንብ እና የጋዜጠኝነት ስነምግባርን የሚጥስ ዕኩይ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህ በቅሌት የታጀበ ስብሰባ እንዲካሄድ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት አገዛዙን በየዓመቱ የፕሬስ ነጻነትን በመደፍጠጥ የቀዳሚነቱን ቦታ ከሚይዙት የፕሬስ ደፍጣጮች መካከል እያስመደበው የመጣ ስለሆነ ይህንን ሁነት ለማደብዘዝ ሲባል በጋዜጠኞች እና በጨቋኙ መንግስት መካከል መተማመን እና ትብብር እንዲኖር ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ ክስተት ነው፡፡ በስብሰባው ወቅት በተደረገው ንግግር የህወሀት ተወካይ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የሬዲዮ ስርጭት ጥያቄ በማቅረብ እና በድብቅ የማስፈራሪያ ድርጊቶችን በመፈጸም በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ መፍጠር እና የስርጭቱንም ይዘት ማስቀየር እንደሚቻል የቀረበውን ሀሳብ ለደህንነታቸው ሲባል አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው ይፋ አድርገዋል፡፡ እየተካሄደ የነበረው ስብሰባ ውይይት በመቅረጸ ድምጽ እንዳይቀዳ እግድ የጣለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማያያዝም ቪኦኤ ጠንካራ የሆኑ ትችቶችን ለሚያቀርቡት የአየር ጊዜ በመስጠት እና ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱትን አመጸኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ መንግስትን ለመገልበጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋሉ በማለት ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ሚኒስትሩ በመቀጠልም ቪኦኤ “አሉታዊ ትረካ” ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰራ ሜዲያ ነው በማለት ቅሬታውን ገልጿል፡፡ የአምባገነን ምልከታ፣ ጥቂት ጥያቄዎችን ከወሰደ በኋላ ሚኒስትሩ ባለፈው ሐምሌ ወር ለቪኦኤ የሰጠው ቃለመጠይቅ የመንግስትን ፖሊሲ በሚተቹ ትችት አቅራቢዎች በቪኦኤ በኩል ትችት የቀረበ በመሆኑ ቅሬታ የተሰማው መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ እንደዚህ ያሉ ተሞክሮዎች ስህተት ናቸው፣ እናም መደረግ አልነበረባቸውም በማለት ለተሰብሳቢዎቹ ተናግሯል፡፡ አወዛጋቢ በነበረው የቪኦኤ ቃለመጠይቅ የህወሀት ሚኒስትር ካለው እውነታ በተጻረረ መልኩ ፕሬዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስለሆነ አጽድቆታል በማለት የተዛባ መረጃ አሰራጭቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት የመን ላይ የታፈነው እና በኢትዮጵያ ውስጥ ስቃይ እየተፈጸመበት ያለው ታዋቂው አመጸኛ አንዳርጋቸው ጽጌ መልካም የሆነ አያያዝ እየተደረገለት እንደሆነ እና እንዲያውም የልማት ፕሮጀክቶችን በማድነቅ ላይ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ አንዳርጋቸው መጽሐፍ እንዲጽፍ ላፕቶፕ የተሰጠው መሆኑን ተናግሯል፡፡ ሚኒስትሩ እና አምባሳደሩ ሁለቱም መንግስት ከቪኦኤ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት እና ጋዜጠኞች አዎንታዊ ትረካ እና ስዕሎችን አጉልተው ማውጣት እንዳለባቸው እና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያደርግላቸው ግልጽ ያደረጉ መሆናቸውን ምንጮቹ ይፋ አድርገዋል፡፡ ባለስልጣኖቹ ሰባት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦች ያሉበትን ስብሰባ እየመሩ ባሉበት ጊዜ ሲሰጡት በነበረው መመሪያ ቪኦኤ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስተላልፈው የሬዲዮ ስርጭት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ መዘገብ ያለበት ከአሉታዊ ትረካዎች እና አስተያየቶች፣ እንዲሁም አንገብጋቢ ከሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ከሙስና ይልቅ አዎንታዊ እና የልማት ስራዎችን መዘገብ እንደሚያስፈልግ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚህ ብቻ ሳያቆም ንግግሩን ቀጥሎ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተገኙ ያላቸውን ጥቂት ዕድገት እና መሻሻሎች ከዘረዘረ በኋላ ጋዜጠኞቹ እራሳቸው እውነታውን በግንባር ወደ ሀገር ቤት በመሄድ ማየት እንዳለባቸው የግብዣ ጥሪ አስተላልፎላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ስለቪኦኤ ውስጣዊ የስራ እንቅስቃሴ ቀጣይነት ባለው መልኩ መረጃ እንደሚቀበል ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ይፋ አድርገዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞቹ በየስራ ክፍሎቻቸው ማን ምን እንደሚሰራ እያንዳንዱን ነገር እንደሚያውቁ እና እነዚህ ጋዜጠኞችም ከዚህ አንጻር እራሳቸውን እንደገና በጥንቃቄ መመርመር እንዳለባቸው በይፋ የተናገረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ አንድ ስሙ እንዳይታወቅ የፈለገ የስብሰባው ተሳታፊ የሆነ የቪኦኤ የስራ ባልደረባ እንዲህ በማለት ሀሳቡን ገልጿል፣ “በእንደዚህ ዓይነት ስራዎች ላይ ልንከተላቸው የሚገቡ ሕጎች፣ የአሰራር ሂደቶች እና የሙያ ስነምግባሮች አሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምሽት ከመሆኑ አንጻር ሰራተኛው ሁሉ ለመኝታ ወደየቤቱ በሄደበት ሁኔታ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድርጅቱ ኢዲቶሪያል ክፍል ውስጥ በመገኘት ጥቂት የድርጅቱ ሰራተኞችን በመያዝ እንደዚህ ያለ ስብሰባ ማካሄድ በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቅ አዲስ እና ያልተለመደ ነገር ነው“ በማለት ሀሳቡን ግልጽ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ምንጩ ከዚህ ጋር በማያያዝ እንደገለጸው የአሰራር የዕዝ ሰንሰለቶችን በመጣስ የቪኦኤን ነጻነት በገደበ መልኩ እየተካሄደ ባለው በዚህ ስብሰባ ላይ እኔ እና መሰል ባልደረቦቼ በእጅጉ አዝነናል የሚል መልዕክት እንዳስተላለፈ ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የስብሰባ ምንጮች እንዲህ የሚል ግልጽ የሆነ መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ጠቁመዋል፣ “ስለቪኦኤ የአዘጋገብ ፕሮግራም እና ስለሌሎች ማናቸውም ጉዳዮች ለመወያየት እና ቅሬታን ለማቅረብ ሲፈለግ ባለስልጣኖች የኢዲቶሪያል ስብሰባ ለማድረግ የዩኤስ ፌዴራል መንግስት ሰራተኛ የሆኑትን የተመረጡ ጥቂት የቪኦኤ ጋዜጠኞች ቡድንን በምሽት ስብሰባ ከመጥራት ይልቅ የተለመደውን የአሰራር ስርዓት እና የዕዝ ሰንሰለት መከተል ነበረባቸው“ ብሏል፡፡ ሌላው ምንጭ በመቀጠል ከተሰብሳቢዎች የቀረበውን እንዲህ የሚለውን አስተያየት ይፋ አድርጓል፣ “እኛ ለቪኦኤ የምንሰራ ነጻ ጋዜጠኞች ነን፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወይም አምባሳደሩ ወደ ቪኦኤ ዘልቀው በመምጣት ስራዎቻችንን እንዴት መስራት እንዳለብን የሚያስገድዱን ወይም ደግሞ መመሪያዎችን የሚሰጡን ለምንድን ነው? ይህ ዓይነት አካሄድ አግባብነት የሌለው የሙያ ጣልቃገብነት ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን ይህ ጉዳይ በእኛ የማሰብ ችሎታ እና ሙያዊ ብቃት ላይ የተሰነዘረ ግልጽ ዘለፋ ነው“ ብሏል፡፡ ይኸው ምንጭ፣ “ቪኦኤ ያለምንም ፍርሀት እና ከምንም ዓይነት አድልኦ በጸዳ መልኩ የመስራት ተግባሩን መቀጠል እንዳለበት ጠንካራ እምነት አለኝ“ ብሏል፡፡ ቪኦኤ እንደ ነጻ የሜዲያ ተቋም በትክክለኛ እና በእውነት ላይ የተመሰረተ ዘገባን የማቅረብ ተልዕኮን የሚያራምድ ጠንካራ የሆነ ኃላፊነትን የተሸከመ ድርጅት እንደሆነ አጽንኦ በመስጠት ግልጽ አድርገዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ “ሕግን መሰረት አድርጎ የተቋቋመውን እና ሕጋዊ ስልጣን ያለውን የቪኦኤን የመተዳደሪያ ደንብ እና የሙያ ስነምግባር ማንም ድርድር ሊያደርግበት እና ሊለውጠው አይችልም“ ብለዋል፡፡ ይኸ ቅንነት የጎደለው ስብሰባ “አምባገነኑ እየተመለከታችሁ ነው“ የሚል ቀጥተኛ ያልሆነ እንደምታ ይኖረዋል በማለት ሌላው ምንጭ ጠቁሟል፡፡ ለስራ በጣም ምቹ የሆነ እና ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ በዚህ የፌዴራል መንግስት ህንጻ ውስጥ እንደዚህ ያለ ክስተት እንዴት እና ለምን እንደተፈጠረ ጥቂት ሰዎች በጣም ያሳሰባቸው ስለሆነ ድርጊቱ ለምን እንደተፈጸመ ሊያጣራ የሚችል አጣሪ አካል መቋቋም እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ባለስልጣኖቹ ለቪኦኤ የስራ ባልደረቦች የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሮች በሰፊው ተከፍተው የቆዩ መሆናቸውን ነግረዋቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑ የስብሰባው ተሳታፊዎች ባለስልጣኖቹ የመጡት በስቱዲዮ በመገኘት ቃለመጠይቅ እንዲሰጡ ነው ተብሎ የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ እና እዚህ ከገባን በኋላ እየተደረገ ያለው የኢዲቶሪያል ሕገወጥ ስብሰባ መሆኑን በመመልከቴ ወደ ስሰብሰባው ከፍል በመግባቴ ጸጸት ተሰምቶኛል በማለት ተናግሯል፡፡ የኢትዮ-አሜሪካ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አበበ ኃይሉ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ የተሰማቸውን ሀዘን እና እምነት ማጣት እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገዋል፣ “በአሁኑ ጊዜ በቪኦኤ ላይ እየተደረገ ያለው ድርጊት የቪኦኤን ታማዕኒነት የሚያጠፋ ስለሆነ ድርጊቱ በድርጅቱ ህልውና ላይ ያነጣጠረ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው፡፡ እንደ ኢትዮ-አሜሪካውያን ዜጎች ለዚህች ታሪካዊ ለሆነች ሀገር ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪከ ግብር ከፋይ ሕዝቦችም ነን“ ብለው ነበር፡፡ አቶ አበበ አስተያየታቸውን በመቀጠል ቪኦኤ እና የቪኦኤ የስራ ባልደረቦች በሌላ በውጭ ኃይል ጣልቃገብነት የመጦዝ እና የመታዘዝ ዕድል እንዳይገጥማቸው የሜዴያን ነጻነት ለማስከበር ወጥተን መጠየቅ እንዳለበን ምክንያት የሚፈጥር ጉዳይ ሆኗል፡፡ በመጨረሻም ይኸ ድርጊት በጠቅላይ የምርመራ ጽ/ቤት/Inspector General መመርመር እንዳለበት ጠንካራ እምነነት አለኝ በማለት ጥቆማ አቅርበዋል፡፡ የውጥረት ታሪክ፣ በኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው አገዛዝ ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያ በመፈጸም፣ በዜጎች ላይ ስቃይ በማድረስ፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም፣ በሙስና በመዘፈቅ፣ ሕዝብን በጅምላ በማፈናቀል፣ በመሬት ቅርምት ወረራ በመረባረብ፣ በዜጎች ላይ አድልኦ በመፈጸም እና በሌሎች ዓይነት ጅምላ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በሰዎች ልጆች ላይ በሚፈጽማቸው ሰብአዊ ወንጀሎች በሰፊው ይተቻል፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የተከሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተፈጥሮ የነበረውን ውዝግብ ተከትሎ አገዛዙ በጉዳዩ ላይ የዩኤስ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ክሱ ውድቅ እስከሚደረግ ድረስ በአራት የቪኦኤ ነባር ጋዜጠኞች ከሌሎች በርካታ ተወንጃዮች ጋር በመጨመር የሀገር ክህደት እና የዘር ማጥፋት መፈጸም የሚል የውንጀላ ክስ ተመስረቶባቸው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 የቪኦኤን እና የሌሎች ዓለም አቀፍ የዩኤስ ዜና ማሰራጫዎችን የሚገመግም ሶስት አባላትን ያካተተ የሬዲዮ ስርጭቱ የቦርድ አመራሮች/Broadcasting Board Governors (BBG) ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ሄዶ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በስልጣን ላይ የነበረው አገዛዝ በቬኦኤ የስርጭት አድማስ እንዳያገኙ እና ቃለመጠይቅም እንዳይደረግላቸው የሚፈለጓቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር እና ሌሎች አመጽ ያካሂዳሉ ብለው የፈረጇውን ድርጅቶች ዝርዝር ያካተተ ረዥም ቅሬታ አቅርበው ነበር፡፡ የቀድሞው የአፍሪካ ቀንድ የቪኦኤ ዋና ኃላፊ የነበሩት ዴቪድ አርኖልድ አገዛዙ ትችት ለሚያቀርቡት እና አመጽን ለሚያራምዱት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ቪኦኤ መድረክ እንዳይሰጣቸው ይፈልጋል በማለት ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ ሆኖም ግን አርኖልድ ሀሳባቸውን ግልጽ ካደረጉ በኋላ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከስራቸው እንዲታገዱ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ቪኦኤን ሀገሪቱን ካወደመው እና የዘር ማጥፋት ሰይጣናዊ የቅስቀሳ ድርጊት በማድረግ በመጥፎነቱ ከሚታወቀው ከሩዋንዳው ሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስ ጋር አንድ ዓይነት ነው በማለት ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡ ይህንንም በማስመልከት በኢትዮጵያ የሚሰራጨውን የቪኦኤን የስርጭት ሞገድ ካፈነ/ጃም ካደረገ በኋላ አምባገነኑ መለስ እንዲህ የሚል ዲስኩር አሰምቶ ነበር፣ “በብዙ መንገድ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የመጫረሻ ዝቅተኛ የሆነውን የጋዜጠኝነት ስነምግባርን የማያሟላ እና የሁከት ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ የሩዋንዳውን የሬዲዮ ኮሊንስን ተሞክሮ እንዳለ የሚተገብር ሜዲያ እንደሆነ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ እምነት አድርቦብናል“ ብሎ ነበር፡፡ ይኸው የውንጀላ ክስ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ “መሰረተ ቢስ እና ቆጥቋጭ” በሚል ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ የአሜሪካ የመንግስት መምሪያ ለቀረበው የውንጀላ ክስ ምላሽ እንዲሆን በማሰብ ይልቁንም መንግስት የሰው ልጆች መሰረታዊ መብት የሆነውን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዲያከብር ጠይቋል፡፡ የሙያ ስነምግባር መርሆዎች፣ የቪኦኤ የሙያ የስነምግባር መርሆ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው የቪኦኤ ቋሚ ወይም ደግሞ የኮንትራት ሰራተኞች በተለዬ ምክንያት በልዩ ትዕዛዝ በተላለፈ የስልጣን ተዋረድ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ መንግስት ወይም ደግሞ የሜዲያ ተቋም ሊያገለግሉ አይችሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጨቋኝ አገዛዝ መዳፍ ስር ወድቀው ለሚሰቃዩ ህዝብች ትክክለኛ መረጃ እና ዜና በማቅረብ ረገድ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ የቪኦኤ የጋዜጠኝነት የስነምግባር መርሆ እንዲህ በሚለው ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፣ “ቪኦኤ በነጻነት እና በዴሞክራሲ ላይ ሙሉ እምነት እና ተስፋ ላላቸው ህዝቦች ብሄራዊ ጥቅምን ለመጠበቅ እና ለዓለም ህዝብ በተለይም ደግሞ ትክክለኛ መረጃ ለማያገኙት ህዝቦች ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ ያደርጋል“ ይላል፡፡ ባለፈው ዓመት በህወሀት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ የተሟሉ የሳቴላይት መሳሪያዎችን በመጠቀም እና ዓለም ሕጎችን በማክበር ትክክለኛ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በመከተል እና በስራ ላይ በማዋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መረጃዎችን እና ዜናዎችን የሚያሰራጩትን ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች ስርጭትን ቪኦኤን ጨምሮ በማፈኑ/ጃም በማድረጉ ቢቢጂ/BBG ከቢቢሲ/BBC፣ ዶቼ ዎሌ/Deutsche Welle እና ከፍራንስ 24/France 24 ጋር በጋራ በመሆን አገዛዙ ሰብአዊ መብቶችን በሰፊው እየደፈጠጠ ነው በማለት አውግዘውታል፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዲህ የሚል ተካትቶ ይገኛል፣ “ይህ ጣልቃገብነት ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ሞገድ የስርጭትን አጠቃቀም እና የሳቴላይት ስርዓቱ የሚመሩባቸውን ደንቦች በተጻረረ መልኩ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 19ን በመተላለፍ ግለሰቦች ነጻ የሜዲያ ሽፋን መረጃዎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ወይም ጃም አድርጓል“ የሚል የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የቢቢሲ አገልግሎት ቡድን ተጠባባቂ ዳይሬክተር የሆኑት ሊሊያን ላንዶር የአገዛዙን አፋኝነት በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የዓለም አቀፉን የዜና ማሰራጭ አውታሮች አውከዋል፡፡“ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ፣ ለጠንካራ ትችቶች እና ለሜዲያ ሽፋን ጠላት በመሆን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ  የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ፕሮግራምን ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በእራሱ ስልጣን ስርጭቱን ለማቋረጥ እና ለመዝጋት ያለ የሌለ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህንን ያህል ጥረት በኢትዮጵያ የቪኦኤን አጭር ሞገድ እና የሳቴላይት ስርጭት ለማፈን/ጃም ለማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖዎችን ሲያደርግ የቆዬ ቢሆንም ቅሉ ዓላማ አድርጎ የተነሳበትን ግብ ሳይመታ እና የታለመውን ውጤት ሳይስገኝ የውኃ ላይ ኩበት ሆኖበት ቀርቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ድርጅት/CPJ የጽሁፍ እና የሕትመት ምርመራ የሚደረግባቸውን 10 ዋና ዋና ጨቋኝ መንግስታት የደረጅ ዝርዝር ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል በ4ኛነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የCPJ የምርመራ ውጤት ዘገባ እንደሚያመለክተው “ከፍተኛ የሆነ የህትመት እና የሜዲያ ምርመራ ከሚያደርጉ ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ በ4ኛነት ደረጃ ላይ የምትገኝ በመሆኗ ምክንያት የጋዜጠኞች እስራት በገፍ የሚከናወን በመሆኑ በርካታ ጋዜጠኞች ሀገራቸውን እየተው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ እ.ኤአ. በ2014 በጦማሪያን እና በነጻው ፕሬስ ህትመት አዘጋጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የኃይል እርምጃ በመወሰዱ ምክንያት ከ30 በላይ የሚሆኑ ጋዜጦች ለስደት ተዳርገዋል፡፡“ CPJ ማንኛውንም ትችት ማቅረብ እና ሀሳብን በነጻ መግለጽ ወንጀለኛ የሚያደርገውን እ.ኤ.አ በ2009 የወጣውን የጸረ-ሽብር አዋጅ አውግዞታል፡፡ አገዛዙ ይህንኝ ያህል ጥረት እያደረገ የህወሀት የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን የማፈን እና በጋዜጠኞች እና በሰላማዊ አመጸኞች ላይ የሀሰት የውንጀላ ክሶችን ቢመሰርትም ያሰበው እና የሚያደርገው ሁሉ የእምቧይ ካብ እየሆነ ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁን በቅርቡ ደግሞ የእስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ በቀጥታ ከቪኦኤ ጋዜጠኞች እና ከሌሎች ነጻ የሜዲያ ተቋማት ጋር በግንባር በመገናኘት እያደረገ ያለው ንግግር አገዛዙ ከውስጥ የግንኙነት መረብ አድማሱን እያሰፋ እና እያጠናከረ እንዲሁም ካሮት እና ዱላ እያሳየ እያስፈራራ  ያለው ዕኩይ ድርጊት ያለምንም ጥርጥር በአፍሪካ ቀንድ የቪኦኤ ክፍል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ከዚህም በላይ ከጋዜጠኝነት ስነምግባራቸው በተዛነፈ መልኩ ካሮት እየተሰጣቸው ለርካሽ ጥቅም በማጎብደድ መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡ ቪኦኤ በሚስጥር ስለተካሄደው ስብሰባ ምንነት እና በኢትዮጵያ የቪኦኤ የሬዲዮ ስርጭት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በስብሰባው ክፍልም የተደረገውን ውይይት በማስመልከት በዚህ ዘገባ አጠናቃሪ ለቀረቡለት ጥያቄዎች እስከ አሁን ድረስ ምላሽ አልሰጠም፡፡ – See more at:http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47894#sthash.kLVnFy3E.dpuf

የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትን እየለቀመ ከመከላከያ ኃይሉ እያባረራቸው መሆኑ ታወቀ፡፡


ህወሓት በ1983 ዓ.ም መላ አገሪቱን በነፍጥ እንደተቆጣጠረ በሁለት ያለፉ የኢትዮጵያ መንግስታት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ፈሶበት ለዘመናት በስንት ልፋትና ጥረት የተገነባውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ባደረበት ጭፍን ጥላቻና ቂም ብቻ ተመስርቶ “የደርግ ነው” በሚል ሰበብ ባንድ ጀምበር ንዶ ማፈራረሱን አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡
ከበረሃ የመጡ ድኩማን ታጋዮቹን ለሙያው የሚመጥን ምንም አይነት ዘመናዊ ዕውቀት ሳይኖራቸው የጀነራልነት ማዕረግ በማሸከም በአየር ኃይሉና በምድር ኃይሉ ውስጥ በሚገኙ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ እነሱን ብቻ አስቀምጦ ስልጣኑን ለመጠበቅ ብቻ እንዲተጉለት በማድረግ የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡
ህወሓት የተባለው ዘረኛ ቡድን ውስጡ በቂምና በጥላቻ ብቻ ተሞልቶ ያፈራረሰውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አደጋ ባንዣበበበት ጊዜ ጥሪ በማድረግ መልሶ ለመሰብሰብ የሞከረ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ አብዛኞቹን ከተጠቀመባቸው በኋላ እንደገና አባሯቸዋል፡፡
አሁን ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እያፋፋመው ከሚገኘው የአርበኝነት ትግል ጋር በተያያዘ ከትግራይ ተወላጅ የህወሓት ተጋዮች ውጭ በሆኑ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ዕምነት በማጣቱ የመከላከያ ኃይሉን የማጥራት የወቅቱ አንገብጋቢ ውሳኔውን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በማባረር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል፡፡
ቂምና በቀሉ መቸም የማይበርድለት ህወሓት በተደጋጋሚ የደም ቁማር ሲቆምርባቸው ከኖሩት የተባረሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አብዛኞቹ የአርበኝነት ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡
Ethio Hagere's photo.
Ethio Hagere's photo.

በባህርዳር የባጃጅ ሾፌሮች አድማ መቱ




የባህርዳር ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በከተማው ባጃጆች ከአንድ መስመር ውጭ እንዳይሰሩ ከመከልከላቸው ባሻገር ኮንትራት ጭናችኋል በሚልና በሌሎችም ሰበቦች በየቀኑከፍተኛ ቅጣት ስለሚጣልባቸውና ቅጣቱ ከሚያገኙት ገቢ በላይ በመሆኑ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ መገደዳቸው ተናግረዋል፡፡ ታክሲዎች በማይደርሱበት አካባቢ ጭምር ኮንትራት ሲጭኑ 400 ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የገለፁት ሾፌሮቹ፣ በሌሎች አጋጣሚዎችም በየቀኑ ስለሚቀጡ ለኪሳራ እንደተጋለጡ ገልፀዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ለገዥው ፓርቲ ሰዎች ቅርበት ያላቸው የባጃጅ ሾፌሮች የተሻለ ገቢ በሚገኝበት አካባቢ ስምሪት ሲሰጣቸው ሌሎቹ ገቢ ወደሌለበት እንዲሰማሩ በመደረጋቸው፤ ይህም ቅሬታ አስነስቶ እንደቆየ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ሁሉም በተደጋጋሚ ከቅጣት ባለመዳናቸው ባለፈው ሳምንት ጀምሮ አብዛኛዎቹ የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ በዛሬው ቀን ሁሉም ስራ ማቆማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት በከተማው የትራንስፖርት ችግር አጋጥሟል ተብሏል፡፡

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)


መብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር። ሰዐቴን ሳየዉ ከሌሊቱ ስምንት ሰዐት ተኩል ይላል። ከአልጋዬ ላይ ዘልዬ ወረድኩና ሰዉነቴን ታጥቤ ልብሴን ከለበስኩ በኋላ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ “I’m ready” አልኩ። የመኪናችን መብራት ጨለማዉን እየገላለጠዉ የአስመራ ከረንን መንገድ ተያያዝነዉ። መኪናዉ ዉስጥ ከገባሁ በኋላ እንደገና አፌን የከፈትኩት ባሬንቱ ደርሰን ቁርስ ሳዝ ነዉ። ባሬንቱ በግዜ መድረሳችን ደስ ቢለኝም የቀረን መንገድ ርዝመት ታየኝና ቁርስ መብላቴን ትቼ . . . በሰዐት ይህን ያክል ብንጓዝ እያልኩ ዋናዉ ጉዳያችን ቦታ የምንደርስበትን ሰዐት ማስላት ጀመርኩ። የስሌቱ ዉጤት ከሦስት ሰዐት ሲበልጥብኝ ተናደድኩ። ቀሪዉ መንገድ ገና ሳልጀምረዉ ሰለቸኝ። በተፈጥሮዬ መንገድና መኃላ ሲረዝም አልወድም።Patriotic Ginbot7 fighters
ተሰነይ ስንደርስ መኪናዉ ዉስጥ የነበረዉ ሰዉ ሁሉ ቡና ካልጠጣሁ አለ። መኪናችንን አቁመን በቁማችን ቡናችንን ፉት አድርገን መንገዳችንን ተያያዝነዉ። እሁድ ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም አርበኞች ግንቦት ሰባትን የፈጠሩት ሁለት ድርጅቶች ከተዋሃዱ በኋላ ለሁለተኛ ግዜ የሰለጠኑ ታጋይ አርበኞች የሚመረቁበት ቀን ነበር። ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነቱን የምርቃት ዜና የምሰማዉ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ብቻ ስለነበር እቦታዉ ደርሼ የምረቃዉን ስነስርዐት ለማየት የነበረኝ ጉጉት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር። የምሳ ሰዐት ከመድረሱ በፊት በቀኝ በኩል ዋናዉን መንገድ ለቅቀን ዉስጥ ዉስጡን ወደ ምርቃቱ ቦታ የሚወስደዉን ኮረኮንች መንገድ ተያያዝነዉ።
ግቢዉ ዉስጥ ያለዉ ጥድፊያና ግርግር አንድ ትልቅ ዝግጅት መኖሩን በግልጽ ይናገራል። የተለያየ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱና መሳሪያ የተሸከሙ አርበኞች ግቢዉን ሞልተዉታል። ያነገቱትን ጠመንጃ ስመለከት ቆራጥነታቸዉ ታየኝ። በቀጭኑ ተጎንጉኖ ማጅራታቸዉ ላይ የወደቀዉን ፀጉራቸዉን ሳይ ቴዎድሮስና ዮሐንስ ትዝ አሉኝ። ፈገግታ በፈገግታ የሆነዉን ፊታቸዉን ስመለከት ደግሞ የእናት አገሬ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ደጃፍ ላይ መሆኑ ታየኝና የኔም ፊት እንደነሱ በፈገግታ ተሞላ። ተራ በተራ እየመጡ “ጋሼ አፍሬም” እንደኳን ደህና መጣህ ብለዉ ሲጠመጠሙብኝ በአንዱ ትከሻዬ ፍቅራቸዉ በሌላዉ ጀግንነታቸዉ ዘልቆ ሰዉነቴ ዉስጥ ገባ። ጥንካሬያቸዉ በጅማቴ ፍቅራቸዉ በደም ስሬ ዘለቀ። እኔነቴ ሲታደስና በአገሬ ላይ ያለኝ ተስፋ ሲለመልም ተሰማኝና ደስ አለኝ። አዎ ደስ አለኝ . . . እየመጣ የሚሄድ ግዜያዊ ደስታ ሳይሆን የዉስጥ አካላቴን የዳሰሰ ዘላቂ የመንፈስ ደስታ ተሰማኝ። በጣም ደስ የሚልና በአሁኖቹ ቋንቋ “የሚመች” ቀን ነበር። የዕለቱን ዝግጅት ለማየት መቸኮሌን ያወቁት እግሮቼ የምረቃዉ በዐል ወደሚከበርበት ዳስ- ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት የናፈቀዉ ልቤ ደግሞ ወደ ወደፊቷ ኢትዮጵያ ይዘዉኝ ጭልጥ አሉ፡ . . . ለካስ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሩቅ አይደለችም።
“ማነዉ ሚለየዉ . . .ሚለየዉ፤ ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” የሚለዉን የጃሉድ ዘፈን በርቀት ሲሰማ በቀኑና በዘፈኑ መግጠም ተገረምኩ። “እዉነትም ይህ ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” እያልኩ በለሆሳስ ለራሴ እየነገርኩት ዳሱ ዉስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ። እርግጠኛ ነኝ ይህንን ጽሁፍ የሚያነብ ሰዉ ዳሱ ዉስጥ የነበረዉን ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ የጀግንነት፤ የቆራጥነት፤ የእልህና የመተማመን ልዩ ስሜት መረዳት የሚችለዉ እኔ በዚህ ባልተባ ብዕሬ ስገልጸዉ ሳይሆን እንዳዉ በደፈናዉ ዳሱ እራሱ ኢትዮጵያዊ ነበር ብዬ ባልፈዉ ነዉ።
አገራችን ኢትዮጵያ ከራሱ ምቾትና የተደላደለ ኑሮ ይልቅ የወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚያንገበግበዉና እራሱን ለፍትህ፤ ለአንድነትና ለነጻነት ለመሰዋት ዝግጁ የሆነ የየዘመኑ ምርጥ ትዉልድ አላት። ይህንን የኛን ዘመን ምርጥ ትዉልድ ነዉ አርቲስት ጃሉድ “ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” ብሎ በጣፋጭ ዜማዉ ያወደሰዉ። እኔ ጥርጥርም የለኝ ይህ ትዉልድ አንድና ሁለት ብቻ ሳይሆን ለቁጥር የሚታክቱ ብዙ ፍም እሳቶች አሉት። ችግሩ የእሳት ነገር አዚህ ቤት ነደዳ እዚያም ቤት ነደደ ስራዉ ማቃጠል ነዉና አንዱን እሳት ከሌላዉ እሳት መለየት አስቸጋሪ ነዉ። እኔም ችግሬ እዚህ ላይ ነዉ። ፊት ለፊቴ ላይ ቁጭ ብለዉ ስለማያቸዉ ፍም እሳቶች (ጀግኖች) ላወራችሁ እየፈለኩ ምርጫዉ አዋጅ ሆነብኝ. . . የራሱ ጉዳይ ብዬ አንዱን ጀግና መረጥኩ። ይህንን ዛሬ የምተርክላችሁን ጀግና ስመርጥ ግን እንዳዉ በደፈና አልነበረም። ጉዳይ አለኝ . . . . ጉዳዩ አንዲህ ነዉ።
በዕለቱ በተመራቂ አርበኞች ተዘጋጅተዉ ከቀሩቡት የተለያዩ የኪነት ስራዎች ዉስጥ አንዱ የድራማ ዝግጅት ነበር። ሦስት የተለያዩ ድራማዎች መታየታቸዉ ትዝ ይለኛል። ዳሱ ዉስጥ የተሰበሰበዉን በብዙ መቶዎች የሚቆጠር ሰዉ ስሜት የኮረኮረዉና የእያንዳንዱን ሰዉ የልብ ትርታ ሰቅዞ የያዘዉ ግን በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተከወነዉ የመጨረሻዉ ድራማ ነበር። ድራማዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ እየተባለ በየቀኑ በህወሃት የደህንነት ሠራተኞች እጃቸዉ እየታሰረ በየወንዙና በየፈፋዉ በግፍ እየተገደሉ ስለሚጣሉ ኢትዮጵያዉያን የሚተርክ ድራማ ነበር።
ድራማዉ “ኮሜዲ” የሚባል ክፍል የለዉም። ተጀምሮ እስኪያልቅ “ትራጄዲ” ብቻ ነዉ። ያሳዝናል፤ ያስቆጣል፤ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ አንጀት ያቆስላል፤ ልብ ያነድዳል . . . ወይ ነዶ ያሰኛል ። እኔማ እንኳን ትራጄዲ አይቼ በተፈጥሮዬ ሆደ ቡቡ ነኝና በደል ስመለከት ማዘን ልማዴ ሆኖ አምባዬ መፍሰስ የጀመረዉ ገና ድራማዉ ሲጀምር ነበር። በተለይ አናታቸዉ እየተደበደበ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ በግድ እንዲቆፍሩ የተደረጉትን ሁለት ወጣት ወገኖቼን ሳይ ሆዴ ባባ፤ አንጀቴም ቆሰለ። ልቤ ዉሰጥ የነደደዉ እሳት ትንታጉ እየተንቦገቦገ ወጥቶ የዉጭ ሰዉነቴን ጭምር ለበለበዉ። ለወትሮዉ ነገር ማመዛዘን የሚቀድመዉ አዕምሮዬ በቀል በቀል አሰኘዉ። የነደደዉ ልቤም ለበቀል አደባ። ጉድጓዱ ተቆፍሮ ካለቀ በኋላ የደህንነት ሠራተኛዉ AK ጠመንጃዉን አንደኛዉ ወጣት አገጭ ላይ ቀስሮ በአፈሙዙ አንገቱን ቀና እንዲያደርግ እያስገደደዉ . . . “አየኸዉ የምትገባበትን ጉድጓድ” እያለ ወጣቱ ወገኔ ላይ ሲሳልቅበት ሰማሁና በሀይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ኢትዮጵያዊነቴን ጠላሁት። አጠገቡ የቆመዉና በቁሙ ሞቱን የሚጠባበቀዉ ሌላዉ ወጣት ወገኔ ደግሞ . . . ግደለኝ . . . ግደለኝ. . . ግደለኝ እንጂ! . . . ምን ትጠብቃለህ እያለ የጓደኛዉን ሞት በአይኑ ከሚያይ የራሱን ሞት የሚለምነዉን ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ድምጽ ስሰማ ደግሞ 360 ዲግሪ ተገለበጥኩና ከደቂቃዎች በፊት የጠላሁትን ኢትዮጵያዊነት መልሼ ወድድ አደረኩት። የወያኔዉ ጨካኝ ነብሰ ገዳይ ፉከራና ቆራጡ ኢትዮጵያዊ ያደረጉት የቃላት ምልልስ እምባዬን ጎትቶ አመጣዉና ፊቴ እምባ በእምባ ሆነ። ያ ከግማሽ ሰዐት በፊት ሲጨፈርበትና ሲደነስበት የነበረዉ ዳስ ሰዉ የሌለበት ባዶ ቤት ይመስል ጭጭ አለ። እኔ ኤፍሬም ሰዉ አልገድልም፤ በእኔ እጅ የሰዉ ህይወት ይጠፋል ብዬ አስቤም አልሜም አላዉቅም። ያንን የህወሃት ቅጥረኛ በዚያች ሰዐት ባገኘዉ ኖሮ ግን ለመበቀል ሳይሆን ለሰዉ ልጅ ህይወት ክብር ስል እገድለዉ ነበር።
ድራማዉ እንዳለቀ ወደ ዉጭ ወጣሁና ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ብቻዬን ቁጭ አልኩ። ሀሳብ. . . የትናንት ሀሳብ፤ የዛሬ ሃሳብ፤ የነገ ሀሳብ፤ የከረመ ሀሳብና ሁሉም ሀሳብ አንድ ላይ ተሰባስበዉ ወረሩኝ። ግራ ሲገባኝና መላቅጡ ሲጠፋኝ ግዜ ትንፋሼን ዋጥ አደረኩና አንቺ እማማ ብዬ አገሬን ተጣራሁ . . . አሁንም አሁንም ደግሜ ተጣራሁ። ህመሟ ብርቱ ነበርና አልሰማችኝም። አይዞሽ ይህ ቀን ያልፍና አንቺም ከህመምሽ እኔም ከማያባራዉ የሀሳብ በሽታ ድነን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን ብዬ ከአገሬ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዳሱ ዉስጥ ከነበሩት አርበኞች ጋር ተቀላቀልኩ። እለቱን ሲያስጨፍረን የዋለዉ አደራ ባንድ “ነይ ደኑን ጥሰሺ” የሚለዉን ቆየት ያለ የመሀሙድ አህመድ ዘፈን ሲጫወት ልጅነቴ ትዝ አለኝና ከፍም እሳቶች ጋር መደነስ ጀመርኩ።
ጭልጋን ይዞ፤ጋይንትን ይዞ፤ የጎበዞቹን ጎራ ጃናሞራን ይዞ፤ ደምቢያን ይዞ፤ ወልቃይት ጠገዴን ይዞ፤ ላይ አርማጭሆንና ታች አርማጭሆን ይዞ ወዘተ . . .ድፍን ጎንደር የጀግኖች አገር ነዉ። አዎ! ወልቃይት ጠገዴ ከጀግናም የጀግና አገር ነዉ።ወልቃይት ጠገዴ ጎንደሬ አይደለህም ተብሎ ከተነገረዉ ከሃያ አራት አመታት በኋላ ዛሬም ህልዉናዉን ለወያኔ ፋሺስቶች አላስረክብም ብሎ ጎንደሬነቱን ለማረጋገጥ ሽንጡን ገትሮ የሚዋጋ የጀግኖች አገር ነዉ። ጎንደር የአፄ ቴዎድሮስ፤ የእቴጌ ምንትዋብ፤ የፊትአዉራሪ ገብርዬ፤ የአየለ አባ ጓዴና የጄኔራል ነጋ ተገኝ አገር ናት። ጎንደር ኢትዮጵያ ከሌለች እኛ የለንም ብለዉ ሙሉ ህይወታቸዉን ለትግል የሰጡ እነ ታማኝ በየነንና እነ አርቲስት ሻምበል በላይነህን ያበቀለች አገር ናት። ወላድ በድባብ ትሂድ. . . የጎንደር ማህፀን ዛሬም አልነጠፈም።
ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት ጀግና ተወልዶ ያደገዉ አማራ ክልል ጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሟ ጫኮ በምትባል ቦታ ነዉ። የገበሬ ልጅ ነዉ፤ እሱም ምኞቱ ገበሬ መሆን ነዉ። የሚኖረዉ መተማ ከተማ ዉስጥ ነዉ። ስሙ መሠረት ሙሌ ይባላል። ፈገግታ የማይለየዉ ፊቱ የዋህነቱንና ገራገርነቱን አፍ አዉጥቶ ይናገራል። ሲናገር ረጋ ብሎ ነዉ። አተኩሮ ላየዉ ሰዉ አይነ አፋር ይመስላል፤ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ግን እንደ መሠረት ሙሌ ደፋር ሰዉ የለም። አይኑ እፊቱ ላይ ቆሞ ከሚያናግረዉ ሰዉ አይን ጋር ሲጋጭ አንገቱን ይሰብራል። እቺ የሰዉ አይን የመሸሽ በሽታ ደግሞ አበሾች ስንባል የሁላችንም በሽታ ናት። ጠይም ፊቱ ላይ እንደ ችቦ የተተከሉት የመሠረት ሙሌ አይኖች የሰዉን ዉስጥ ዘልቀዉ የሚያዩ ይመስላሉ። ሰዉነቱ ደንዳና ቁመቱ መካከለኛ ነዉ። ልቡ ግን ትልቅ ነዉ። አዎ መሠረት ሙሌ ልቡ ትልቅ ነዉ።
ዕለቱ ሰኞ ነዉ – ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓም። የህወሃት የደህንነት ሰዎች አንድ ኮሎኔልና ሌሎች አራት ሰዎች ተገድለዋል በሚል ድፍን መተማን እያመሷት ነዉ። እያንዳንዱ የመተማ ነዋሪ በግድያዉ የተሳተፈ ይመስል በአጠገባቸዉ ያለፈዉን ሁሉ ወንድ፤ ሴት፤ ወጣትና ሽማግሌ ሳይለዩ ሁሉንም እያስቆሙ አጥንት ዉስጥ ዘልቆ የሚገባ ስድብ ይሰድባሉ፤ ይደበድባሉ ያስራሉ። በሠላም አዉለኝ ብሎ በጧት የተነሳዉ መሠረት ሙሌ የእህል ወፍጮዉን አስነስቶ የዕለት ስራዉን ለመጀመር ጉድ ጉድ ማለት ጀምሯል። ሴቶች እህላቸዉን ያስመዝናሉ። ሸክም የተራገፈለት አህያ ያናፋል። ነጋዴዉ፤ ደላላዉ፤ ገበሬዉና ሸማቹ ዋጋ ቀንስ ዋጋ ጨምር እያሉ ይንጫጫሉ። መተማ መደበኛ ስራዋ ላይ ናት።
“ቁም . . . እጅ ወደ ላይ . . . እንዳትነቃነቅ” የሚል ድምጽ የደራዉን የመተማ ገበያ በአንድ ግዜ ጭጭ አሰኘዉ። መሳሪያ ያነገቡ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰራተኞች ከመኪና እየዘለሉ ወርደዉ መሠረትን የፊጥኝ አስረዉ መኪናዉ ላይ ወረወሩት። ምነዉ? ምን አጠፋሁ . . . ዬት ነዉ የምትወስዱኝ? አለ መሠረት በሁኔታዉ እጅግ በጣም ተደናግጦ። አንድ አጠገቡ የነበረዉ የህወሃት ነብሰ ገዳይ . . . ዝም በል ብሎ በጥፊ አጮለዉና ለአርበኞች ግንቦት 7 የመለመልካቸዉን ሰዎች አድራሻና ስም ዝርዝር ካላመጣህ ዕድሜህ ከአንድ ጀምበር አያልፍም አለዉ።
መኪናዉ ዉስጥ ከተቀመጡት ሁለት ሰዎች አንደኛዉ አንሂድ ብሎ በእጁ ምልክት ሲያሳይ መሬት ላይ የነበሩት ፖሊሶች እየዘለሉ መኪናዉ ላይ ወጡና መሠረትንና ሌሎች ሦስት እስረኞችን የያዘችዉ ቶዮታ ሂሉክስ መኪና ፍጥነት እየጨመረች የመተማ ሁመራን መንገድ ተያያዘቸዉ። በሚቀጥለዉ ቀን ጧት ሲነጋጋ ሁመራ ደረሱና አራቱ እስረኞች እጃቸዉ እንደታሰረ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደረገ። ከምሽቱ ሦስት ሰዐት ሲሆን መሠረትና ጓደኞቹ እጅ ለእጅ እንደተሳሰሩ ጉዞ ወደ ተከዜ ወንዝ ሆነ። የዚህች ከንቱ አለም የመጨረሻ ጉዟቸዉ ነበር።
ዶማና አካፋ ያዙ እንጂ . . . ደግሞም ፈጠን በሉ ግዜ የለንም. . . አለ የነብሰ ገዳዮቹ አለቃ። ከሁመራ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ተከዜ ወንዝ የሚያደርገዉ ጉዞ በህይወቱ የመጨረሻዉ ጉዞ እንደሆነ የተረዳዉ መሠረት . . . አንተዬ ልትገድሉን ነዉ እንዴ ብሎ ጠየቀ። ፊት ለፊቱ የነበረዉ ፖሊስ ከተቀመጠበት ዘልሎ ተነሳና . . .ዝም በል . . . አንተ የሴት ልጅ . . . ምን አስቸኮለህ ይልቅ የተጠየከዉን ጥያቄ መልስ አለዉና የያዘዉን የእጅ መከርቸሚያ ካቴና ፊቱ ላይ ወረወረበት። ካቴናዉ ሳይሆን ከዚያ ባለጌ አፍ የወጡት ቃላት ጅማቶቹ ድረስ ዘልቀዉ ገብተዉ መንፈሱን ጎዱትና መሠረት ለመጀመሪያ ግዜ ተስፋ ቆረጦ . . . ምንም የምሰጥህ መልስ የለኝም አለና አንገቱን ደፋ። . . . አንቺ ወላዲት አምላክ ምነዉ . . . ምን አደረኩሽ ብሎ ቀና ሲል እሱንና ሦስት ጓደኞቹን ለመዋጥ አፋቸዉን ከፍተዉ የሚጠባበቁትን አራት ጉድጓዶች ተመለከተ። አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ተከታታይ የጥይት ድምጽ ሰማ። ዞር ሲል ፖሊሶች አብረዉት ከታሰሩት ሦስት እስረኞች ዉስጥ አንዱን በእግራቸዉ እየገፉ የተቆፈረዉ ጉድጓድ ዉስጥ ሲጨምሩት አየ። ደቂቃዎች የቀሩት የሱ የራሱ ህይወት ሳይሆን በህወሃት ነብሰ ገዳዮች በግፍ የተገደለዉ የጓደኛዉ ህይወት አንገበገበዉ። አዘነ – በአይኑም በሆደም አነባ። “አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም” ብሎ የተናገረዉ የራሱ ድምጽ ጆሮዉ ላይ አቃጨለበት። መሠረት ሞት ፈርቶ አያዉቅም፤ ግን ህይወቱ የህይወትን ክቡርነት በማይረዱ ባለጌዎች እጅ እንድታልፍ አልፈለገም። ያ የንጹሃን ኢትዮጵያዉያንን ሰዉነት ማፍረስ የለመደዉ የህወሃት ጠመንጃ ወደሱ ከመዞሩ በፊት አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብሎ ወሰነ። እጁ ከጓደኛዉ ጋር የታሰረበትን ገመድ በጥርሱ በጣጠሰዉና ከቀለሁ እንደተላቀቀ ጥይት ተወርዉሮ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ጫካ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። የህወሃት ነብሰ ገዳዮች የጥይት ናዳ ለቀቁበት፤ እሱ ግን ጫካ ጫካዉን ይዞ ወደማያዉቀዉ ቦታ ሩጫዉን ተያያዘዉ።
መሠረት- ቆራጥነቱና የልቡ ትልቅነት ጉልበት እየሆኑት ነዉ እንጂ ያ የሚጠላዉ የህወሃት ጥይት አካሉን በሳስቶ ወንፊት አድርጎታል። ሰዉነቱ ቁስል በቁስል ሆኗል። ከራሱ ሰዉነት እንደ ጎርፍ የሚፈስሰዉ ደም ጠልፎ የሚጥለዉ እስኪመስለዉ ድረስ አካሉ ደምቷል። ሩጫዉን ግን አላቆመም። ደም እንዳይፈሰዉ ጥይት የበሳዉን ቦታ ሁሉ በሁለት እጆቹ ሸፈነ። እንደኛዉ ቁስል ጋብ ሲልለት እጁን ከሱ ላይ እያነሳ ሌላዉን ቁስል ሸፈነ። ደሙ መፍሰሱን ግን አላቆመም። መሠረትም ሩጫዉን አላቆመም። መሠረት ሙሌ ህይወቱን ለማዳን ወደ ፊት የህወሃት ነብሰ ገዳዮች ደግሞ ወንጀላቸዉን ለመደበቅ ወደኋላ በተለያየ አቅጣጫ ሩጫቸዉን ተያያዙት። ሁለቱም አግሬ አዉጭኝ አሉ።
መሠረት ሞትን እየሸሸ መሆኑን ነዉ እንጂ ከሞት ለመራቁ ምንም ዋስትና አልነበረዉም። ደግሞም መሮጡን ብቻ ነዉ እንጂ ወዴት እንደሚሮጥ አያዉቅም ነበር። ከኋላዉ የሚከተለዉ ማንም ሰዉ እንደሌለ ቢረዳም ከፊት ለፊቱ ህይወቱን የሚታደግለት ሰዉ እስኪያገኝ ድረስ ሩጫዉን ቀጠለ። ጧት ጎህ ከመቅደዱ በፊት “ጠጠዉ በል” የሚል ድምጽ ሲሰማ ያ ሁሉ ሩጫዉ መልሶ ሞት ዉስጥ የከተተዉ መሰለዉና ደነገጠ። ሩጫዉን እንዳይቀጥል ቁም ያሉት ሰዎች ከበዉታል። እሺ ብሎ እንዳይቆም ሞትን አልቀበልም ያለዉ ልቡ አሁንም እንደደነደነ ነዉ። ትንፋሹን ሰበሰበና. . . ማናችሁ እናንተ ብሎ ያቆሙትን ሰዎች ጥያቄ ጠይቆ መልሱን ሳይሰማ ተዝልፍለፎ መሬቱ ላይ በግንባሩ ተደፋ።
የኤርትራ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች መሠረትን አንድ ወር ሙሉ በህክምና ሲንከባከቡት ቆዩና እሱ እራሱ በጠየቃቸዉ መሠረት ሃሬና ወስደዉ ለአርበኞች ግንቦት 7 አስረከቡት። መሠረት ሙሌ ጥቅምት 7 ቀን ከተመረቁት አርበኞች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ለዚህ ጀግና ያቀረብኩለት የመጨረሻ ጥያቄ . . . ሊገድሉህ የነበሩትን የህወሃት ሰዎች አሁን ብታገኛቸዉ ምን ታደርጋቸዋለህ የሚል ጥያቄ ነበር። ነጻ አወጣቸዋለኋ! አለኝና ጭፈራዉ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። አርግጠኛ ነኝ መሠረት ሙሌ አንድ ቀን ሁላችንንም ሸገር ላይ ያስጨፍረናል። ቸር ይግጠመን።
ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር
ebini23@yahoo.com

Thursday, October 29, 2015

መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።


መምህር ግርማ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ወድቅ ተደርጓል። …” ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ ” መምህር ግርማ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል::የፖሊስ የምርመራ ቡድን በበኩሉ እሳቸው ቢለቀቁ ሌሎች ተፈላጊዎችን እና የተለያዩ ሰነዶችን ስለሚያሸሹብን ጥያቄያቸው ውድቅ ይሁን ብሏል።ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር መርምሮ ፖሊስ አብዛኛውን የምርመራ ስራ ያካሄደ በመሆኑ ለቀሪ የምርመራ ስራዎቹ ይረዳል በማለት ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 7 ቀን ብቻ ፈቅዷል።ውጤቱን ለመጠባበቅም ለጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
የወንጀሉ ዝርዝር
ፖሊስ መምህር ግርማ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 ዓ.ም ነው ብሏል።በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው:እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።
እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል።
የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በ800 ሺህ ብር ይሸጡታል።ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው።
ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው ወሰዱ፤ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ።ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ወደ እኛ መጥተው አመለከቱ የሚለው ፖሊስ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንትበቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው።
ተጠርጣሪው እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።ጠበቃቸውም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል አይደለም፤ ፖሊስም የሚጠበቁ ምርመራዎቹን አጠናቋል፤ ደንበኛዬ የዋስትና መብታቸው ይከበርልኝ በማለት ጠይውቋል።ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።
12187782_889280251140205_7742261918983278738_n

በጅንካ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅ ተነስቷል፡፡


የህወሓት አገዛዝ በጅንካ የተነሳውን ጠንካራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማርገብ ከሌላ አካባቢ የፌደራል ፖሊስና ልዮ ኃይል ጦር ጭኖ በአካባቢው አስፍሯል፡፡ ሆኖም አመፁን በኃይል ለማብረድ በአካባቢው ለሚገኙ የህወሓት የታጠቁ ኃይሎች ህዝቡ በአንድነት ተባብሮ ምግብና ውሃ መሸጥ በማቆሙ የፌደራል ፖሊስና የልዩ ኃይል አባላት በአካባቢው ለመቆየት በእጅጉ ተቸግረው ይገኛሉ፡፡
አገዛዙ ከሌላ አካባቢ ምግብና ውሃ ገዝቶ በማቅረብ ችግሩን በማቃለል የታጠቁ ኃይሎቹን በአካባቢው ለማቆየት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
በኮንሶ፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር ከፍተኛ ረሃብ መግባቱ ተሰማ፡፡
በበርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ከ16 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለምግብ እጥረት ተዳርጎ የሚደርስለት ጠፍቶ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ከፍተኛ እልቂት እያንዣበበበት ይገኛል፡፡ ነገር ግን የህወሓት አገዛዝ አሁንም ቢሆን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም ለሚያስችሉት ተግባራት ከፍተኛ ወጭ እያፈሰሰ በረሃብ የሚያልቀው ኢትዮጵያዊ ምንም ደንታ አልሰጠውም፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመድፋት ከፍተኛ ድግስ ማሰናዳቱን እና በከፍተኛ የውሎ አበል ክፍያ በያዳራሹ በስብሰባ ስም መመሸሸጉን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡
ህወሓት ድርቅንና በህዝብ ላይ የሚመጣን የረሃብ እልቂት እንዳውም ለገቢ ምንጭነት የመጠቀም የቆየ ልምድ እና ባህል እንዳለው ብዙዎቹ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
በተለይም ደግሞ አሁን በኮንሶ፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር የገባው አደገኛ ጠኔ ከሌሎች አካባቢዎች የከፋ እና ጊዜ የማይሰጥ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡


በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡
በእነ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ ትዕዛዝ በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እየታፈኑ ወደ ልዩ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው፡፡
አቶ አበበ አስፋው፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ ካሳ እና ልጃቸው አየለች አበበ ዛሬ ጠዋት በደህንነቶች እና በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ ወህኒ ተወስደዋል፡፡ በተጨማሪም ደረጀ የተባለ ወጣት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ሉሉ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባልም በቁጥጥር ስር ውሎ በአሁኑ ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች በጥብቅ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
ባጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ መሆኑን ከቦታው እየደረሱን የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Wednesday, October 28, 2015

የአሜሪካ ኢምባሲ የመኢአድ ፕሬዝዳንት የአቶ ማሙሸት አማረን ቪዛ ከለከለ


በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ዉስጥ ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ዉስጥ ይሰፍን ዘንድ ከሃያ አራት አመታት በላይ ሲታገል የኖረዉ እዉቁ
የፖለቲካ ታጋይ አቶ ማሙሸት አማረ በወያኔ መንግስት ከአስር አመታታ በላይ በእስር ቤት ሲማቅቅ ኖሯል:: በቅርቡ እንኳን
ባልተጨበጠ ዉንጀላ አቶ ማሙሸት አማረ ለወራት በእስር ቤት ሲንገላታ ከርሞ ሁለት የተለያዩ ዳኞች በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ
ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም ብለዉ በመፍረዳቸዉ ነጻ መለቀቁ ይታወሳል::
እንዲያዉም የመጀመሪያዉ ዳኛ በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ ጥፋት አላገኘሁበትም ብሎ ግልጽ ፍትሃዊ ብይን ሲበይንለት
በፖሊስ እምቢተኝነት እና ፖሊስ አለቀዉም ስላለ እስር ቤት ሲማቅቅ መክረሙ ይታወሳል::በመጨረሻም ሁለተኛዉ ዳኛም
ተመሳሳይ ብይን በማስተላለፉ አቶ ማሙሸት አማረ ነጻ መዉጣቱ ይታወቃል::
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ደስታቸዉን ለመግለጽ እና የድርጅታዊ ድጋፋቸዉን ለማጠናከረ በማሰብ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት ( የመኢአድ) ደጋፊዎች እና አባላት ለአቶ ማሙሸት አማረ ግብዣ አድርገዉለት ነበር::
ለአሜሪካ ኢምባሲ በላኩትም የግብዣ ጥያቄ መሰረት ሁሉንም ወጭዉን ማለትም የአዉሮፕላን ጉዞዉን እንዲሁም
የሚቆይባቸዉን ቀናት ወጭዎች ሁሉ በመሸፈን በአምሳ አንዱ የአሜሪካ ግዛቶች እየተዘዋወረ ደጋፊዎችን እንዲያበረታታ
የመኢአድ አባላትን ደግሞ በርትተዉ የድርጅቱን ስራ እንዲሰሩ ለማበረታታን እንዲችል ለማድረግ አቅደዉ ግብዣ አደረጉለት::
በአዲስ አበባ የመሸገዉ የአሜሪካ ኢምባሲ ግን አስቂኝ ምክንያት በመፍጠር አቶ ማሙሸት አማረን ቪዛ ከልክሎታል::
ከሃያ አራት አመታት በላይ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ የፖለቲካ ትግል ዉስጥ የኖረን ሰዉ : ህይወቱን ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል
የሰጠን ሰዉ እንዲሁም ከአስር አመታት በላይ በአምባገነኑ የወያኔ በእስር ቤት ሲማቅቅ የኖረን ሰዉ ሀብት አላፈራህም :
ንብረት የለህም: ሚስት እና ልጆች የሉህም ስለሆነም ቪዛ አንሰጥህም በሚል ተልካሻ ምክንያት ወደ አሜሪካን ሀገር
በመሄድ ደጋፊዎችን እና አባላትን እንዳያነቃቃ ከልክሎታል:: ይሄ ዉሳኔ በአጠቃላይ አስቂኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ሰላማዊ
የዲሞክራሲ ሂደት ላይ ደግሞ የተሰነዘረ ተደጋጋሚ ጥቃትን ለማሳዬት አንዱ መገለጫ መሆኑ ግልጽ ነዉ::
የአሜሪካ መንግስት ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ አይናቸዉን በጨዉ ታጥበዉ የወያኔ መንግስት ያድረገዉን የ2007 ዓም
ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነዉ ሲሉ አዉጀዉ መሄዳቸዉ ሳያንስ አሁን የአሜሪካ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የሚያሳድረዉ ልዩ ልዩ
ተጽዕኖ እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል:: ይሄ በማሙሸት አማረ ላይም የተሰጠዉ ዉሳኔ አንዱ መገለጫዉ መሆኑን ያሳያል::
የአሜሪካ ኢምባሲ የመኢአድ ፕሬዝዳንት የአቶ ማሙሸት አማረን የአሜሪካ ጉዞ ዉድቅ ማድረጉ ከወያኔ መንግስት በተቀበለዉ ትዕዛዝ ሳይሆን አይቀርም የሚል እምነት አለኝ የሆነ ሆኖ አሜሪካኖቹም ሆኑ ሌሎች ምዕራባዉያን የወያኔ መንግስት ወዳጆች ጠንቅቀዉ ሊረዱት የሚገባዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በራሱ የሚያረጋግጥ ህዝብ እንደሆነ ነዉ:: ስለሆነም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱ እስኪረጋገጥለት ሰላማዊ ትግሉ ከመላዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እንዲሁም ሌሎች ዲሞክራሲያን ሀይሎች ጋር በመሆን ማጧጧፍ እንዳለበት የሚያሳይ ዉሳኔ እንጅ ትግሉን ወደኋላ የሚቀለብሰዉ አይደለም ስለሆነም በዉጭ ያለዉ ደጋፊና አባላት እንዲሁም በሀገር ዉስጥ ያለዉ ደጋፊና አባላት መኢአድን በማጠናከርና ዲሞክራሲያዊ ትግሉን በማጧጧፍ ለስራ መነቃቃት ይገባናል ብየ አምናለሁ ፡፡
Legese Weldehana's photo.

Tuesday, October 27, 2015

ሰውዲ አረቢያ በገንዘብ እጦት ችግር ክፉኛ ልትመታ ነው ተባለ


ነገሩ ቀልድ እና ሟርት ይመሰላል፣ ነገር ግን እውነት ነው ።ለብዙዎች እርጥባን እና ምጽዋት በመቸር እንደ ጣኦት የምተመለከው ስውዲ አረቢያ እንደ አለማቀፍፉ የገንዘብ ማእከል (አይ ኤም ኤፍ) ሰሞነኛ ማሰጠንቀቂያ ከሆነ (ይህቺው የአለማችን ቁጥር አንድ የተፈጥሮ ነዳጅ አመራች እና ሻጭ አገር) በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ውስጥ ክፉኛ የገንዘብ እጦት ችግር ሊገጥማት አንደሚችል አስጠንቅቋል።
የአሜሪካው ኬብል ኔውስ ኔት ዎርክ(CNN ) በሰኞ ጥቅምት 25 2015 ዘገባው እንደ ገለጸው ከሆነ በአሁኑ ወቅት በአለም ገበያ ላይ ያለው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአማካኝ በበርሚል $50( ሃምሳ ዶላር) ሆኖ ከዘለቀ የዋጋ ማሽቆልቆሉ በ አምራቾቹ ላይ የ 360 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ሰለሚፈጠር ዋንኛ ነዳጅ አቅራቢያዋ እና ነዳጅም ስትንፋሷ የሆነው ሰውዲ አረቢያን ጨምሮ በቀጣዩ 5 ወይም ከዚያ ባነሰ አመት ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ እጦት የገጥማቸዋል ሲል አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አስጠንቅቋል።ሪፖርቱ ጎረቤት ኦማን እና ባህሪንም ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸው ተንብዮዋል።ከ አመት በፊት በበርሚል$ 100( አንድ መቶ ዶላር) የነበረው ነዳጅ ዘይት በቅርቡ እሰከ $45 ዶላር መወረዱ እና ሰወዲ አረቢያ የመሳሰሉት አገሮች ከመጠባበቂያ ፉንዳቸው እስከ መቆንጠር ተገደዋል ተበሏል።”ነዳጅ ሻጮች አገሮች ገቢያቸውን እና ወጪያቸወን ማሰተካከል የጠበቅባቸዋል” ሲል IMF ምክሩን ለእነ ስውዲ አረቢያ ሰጥቷል።
የእነ ስውዲ አረቢያ የኢኮኖሚ መንገዳገድ የመጣው በአካባቢው በተቀሰቀሰው የእርሰ በርስ ጦርነት እና የገበያው መናጋት በተፈጠረ ማግስት መሆኑ ሁኔታውን አባብሶታል ተብሏል።ስወዲ አረቢያ ከችግሯ ለማገገም ነዳጅ በበርሜል በያንስ $106 መሸጥ የግድ ይላታል ያለው ሪፖርቱ ስውዲ አረቢያ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቦንድ በመሽጥ ችግሯን ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም በጎረቤት የመን የሚገኙ የሺያት አማጺያኖችን ለመዋጋት በሚል ሽፋን እና ደንበሯን ለማሰከበር ስትል እኤአ 2014 ብቻ የመከላከያ ባጀቷን ወደ 80.8 ቢሊዮን ዶላር(17% ጭማሪ አና በ አለማችን 4ኛዋ ለመከላከያ ወጪ አድራጊ አገር አደርጓታል። አሜሪካ 610 ቢሊዮን ፣ቻይና 216 ቢሊዮን ዶላር ፣ሩሲያ 81 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ከ 1 እስከ 3 ይከታተላሉ) የመደበች፣ በ 2011 አካባቢውን ያመሰቃቀለው የአረብ ስፕሪንግ (የአረብ አብዮት)ከደጃፏ ጎራ አንዳይል ጥረት የምታደረገው ሪያድ የዜጎቿን ቁጣ ለማብረድ ስትል የማሕባራዊ (social) እና የመከላክያ ወጪዋን በቀላሉ የምትቀነስ አይመስልም ተብሏል
የሰውዲ ነገር ሲነሳ ከሁለት አመት በፊት ኑሮን ለማሸነፍ እና አንጀራ ፍለጋ ወደ ግዛቷ የገቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምስኪን አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኛ እህቶቻችን እና የጉልበት ሰራተኞች ወንድሞቻችንን ጨረቄን እና ማቄን ሳይሉ እጅግ ኢ-ሰብ እዊነት በተሞላው መንገድ ከግዛቷ ጠራርጋ ማባረሯን በርካታ አትዮጵያዊያኖችን ማሳዘኑ እና ማስቆጣቱ አይዘነጋም። ያንንም መጥፎ አጋጣሚ ብዙዎች “ብ ሔራዊ ውርደት” ሲሉት ተደምጠዋል።
ማን ያውቃል የዛሬ 50 እና 60 አመትታት የግመሎች እና የፍየሎች መፈንጪያ የነበረችው ያቺ ከበረሃው ከረሰ ምድር ውስጥ በሚቀዳ የነዳጅ ሃብቷ ብቻ የአለም ጡነቸኞችን ሳይቀር የመታሰገዳቸው ስውዲ አረቢያ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ኪሳራው ሲበረታባት እና ደግነታችንን ከቅደመ አያቶቿ ሰለመታውቅ ወደ ሃበሽ ምድር(ኢትዮጵያ) ለመሸሸግ ዜጎቿን ትልክ ይሆናል፣ሰደቱ ወደ አረቡ አለሙ መሆኑ ቀርቶ ወደሰው ልጆች መፍለቂያ (ኢትዮጵያ) የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም ። ኋለኞች ፊተኞች ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ የሚባለው ስለዚህ አይደል?።

ራያ ቆቦና የወያኔ ሴራ


ራያ ቆቦ አካባቢ በኢትዮጵያ እጅግ ለም ከሚባሉ መሬቶች አንዱ ነው። ወያኔ በምስራቁ አቅጣጫ ከዓለታማ ክልላቸው ባሸገር ያሉትን ለም የወሎ ወረዳዎች ከወሰዱ ቆዩ ኮረም፣መሆኒ፣ራያ፣አዘቦ….ልጆቹም የአማርኛ መጻህፍቶች እየተቃጠሉ በትግርኛ እንዲማሩ ተደረገ።
አሁን ደግሞ ዓይን ባወጣ መልኩ ቆቦ ወረዳን ለመዋጥ አሰፍስፏል። ድንበራችን አለውሃ ድረስ ነው የሚለውን ትርክት በየቀኑ ከሊቅ እስከ ደቀቅ የሚያነበንቡት ነው። የህወሀት ማባበያ የሚሆኑ አሳሂ ስልቶችም ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። ለምሳሌ ቆቦ ወረዳ ባዛር ሲያካሂድ የአማራ ክልል መንግስት በጀት አልያዝኩም በሚል ሰበብ ገሸሽ ሲል እነ አባይ ወልዱ ስፖንሰር እና አጋፋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተደረገ። በሌላ ጊዜ ለአማራ ክልል የልማት ቴሌቶን ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሲዘጋጅ የትግራይ ክልል ቆቦ ወረዳ ላይ ት/ቤት ፣ጤና ጣቢያ ለመስራት ቃል ሲገባ አይተናል። ያለምንም ምክንያት ከመቀሌ ወደ ቦታው እየመጡ የሙዚቃ ኮንሰርትና ሰርከስ የሚያሳዩበት ጊዜም አለ።
አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉትም ትግራይ በቆቦ አይወሰንም። ይልቁንም ወልደያ ድረስ strategic interest እንዳለው ይናገራሉ። ከወልደያ ወጣ ብሎ የቆመው “እንኳን ወደ ትግራይ ደህና መጣችሁ” የሚለው ታፔላ ራሱ አመላካች ነገር አለው። የወደቅ ግንድ ምሳር ይበዛብታል እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከትግሬ ባሻገር ኦነግ ስንቱን ክ/ሀገር አቃራርጦ መጥቶ ራያ የኔነው ሲል እያየን ነው። ተቆርቋሪ ሞግዚት የሌለው ህዝብ መቼም እንዲህ ነው!

ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በአማራነት ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም !

አካባቢያችንን በብሄር ለማተራመስ በደቡብ ወገኖቻችን ስም የሚነግዱ ግለሰቦች ኦሮሞና አማራን ለማጋጨት የተጀመረው ዘመቻ ከወዲሁ ገድብ ሊበጅለት ይገባል። በተለይ ደቡብን እንወክላለን የሚሉ ግን የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈፀም የሚራወጡ ግለሰቦች ሰሞኑን ለህዝብ አሳቢ ለሃገር ተቆራቋሪ መስለው ዲፕሎማት ሲራክ ላይ የከፈቱት ዘምቻ በኦሮሞ ህዝብ የተፈፀመ እንዳልሆነ እይታወቀ ለምን ብሄራችንን የዚህ አስፀያፊ የስም ማጥፋት ዘመቻቸው አካል ለማድረግ እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም። በየትኛውም አቅጣጫ የኦሮሞን ህዝብ የሁከት መነሻ ለማድረግ ለምን ተፈለገ ? ይህ በነሰመረ እና ሙሉካ የሱፍ የተጀመረው አሰቃቂ ዘምቻ ማንን ለመምታት ነው ? ቆንስላው የሁሉንም ብሄር ተዋጾ ግበአት ያደረገ በመሆኑ በቆንሳው ዙሪያ ለሚከሰቱት ማናቸውም ችግሮች ሚሲዮኑ መጠየቅ ሲገባው አቶ ሲራክን ለምን ነጥሎ ማጥላላት ማብጠልጠል አሰፈለገ ? አቶ ሲራክ ላይ ዘምቻ በተከፍተ ማግስት ከጉዳዩ ጋር በምንም ማመዘኛ ግንኙነት ከሌለው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ጋር ማያያዝስ ለምን ተፈለገ ? እነስመረ የአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠር ዘምቻ ለምን በኦሮሞ ህዝብ ስም ማካሄድን መረጡ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ወደፊት በዝርዝር ለማየት የሚሞከር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዛሬ በፍቅር በሰላም እየኖረ ያለውን ማህበረሰብ በብሄር ለማተራመስ ነዚህ ወገኖች የጀመሩት ዘምቻ ከቆንስላ አልፎ በአካባቢያችን የሚገኙ ታዋቂ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው ጣላቻ የነሰመረን የነሙልካ ድብቅ አጀንዳ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ እንዳለሆነ የበለጠ ግልጽ ማድረግ እንወዳለን ፡፡ እነዚህ በደቡብ ህዝብ ስም ቆንሳላ ውስጥ መሽገው የአዞ እንባ የሚያነቡ ግለሰቦች እና አጋሮቻቸው አአካባቢያችንን በብሄር ለማተራመስ እያሰሙ ያለው ጩሀት ገድብ ሊበጅለት ይገባል። ቆንስል ሙንታሀ የጉዳዩን አሳስቢነት ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው አብረው እየበሉ አብረው እየጠጡ እነሰመረ የስራ በልደረባዎ ላይ የጀመሩትን የስም ማጥፋት ዘምቻ ማስቆም ይጠበቅቦታል። ከሁሉም በላይ በህዝባችን ስም «፡ኦሮሞ » እይነገዱ የሚገኙ እነዚህ ግለስቦች ድብቅ አጀንዳዎቻውን በዚህ መልኩ ለማስፈፀም መሞከራቸው ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚከፋ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆን የለበተም ። የአቶ ሲራክ ለግምገማ መቅረብ አለመቅረብ በካባቢያችን የብሄር ግጭት ማስነሳት በሚችል መልኩ ቅስቀሳ ማድረግ በስደት ዓለም ለሚኖረው ህዝባችን በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ ስለሚሆን ሊታሰብበት ይገባል። አቶ ሲራክ መጠየቅ በሚገባው ይጠየቅ እንጂ በአማራነቱ አሊያም የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ ብቻ ሊገፋ እና አመታት ሲሰራ የነበር ድንቅ ስራዎቹ በግለሰብ ጥላች በአንድ ቀን ጀምበ ሊናድ አይገባም ።ማንም ምንም ይሁን ምን ሊጠየቅ በሚገባበት ነገር ሁሉ መጠየቅ እንዳለበት ግልጽ ቢሆነም ቆንስላው እንደ ተቋም በደንብና ስረአት የሚመራ ሆኖ ሳለ በነ ቆንስላ ሙንተሃ አስተባባሪነት አቶ ሰመረ እና የዘንድሮ የሴቶች ማህበር ተብየ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ አንድ ብሄር ላይ ለመዝመት በእጅ አዙር እየተፈፀመ ያለው አስፀያፊ ና አስነዋሪ የስም ማጥፋት ዘምቻ በተለይ ወ/ሮ ሙንተሃ ካሉበት የስራ ኃላፊነት አንጻር የሚመጥን ባለመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል። ቆንስላውን በብሄር ለማመስ በኦሮሞ ህዝብ ሽፋን አንዳንድ ደቡብን ወክለናል በሚሉ ግለሰቦች በየሶሻል ሚዲያ ገጽ ላይ የሚለጠፈው ፈር የለቀቀ አካሄድ ለአካባቢያችን ሰላም ጠንቅ መሆኑ ልብ ሊባል ይገበዋል። አያበሬ ምነው ገደሉን ሳታይ አየነት ግልጽ ሰህተት ውስጥ በመግባት በአካባቢያችን ታዋቂ ሰዎችና በቆንስላ ሃላፊዎች ላይ የተጀመረው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሽፋን መስጫው መልካም አስተዳደር የሁን እንጂ ግቡ በአካባቢያችን የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠር ነው ። ቆንሳል ግቢ ውስጥ እየተፈፀመ ካለው ፈር የለቀቀ ድርጅታዊ አሰራር ሃሜትና ግምገማ እየታየ ያለው አስነዋሪ ተግባር አደባባይ ወጥቶ አንዱ በሌላው ላይ እያስወራ ያለው አስነዋሪ ድርጊት በአንድ ብሄር ላይ ያነጣጠር የስም ማጥፋት ዘምቻ በመሆኑ ከወዲሁ ሊገደብ ይገበዋል ። ህይወት ፀጋዬ ከጅዳ ቆንስላ ግቢ
Addis Zemen Addis Zemen's photo.

Monday, October 26, 2015

ድምፃዊው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀለ!!


በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት አማኑኤል መንግስቴ ይባላል። ድምፃዊ ሲሆን “የቋራዉ አንበሳ” በሚለዉ ተወዳጅ ስራዉ በህዝብ ዘንድ በስፋት ይታወቃል። አማኑኤል የወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ልጅ ሲሆን እናቱ ወ/ሮ እማዋይሽ የመፈቅለ መንግስት ሙከራ አድርጋችኋል በሚል በሕወሓት አገዛዝ የፈጠራ ክስ ሰለባ ሆነው የእድሜ ልክ እስር ከተፈረደባቸው ፍርደኞች አንዷ ናት። ዛሬ የአማኑኤል ታሪክ ተቀይሯል። የሕወሓት የግፍ አገዛዝ ከሚወዳት እናቱና ከሚወደው ሞያው ነጥሎታል። የሙዚቃ ህይዎቱን ትቶ የሕወሓት አገዛዝን ለመፋለም በረሀ የወረዱ አርበኞችን ተቀላቅሏል። ጨቋኙን የሕወሓት አገዛዝ ማስወገድ የሚቻለው በትጥቅ ትግል ብቻ መሆኑን በማመኑ ለዚህ ውሳኔ መብቃቱን ተናግሯል። አማኑኤል መንግስቴ በርካታ ወጣቶችን አስከትሎ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን መቀላቀሉ ታውቋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር በጥምረት ከሚሰሩ ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡


ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡:
እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

Saturday, October 24, 2015

በአማራ ህዝብ ስቃይ፣ ስደት፣ መፈናቀልና ሞት እየጨፈረ ያለው ብአዴን

ብአዴን የአማራን ህዝብ ማንነት፣ ባህል፣ እምነት፣ ቦታና ታሪክ ለማጥፋት በህወኃት የተፈበረከ የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው። ራያ፣ ቆቦ፣ ሁመራን ለትግራይ ያስረከበው ይህ የወያኔ ገረድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጎንደርን ለም መሬቶች ለሱዳን በማስረከብ በህዝባችን ላይ የፈፀመው ግፍ ትውልድ ይቅር የማይለው ነው። የአማራ ህዝብ በዚህ ተላላኪ ድርጅት አማካኝነት በአደባባይ ተሰድቧል፣ ተዋርዷል፣ ተፈናቅሏል፣ ተሰዷል፣ ተገድሏል አሁንም በመፈናቀልና በመገደል ላይ ይገኛል።
ወያኔ /ህወኃት የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ከተነሳበት ከ1967 ዓ• ም ጀምሮ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ለአገራቸውና ለህዝባቸው የሚቆረቆሩ ወገኖችነ እየታደኑ ተገድለዋል፣ በመገደልም ላይ ይገኛሉ።
ይህ ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎ ወያኔ በሎሌው ብአዴን አማካኝነት የአማራን ህዝብ ማሰር፣ ማፈናቀልና መግደል አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በአሁኑ ሰዓት በወልቃይት ፀገዴ የአማራ ህዝብ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ስቃይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ነው። በአማራ ህዝብ ስቃይ፣ ስደት፣ መከራ፣ መፈናቀልና ሞት ምክንያት የሆነውን ህዳር 11 ቀን የወያኔን የድል በዓል ለማክበር ከበሮ እየደለቀ ያለውን ብአዴንን በቃ ብሎ ህዝባችን ለነፃነቱ መነሳት አለበት።
ስለዚህ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የምትኖሩ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ በመሰባሰብ ለዚህ አረመኔያዊ ግፍ የሚመጥን ቁመና በመፍጠር ህዝባችንን ከመፈናቀል፣ ከስደትና ከሞት ለመታደግ በእውነት የአማራን ህዝብ የሚወክል ድርጅት መመስረት ይጠበቅብናል። ይህን ግፍ እያየን እንዳላዬን፣ እየሰማን እንዳልሰማን ዝም ብንል መዳን ለአማራ ህዝብ ከሌላ ስፍራ ይመጣለታል። እኛ ግን በታሪክ መታሰቢያ አይኖረንም። በመሆኑም መላው የአማራ ተወላጅ ገበሬው፣ ተማሪው፣ ነጋዴው፣ ምሁሩና ወታደሩ በአስቸኳይ በያለበት በመደራጀት የትውልድ አድን ንቅናቄ እንዲጀምር እናሳስባለን።
እኔ እንደ አማራ ተወላጅነቴና እንደ ኢተረዮጵያዊነቴ በዚህ ችግር ዙሪያ ከተለያዩ የአማራ ምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ ላይ እገኛለሁ። በቅርብ ቀን ይህን የህዝብ ስቃይና ሞት የሚመክት እውነተኛ የአማራ ንቅናቄም እንፈጥራለን። እስከዚያው ግን ህዝባችን የብአዴንንና የወያኔን እኩይ ተግባር በያለበት በመመከት በቅርብ ለሚመሰረተው ንቅናቄ ግብአት የሚሆን አቅም እንዲፈጥር በአክብሮት እንጠይቃለን።
ሁለንተናዊ ነፃነትና ክብር ለአማራ ህዝብ!!
ነፃነት ለሃበሻ

አርበኞች ግንቦት ሰባት በስዊድን PATRIOTIC GINBOT 7 SWEDEN

Friday, October 23, 2015

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሌሉ ገለፀ


‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ
• ‹‹የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደሌሉ ማረሚያ ቤቱ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ ገልፆአል፡፡ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ለምን እንዳላቀረበ እንዲያብራራ፣ እንዲሁም ለምስክርነት እንዲያቀርብ ለዛሬ ለጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ተከሳሾቹ ማረሚያ ቤቱ ሲያጉላላቸው ቆይቶ አሁን የለም ማለቱ ትክክል እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ ማረሚያ ቤቱ ምላሽ የሰጠው በአራተኛው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቅሶ የፍርድ ሂደታቸውን ከሚገባው በላይ እያጓተተ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ገልፆአል፡፡ ‹‹መከላከል ከጀመርን አንድ አመት ከስድስት ወር ሆነ፡፡ በግዞት ነው ያለነው፡፡ የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› ያለው አቶ አሸናፊ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ‹‹ፌዝ ነው›› ብሎታል፡፡
3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ሲጠቅሱ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ እንደሆኑ በመጠቆም ተቃውሞ አሰምቶ እንደነበር፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ ቃሊቲ እንደሚታሰር ገልፆ ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው እንደሌሉ መግለፁ ‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› ብሏል፡፡ ‹‹የእድሜ ልክ ወይንም የሞት ፍርደኛ የት ነው የሚታሰረው?›› ሲልም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
3ቱ ተከሳሾች የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸውን እንደያዙ በቴሊቪዥን መግለፃቸውን አስታውሰው አሁንም ለሁለቱ አካላት ደብዳቤ እንደሚፅፉ ለፍርድ ቤቱ አሳውቀው የነበር ቢሆንም ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ሆኖም ግን 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም 4ኛ ተከሳሽ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲቀርቡለት የሚያቀርበውን አቤቱታ ተመልክቶ ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት ለጥቅምት 23/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የቁጥሩ መንግስት እና የአድዋ ውሃና ፍሳሽ መስርያቤት የእናት ልጅ ወይንስ የእንጀራ ልጅ


ስለ ንፁህ ውሃ ለመወያየት የሁሉም ክልሎች የውሃ መስርያቤት ኃላፊዎች አድዋ ድረስ እንዲሄዱ ከተደረገ በኃላ ”ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት አቶ አባይ ወልዱ” ”ስለ ውሃ ለመነጋገር እዚህ ድረስ በመምጣታችሁ ተሞክሮ ስለምናገኝ ደስ ይለናል” ካሉ በኃላ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ገርባ ንግግር ሲያደርጉ እንዲህ አሉ ”ባለፉት 5 አመታት ብቻ 41 ሚልዮን ሕዝብ ንፁህ ውሃ ማድረስ በመቻላችን ከሣሃራ በታች ካሉ አገሮች ቀዳሚ ሆነናል።አሁን የንፁህ ውሃ ሽፋናችን 80% ደርሷል” ሲሉ ተናገሩ።ውሸት በቁሙ ሲሄድ ማለት ይህኔ ነው።አቶ ኃይለማርያም አዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ውሃ እያገኘ አይደለም ካሉ ገና ሁለት ዓመት አልሞላውም። እና አቶ ከበደ ምነው ቁጥሩን አከበዱት? እና ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር፣ከሐረር እስከ ባህርዳር ንፁህ ውሃ አጥተው ቢጫ ጀርካል ይዘው የሚንከራተቱት ኢትዮጵያውያን 20% ውስጥ ብቻ ያሉ ናቸው ማለት ነው?
የአድዋ ውሃና ፍሳሽ መስርያቤት የእናት ልጅ ወይንስ የእንጀራ ልጅ?
========================================
ከላይ እንደጠቀስኩት የውሃ ፎረም እየተደረገ ያለው አድዋ ላይ መሆኑን ስሙን በእንግሊዝኛ ብቻ የምፅፈው የአማርኛ መሃይም የሆነው EBC ገልጧል።ማታም ይደግመው ይሆናል።የእኔ ጥያቄ የአንዲት ከተማ የውሃ ፍሳሽ መስርያቤት በምን በጀቱ ነው እንደ ዜናው የ 9ክልሎች የውሃ መስርያቤቶችን ኃላፊዎች ባለሙያዎች ወዘተ የትራንስፖርት ወጪ፣የሆቴል እና ሌሎችም ወጪዎችን ችሎ ማዘጋጀት የቻለው? በዜናው ላይ ዋናው መስርያ ቤት ሳይሆን የአድዋ ውሃና ፍሳሽ ቢሮ የጠራው እና ያዘጋጀው ይላል።።የውሃ ፍሳሽ የአንዲት ከተማ ቢሮ ቀርቶ ዋና መስርያ ቤቱ የረባ ወንበር እንደሌለው እናውቃለን።እና ከቢሮ ቢሮም የእናት ልጅ እና የእንጀራ ልጅ አለው እንዴ?
(በነገራች ላይ ከላይ ያወጋሁት በሙሉ የዛሬ ጥቅምት 12/2008 ዓም የቀትር ኢቲቪ ቀዳሚ ዜና ነበር።መንገድ ላይ ስሄድ ሞባይሌን ስነካካት ያሰማችኝ ጉድ ነው)

የህወሃት ባለስልጣናት በከፍተኛ ደረጃ ዶላር እያሸሹ ነው፡


በሰሜን አሜሪካ በህግ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ለአንድ ዶላል በ23 ብር እየቀየሩ ሃብታቸውን በማካበት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።
የኢህአደግ ስረአት ባለ ስልጣኖች ሃብታቸውን ከውስጥ ሃገር ለማውጣት እየተጠቀሙት ያለውን ስልት የኢትዮጵያ ባንኮዎች ከመጉዳት ባለፍ በአሁኑ ወቅት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከባድ ችግር ውስጥ አስገብተውት እንደሚገኙ የገለጸው መረጃ: በአሁን ጊዜ የኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች በሙስና ያጠራቀሙት ሃብት ወደ ዉጭ በማጓጓዝ ላይ ተጠምደው ባሉበት ግዜ ከሰሜን አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከመጠን በላይ በኮትሮ ባንድ ንግድ ለአንድ ዶላል በ23 ብር እንመነዝርላችሓለን በማለት በህዝብ ሃብት በመጫወት ላይ ኣንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው አክለዉ እንዳመለከተው በአሁኑ ጊዜ፡ በዋሽንግተን፤ በዱሲ፤ ስያትል፤ ዴንቭር፤ ሚኒያፖሊስ፤ አትላንታ፥ ቺካጎ፤ በሂውስተን፤ ኦሃዮ፤ ፓርትላንድ፤ ላስቬጋስ፤ ካልፎርኒያ እንዲዚሁም በተለያዩ ከተሞች በአሪዞና በተዘረጉት መረቦች መረጃ ዶላር በኮትሮ ባንድ ንግድ በ23ብር እየተመነዘር መሆኑን መረጃው አስታውቀዋል።
በመጨረሻም አንድ የአሜሪካ ዶላር በህጋዊ መንገድ ብ20.85 ብር እየተመነዘር ቢሆንም በሌቦች የኢህአድግ የገዢው ስረአት ባለ ስልጣናት ግን ዶላር ያለ ህጋዊ መንገድ የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ያለ አግባብበ በመቀየራቸው የተነሳ የሃገር ውስጥ መንዛሪ ከፋተኛ እጥርት እያጋጠመ እንዳለ የተለያዩ ህዝቦች በመግለፀ ላይ ይገኛሉ።

Thursday, October 22, 2015

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሎሚ መፅሄት ማኔጂንግ ደይሬክተር ላይ የ 18 አመት እስር በየነበት !!


የሎሚ መፅሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ ላይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ 18 አመት እስራትና የ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሲበየንበት በመፅሄቱ አሳታሚ ድርጅት ላይ ደግሞ የ 200 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት በዛሬው ዕለት በሌሉበት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፎል!
ከ 800 ሺህ ብር በላይ ታክስ በማጭበርበርና በሌሎች 14 ክሶች ጥፋተኛ የተባለው የሎሚ መጽሄት ዋና ስራ አስኪያጅ በ 18 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነ.
በመጽሔታቸው በወጡ ጽሁፎች ድርጅቱና ሥራ አስኪያጆቹ ሐሰተኛ ወሬ አትሞ በማውጣትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል ‘በሚሉ ሁለት ክሶች ሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር መከሰሳቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤት ቆመውም ነበር.
በተሻገር ጣሰው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምዕመናኑ ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ


‹‹ምዕመናንን የመጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣን አይደለም›› አቡነ ማትያስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰበካ ጉባዔ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር የነበረ ቢሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቢሊዮኖች ብር ማደጉን የገለጹት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ፣ የምዕመናኗ ቁጥር ግን እየቀነሰ መሆኑን አስታወቁ፡፡
ፓትርያርኩ 34ኛውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔን አስመልክቶ ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቤተ ክርስቲያኗ ገቢ በቂ ነው ባይባልም፣ በየጊዜው እያደገ መጥቶ ከመቶ ሺዎች ብር ወደ ቢሊዮኖች ብር አድጓል፡፡ ይኼ የሆነውም ቤተ ክርስቲያኗ ከልጆቿ (ምዕመናን) ከምታገኘው ገቢ ባለፈ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፏ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የምዕመናን ዕድገት የኋልዮሽ እየሄደ መሆኑን የጠቆሙት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ዕድገቱ የኋልዮሽ መሆኑን የሚያውቅ ይኖር ይሆን? ችግሩንስ በሚገባ ተገንዝቦና በቁጭት ተነሳስቶ ችግሩን ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ አለ?›› የሚሉ ጥያቄዎቹን በማንሳት፣ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚቆየው የሲኖዶስ ጉባዔ ምላሽ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኦርቶዶክሳውያን ተልዕኮ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ መሆኑን ሁሉም የዕምነቱ ተከታዮች፣ በተለይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አባቶች እንደሚያውቁ የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ከህሊና መቆርቆር እስከ ሕልፈተ ሕይወት የሚዘልቅ የመስዋዕትነት ዋጋ የሚጠይቅም መሆኑን መዘንጋት እንደሌለባቸው ለጉባዔው ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡
ባህር አቋርጦ፣ ድንበር ተሻግሮ፣ እስከ ምድር ጽንፍ ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በአገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምዕመናንን ማባዛት ብዙ እንዳልተሄደበት ፓትርያርኩ አስታውቀዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ትናንትና ስመ ክርስትና ሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆቿ፣ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደ ሌላ ጎራ መቀላቀላቸው እየናረ መምጣቱን አክለዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምፕ ለመሄድ ለምን መረጡ? የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው? የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት? አስተዳደሩ የማያረካ ሆኖ? የካህን እጥረት? ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው?›› የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱት ፓትርያርኩ፣ መልሱን የጉባዔው ተሳታፊዎች የሚያውቁት ቢሆንም፣ ለሲኖዶሱ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ምዕመኗን የመጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣች ባለመሆኗ ባዶዋን ከመቅረቷ በፊት፣ ለተደራጀና ድንበር የለሽ ትምህርተ ወንጌል መነሳት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ሥራ ለምዕመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ መሆኑን የገለጹት ፓትርያርኩ የሃይማኖቱን መርህ ጠብቀው፣ አስተዳደሩ የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጽ፣ ተዓማኒና ተጠያቂነትን ያሰፈነ፣ የምዕመናንን ልብ የሚያረካ ሥራ መሥራት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻው የሕዝብና ቤት ቆጠራ አሥር በመቶ ምዕመናን ቁጥር መቀነሱ የታወቀ መሆኑን፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አበ እምኔት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ፣ በየገዳማቱ የሚኖሩ መነኮሳትና ሌሎች በድጋሚ ቆጠራ የተደረገላቸው ቢሆንም፣ እንዳልተካተተና ለምዕመናኑ ቁጥር መቀነስም ሌላው ምክንያት መሆኑንም የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምርያ ዋና ኃላፊ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጨ ተናግረዋል፡፡ ለምዕመናን ትምህርተ ወንጌልን በማዳረስ አማኙን ለማብዛት እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት መምርያ ኃላፊው፣ በጋምቤላ ክልል በራሳቸው ቋንቋ ወንጌልን በማዳረስ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ ኃላፊዎችን የሃይማኖቱ አባላት ማድረግ መቻሉን አክለዋል፡፡
ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ ቤተ ክርስቲያኗ ጠንክራ እየሠራች መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ትልቅ ሙስና ይፈጸምበታል የሚባለው የቤተ ክርስቲያኗ ሰፋፊ መሬት ጥናት ተደርጐበት መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡
በተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጥፋት ፈጽመው ሲገኙ፣ ከአንዱ ቤተ ክርስቲያን ተነስተው ወደ ሌላ መዘዋወራቸው ቀርቶ ሙሉ በሙሉ የሚባረሩበት፣ በዘር፣ በመግባባትና ያለችሎታ የሚመደቡበት አሠራር ቀርቶ፣ በዕምነቱ ጥንካሬ፣ በላቀ ዕውቀት ምዕመናኑን በአግባቡ ሊያስተምር የሚችል የታመነበት አስተዳዳሪ የሚሾምበት አሠራር መዘርጋቱን የመምርያ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

Wednesday, October 21, 2015

ለእንዳርጋቸው መታፈን ተጠያቂ የተባሉት ዶ/ር ቴዎድሮስን ሎንዶን ላይ መጋበዝ እደጋ አለው ተባለ

ካለፈው አመት የፈረንጆቹ ሰኔ ወር መባቻ ላይ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ የመን(ሰነኣ ) አለም አቀፍ አወሮፕላን ጣቢያ ላይ ታፈነው ለ አዲስ አበባ መንግስት ተላለፈው የተሰጡት እና ቀደም ሲልም በሌሉበት ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2009 አኤአ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እጣ ፈንታ ያሳሰበው አንድ ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት “ለጥቅሙ ሲል “የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይን ችላ እንዳይል ዳግም እስጥነቀቀ።
በሰው ልጆች ላይ የሞት ብይን እንዳይተገበር የሚሟገተው እና መቀመጫውን ሎንዶን(እንግሊዝ) ያደረገው አለማቀፉ ሪትሪቪው ድርጅት በነገው እለት (ጥቅምት 21 2015 )ሎንዶን ላይ በእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ የውጪ ጉ/ሚ/ር ባለሰልጣናት እና በኢትዮጵያ አቻዎቻቸው መካከል የሚደረገውን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ተኮር ፎርምን በማሰመልከት ዛሬ ባወጣው መግለጫው “ ፎረሙ የሚካሄደው እንግሊዝ እንደ ኢትዮጵያ እና እንደ ስውዲ አርቢያ ከመሳሰሉት በሰበዊ መብት ይዞታቸው ከመወገዙ አገሮች ጋር ያላት ቁርኝት አወዛጋቢ በሆነብት ወቅት ነው ።” ያለው የመብት ተማጋቹ ድርጅት “ ከዚህ በሁዋላ የሰበዊ መብት ጉዳይ የእኛ ቅድሚያ አይሆንም ያለው የእንግሊዝ መንግስት አንዳርጋቸውን አፍነው ከወሰዷቸው ባለሰልጣናት (እነ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ይገኙበታል ተብሏል ) በንግድ ዙሪያ ፎረም መክፈቱ እና የእንግሊዝ ዜግነት ላላቸው ፣በሌሉበት የሞት ፍርድ ለተበየነባቸው እና የሶስት ልጆች አባት ለሆኑት ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ዋንኛ ተጠያቂ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስን በንግድ ሽፋን መቀበል ተጨማሪ ስጋት እና የተሳሳተ መልእክት ያሰተላልፋል።” በማለት የሪትሪቪው ዋና ሃላፊ የሆኑት ሚሲስ ማያ ፎአ ሰጋታቸውን ገልጸዋል።
በሰተመጨረሻም ሚሲስ ማያ “ እንግሊዝ ከአጋሮቿ የንግድ ሽርክና ማደረጓ አንደ ተጠበቀ ሆኖ በሌላ ጎኑ ግን ከእንደ ኢትዮጵያ እና እንደ ሰወዲ አረቢያ ከመሳሰሉት አገሮች ጋር ግብይት ሰታደረግ የሰበኣዊ መብት ረገጣ ሰለባዎችን (እንደ አቶ አንዳርጋቸው የመሳሰሉትን) በጭራሽ መዘንጋት የለባትም።የእንግሊዝ የውጪ ጉ/ሚ/ር ባለሰልጣናት የነገው ፎርምን በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ በቀጥታ የሚጥይቅበት አጋጣሚ ሊያደረገው ይገባል።” በማለት ሎንዶን አቋሟን እንድትፈተሽ የመብት ተማጋቹ ድርጅት ባለሰልጣኑዋ አሳስበዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ላለፉት 16 ወራት ከቤተሰቦቻቸው አይታ ፣ከህግ አማካሪዎቻቸው ፣ ከኢምባሲ ሰዎች ፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከመሳሰሉት ርቀው መታሰራቸው አንዳለ ሆኖ የአገዛዙ የውጪ ጉ/ሚ/ር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም በቅርቡ ከአሜሪካ ራዲዮ የአማሪኛው ክፍል ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ “አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ አዲሱ የናዝሬት ጎዳናን ጎብኝተዋል፣ ላፕ ቶፕም ተሰጥቷቸው ከእስር ቤት መጽሐፍ ለማሳተም በማገባደድ ላይ ናቸው ።”ማለታቸው በበርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም። የህንኑ በነገው እለት በማእከላዊ ሎንዶን የሚከናወነውን የእንግሊዝ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሰልጣናት ፎረምን በተመለከት በመዲናይቱ እና በእካባቢዋ የሚገኙ በርካት ኢትዮጵያዊያን እና ተወለደ ኢትዮጵያዊን እንደ ከዚህ ቀደሙ በሰፍራው በመገኝት ተቃውሟቸውን እና ስጋታቸውን በሰላማዊ መንገድ ያሰማሉ ተብሎ የጠበቃል።
በሌላ ተመሳሳይ ዜና የ16 አመቷ ሴት ልጃቸው ሕላዊት አንዳርጋቸው ከ 5 የት/ቤት ጉደኞቿ ጋር በመሆን በአባቷ መታሰር ዙርያ የሚያውጠነጥን ተውኔት በቅርቡ ሎንዶን ከተማ ውስጥ ለበርካታ ታዳሚዎች በማቅርቧ የተነሳ ላይበሪቲ(ነጻነት ) ከተባለ ድርጅት የአመቱ ተሸላሚ ሆና ሰሞኑን መቅረቧ አና ሸልማቱም እስርኛው እና ወላጅ አባቷን ለማስፈታት እርሷ ፣ ቤተሰባቸው እንዲሁም የተቀረው የእቶ እንዳርጋቸው ደጋፊዎች ለጀመሩት ሰላማዊ ትግል ጉልበት እና ብርታት እንደሚሰጥ መግለጿ ይታወሳል።

“እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል” ለአባይ ግድቡ? ለአባይ ወልዱ? ወይስ ለአባይ ጸሃዬ?


Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.Amdom Gebreslasie's photo.

ለ900ሺ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ሰሙኑን መቀሌ ከተማ ደርሰዋል።
አንድ ሚሊዮን ለሚጠጋ ተረጂ እስከ 350 መኪኖች እህል ጭነው በቀጥታ ከጅቡቲ ትግራይ ገብተዋል።
መንግስት እንዳለው የጫኑት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ሳይሆን ከውጭ በእርዳታ የገባ መሆኑ ጭነው የመጡት ሹፌሮች አውግተውኛል።
“ድርቁ በቁጥጥር ስር ኣውለነዋል” የሚል የትግራይ መንግስት መግለጫ ተደጋግሞ እየተሰማ ባለበት ቅፅበት “ለእርዳታ የመጣው እህል እየተሸጠ ነው” የሚል ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው።
እህሉ መቀሌ ከተማ ወደሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጠ መሆኑና ጥያቄ ላነሱ ሹፌሮች ደግሞ “ድርቁን በቀላሉ ስለተቆጣጠርነው ትርፉ ተሽጦ ለአባይ እንዲሆን ተወስኗል” ተብሎዋል።
ከእኔ ጋር ሁኖ ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት “… የትኛው አባይ ነው? አባይ ግድብ፣ አባይ ወልዱ፣ ወይስ አባይ ፀሃዬ …” ብሎ ጠይቋል።
የትግራይ ገዢዎች ድርቁም እህሉም በቁጥጥራቸው ስር ያዋሉ ይመስላሉ …!!! ድርቅ ካጠቃው፣ ህይወቱ በአደጋ ውስጥ ከገባ፣ ህይወቱን ለማቆየት የጎረሳት ማቆያ ምግብ ከጉሮሮው የሚቀሙ ሌቦች እንጠብቀው።
ኤፍ ኤም ፋና ትግርኛ ፕሮግራም ምስጋና ይድረሳቸውና ትንሽ ብትሆንም የድርቁ ሰለባ ወገኖች ድምፅ አሰምተውናል።
“ወጣቱ ስደት ከመሄድ ትንሽ ተረጋግቶ ነበር። ኣሁን በድርቁ ምክንያት ፈርቶ ባህር እየገባ ነው … ተማሪዎች በዚህ ሁኔታ መማር ኣንችልም ብለው ቤት እየዋሉ ነው … ከ8 ሺ በላይ የቀበሌያችን ከብቶች በምግብና ውሃ እጦት ክፉኛ ተደርቀውብናል … መንግስት ቶሎ ሊደርስልን ይገባል … ” ብለው ሲናገሩ ሰምተናል።

Tuesday, October 20, 2015

የአለም የመገናኛ ብዙሃን ስለኢትዮጵያ ድርቅ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ላይ ናቸው


ኢሳት ዜና         03645-1796634_222183061305326_875283870_n   :-ከታላላቆቹ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መካከል ዘ ኒውዮርክ ታይምስና ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የዜና ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆን፣ ዘ ኒዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ድርቁ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። “ያሲን ሙሃመድ ከአነስተኛ የእርሻ ማሳው ላይ እየወሰደ ጫት ይቅማል፣ ለምን ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጫት ረሃብን ያስታግሳል “የሚል መልስ መስጠቱን የዘገበው ዘ ኒዮርክ ታይምስ፣ በመኢሶ አካባቢ ለወትሮው በክረምት ወር ይዘንብ የነበረውን ዝናብ ዘንድሮ አንድ ጊዜ ብቻ መዝነቡን ገልጿል። ይህ ኢትዮጵያ በ10 አመታት ውስጥ የገጠማት ከባዱ ድርቅ ነው ያለው ጋዜጣው፣ ነዋሪዎች መሰደድ መጀመራቸውን ይገልጻል። የ50 አመቱ ጎልማሳ አቶ ያሲን፣ በሰአት ምግብ መመገቡን ማቆሙን ገልጾ፣ እስከ ሚቀጥለው የመኸር ወቅት ከብቶቹን ቢሸጥ እንኳን ቤተሰቡን ለማቆየት እንደማይችል ገልጿል። “ሌሎች አርሶ አደሮች አካባቢውን ለቀው ” መሄዳቸውንም አቶ ያሲን አክለዋል። መንግስት 8 ሚሊዮን 200 ሺ ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ቢገልጽም፣ አሃዙ እስከ 16 ሚሊዮን እንደሚደርስ ጋዜጣው የተመድን መረጃ ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል። መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ድህነት ለመቀነስ እና መንገዶችን፣ ትምህርት ቤቶችን እንዲሁም የጤና ተቋማትን ቢገነባም፣ የሰዎችን ነጻነት እና የብዙሃን ፓርቲ ዲሞክራሲን ለመገንባት አለመቻሉን ገልጾ፣ ባለፈው ምርጫ 547 የፓርላማ መቀመጫዎችን በሙሉ መውሰዱን ዘግቧል። መንግስት ድርቁን ለመሸፋፈን ሙከራ ማድረጉን ተችዎች እንደሚገልጹ የዘገበው ዘ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ይሁን እንጅ የአደጋ መከላከልና ዝግጅኑት ሃላፊ ምትኩ ካሳ መንግስት 192 ሚሊዮን ዶላር በማዘጋጀት ፈጣን ምላሽ መስጠቱን በመግለጽ ትችቱን ተከላክለዋል። አቶ ምትኩ ጥረቱ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፍልግ ተናግረዋል። አሁን የታየው ችግር አመቱን ሙሉ እንደሚቀጥልና እስከ 15 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚራብ ጋዜጣው ጠቅሷል። በተለይ አሚባራ በሚባለው የአፋር አካባቢ በርካታ እንስሳት ማለቃቸውን የጠቀሰው ጋዜጣው፣ ሁመድ ካሚል የተባሉ የ42 አመት ጎልማሳ 30 የሚሆኑ ላሞቹ በርሃብ እንደሞቱ ገልጿል። አቶ ሃሚድ 7 ልጆቻቸውን ለማብላት ቀሪ ላሞቻቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ መሆኑንም ገልጸዋል። መንግስት ምንም ድጋፍ እየሰጣቸው አለመሆኑንም አቶ ሃሚድ ለጋዜጣው ሪፖርተር ተናግረዋል። በሌላ በኩል በጥቅምት ወር ውስጥ በትግራይ፣ አዊ፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ ምእራብ እና መስራቅ ጎጃም፣ ሰሞንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግ ህምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ኦሮምያ ዞን፣ በአፋር ደግሞ ዞን 3 እና 5 ፣ አብዛኛው የቤንሻንጉል ጉሙዝ አካባቢና ጋምቤላ፣ ኢሉባቡር፣ ጅማ፣ ምስራቅና ምእራብ ወለጋ፣ ቦረና፣ ጉጂ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ አርሲ፣ ባሊ፣ ምስራቅና ምእራብ ሃረርጌ፣ ከፋ እና ቤንች ማጂ ዞን፣ ሲቲ፣ ጂጂጋ ፣ ፊቅ፣ ደጋሃቡር፣ ሊቢን፣ አፍዴር፣ ጎዴ፣ ኮራሄ እና ዋርዴር ዞን እንዲሁም ሃረሪ፣ ድሬዳዋን አዲስ አበባ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፣ በእነዚህ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ከመቻሉ በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎች ሊበላሹ ይችላል ሲል ብሄራዊ የጎርፍ መከላከያ ተቋም አስታውቋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡


አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደትጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

Monday, October 19, 2015

ካልተጠነቀቅን አፋፍ ላይ ነው ያለነው!!


በ ዮሃንስ ሰ.
ቁጥሮቹ አስገራሚ ናቸው – ማለቴ ለኢትዮጵያ። በ1997 ዓ.ም፣ (ከአስር ዓመት በፊት መሆኑ ነው…) የአገሪቱ ገበሬዎች ጠቅላላ የእህል ምርት 119 ሚሊዮን ኩንታል ነበር። አምና ደግሞ፣ 236 ሚሊዮን ኩንታል። እነዚህ፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ቁጥሮች… ስህተት ይሆኑ እንዴ? ሊሆኑ አይችሉም ለማለት አስቸጋሪ ነው። አንደኛ ነገር፣ አስደናቂው የእድገት መረጃ፣ ከሌሎች በርካታ መረጃዎች ጋር ሲጋጭ፣ ምን ታደርጉታላችሁ?
መስኖ፣… እንደድሮው ነው (1% ለመሙላት ብዙ ይቀረዋል)!
መቼም፣ ከእርሻ እድገት ጋር አብሮ፣ የመስኖ ጉዳይ መነሳቱ አይቀርም። ባለፉት አስር አመታት፣ የመስኖ እርሻ ተሻሽሎ ይሆን? አልተሻሻለም – ከጫት እርሻ በቀር። መስኖን በመጠቀም፣ የጫት ማሳዎችን የሚስተካከል የለም።
በበሬ ማረስ? እሱም በሬ ከተገኘ ነው!
ለእርሻ ስራ፣ ሁለት በሬ ካላቸው ገበሬዎች ይልቅ፣ ምንም በሬ የሌላቸው ገበሬዎች ይበዛሉ። በግብርና ከሚተዳደሩ 15 ሚሊዮን የገጠር ቤተሰቦች መካከል፣ ስንቶቹ ምንም በሬ እንደሌላቸው አስቡት – ስድስት ሚሊዮን ተኩል።
ወተትና ቅቤ? ከአንዲት ላም አንድ ሊትር ተኩል?
ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ በገጠር የወተት ምርታማነት፣ ምን ያህል እንዳደገ ጠይቁ። ምንም አላደገም የሚል ምላሽ ነው የምታገኙት – ከስታትስቲክስ ኤጀንሲ።
ስጋ? ለዓመት በዓል ከተገኘ!
የገጠር ነዋሪዎች አመጋገብ እንዳልተሻሻለም፣ የበርካታ ዓመታት መረጃዎች ያሳያሉ። ከአገሪቱ የከብቶች ብዛት ጋር ሲነፃፀር፣ የገጠር ነዋሪዎች ለእርድ የሚያውሏቸው የከብቶች ብዛት፣ 1% አይሞሉም። ለእርድ ከሚውሉ ፍየሎችና በጎች ይልቅ፣ በየአመቱ በበሽታ የሚሞቱት በእጥፍ ይበዛሉ።
እንቁላል? በዓመት አንድ እንቁላል!
ሌላው ቀርቶ፣ እንቁላል እንኳ ብርቅ ነው። ጠቅላላውን የእንቁላል ምርት፣ ገበያ አውጥተው ሳይሸጡ፣ ራሳቸው ቢመገቡት እንኳ፣ በአማካይ ለአንድ የገጠር ነዋሪ፣ በአመት ከአንድ እንቁላል በላይ አይደርሰውም።እነዚህ መረጃዎች በሙሉ፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በየዓመቱ በሚያወጣቸው የተለያዩ ሪፖርቶች ላይ የተገለፁ መረጃዎች ናቸው። ታዲያ፣ አስደናቂው የእህል ምርት እድገት፣ ከእነዚህ መረጃዎች ጋር አይጋጭም? በእርግጥ፣ በእንስሳት ምርት ላይ ምንም እድገት አልተመዘገበም ማለት፣ በእህል ምርት ላይም እድገት ሊፈጠር አይችልም ማለት አይደለም ይላል መንግስት። ለዚህም ይመስላል፤ ሰሞኑን “የእንስሳት እና የአሳ ልማት ሚኒስቴር” ለብቻው እንዲቋቋም የተደረገው።
(“አሳ… እንስሳ አይደለም እንዴ?” የሚል የእግረመንገድ ጥያቄ ብናነሳስ! ለነገሩ፣ ይሄ የመስሪያ ቤቶች አሰያየም፣ ቅጣምባሩ እየጠፋበት መጥቷል። ‘ሥም ካልረዘመ፣ ቁም ነገር የደከመ’ ይሆናል የተባለ ይመስል፣ ‘እና’ የሚል ማስረዘሚያ መጨመር በዝቷል። የጤና ሚኒስቴር፣ ብሎ በአጭሩ ከመግለፅ ይልቅ… የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር… ትንሽ ቆይቶ ደግሞ፣ የጤና ጥበቃ፣ የበሽታ መከላከልና የህክምና አገልግሎት ሚኒስቴር ተብሎ፣ ሥሙ እንዲረዝምለት ይደረግ ይሆናል። Ministery of Health አይደል የሚባለው? ሌላው ደግሞ፣ የእንግሊዝኛ ቃላት ብዛት! ‘ሚኒስቴር’ የሚለው ስያሜ ሳይቆጠር ማለቴ ነው። ፐብሊክ ሰርቪስ… ይህንን በትክክል የሚገልፅ አጭር የአማርኛ አገላለፅ ስላልተገኘ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እሺ፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴርስ? … የግንባታ ሚኒስቴር ሊሉት ይችሉ ነበር።)
ለማንኛውም፣ የእንሰሳትና የአሳ ሃብት ልማት ሚኒስቴርን፣ በአጭሩ የእንስሳት ልማት ሚኒስቴር ሊባል ይችላል። እንደ መንግስት ገለፃ ከሆነ፣ በእህል ምርት ላይ የታየው እድገት፣ እውነተኛ እድገት ነው። በእንስሳት ምርት ላይ፣ ተመሳሳይ እድገት እንዲፈጠር ነው፤ አዲስ የእንሰሳት ልማት ሚኒስቴር የተቋቋመው ብሏል መንግስት።
ሊሆን ይችላል። መንግስት እንደገለፀው፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ በየአመቱ በሪፖርቶቹ እንደዘረዘረው፣ የእህል ምርት ባለፉት አስር ዓመታት በእጥፍ አድጎ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ መረጃዎቹ መፈተሽ አለባቸው። ለዚህም ነው፣ ከሌሎች መረጃዎች ጋር ይጋጫል በሚል፣ የመጀመሪያውን ጥያቄ ያነሳሁት።
በአንድ በኩል፣ ‘መደበኛ ስህተት’ ይከሰታል። የመረጃ አሰባሰብና አተናተን፣ ሙያዊ መመዘኛዎችን ሁሉ ቢያሟላ እንኳ ስህተቶች እንደሚፈጠሩ ይታወቃል። ግን፣ ሳይንሱ፣ ለዚህም መፍትሄ አለው። መፍትሄውን፣ የስህተቱን መጠን መጠቆም ነው (Standard Error ይሉታል)። ለምሳሌ፣ ኤጀንሴው የአምናው የአገሪቱ የእህል ምርት፣ 236 ሚ. ኩንታል እንደሆነ ሲገልፅ፣ ከዚሁ ጋር አብሮ ‘መደበኛውን ስህተት’ ጠቁሟል። ብሳሳት ብሳሳት፣ ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል አይበልጥም ብሏል ኤጀንሲው። በሌላ አነጋገር፣ በእርግጠኛነት ምርቱ መጠን፣ ከ231 ሚ. ኩንታል አያንስም፤ ከ241 ሚ. ኩንታል አይበልጥም” እንደማለት ነው። “በእርግጠኛነት” የምትለዋን አገላለፅ ልብ ብላችኋታል? በቃ፣ “መደበኛው ስህተት”፣ መፍትሄ አገኘ ማለት ነው።
ግን፣ ሌሎች የስህተት አይነቶች አሉ – የሙያ መመዘኛዎችን ባለማሟላት ምክንያት የሚፈጠሩ ስህተቶች። ለእህል ምርት የሚውለው የመሬት ስፋት ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት ምን ያህል አስቸጋሪና አወዛጋቢ እንደነበር ሰምታችሁ ይሆናል። ዘጠኝ ሚሊዮን ሄክታር ነው? ወይስ አስር ሚሊዮን ሄክታር? ይሄን በትክክል አለማወቅ፣ በእህል ምርት ግምት ላይ ከፍተኛ ልዩነት ያስከትላል – የ23 ሚ. ኩንታል ልዩነት። በዚያ ላይ፣ ዝርዝር መረጃ እንዲሰበስቡ የተመደቡ ሰራተኞች፣ ባለማወቅ ወይም በዳተኝነት የሚፈፅሙት ብዙ ስህተት ይኖራል።
የገጠሩ፣ ዳገትና ቁልቁለቱን እየወጡና እየወረዱ፣ ከአርባ ሺህ የገበሬ ቤተሰቦች መረጃ የሚሰበስቡ፣ የማሳ ስፋት የሚመትሩ ከሦስት ሺ በላይ ሰራተኞች የሚፈፅሙት ስህተት፣ ምን ያህል ችግር እንደሚፈጥር አስቡት። የአንዱ ሰራተኛ አንዲት ስህተት፣ ትንሽ ልትመስል ትችላለች። ነገር ግን፣ የኋላ ኋላ፣ የመጨረሻው ሪፖርት ላይ፣ በሦስት መቶ የተባዛ ስህተት ነው የምናገኘው። እንዴት መሰላችሁ? መግቢያ ትኬት የገዙ ሦስት መቶ ደንበኞች የተስተናገዱበት ፊልም ቤትን አስቡ። የመግቢያ ትኬት ዋጋ፣ ሃያ ብር ነው? ወይስ ሰላሳ ብር? ይህንን ለማረጋገጥ ከሰነፍን፣ ስህተቷ፣ የአስር ብር ስህተት ልትመስለን ትችላለች። ነገር ግን፣ ፊልም ቤቱ፣ ከትኬት ሽያጭ ምን ያህል ገቢ እንዳገኘ ስናሰላ ግን፣ ልዩነቱ ይሰፋል – በ6ሺ ብር እና በ9ሺ ብር።
“የአስር ብር ልዩነት ናት” ብለን በዳተኝነት የናቅናት ስህተት፣ የኋላ ኋላ “የሶስት ሺ ብር” ስህተት ልታስከትል ትችላለች። በእነዚህና በሌሎች በርካታ ችግሮች፣ የተከበበ ነው፣ መረጃ የማሰባሰብና የመተንተን ሙያ። ያው፣ በባለሙያ መረጣ፣ በስልጠና፣ በክትትል፣… ለቁጥጥርና ለማመሳከር በሚያመች አሰራር … ወዘተ፣ ችግሮችን ለማስወገድ መጣጣር የግድ ነው። ግን፣ ነገሩ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ከኋላቀር ባህልና ከስልጣኔ ባህልም ጋር የተቆራኘ ጉዳይ ነው። ከኋላቀር ባህል ዋና ዋና ባህርያት መካከል አንዱ፣ “ለመረጃ ብዙም ክብር እና ትኩረት ያለመስጠት ዝንባሌ” ነው።
ምን ማለቴ ነው? ‘ለመረጃ’ (ለእውነታ፣ ለእውቀት… ለሳይንስ) ብዙም ክብር በሌለበት ኋላቀር አገር ውስጥ፣ በአጭር ስልጠና ወይም ተቆጣጣሪ በመመደብ፣ ሁነኛ መፍትሄ ይገኛል ብሎ መገመት፣ አላዋቂነት ነው። ቢሆንም፣… ለዘለቄታው፣ ከድንዛዜ ነቅተን፣ ሳይንስን የሚያከብር ስልጡን ባህል ለማዳበር ካልጣርን በቀር፣ አስተማማኝ መፍትሄ እንደማናገኝ ባያጠራጥርም፤ እስከዚያው፣ ለጊዜው… አጫጭሮቹን ስልጣናዎችንም ሆነ የክትትልና የጥንቃቄ አሰራሮችን… እንደምንም ለመጠቀም መጣጣር ያስፈልጋል። ሙሉ ለሙሉ፣ አስተማማኝ ውጤት ባያስገኝም፤ ስህተቶችን ለመቀነስ ይረዳል። ያው፣… ከኋላቀር ባህል የሚመነጩ እነዚህ ስህተቶችን ሳንዘነጋ ነው፤ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ልዩ ልዩ ሪፖርቶችን ማገናዘብ የሚኖርብን።
እንዲያም ሆኖ፣ በየጊዜው አዳዲስ ስህተቶችን እስካልፈጠረ ድረስ፣ በየዓመቱ የሚያወጣቸው ሪፖርቶች ለንፅፅር ጠቃሚ ናቸው። አንደኛ፣ ለንፅፅር ስንጠቀምባቸው፣ የየአመቱ ስህተት፣ በከፊልም ቢሆን እርስ በርስ የመጣፋት እድል አለው። ሁለተኛ፣ ሌላ ምን አማራጭ አለ? ለጊዜው፣ ከኤጀንሲው ሪፖርቶች ውጭ፣ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም – ጭፍን ስሜትና ጭፍን ግምት ይሻላል ካላልን በቀር። እናም፣ በአስር ዓመታት ውስጥ፣ የእህል ምርት በእጥፍ አድጓል የሚለውን መረጃ በመቀበል እንጀምር።
(በዓለም ደረጃ ሲታይ፣ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን አትርሱ። ግን፣ ለኢትዮጵያጵያ ግን፣ ታይቶ የማይታወቅ እድገት ነው።)
አሁን ጥያቄው፣ ‘ይሄ አስደናቂ እድገት እንዴት ሊመጣ ቻለ?’ የሚል ነው። የመቶ ሚሊዮን ኩንታል እድገት በሰባት ዓመታት ውስጥ?
ምን ተዓምር ተፈጠረ?
ከዚያ በፊት የነበሩ ዓመታትን ደግሞ ተመልከቱ። በ1988 ዓ.ም፣ የአገሪቱ የእህል ምርት 94 ሚ. ኩንታል ነበር።
የምርቱ መጠን፣ ለአመታት ከዚህ በላይ ብዙም ፈቅ አላለም። 1995 እና 96 ዓ.ም ድረስ፣ እድገት አልታየም። የእህልም ምርት፣ እዚያው ከ95 እስከ 100 ሚ. ኩንታል ገደማ ነው፣ ሲረግጥ የነበረው። የሕዝብ ቁጥር በየአመቱ ይጨምራል። ከአንድ እስከ ሁለት ሚሊዮን ሲጨምርና፤ የእህል ምርት ሲደነዝዝ ምን ማለት እንደሆነ ይገባችኋል። ድህነት እየተባባሰ ነበር ማለት ነው።
እናም፣ ድንገት በአዲሱ ሚሌኒዬም ምን ተፈጠረና ነው፣ በአስር ዓመት ውስጥ የእህል ምርት በእጥፍ መት መቶ ሚሊዮን ኩንታል የጨመረው? የእህል መጨመሩ አይደለም ጥያቄው። ባይጨምር ኖሮ፣ ቢያንስ ቢያንስ የ30 ሚሊዮን ኩንታል እህል በእርዳታ ካልተገኘ፣ ብዙዎች በረሃብ ይሞታሉ። የጭማሪው መጠን ነው አከራካሪ ሊሆን የሚችለው።
ለምን አከራካሪ ይሆናል? መስኖ ሳይስፋፋ እድገት?
እንግዲህ፣ ከ97 ወዲህ የገበሬዎች ምርታማነት በእጥፍ ከጨመረ፣ በተወሰነ ደረጃ ጥሪት የማፍራት ተጨማሪ አቅም አይፈጥርላቸውም? ለምሳሌ፣ ለእርሻ፣ ለምግብ እና ለገበያ የሚጠቅሙ የቤት እንስሳትን መግዛትና ማርባት አይጀምሩም? የእርሻ አሰራራቸውን አያሻሽሉም? ለምሳሌ በመስኖ?
ሁለቱም፣ በተግባር አልታዩም። መስኖ ቢስፋፋ ኖሮ፣ የዘንድሮው ድርቅ እጅጉን ፈታኝና አስጨናቂ ባልሆነ ነበር።
በመስኖ ሁለት ሦስቴ በዓመት ማምረት… እየተባለ ብዙ ቢወራም፣ ያን ያህልም የመሻሻልና የመስፋፋት ፍንጭ አይታይበትም። መስኖ ተስፋፍቷል ከተባለ፣ በኢትዮጵያ ገጠሮች ሳይሆን፣ በኢቢሲ ካሜራዎችና ስቱዲዮ ውስጥ መሆን አለበት። ከዚያ ውጪ፣ በገበሬዎች እርሻ ላይ፣ ከአስር ዓመት በፊትም ወደ 170ሺ ገደማ ሄክታር ብቻ ነበር በመስኖ የሚለማው። የጫት ማሳዎች ላይ 20ሺ ሄክታር ጭማሪ የመስኖ እርሻ ከመታየቱ በቀር፣ ለውጥ አልመጣም። የአምናው የመስኖ ልማት፣ 190ሺ ሄክታር ገደማ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ሌሎች ጥንታዊ የእርሻ አሰራሮችም አልተለወጡም።
በሬ፣ ካልተከራዩ ችግር ነው።
እርሻ፣ እንደጥንቱ በበሬ የሚታረስ መሆኑ አይደለም ችግሩ። በበሬ ማረስም አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። ጥንድ በሬ ካላቸው ገበሬዎች ይልቅም፣ ምንም በሬ የሌላቸው ገበሬዎች ይበዛሉ።
ከአምስት ዓመት በፊት፣ በአገሪቱ ገጠሮች የነበሩት የገበሬ ቤተሰቦች ወደ 13 ሚሊዮን ገደማ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 5 ሚሊዮን ያህሉ ቤተሰቦች፣ አንድም በሬ አልነበራቸውም።
ዛሬስ?
በቅርቡ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ ከጠቅላላ 15 ሚሊዮን ገደማ የገበሬ ቤተሰቦች መካከል፣ ሁለት በሬ ወይም ከዚያ በላይ ያላቸው፣ አምስት ሚሊዮን አይሞሉም። ምንም በሬ የሌላቸው ደግሞ፣ ስድስት ተኩል ሚሊዮን። በበሬ ማረስ፣ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም ማለት ነው።
ወደ እንሰሳት ሃብት እናምራ።
ከአስር ዓመት በፊት፣ በ97ዓ.ም፣ ከመቶ የገጠር ቤተሰቦች፣ ሃያዎቹ ቤተሰቦች በሬም ሆነ ላም አልነበራቸውም። ዛሬስ? ዛሬም ተመሳሳይ ነው። በ2007 ዓ.ም፣ ከመቶ የገጠር ቤተሰቦች መካከል፣ 23ቱ ቤተሰቦች፣ በሬና ላም የላቸው። በአጠቃላይ፣ ግማሽ ያህሉ የገበሬ ቤተሰብ፣ ወይ ምንም ከብት የለውም፤ አልያም ከአንድና ከሁለት በላይ ከብት የለውም።ምናልባት፣ የእነዚህ ገበሬዎች ኑሮ ባይሻሻልም፣ የሌሎች ታታሪ ገበሬዎች ኑሮ በፍጥነት እየተሻሻለ ቢሆንስ? ደግሞም፣ ኑሮ የሚለካው፣ በከብቶች ቁጥር ላይሆን ይችላል። የጠወለጉና የደከሙ፣ ደርዘን ከብቶችን ከማንጋጋት፣ አንድ ጥጃ በማደለብና፣ አንዲት በወተት የምታንበሸብሽ ላም በመንከባከብ፣ የበለጠ ገቢ ሊገኝ ይችላል።
ማደለብ? ማደለብ… የሚባለው እንኳ እንርሳው። አብዛኛው ገበሬ (ማለትም ከ99% በላይ የሚሆነው ገበሬ)… ከብት የሚያረባው፣ አንድም የእርሻ በሬ ለማግኘት ነው። አልያም ለወተት ሲል ነው። ይሄ ባለፉት አስር አመታት ቅንጣት ታህል ለውጥ እንዳልታየበት፣ በየአመቱ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርቶች ይመሰክራሉ። በ1997 እና በ2007 መካከል ምንም ልዩነት የለም። የሚደልቡ ከብቶች፣ 1% እንኳ አይሆኑም።
እሺ። ወተትስ?
የወተት ምርትም ቅንጣት አልተሻሻለም የሚል መልስ እናገኛለን – ከኤጀንሲው ሪፖርቶች። በሁለት አቅጣጫ ልናየው እንችላለን።
በአማካይ ለአንድ የገጠር ነዋሪ ምን ያህል ወተት ይደርሰዋል? በዘጠኝ ቀን አንድ ሊትር ወተት። ይሄ አልተለወጠም። በአስር አመታት ውስጥ።
ከአንዲት ላም ምን ያህል ወተት ያገኛሉ? ብለን መጠየቅም እንችላለን። በ97 ዓ.ም እና በ2007 ዓ.ም መካከል ብዙም ልዩነት የለውም። ትንሽ ቀንሷል። ግን በጣም ተቀራራቢ ነው። በቀን አንድ ሊትር ተኩል አይሞላም – ከአንዲት ላም የሚገኘው የወተት መጠን።
በአጭሩ፣ የእርሻ በሬ ችግር፣ አልተቃለለም። የወተት ምርትም አልተሻሻለም።
ምናልባት፣ ገበሬዎች “የፕሮቲን” ፍጆታቸውን ከፍ እያደረጉ ከሆነስ?
ማለቴ፣ ስጋ መብላት ካዘወተረ ማለቴ ነው። ለማድረግ ነ ስለጨመረ ቢሆንስ?
በ97 ዓ.ም፣ የገጠር ነዋሪዎች፣ ሶስት መቶ ሺ ገደማ ከብቶችን ለእርድ አውለዋል። በአመት፣ አንድ በሬ ለ200 ሰዎች እንደማለት ነው። በ2007 ዓ.ምስ? ያው ተመሳሳይ ነው። ለሁለት መቶ ሰዎች፣ በአመት አንድ በሬ! ለአርባ ቤተሰብ፣ በአመት የአንድ በሬ ቅርጫ እንደማለት ነው። ይህም በአስር አመታት ውስጥ አልተሻሻለም።
በግና ፍየልስ? በአማካይ ከሰባት ቤተሰቦች መካከል አንዱ ብቻ ነው፣ በአመት በግ ወይም ፍየል የማረድ አቅም የነበረው። በ2007 ደግሞ፣ ከስድስት ቤተሰቦች መካከል፣ በግ ወይም ፍየል የማረድ አቅም ያለው፣ አንዱ ቤተሰብ ነው።
ያው፣ ገበሬዎች ሥጋ መብላት አልጀመሩም። የ“ፕሮቲን” ፍጆታ፣ ብዙም አልተለወጠም። በዶሮ እና በእንቁላል ካላካካሰው በስተቀር!
አሳዛኙ ነገር፣ ግማሽ ያህሉ የገጠር ቤተሰብ፣ ዶሮ አያረባም። ምናልባት፣ የዶሮ በሽታ እያስቸገረው ይሆናል። የዶሮ እርባታ፣ በእውቀት ካልሆነ በቀር አያዋጣም።ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደሚለው ከሆነ፣ ካቻምና፣ 80 ሚሊዮን ጫጩቶች ተፈልፍለዋል። ግን 50 ሚሊዮን ያህል ዶሮዎች ደግሞ ሞተዋል። አምና፣ 90ሚ. ጫጩቶች ተፈልፍለዋል። ግን፣ 60ሚ. ዶሮዎች ሞተዋል።
ለዚህም ሳይሆን አይቀርም፤ ባለፉት አስር አመታት፣ የእንቁላል ምርት ምንም አልጨመረም። የገጠሩ የሕዝብ ብዛት፣ በ15 ሚሊዮን ጨምሯል – ወደ 80 ሚሊዮን ገደማ። በአመት የሚገኘው የእንቁላል ምርት ግን 100 ሚሊዮን ገደማ ላይ ቆሟል። ከገበያ የተረፈ እንቁላል፣ ለአንድ ሰው በአመት አንድ እንቁላል ላይደርሰው ይችላል።
ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ቤተሰቦች፣ የአንድ በሬ ባለቤት ናቸው። ለማረስ፣ በተውሶ ወይም በኪራይ አንድ በሬ ማሟላት ይኖርባቸዋል። ሁለት በሬ ወይም ከዚያ በላይ ያላቸው የገጠር ቤተሰቦች፣ ወደ 4 ሚሊዮን ገደማ ነበሩ – የዛሬ አምስት አመት።

ኃይሌ ገብረመድህን ዓለሙ የተባለ በጎንደር ከተማ የቀበሌ 18 ነዋሪ ግለሰብ ዓጠራጣሪ በሆነ ሁኔታ ተገደለ፥


ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ ም ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ዓካባቢ በሚኖርበት ቀበሌ ከጓደኛው ጋር ባመሹበት የተገደለው እውቅ ባለጸጋ ገበሬ፥ በሰሜን ጎንደር በተለይም በዓርማጭሆና በጠገዴ ወረዳዎች በመልካምነቱ ከፍ ያለ ዝናን ያተረፈ፥ በብዙዎች የተከበረ ደህና ጎበዝ እንደነበረ በሰፊው ይነገራል፥ ኃይሌ ገብረመድህን ዓለሙ ነብስ ይማር!
በተለይም ባለፈው ዓመት ተቀስቅሶ በነበረው የክልል ዓንድና የክልል ሶስት የድንበር ውዝግብ ላይ፥ ዓካባቢውን ወክለው ከሕዝብ ጎን በመቆም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ካደረጉ የሰሜን ጎንደር ተወላጆች ጋር ስሙ ይጠራ እንደነበር ይታወቃል፥እሄን የድንበር ግርግር ተከትሎ በማህበረሰቡ ያገኘው ተደማጭነትና ተወዳጅነቱ በወያኔዎች ጥርስ እንዳስነከሰበት በዋናነት ይጠቀሳል፥ በብዙ የወገን ተቆርቋሪ ኢትዮጵያን ላይ ሲፈጸም የኖረው የሞት እጣ ደርሶበት፥ ዛሬ እሄን ጀግና ገበሬ፣ የዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የግፍ ሰለባ ዓድርጎታል፥
ይህ ዓይን ያወጣ በዓደባባይ የተፈጸመ የግድያ ወንጀል፥ የክልሉ የምክር ቤት ዓባል ወንድም እጂ ይፈጸም እንጂ ግድያው ላይ ዓብረው የነበሩት የምክር ቤት ዓባል፥ ዓቶ ቻሌ ዓለሙ እራሳቸው ከጓዶቻቸው ጋር በመሆን ያደረጉት የተቀነባበረ ወያኒያዊ ተግባር መሆኑን የሚያሳብቁ ብዙ መረጃዎች እየተጠቀሱ ነው፥ ወጣቱ ገበሬ ዓቶ ኃይሌ፥ ዓገሩንና ሕዝቡን የሚወድ፥ ለተበደለ ሰው ተቆርቋሪ፥ ለተቸገረ ወገን ደራሽ፥ የተጣላ ዓስታራቂ፥ ዋስ ጠበቃ የሚሆንና፥ በሕብረተሰቡ ተወዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ወደ ዓርባ ዓመት የሚጠጋና የሶስት ታዳጊ ልጆች ዓባት መሆኑም ተገልጿል፥ኃይሌ ገብረመድህን ዓለሙ / Haile Gebremedhin Alemu
ለግድያ የሚያደርስ ምንም ምክንያት በሌለበት የመዝናኛ ቤት ውስጥ፥ የተቀነባበረ እርምጃ በሚመስል መልኩ ባለተጠበቀ ሁኔታ የተፈጸመውን ግድያ፥ በቅርበት የታዘቡ የዓካባቢው ነዋሪዎችና፥ የዓቶ ኃይሌን ማንነት ለሚያውቁ ሁሉ፥ በዚህ ወንጀል ላይ የመንግሥት እጂ ያለበት ያስመስለዋል ሲሉ ግምታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፥ ብቻውን ሳይሆን 8 እራሱን ገብቶ ነፍስ ያጠፋው፥ ገዳይ ማንነት ቢታወቅም በብዙ ሰዎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ዓሰቃቂ ወንጀል ፈጽሞ ያለምንም ጠያቂ መኪናውን ዓስነስቶ ማምለጡና፥ በሰዓቱ የዓካባው መብራት እንዲጠፋ መደረጉ፥ከገዳዩ ጋር ዓብረውት የነበሩ ግለሰቦች በጥይት ተመቶ የወደቀውን ቁስለኛ ለመርዳት ምንም ሳይሞክሩ ጨለማን ተገን ዓድርገው መሸሸታቸው፥ የገዥውን ሥርዓት ዓራማጅ ማንነታቸውና፥ ከገዳይ ጋር ያላቸው የዝምድና ትስስር ሲጨመርበት፥ ዓጥምደው እንዳጠፉት ጥርጣሬውን ዓጠናክሮታል፥ ዓብሮት ከነበረው የምክር ቤት ዓባል ወንድሙ ጋር፥ ለማምለጫ የተጠቀሙባት የገዳይ መኪና መለያ ሰሌዳዋ ተነቅሎ ጎንደር ዓየር ማረፊያ ቆማ መገኘቷ ደግሞ ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ያደርገዋል፥የዓቶ ኃይሌ ነፍስ በእጇ ላይ ማለፉን ዘግየት ብላ በስፍራው ከደረሰችው የሟች ሚስት የተረዱ፥ በዓካባቢው የነበሩ ሰዎች በሰዓቱ የጸጥታ ዓስከባሪ ፖሊስ ወይም ወደ ህክምና የሚወስድ ሌላ ዓካል ደርሶለት ቢሆን ኖሮ ሕይቱ ሊተርፍ ይችል እንደነበረ ዓስተያየታቸውን ይሰጣሉ፥

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግብጽና የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን አስጠነቀቁ


ግብጽና ኢትዮጵያ ሊዋጉ ነው እንዴ? ይሄ መግለጫ አላማረኝም
“በሰላም የመኖር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ግብጽ የተለያየ መስርያ ስለገዛች በመሳርያ ኃይል ኢትዮጵያን አታንበረክክም:: ነው እንጂ ግብጽን አንፈራም:: ግብጽ ጠቅላላ አገር ምድሩን መሳርያ ማድረግ ትችላለች ከፈለገች:: የሚዋጋው ግን መሳርያ አይደለም:: እኛም ራሳችንን የመከላከል መብት አለን:: እንከላከላለንም” ኃይለማርያም ደሳለኝ
“ግብጽ ከካይሮ ተነስታ ኢትዮጵያን አታጠቃም:: እኩይ ዓላማ ያላቸው ጎረቤቶቻችን ለዚህ አላማ ድጋፍ ከሰጡ ግን እናስጠነቅቃለን:: ጣታቸውን ካንቀሳቀሱ አስቀድመን እንጨርሳቸዋለን” ኃይለማርያም ደሳለኝ
ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲህ አይነት መራር መግለጫ ሲሰጡ ብዙም አይሰሙም:: ዛሬ ግን ግብጽንም ለግብጽ ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ የኢትዮጵያን ጎረቤቶች መራር ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::
“አስቀድመን እንጨርሳቸዋለን” እስከማለት የደረሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብጽንም አልማሯትም:: ” ግብጽ አገር ምድሩን መሳርያ ብታደርገው መሳርያ ብቻውን አይዋጋም” እስከማለት ያደረሳቸው ምን ይሆን?
የኢትዮጵያ ደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ሰው የሆኑትን አቶ ጌታቸው አሰፋም ያለወትሯቸው እዚህ አሜሪካ መሆናቸው ተወስቷል::ኢሳትንም ከራሺያ ሳተላይት ለማውረድ ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እንዳካሄደች ኢሳት ዘግቧል:: በተመሳሳይ ዜናም ኢትዮጵያ ሰራዊት ምልመላ መጀመሯ ተዘግቧል::
ስምንትና ዘጠኝ ሚሊዮን ሰው በረሃብ ውስጥ ባለበት ሰዓት የወቅቱ ዜና ረሀቡና እርዳታ መሆን ሲገባው ይሄን ጦርነት መሰል መግለጫ በዚህ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒትሩ የሰጡት ምን ችግር ቢኖር ይሆን?

ነአምን ዘለቀ አርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ ነው አሉ


“የኤርትራ መንግስት ከራሷ ጋር የታረቀች ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት ይፈልጋል”
“ሁሉንም ፖለቲካ ሃይሎች ያካተተ የሽግግር ሂደት ይኖራል”
“የወደብ ጥያቄን በተመለከተም ወደፊት በድርድር/በሰጥቶ መቀበል የሚፈታ ይሆናል እንጂ አሁን የትግሉ አጀንዳ መሆን የለበትም”
“የመረጃ ትንሽ የለውም… መረጃ አይናቅም”
(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ ትናንት ማምሻውን ለአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ የተደረገው ዝግጅት በታሪካዊነቱ እንደሚቀመጥ የሚኒሶታ ነዋሪዎች አስታወቁ:: በሚኒሶታ ታሪክ ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት በአንድ ቀን 78 ሺህ ዶላር በላይ ሲሰበሰብ የትናንቱ የመጀመሪያው ነበር::
ከ200 በላይ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተሰባሰቡበት በዚሁ ታሪካዊ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ነአምን ዘለቀ እና ወጣት ሚካኤል ከላስቬጋስ ነበሩ:: ይህ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት የተከፈተው የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ከአስመራ በቭዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ነበር::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመልዕክታቸው እየተደረገ ያለው ትግል አንድን አምባገነን ጥሎ ሌላ አምባገንን ለመተካት ሳይሆን የተሻለች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት እንደሆነ አስምረውበታል:: ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም በኢትዮጵያ አንድነት በመተማመን በመነጋገር ላይ መሆናቸውን እና ጥሩ ነገር እንደሚሰማም የገለጹት ፕሮፌሰሩ በቶሎ ትግሉ እንደሚጀመር አስታውቀዋል::
በዕለቱ በአዳራሹ በክብር እንግድነት የተገኙት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ ባሰሙት ንግግር “አርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ ነው” ብለዋል:: ይህን ሲያብራሩም “የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋናዩም ተመልካቹም ሕዝቡ ነው:: ንቅናቄው ዘረኝነትን በተንገሸገሸ – እኩልነት; ፍትህ እና ሰላም በተጠማው የኢትዮጵያ ተማሪ… ወጣት… ገበሬ.. ሴት… ወንድ ውስጥ ያለ ሕዝባዊ ትግል ነው:: ይህም ማለት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ንቅናቄው አለ ማለት ነው:: ይህ መንፈስ ሥር እየሰደደ ሄዷል:: አሁን ባለው ዘረኛው ስርዓት ብዙዎች ተገድለዋል… በግፍ ታስረዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተንገላተዋል:: እነዚህ ሁሉ ሚሊዮኖች በውስጣቸው የአርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ አላቸው::”
አቶ ነአምን ንግግራቸውን ቀጥለው “የወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ በግፍ ብዙዎችን ከመሬታቸው ፎቅ ካልሰራችሁ እየተባሉ እንዲገፉ አድርጓል:: ቦታቸው ተቸብችቧል:: እነዚህ ዜጎች መሥእረታዊ የዜግነት መብታቸውን ተነጥቀዋል:: በጋምቤላ በደቡብ እየተደረገ ያለው ይኸው ነው:: የዘር ማጥፋት እየደረሰባቸው ነው:: እነዚህ የወያኔ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻቸን ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ናቸው:: ብዙ ኢትዮጵያውያን ካለፍርድ በ እስር ይማቅቃሉ:: ፍርደ ገምድሉ ሥር ዓት በፍትህ ላይ ቀልደዋል:: በነዚህ ሚሊዮኖች ውስጥ ሁሉ የአርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ አለ” ብለዋል::
“በኮንትሮባንድና በዘረፋ የተሰማሮ 90% የሕወሓት ጀነራሎች እና መኮንኖች ሃብታም በሆኑበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ… አርበኞች ግንቦት 7 አለ:: ሠራዊቱ በከንቱ የወያኔ ጣልቃ ገብነትና ወረራ ደማቸው ደመከልብ ለመሆን ችሏል:: ይህ ሠራዊት እኩልነትን የተጠማ ሠራዊት ነው::” በማለት አሁን ስላለው የሕወሓት/ኢሕ አዴግ ሠራዊት ስለሚደርስበት የዘር መድልዎ የጠቀሱት አቶ ነአምን የትግሉ መዳረሻ የት ነው? በሚለው ንግግራቸው አርበኞች ግንቦት 7 መዳረሻ ዴሞክራሲያዊ ሥር ዓት መገንባት እንደሆነ ገልጸዋል:: አሁን ያለው ሥርዓትም በኃይል የወጣ የመጨረሻው አምባገነን ሥርዓአት ይሆናል ብለዋል::
“ሁሉንም ፖለቲካ ሃይሎች ያካተተ የሽግግር ሂደት ይኖራል:: ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር ቁጭ ብለን የምንነጋገርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም” ያሉት አቶ ነአምን በ3ኛ ደረጃ ስለ ኤርትራ መንግስት አብራርተዋል::
“የኤርትራ መንግስት ከራሷ ጋር የታረቀች ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት ይፈልጋል:: እንድትበታተን ይሰራል ብለን አናምንም:: ኢትዮጵያን የማዳከም ስልት ወይም ፖሊሲ ኤርትራ አላት ብለን አናምንም:: በጣም ጤናማ ስኬታማ ኢትዮጵያ እንድትኖር የኤርትራ መንግስት እንደሚፈልግ ነው የምናውቀው” በማለት የተናገሩት አቶ ነአምን አርበኞች ግንቦት 7 ከኤርትራ መንግስት ጋር ኢትዮጵያን በሚመለከት ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች; በወደብ ጥያቄ ለመደራደር ምንም ዓይነት ስልጣን እንደሌለው እንዲሰመርበት እፈልጋለሁ ብለዋል::
“የወደብ ጥያቄን በተመለከተም ወደፊት በድርድር/በሰጥቶ መቀበል የሚፈታ ይሆናል እንጂ አሁን የትግሉ አጀንዳ መሆን የለበትም” ያሉት አቶ ነአምን በ4ኛ ደረጃ በውጭ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ ይህ የነፃነት ትግል ምን እንደሚጠብቅ አብራርተዋል:: በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህን ትግል በዲፕሎማሲው; በቁሳቁስ እና በገንዘብ ሊደግፍ እንደሚገባ ያስታወቁት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ “በውጭ ያለው ኃይል በየከተማው ያሉትን ሴናተሮችን እና ኮንገረሶችን ስለኢትዮጵያ መንግስት ጥፋቶች ሊነግሩ ይገባል:: በየከተማው ባሉ ሚዲያዎች እየወጡ በመጻፍና በመናገር የዲፖሎማሲው አካል በመሆን ትግሉን ማገዝ ይገባቸዋል:: የህክምና ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችም እንዲሁ በመድሃኒት አቅርቦት ላይ ብዙ ይጠበቅባቸዋል” ያሉት አቶ ነአምን አርበኞች ግንቦት 7 ጠላትን በተመለከተ ትልቅ የመረጃ ማሰባሰቢያ ኔትወርክ እንዳለው ጠቁመው ሁሉም ኢትዮጵያዊ መረጃዎችን ለድርጅቱ በተዘራጋው መዋቅር በኩል እንዲያስተላለፍ ጠይቀዋል:: “የመረጃ ትንሽ የለውም… መረጃ አይናቅም” ያሉት አቶ ነአምን በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ በስር ዓቱ ላይ እስካሁን እያሳየ ያለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት እንዲቀጥል አበክረው ጠይቀዋል::
ከነመሪዎቹ አስመራ ለሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 መርጃ የተደረገው ጨረታ ላይ የግንባሩ ሴት ታጋዮች ምስል ቀርቦ 20 ዶላር ከተሸጠ በኋላ ወደ ጥያቄና መልስ ተገብቷል::
ፖስትሮድ የሚገኙ የኤርፖርት ታክሲ ሾፌሮች 10 ሺህ ዶላር አዋጥተው ሰጥተዋል::
በስፍራው “የፈራ ይመለስ” የሚል ቲሸርትና ህፃናትን ሳይቀር ያሳተፈ የገንዘብ ልገዛ ለግንባሩ ተደርጓል::
ከተሰብሳቢውም በአሁኑ ወቅት የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሃይማኖቶች ውስጥ ጣልቃ በመግባት በተለይ ተሃድሶ የሚባል ነገር በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በመፍጠር ሕዝቡን ለማለያየት አውቆ እየሠራ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 እንዴት እንደሚመለከተው; ሞላ አስገዶም የትህዴን ሠራዊቱን ይዞ ወደ ወያኔ ሲገባ ከግንባሩ በቂ ምላሽ አልተሰጠም የሚል; አቶ ነአምን በቭኦኤ ላይ ቀርበው ስለአሜሪካዊ ዜግነት እንዳላቸው ሲጠየቁ ለምን መመለስ እንዳልፈለጉና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል::
አቶ ነአምን አሁንም የአሜሪካዊ ዜጋ ስለመሆናቸውና ስላለመሆናቸው መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸዋል:: ይልቁንም በቅርብ ጊዜ የሕወሓት አስተዳደር “የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ስለሆኑ እንከሳቸዋለን” ማለቱን ጠቅሰው “ይምጣና ይሞክረን:: እንደውም ክስ ቢመሰርቱብን ጥሩ ነው:: በክሱ ሂደት ምን ዓይነት ወንጀሎችን እንደሰሩ እናሳያቸዋለን” ብለዋል:: አቶ ነአምን አክለውም የሰሞኑ የወያኔ ድንፋታ የአሜሪካንን ሕግ ካለማወቅ የመጣ መሆኑን አስምረውበታል::
በሞላ አስገዶም ዙሪያ ለሕወሓት መንግስት በቂ የሆነ ምላሽ አልተሰጠበትም ለሚለው ጥያቄም “በቂ ምላሽ ስለሰጠንበት እኮ ነው ዛሬ ይህን ሁሉ አዳራሽ ሙሉ ሰው ያያችሁት” ሲሉ መልሰዋል::
የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ በተለይም የአቶ ነአምን ዘለቀ ንግግርን ማንኛውም ጋዜጠኛ እንዳይቀርጽ መከልከሉ ተሰብሳቢውን አሳዝኗል:: በተለይ አርበኞች ግንቦት 7 ለመናገር ነፃነት እታገላለሁ የሚል ድርጅት በመሆኑ እንዲህ ያለው የጋዜጠኛ ክልከላ ገና ከጅምሩ እንዲህ ከሆነ የወደፊቱ ያሳስበናል የሚሉ አስተያየቶችም ተደምጠዋል:: በአጠቃላይ ግን አርበኞች ግንቦት 7 በሚኒሶታ የተሳካ ገቢ ማሰባሰብ ማድረጉን በሙሉ አፍ መመስከር ይቻላል::