Friday, April 1, 2016

አምስተኛ ወሩን ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀረው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው


በየካቲት ወር በሂርና የተደረገ ተቃውሞ
ከተጀመረ አምስተኛ ወሩን ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀረው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞ በአንዳንድ ከተሞች በሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ከትናንት በስቲያ፣ ትናንትና ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማና ደባዩ በተባለ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት እንዲሁም በበደሌ ከተማና በኢሉአባቦር ለሊሳ ሃሮ ቶሬ በተባለች የገጠር ቀበሌ ተማሪዎች እንደታሠሩና በአስለቃሽ ጭስ ምክንያት፤ ሆስፒታል እንደገቡ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ፖሊስ እና የከተማ መስተዳድሩ ኃላፊዎች መረጃው የተሳሳት እንደኾነ በተለይ በቢሾፍቱ ምንም እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በኢሉአባቦር ዞን ለሊሳ ሃሮ ቶሬ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት የተወረወረ አስለቃሽ ጭስ አለመኖሩን ገልጸው “ተጎድተው ሆስፒታል የገቡት አንድ ስድስት ተማሪዎች የፖሊስ ዱላ ሲያዩ በድንጋጤ ተረጋግጠው ነው” ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment