በድርቁ ምክንያት ከሰቆጣ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ውስጥ የሰፈሩ ከ250 አስከ 300 የሚሆኑ ዜጎች በዛሬው እለት በደብረ ብርሃኑ መስተዳድር ወደመጡበት አደሚመለሱ ተነግሯቸዋል።
ስደተኞቹ ወደ መጡበት ከተመለሱ ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው የሚጠብቃቸው ሞት እንደሆነ በመግለፅ ለወገን የድረሱልን ጥሪ አስተላልፈዋል።
የደብረ ብርሃን ህዝብ ስደተኞቹን በአቅሙ ለመርዳት የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን በወያኔ መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ በስደተኞቹ ላይ በተላለፈው ኢ-ሰብአዊ ውሳኔ ክፉኛ ልቡ መሰበሩን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ሞት ለተፈረደባቸው ርሃብተኛ ወገኖች ድምፅ በመሆን በነፍስ እንዲደርስላቸው ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

No comments:
Post a Comment