
የዛሬ አመስት አመመታት አካባቢ ነበር ህወሃታዊያን በአለቃቸዉ ድንገተኛ ፖለቲካዊ አካሄድ ምክንያት አባይን እንገነባለን ብለዉ የተነሱት ቅሉ አባይን ከመገደቡ ጀርባ የነበረዉ የተለያየ ምክንያታዊ አመለካከትና ዉሳኔ ከግልና ከቡድን ጥቅም አንጻር የተንጸባረቀ እንደነበር ብዙሃን ተናግረዋል ዛሬ ላይ ቆመን ስንመለከት ከመከላከያ ሰራዊት አንጻር በጥቂቱ የቦንድ ገንዘብ አሰባሰቡና አበላዊ ወጪዉ ምን እንደሚመስል የደረሰን መረጃን ተገን በማድረግ አስቀምጠናል። የአባይ ግድብ መሰረት ከተጣለ የዛሬ አምስት አመት ወዲህ በግድቡ ዙሪያ ላይ አራት የሻለቃ ጦሮችን በማዋቀር ወያኔ ወታደራዊ ካሞፑን በስፍራዉ ገናባ በለመደዉ የለብለብ ወታደራዊ ስልት የስድስት ወራት ብቻ የመኮንነት ስልጠናዎችን በመስጠት ከትግራይ ክልል የሆኑ አመራሮችን ብቻ በየሻለቃዉ አዛዥነት እንዲሾሙ በማድረግ 1. ምክትል ኮማንደር ጌታቸዉ ኪሮስ የህዳሴ ግድብ ዲቪዥን ዋና አዛዥ 2. ኮማንደር ሐየሎም የዲቪዥን ምክትል ዋና አዛዥ 3. ኮማንደር ሐይሌ መሐሪ የሁለተኛ ሻለቃ ዲዚዥን ዋና አዛዥ እያለ በመዉረድ እስከ ዝቅተተኛዉ ማእረግ ድረስ የአንድ ብሄር አባላት ብቻ ሙሉ ስልጣኑን እንዲቆናጠጡ አደረገ። በተያያዥነት ባስቀመጥነዉ የቦንድ ክፍያ መረጃ መሰረት አንድ የመከላከያ አባል አንድ ሺ.. (1.000) ቦንድ እንዲከፍል ይገደዳል ክፍያዉን የጨረሰ አባል ከታች የምትመለከቱትን ሰርተፍኬት ብቻ ይወስዳል በአባይ ግድብ ዙሪያ የተሰማሩት የመከላከያ አባላት አመራሮች እና የሻለቃ መምሪያዉ ከመከላከያ በጀት ዉጪ አብዛኛዉ ወጪ የሚሸፈነዉ በግድቡ ስም በሚሰበሰብ ወጪ ነዉ። ወታደራዊ አመራሮቹ የዉሎ አበል፣ የጉዞ አበል፣ ወርክሾፖችና ተጨማሪ የስልጠናዎች አበል እንዲሁም ልዩ ወጪዎችን ባጠቃላይ ከዚሁ የሚጠቀሙ ሲሆን የትራንስፖርት የነዳጅና የመሳሰሉት ሁሉ በአንድነት የግድቡ ወጪ አካል ናቸዉ። በተዘዋዋሪ መንገድ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሔሮች በምንም መልኩ ተጠቃሚ ያልሆኑበት ወታደራዊ የአጠቃቀም ስልት ለአንድ ብሔር ብቻ እንዲዉል ተደርጓል! እየተደረገም ነዉ! በመሆኑም የተቀሩት ኢትዮጵያዊያን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በገዛ ሐገራቸዉ ላይ የመስራትና የመኖር እንዲሁም ተጋሪ መብትና ጥቅም እኩል የማግኘት ህልዉናቸዉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተገፈፈ ነዉ። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! ! ( ጉድሽ ወያኔ )
No comments:
Post a Comment