Monday, April 4, 2016

ሥጋ ላኪዎች ወደ ሳዑዲ መላክ የነበረበት ሥጋ ሳይላክ በመዘግየቱ አየር መንገዱ ካሳ እንዲከፍል ጠየቁ ::


ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መላክ የነበረበት ሥጋ እስከ ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ሳይላክ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ማቀዝቀዣ ውስጥ በመቆየቱ ምክንያት፣ ላኪዎች ለደረሰባቸው ኪሳራ አየር መንገዱ ካሳ እንዲከፍላቸው ጠየቁ፡፡ አየር መንገዱ በበኩሉ ሥጋው ሳይላክ የቆየው በወቅቱ ባጋጠመው የካርጎ አውሮፕላን እጥረት መሆኑን አስታውቋል፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው ላኪዎች እንደገለጹት፣ ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ይጠበቅ የነበረው ሥጋ ከመላኪያው ቀን በመዘግየቱ በደንበኞቻቸው ዘንድ የብልሽትና የጥራት ጥያቄ ከማስነሳት አልፎ ለከባድ ጉዳት እንዳያጋልጣቸው ሥጋት አድሮባቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment