Friday, April 8, 2016

86 ዳኞች ያስገቡት የስራ መልቀቂያ ታገደ


48 አቃቢያነ ህግ እና 86 ዳኞች የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ሲታወቅ፣ የክልሉ ባለስልጣናት የመልቀቂያ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የግድ ትሠራላችሁ መባለቸው ተጠቆመ። የህግ ባለሙያዎቹ ከስራ ለመልቀቅ የወሠኑበት ምክንያት 1ኛ የዳኝነት ነጻነት ሥለሌለ 2ኛ ዳኞች በህግ መሠረት በነጻነት ለመሥራት ሥላልቻሉና በካድሬዎች መታዘዝ ስለመረራቸው 3ኛ የዳኝነት ነጻነታችን ተነጥቀን የፖሊስ የበላይነት የሚያረጋግጥ ሥርአት ስለነገሰ 4ኛ ዳኞች የወሠኑት ውሣኔ ህጉ በሚፈቅደው በይግባኝ እንዲታይ እንደማድረግ ወይም ስልጣን በሠጠው አካል እርምጃ እንደመውሠድ አሊያም ጥፋት ካጠፋ በፍርድ ቤት እንደመቅጣት ፈንታ ጉዳዩ በማይመለከታቸው የቀበሌ ሠዎች ጭምር ነጻነታቸው ስለሚነጠቅ ..ወዘተ ምክንያቶች የመልቀቂያ ጥያቄ ለማስገባት መገደዳቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል።
(አስገደ ገ/ስላሴ)

No comments:

Post a Comment