Friday, April 15, 2016

በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…


በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…
ችግሩ በርትቶ ትምህርት እስከ መዝጋት የደረሱ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ቀደም ሲል በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው የፈተና ሰሌዳ መሰረት አያስፈትኑም ተብሏል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የህዝብ ተወካዮች ዛሬ ላነሱላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡
ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት እና ረብሻ ተማሪዎች ተሳታፊ ነበሩ፣ የስነ ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ለመሆኑ ምን ፈይደዋል ሲሉ ሚንስትሩን ጠይቀዋል፡፡
አንድ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ትምህርቱ መወቀስ የለበትም የሚል ምላሽ የሰጡት አቶ ሽፈራው ተማሪዎቻችን ጥያቄ ማንሳታቸው እና መሞገታቸው ስህተት የለበትምብለዋል፡፡
በመላው ሀገሪቱ 40 ሺ ትምህርት ቤቶች አሉን የሚሉት አቶ ሽፈራው ሁከትና አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረው በኦሮሚያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ብቻ ነበር ብለዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 13 ትምሀርት ቤቶች ትምህርት ለማቋረጥ ተገድደዋል ብለዋል፡፡
ተማሪዎቻችን መስታወት እንኳን አለሰበሩም፣ ድንጋይም አልወረወሩም፣ ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ ነው ያቀረቡት ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ትምህርታቸውን ተረጋግተው ላልተማሩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የብሄራዊ ፈተና መውሰጃ ጊዜው ይራዘማል ተብሏል፡፡
ከክልሎቹ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment