Saturday, April 30, 2016

ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ እየሞከረ ነው


የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል ትግል አይንበረከክም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካም ሆነ የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉት ተባብረው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ሲያሳርፉ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት በከፍተኛ ደስታ ነው የተቀበሉት።
አንዳንዶች አርበኛውን በገንዘብ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ከወዲሁ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ በወያኔ ጎራ በኩል ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምንም የተሰማ ነገር የለም። ጥያቄው… ለወትሮው ትንሽ ትልቁን “የግንቦት 7” አባል ነው ብሎ በመፈረጅ ንጹሃንን እስርቤት የሚወረውረው ወያኔ በይፋ ስለተከፈተበት ጦርነት ለምን ዝምታን መረጠ? ነው።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ሥርዓት ህዝብ እጅግ እንደጠላውና ሆ ብሎ ሊነሳበት እንዳቆበቆበ ይረዳል። ስለዚህም ጉዳዩ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖ የህዝብ መነጋገሪያ እንዲሆን አይፈልግም። ያ ሆነ ማለት የተዳፈነው ፍም እሳት ፊቱ ላይ ተረጨ ማለት ነው።
ለዚህም ይመስላል በአርበኞች ግንቦት 7 የተሰነዘረበትን ጥቃት ለማብረድ ድምጹን አጥፍቶ መውተርተርን የመረጠው።
ሌላው ተጨማሪ ማስረጃ ደግሞ ወያኔ በአርበኞች ግንቦት 7 የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከት ወደ አካባቢው እያሰማራ ያለው የጦር ክፍል ከአንድ ጎሳ የውጡና ቀደም ሲል በጡረታ ተሰናብተው ወያኔ ከወልቃይት ህዝብ ላይ ነጥቆ በሰጣቸው ለም መሬቶች ላይ የግብርና ስራ እያካሄዱ የሚገኙ የቀድሞ የህወሃት አባላት መሆናቸው ነው።

የአውስትራሊያና የካናዳ መንግስታት ዜጎቻቸው ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አሳሰቡ


የአውስትራሊያ መንግስት የዛሬ 15 ቀን በጋምቤላ ክልል ከ208 ሰዎች በላይ መገደላቸውንና 108 ህጻናትና ሴቶች መጠለፋቸውን ተከትሎ፣ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማሳሰቢያ አወጣ። የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስትር በመግለጫው እንዳመለከተው፣ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ለማድረግ እቅድ ያላቸው አውስትራሊያውያን ለጉዞ ከመዘጋጀታቸው በፊት የጉዞውን አስፈላጊነት መመርመር እንደሚገባቸው ገልጿል።
የአልሻባብ አሸባሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የመንግስት ህንጻዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎችና የውጭ ዜጎች በሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰውም የአውስትራሊያ መንግስት የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ መግለጫ አስታውቋል።
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በማንኛውም ሰዓት ሊደርስ የሚችለውን የሽብርተኝነት ጥቃት በመገንዘብ የአውስትራሊያ ዜጎች ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማሳሰቡ በዚሁ ትናንት በወጣው ማሳሰቢያ ላይ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል ሲደረግ የቆየው ተቃውሞ በማንኛውም ሰዓት ሊያገረሽ ስለሚችልና በአካባቢውም አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ባለመኖሩ አውስትራላውያን ወደኦሮሚያ ክልልና አካባቢው እንዳይጓዙ በማሳሰብ፣ ዜጎቹ ተቃውሞ ወደሚካሄድባቸው ስፍራዎች እንዳይጓዙ የአውስትራሊያ መንግስት የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ መግለጫ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም በሚደረጉ ታላላቅ ስብሰባዎችን ዜጎቹ እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ የሚጓዙበት አካባቢ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ማረጋገጫ ካላገኙ አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።
በተለይም በአዲስ አበባ የመርካቶ አካባቢ፣ የሱማሌ ክልልና ድንበር አካባቢዎች፣ የኤርትራና ሱዳን ድንበር አካባቢዎች፣ የኬንያና የደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢዎች፣ የጋምቤላ፣ በአፋር ክልሎች፣ የጸጥታ ችግር ያለባቸው በመሆናቸው ዜጎቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች እንዳይጓዙ የአውስትራሊያ መንግስት የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የካናዳ መንግስት በኤርትራ፣ በሱማሌ፣በኬንያ፣ በሱዳና ደቡብ ሱዳን የድንበር አካባቢዎች ዜጎቹ እንዳይጓዙ ጠቅሶ፣በጋምቤላ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በአምቦ አካባቢም ዜጎቹ እንዳይጓዙ አሳስቧል።

የስራ ማቆም አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቁ የደሴ መምህራን እየተዋከቡ ነው ።


ሚያዚያ 14፣ 2008 ዓም የደሴ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አጠቃላይ 3ኛ ጉባኤ ተደርጓል። በስብሰባው ላይ የ33 ትምህርት ቤቶች የመሰረታዊ መምህራን ማህበር አመራሮች፣ የደሴ ከተማ ብአዴን ተወካይ፣ የትምህርት መምሪያ ሃላፊና የደህንነት ሰዎች ተገኝተዋል። የስብሰባው አጀንዳ የመምህራን ማህበር አመራሮችን ምርጫ ለማካሄድ ቢሆንም፣ ስብሰባው እንደተጀመረ መምህራን አሁን ስብሰባ ለማካሄድ አንችልም የሚል ተቃውሞ አሰምተዋል። የመምህራን መሰረታዊ ማህበራት አመራሮች ፣ “እኛ ከዚህ በሁዋላ ምርጫ አንፈልግም፣ ኢህአዴግ 25 አመታትን ገዝቷል፣ በቃው፣ ለውጥ አላየንም፣ ልማትና እድገት የለም፣ እኛ በረሃብ እየተሰቃየን ነው ፣ ማህበራችንን ማዋቀር አንፈልግም፣ ከፖለቲካ ነጻ አይደለም” ያሉ ሲሆን፣በተለይ መምህራን የትምህርት ጥራት እናስጠብቃለን እያልን ባለንበት ወቅት ትምህራታቸውን ያላጠናቀቁ መምህራን እየተመደቡ ዜጎቻችንን እያበላሹ በመሆኑ፣ ይህንንም እየተቃወምን ስለሆነ ህገመንግስታዊ መብታችንን ለማስጠበቅ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደምናደርግ እናሳውቃለን ብለዋል። መምህራኑ ተቃውሞአቸውን ካቀረቡ በሁዋላ፣ በታዛቢነት የተገኙት የብአዴን ተወካይ፣ የትምህርት መምሪያ፣ የትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊና ካድሬዎች የመምህሩን መብት በማፈንና በማስፈራራት ስብሰባውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ለማስኬድ ጥረዋል። ባለስልጣናቱ ከፉከራ የዘለለ የምታመጡት የለም እንዳሉዋቸው የሚናገሩት መምህራን፣ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የስራ ማቆም አድማ ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ከስብሰባው በሁዋላ አንድ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርግ በመግለጽ ጽሁፍ ማቅረቡንም መምህራን ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም በደሴ የጸጥታ ሃይሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተመድበው ቅኝት በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ መምህራን ከኑኖረና ከአስተዳደር በደል ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆኑ፣ መንግስት የጥያቄው መግፋት እያሳሰበው መምጣቱን ተከትሎ በቅርቡ ለመምህራን የቤትና የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያመቻች ገልጿል።
Daniel Mulatu's photo.

Friday, April 29, 2016

የወያኔ መንግስት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ ለማሳፈን ለደቡብ ሱዳን መንግስት 39.5 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉ ተነገረ


የቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የጋምቤላ ጭፍጨፋን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ። የጭፍጨፋውን ሂደት በማዛባት፣ የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በመገደዳቸውና ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ሰለነሳቸው ፕሬዚደንትነታቸውን ጥለው ድንበር አቋርጠው መሸሻቸውን በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
ከሰኔ ወር 1978 ጀምሮ በነርስነት የመንግስት ስራ መጀመራቸው፣ በኋላም እስከ ክልል ፕሬዚደንትነት በዘለቀው አገልግሎት 18 ዓመታት መቆየታቸውን ያስረዱትና የ8 ልጆች አባት መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኦኬሎ አኳይ የዛሬ 15 ዓመት በጋምቤላ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የተፈጸሙ ድርጊቶችን ለችሎቱ ዘርዝረዋል።
ታህሳት 5 ቀን 1996 ዓም በጋምቤላ የህወሃት ታጋይ በነበሩት ሻለቃ ጸጋዬ መሪነት የተንቀሳቀሰው የሃገር መከላከያ ሰራዊት 424 የአኝዋክ ወንዶችን ለይቶ መግደሉ በስም በዕድሜ በዖታና በአድራሻ ተለይቶ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከመሰራጨቱ በፊት የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ዶ/ር ገብረዓብ ባርናባስ ዕለቱን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ግጭቱ የአኝዋክና ኑዌር ነው ማለታቸውን አቶ ኦኬሎ በጽሁፋቸው አስታውሰዋል።
በርሳቸው በኩል በማግስቱ ታህሳስ 6 ለጀርመን ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት ግጭቱ የአኝዋክና ኑዌር አይደለም በማለት ማስተባበላቸውን ገልጸዋል።
ሆኖም የወቅቱ ጠ/ሚኒስትር የነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በጋምቤላ ም/ቤት ውስጥ በተደረገ ግምገማ ጭፍጨፋው የአኝዋክና የኑዌር ግጭት ተብሎ እንዲገለፅ ግፊት ሲደረግ አሻፈረኝ በማለታቸው፣ ስብሰባው እርሳቸው በሌሉበት በኢትዮጵያ ሆቴል መካሄዱን በጽሁፋቸው አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው ስብሰባ የሟቾቹ ቁጥር 60 ተብሎ እንዲጠቀስ ከጾታም አንጻር 59 ወንድና አንዲት ሴት መሆናቸውን እንዲገለጽ ስምምነት መደረሱን ዘርዝረዋል።
የወቅቱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር እና የህወሃት መስራች በነበሩት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘጋጀውን ይህንን የውሳኔ ሃሳብ እንዲፈርሙ፣ ካልፈረሙ ከፕሬዚደንትንነት ወርደው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው በስብሰባው ላይ ከነበር የኑዌር ተወላጅ መረጃ ሲደርሳቸው፣ ሃገር ጥለው መጥፋታቸውን ዘርዝረዋል።
ግድያው በተፈጸመ በ24ኛው ቀን ታህሳስ 29 ይህ ውሳኔ ሲተላለፍባቸው፣ በማግስቱ ጠዋት ታህሳስ 30/1996 በድንበር አቋርጠው መውጣታቸውን ከጽሁፋቸው መረዳት ተችሏል።
ወደስደት ካመሩ በኋላ ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ስለነሳቸው በጋምቤላ ለሚፈጸመው በደል ስለተሰማቸው የመብት ትግል ለማድረግ መነሳታቸውን፣ ሆኖም የመገንጠል አላማ አለማራመዳቸውን ጠቅሰዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት በ23 ሚሊዮን ዶላር ጁባ ላይ ለኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይል እንደሸጣቸውም በጽሁፋቸው ዘርዝረዋል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት ዕርሳቸውን ለማሰርና ለመወንጀል 39.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን አብራርተዋል።
“የኢህአዴግ አባል እንዲሁም የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች አባል ሆኜ አላውቅም፣ እንደ አቶ መለስ ዜናዊም የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ አይደለሁም፣ የእነሱ ፕሬዚደንትነትም ሆነ ሚኒስትርነት አያጓጓኝም” ያሉት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ይልቅ አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍ/ቤት እንደሚፈለጉ አብራርተዋል። ወንጀለኞቹ ያሉዋቸውም በስም ዘርዝረው አብረዋቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። “መለስ ዜናዊና ግብረ-አበሮቻቸው ኡምድ ኦባንግ፣ ጸጋዬ በየነ፣ ገብረዓብ ባርናባስ፣ አባይ ጸሃየ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣ አባዱላ ገመዳ፣ አልማው አላምረው እና ታደሰ ሃይለስላሴ” አለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍ/ቤት ሊቀርቡ እንደሚገባ ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
ከ10 ዓመታት በላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ማምራታቸውን ተከትሎ ከሁለት አመት በፊት በደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት አቶ ኦኬሎ አኳይ፣ የተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ውድቅ ቢሆንም፣ ጋምቤላን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ተንቀሳቅሰዋል በሚል በዚህ ሳምንት የ9 አመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ርሳቸው ለፍርድ ቤት በቀረቡት ጽሁፍ ኣንዲሁም፣ በማስረጃነት ባያያዙት ሰነድ በኢትዮጵያ አንድነት ከምያምኑ ድርጅቱ ጋር ትብብር ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከድርጅት አባልነት መባረራቸውን በመግለጽ፣ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ለቀረበላቸው ክስ ድርጊቱን አምነው ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ማድረግ ወንጀል

ሰበር መረጃ…. ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የነጻነት ሀይሎችን ተቀላቀሉ!


የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የመከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች የደረሳቸዉን መረጃ ተገን በማድረግ 11.250 ( አስራ አንድ ሺ ሁለት መቶ ሐምሳ ) የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በ5 ወራት ጊዜ ዉስጥ ከየመን ከሱዳናና ከሊቢያ ወደ ኤርትራ በመጓዝ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅለዋል!!
ይላል… በሶስቱም ሐገራት የኢትዮጵያ ኢንባሲዎች ላይ የተሰመየዉ የመረጃ ቃል አቀባይ።
ምንጫችን እንደጠቀሱት የወያኔ ባለስልጣናት ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ወድቀዋል! 
በተለይም የመንና ሊቢያ የሚገኙ ብዛት ያላቸዉ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰን በግፈኛዉ አጋዚ ከምንገደልና የወያኔ የግፍ እስር ቤቶች ዉስጥ ከምንማቅቅ ብሎም ማእበል ከሚበላን በረሐ ሄደን መስዋትነት በመክፈል ሐገራችን ነጻ ብናወጣ እንመርጣለን በሚል ዉሳኔ! ከሊቢያዋ ቶብሩክ ( TOBRUK ) እና አካባቢዉ በመነሳት የሐኒሽ ደሴቶችን በጀልባ በማቋረጥና የሱዳንን ድንበር በመጣስ ወደ አርበኞቹ ተቀላቅለዋል ።
ወታደራዊ ደህንነቱ ከፈተኛ ስጋት ላይ ከመዉደቁ የተነሳ ለሐገር መከላከያ ያቀረበዉን መረጃዎች ተንተርሶ የመንና ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሐገር ቤት የመመለሱ ስራ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ተወስኖ ወያኔያዊያን ባለስልጣን ያስመረሩትን ወጣት ትዉልድ ለማታታለልና ወደ ሐገር ለመመለስ የትራንስፖርት ወጪዎችንና የጉዞ ሰነድ ዝግጅቶችን በመበጅት ስራ ላይ ተጠምደዋ።
ይህን በተመለከተ ከአርበኞች ግንቦት 7 ወይም ከሌሎች የነጻነት ሐይሎች የተገኘ ፍንጭ ባይኖርም ከትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን በኩል ግን እዉነታዉን የሚያረጋግጡ ድርጊቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
 

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲሱ ትውልድ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲጠብቅና የታሪክ ህፀፆችን እንዲያርም ጥሪ አቀረበ


የኢትዮጵያ አንድነት የመጠበቅና የታሪክ ህፀፆችን ማረም ከአዲሱ ዘመንት ዲሞራቶች ይጠበቃል ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ። ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ የዘንድሮ ግንቦት 20” በሚል ርዕስ ሰሞኑን ከወህኒ ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ፅሁፍ ኢህአዴግ ወደስልጣን የመጣበትን 25ኛ አመት በማስመልከት ያለፉትን 50 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።
በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ የነበረው የሃይል አሰላለፍ እንዲሁም በህብረ-ብሄርና በብሄር ፓርቲዎች መካክል የነበረውን ልዩነት በመዘርዘር ለኢትዮጵያ ችግር ዘላቂ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ አቅርቧል።
“ተማሪዎች እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ ከ55 ዓመታት በኋላም የዮሃንስና የምኒሊክ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ የፈጠረው ሽኩቻ የኢህአዴግ ቅኝት ጸረ-ዲሞክራሲ እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት ግብዓቶች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሲያጠቃልልም “የታሪክ ጣጣ የኦሮሞና የሶማሌ ብሄርተኞችን ነፍስ ዕረፍት እየነሳ ነው፥ የታሪክ ህፀጾች የማይቀበሉ ቀላል የማይባሉ የፖለቲካ ሃይሎችም አሉ፥ ይህ ሁሉ ተደማምሮ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው፣ መፍትሄውም ከአዲሱ ዘመን ዲሞክራቶች ይጠበቃል” በማለት ለሃገሪቱ ችግር ዕውነተኛና ዘላቂ መፍትሄ እንደሚጠበቅ ጥሪ አቅርቧል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመስከረም ወር 2004 ጀምሮ በአሸባሪነት ተከሶ በወህኒ ቤት የሚገኝ ሲሆን፣ የ18 ዓመታት እስር እንደተፈረደበት ይታወቃል። ክሱም ሆነ ፍርዱ እውነትም ሆነ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ለማመልከት ወይንም በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰሩን ለማስረዳት በጽሁፉ ግርጌ “የህሊና እስረኞች” ሲል አስፍሯል።
 

Wednesday, April 27, 2016

ሰበር ዜና ወያኔ የሚመራዉ የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ወታደራዊ ደህንነት በትናንትናዉ እለት ከ900 በላይ ወታደሮች ማጣቱን ለጠ/መከላከያ አሳዉቋል።


በዚሁ መረጃ መሰረት ወታደራዊ ደህንነቱ እንዳሳወቀዉ የሰሜኑ እዝ ዘመቻ መምሪያ እና ስምሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ አስተላለፍ የላቸዉም! የወታደራዊ ፖለቲካ መምሪያዎችም በንቃትና በወቅታዊ ሁኔታዎዎች ከተጻራሪዎች አንሰዉ ተገኝተዋል! ሰራዊቱ የመዋጋት መንፈሱ ደካማ ነዉ! መግባባትና መከባበር በዉስጡ ጠፍቷል! የጎሳ መናጎጡ በእጅጉ እየከረረ በመምጣቱ አደጋ ላይ ነን
በተለይ በሰራዊቱ ዘንድ አስደንጋጭ ተብሎ የተወሰደዉ ከሰሞኑ በተደረጉ ዉጊያዎች ከተጻራሪ ሐይሎች የተኩስ እሩምታ የሰሙ ገበሬዎች ከኍላችን እየመቱን መሐል ላይ አጣብቂኝ ዉስጥ እየገባን ነዉ ሰራዊታችን ወደ ፊትና ወደ ኋላ መዋጋት ተስኖት እጁን እየሰጠ ሲሆን ከጀርባ የሚደበድቡን የራሳችን ሰራዊቶች ናቸዉ በማለት እርስ በእርሱ እስከመሞሻለቅ ደርሷል በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች በሰሞኑ ብቻ በተደረጉ ጥቃቶች 900 ያህል ወታደሮች ተሰዉረዋል ሲል ብሶቱን አስተላልፏል።
ድል ለኢትዮ ጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ
 

ሰበር መረጃ… በስነ ምግባር ጉድለት ከአርበኞች ግንቦት 7 የተባረሩ ግለሰቦች በስለላ ላይ


የዉድ ሐገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊነት መደፈርና የህዝቦቿ መብት መገፈፍ አስቆጥቶት ዱር ቤቴ ያለዉ ጀግናዉ የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት ያስተጋባዉን የክተት አዋጅ ተነተርሶ በእዉነተኛ የሐገር ፍቅርና አለኝታነት ተንሳስተዉ በርካቶች የድርጅቱን ጥሪ በመቀበል ትግሉን ተቀላቅለዋል።
በመሆኑም ዛሬ ድርጅቱ በሁለት እግሩ የቆመ የህዝብ አለኝታና ተስፋነቱን በመላዉ ሐግሀራችን አድማስ ላይ ሲያሰፋና ሲያንጸባርቅ እጅግ ኢምንቶች ደግሞ በስነ ምግባር እና በዘቀጠ አስተሳሰባቸዉ ወደ ፊት ሊራመዱ የማይችሉ እንዲሁም የትግሉ እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችሉ የተረጋገጠባቸዉ ግለሰቦች በአርበኞች ግንቦት 7 ዲሞክራሲያዊ አሰራር መሰረት በሰላም ከትግል ስፍራ እንደተሰናበቱ ከሶስት አመታት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ መግለጫዎች ለመረዳት ተችሏል።
በመሆኑም ከእነዚህ ኢምንቶች መካከል ቴድሮስ ስዩም የተባለዉ ግለሰብ ከትግሉ ሜዳ ከተሰናበተበት ወቅት አንስቶ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድንን መረጃ ቢሮ በማገልገል ላይ ይገኛል ቴድሮስ ስዩም የትግራይ ብሔር ተወላጅ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ በወንዶች ጸጉር የማስተካከል ስራ ይተዳደር የነበረ ግለሰብ ነበር።
ቴድሮዝ ስዩም በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ዱባይ እና ቻይና በመላለስ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል ዋና አላማዉ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኢትዮጵያ፣ እንዲሁም ከተለያየ ሐገራት እየተዘዋወሩ የሚነግዱ ግለሰቦችን በተለይም ዱር ቤቴ የከተቱትን ጀግኖች ይረዳሉ የተባሉ ግለሰቦችን ማሳደድ እና ማንነታቸዉን ወደ ወያኔ ብሔራዊ መረጃ ማሳለፍ ነዉ።
በመሆኑም ማንኛዉም ሐገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህን ግለሰብ በአንክሮ እንዲመለከተዉ ስንል እናሳስባስለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
Gudish Weyane's photo.

ቅዳሜና ዕሁድ በጋምቤላ ከተማ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተካሄደ በኋላ መንግስት መጠነ ሰፊ የአፈሳ እርምጃ እየወሰደ ነው።


ቅዳሜና ዕሁድ በጋምቤላ ከተማ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተካሄደ በኋላ መንግስት መጠነ ሰፊ የአፈሳ እርምጃ እየወሰደ ነው። ዛሬ ጋምቤላ ከተማ ቤት ለቤት አሰሳ ሲደረግ ነው የዋለው። ሆቴሎች መደብሮች ተበርብረዋል። በከተማዋ የሰው እንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎበታል። በየመንገዱ መታወቂያ የሚጠይቁ ፌደራል ፖሊሶች ነዋሪውን ሲያንገላቱት፡ ወጣት ከሆነ ሲደበድቡት እንደነበረ እማኞች ገልጸዋል። ”በኦሮሚያ ተቃውሞ ያልተሳካላቸው ጸጉረ ልውጦች ገብተዋል” በሚል ፍተሻው ከፍተኛ እንደነበረ ያነጋገርናቸው አስታውቀዋል። ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን በጋምቤላ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ ማስጣል ያልቻለ ፌደራል ፖሊስ፡ ገዳዮቹ ላይ አንድም እርምጃ ሲወስድ ያልታየ መንግስት፡ በሟች ወገኖች ላይ ጡንቻው ፈርጥሞ ታየ – ጋምቤላ ላይ።

Tuesday, April 26, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በመተማ የወያኔ ሰራዊት ላይ ጉዳት አደረስኩ አለ

ከማክሰኞ ዕለቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃት በኋላ የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኛ ወታደሮች ተሞልቶ ሲቪሎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የሆስፒታሉ ምንጮቻችን እንደገለፁት እስከ ትናንትና ድረስ ከ40 በላይ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና የቁስለኞች ቁጥር ቢያንስ በየአንድ ሰዓት ልዩነት እየጨመረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አንድ የሸዲ ነዋሪ ከየቦታው የተለቃቀሙ ከ26 በላይ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከቱን መስክሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት ጦር ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ 36 አውቶብስ ሙሉ ፌደራል ፖሊስ በመተማና በዙሪያዋ ተራግፏል፡፡

የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት በመተማ የወያኔ ሰራዊት ላይ ጉዳት አደረስኩ አለ

የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት መተማ አካባቢ በአንድ ግንባር ላይ ብቻ በህወሓት ጦር ኃይል ላይ በፈፀመው ጥቃት የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና በርካታ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
====================================================
ከማክሰኞ ዕለቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃት በኋላ የሸዲ ሆስፒታል በቁስለኛ ወታደሮች ተሞልቶ ሲቪሎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የሆስፒታሉ ምንጮቻችን እንደገለፁት እስከ ትናንትና ድረስ ከ40 በላይ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና የቁስለኞች ቁጥር ቢያንስ በየአንድ ሰዓት ልዩነት እየጨመረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አንድ የሸዲ ነዋሪ ከየቦታው የተለቃቀሙ ከ26 በላይ አስከሬኖች ሲቀበሩ መመልከቱን መስክሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት ጦር ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ 36 አውቶብስ ሙሉ ፌደራል ፖሊስ በመተማና በዙሪያዋ ተራግፏል፡፡

Sunday, April 24, 2016

ከ30 በላይ ህገወጥ ተቋራጮች የ40/60 መርሃግብር ቤቶችን እየገነቡ ነው


መረጃ እንደሚያሳየው፥ በቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሳይመዘገቡ እና ማጣሪያ ሳይወስዱ ሰባት ተቋራጮች አሁን ግንባታ ላይ ናቸው።
— በኢንተርፕራይዙ ተመዝግበው ማጣሪያው ላይ ያልተሳተፉ 12 ተቋራጮች በመርሃ ግብሩ ቤቶች እየገነቡ ነው።
— የቴክኒክ ብቃታቸው ዜሮ ነው የተባሉ አምስት ተቋራጮች ደግሞ እዚሁ ስራ ላይ አሉ።
— ሙሉ በሙሉ ስልጠና ያልወሰዱ ሁለት፣ የሀሰት ፍቃድ ያላቸው ስምንት ተቋራጮች በጥቅሉ 34 ተቋራጮች በህገ ወጥ መንገድ ገብተው የ40/60 ቤቶችን በመገንባት ላይ ናቸው።
በመርሃ ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ህገወጥ ተቋራጮች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያድግ እንደሚችል ነው የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይሉ ቀንአ የገለጹት።
ተቋራጮች ወደ ስራ እንዴት ነው የሚገቡት?
አዲስ አበባ በ40/60 መርሃ ግብር ከ38 ሺህ በላይ ቤቶች እየተገነቡባት ነው።
እነዚህን ቤቶች የሚገነቡ ከ100 በላይ ተቋራጮች ደግሞ አሁን በስራ ላይ ናቸው።
ይህንን ሰራ የሚያከናውኑ ተቋራጮች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ቢሮ በማምራት ይመዘገባሉ፤ ከዚያም ስልጠና ይወስዱና ይገመገማሉ።
ግምገማው አቅማቸውንና ህጋዊነታቸውን የሚመለከት ሲሆን ፥ ማጣሪያውን ያለፉ ተቋራጮች ወደ ስራ ይገባሉ።
ህጋዊው አሰራር ይህ ሆኖ ሳለ በመስሪያ ቤቱ ባልደረቦችና በደላሎች አማካኝነት ድርድር ይቀርብልናል ይላሉ አስተያየታቸውን የሰጡን ተቋራጮች።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ፥ በቤት ልማት ፕሮግራሙ ላይ የተቋራጮች የስራ ስምሪት በጨረታ ሳይሆን ቁርጥ ዋጋ ተቀምጦላቸው በደረጃቸው መሰረት ነው የሚከናወነው ብለዋል።
በ40/60 መርሃ ግብርም ከደረጃ 1 እስከ 3 ያሉ የስራ ተቋራጮች ናቸው እንዲሳተፉ የሚፈቀድላቸው ያሉት ሀላፊው፥ ግልፅ የሆነ መመሪያ እና መስፈርት የሌለ መሆኑ ይህን መሰሉን ችግሩ መፍጠሩን ተናግረዋል።
ወደ ስራ የሚገቡ ተቋራጮችን መቆጣጠር በዋናነት የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሀላፊነት ነው ባይ ናቸው አቶ ይድነቃቸው።
ከ30 በላይ ህገወጥ ተቋራጮች እየተሳተፉበት ያለው የ40/60 መርሃ ግብር ከተጀመረ ሁለት አመት አልፎታል።
ኢንተርፕራይዙም እነዚህን ህገወጦች እየለየ መሆኑንና ለህግ ለማቅረብ ጥናት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
የኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይሉ ቀንአ፥ “ወደዚህ ሀላፊነት ከመጣሁ አጭር ጊዜ ነው፤ ከአሁን በፊት በነበረው አስተዳደር የተፈጠሩ ችግሮችን በማስተካከል ላይ ነኝ፤ ከሁለት አመት በላይ ለዘለቀው ችግርም መፍትሄ እያፈላለግን ነው” ብለዋል።
ለህገወጥ ተቋራጮቹ መብዛት የፈቃድ አሰጣጡ ጉድለት አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ያነሳንላቸው የከተማዋ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ዮናስ አያሌውም፥ “ቢሮው ከተቋቋመ አራት ወሩ ነው፤ ችግሩ ደግሞ ከሁለት አመት በላይ ሆኖታል” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
በተቋራጮቹ የሚገነቡ ቤቶች ጥራት ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
እነዚህ ህገወጥ ተቋራጮች በሚገነቧቸው ቤቶች ጥራትም ሆነ ፍጥነት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ የሚጠበቅ ነው።
የከተማዋ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ግን ከጥራት ጋር በተያያዘ የከፋ ጉዳት አያደርሱም ባይ ናቸው።
ለዚህም ለግንባታ የሚውሉ ግብአቶች ሙሉ በሙሉ በመንግስት የሚቀርቡ መሆናቸውን በምክንያትነት ያስቀምጣሉ።
ተቋራጩ የጉልበት እና ሙያ ስራ ብቻ ነው የሚያከናውነው፤ የክትትል እና ፍተሻ ስራ ስለሚከናወንም የጥራት ችግር አይፈጠርም ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ህገወጥ ተቋራጮቹ ተለይተው ለህግ ሊቀርቡ እንደሆነም የስራ ሀላፊዎቹ ነግረውናል።
ተቋራጮቹን በዚህ መልኩ በፕሮጀክቶቹ ላይ እንዲሳተፉ አድርጋችኋል የተባሉ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሰራተኞች እና አመራሮችም በተመሳሳይ ከሀላፊነት እንዲነሱ፣ እንዲታገዱ እና በህግ እንዲጠየቁ መደረጉንም ነው የገለጹት።

Friday, April 22, 2016

በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን መነቃነቃቸው እየተሰማ ነው!


በስዊድን በሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ የገጠመውና የውርደት ካባን የተከናነበው የሕወሓቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ትናናንት ኖርዌይ መግባቱ እየተነገረ መሆኑን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ወንጀለኛውን ግለሰብ በዓለም አደባባይ ለማዋረድ እያደኑት እንደሚገኙ ተሰምቷል። በኖርዌይ መዲና ኦስሎ የሚገኙ ታላላቅ ሆቴሎች በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተከበዋል። በጉዳዩ ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ እየሰሩ መሆኑም እየተነገረ ነው። በኦስሎ ከፍተኛ ውጥረት አለ። ግለሰቡ እንደ ዓይጥ ከጉሮኖው መሽጎ ካልወጣ በስተቀር የውርደትና የሀፍረት ካባን በኖርዌም መከናነቡ አይቀሬ ይመስላል። እንግዲህ ምን እንደሚከሰት እናያለን!

ታንዛኒያና ኬንያ በ74 ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው


በታንዛኒያ በሕገወጥ ስደተኝነት ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩ 74 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ድንበር ከተማ ታቬታ ተጥለዋል። ድርጊቱ ያስቆጣት ኬንያ “በዓለምአቀፍ ሕግ የታንዛኒያን ሸክም የምቀበልበት እዳ የለብኝም” በማለት አውግዛ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከእስር የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያን ወደ ታንዛኒያ እንደምትመልስ ገልጻለች።
ታንዛንያ እስረኞቹን ወደሀገራቸው ኢትዮጵያ ከመመለስ ይልቅ ወደ ኬንያ ወስዳ የመልቀቋ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም
(ምንጭ:- ኒውስ24)

ወህኒ ከተጋዙት ሙስሊሞች አንዱ የሆነው ኢስታዥ ኑሩ ቱርኪ፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት የግድያ ሙከራ ተደረገበት


የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው በአሸባሪነት ተወንጅለው በወህኒ ቤት ከሚገኙ ሙስሊሞች በአንዱ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ። የግድያ ሙከራውን ያደረገው በእስር ቤት ውስጥ እስረኞችን የሚከታተል ሰላይ መሆኑን የአይን ምስክሮች ለኢሳት በላኩት መረጃ አመልክተዋል።
የግድያው ሙከራው በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የተቀነባበረ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፣ ዓላማው የኮሚቴው አባላቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማስገደድ እንደሆነ ያምናሉ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ወደ ወህኒ ከተጋዙት ሙስሊሞች አንዱ የሆነው ኢስታዥ ኑሩ ቱርኪ፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት የግድያ ሙከራ የተደረገበት ሃሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓም መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል።
በህገ-ወጥ የሰው ዝውውር ተወንጅሎ የ12 ዓመታት እስራት የተፈረደበት ግለሰብ የግድያውን ሙከራ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ በአትክልት መኮትኮቻ መሳሪያ ወይንም ፋስ የኡስታዝ ኑር ቱርኪን አንገት ከመታ በኋላ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ መሬት ላይ ወድቋል። በተኛበት ሆዱ ላይ በድጋሚ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ ቢሆን፣ በደመ-ነፍስ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በመገልበጡ እንደሳተው ለኢሳት የደረሰው ዜና ያብራራል። ኢስታዝ ኑር ቱርኪ አደጋው ከደረሰበት በኋላ ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን፣ በኋላ ግን መትረፉ ከተረጋገጠ በኋላ እስረኛው ጉዳዩን በማወቁ ለህክምና ወደዝዋይ ሆስፒታል መወሰዱን ለመረዳት ተችሏል።
ወላጅ አልባ ህጻናት እንዲሁም ጧሪ የሌላቸው አረጋውያንን በመርዳት በበጎ አድራጎት ተግባሩ የሚጠቀሰው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ፣ ጥቃቱ በተቀነባበረ ሁኔታ እንደተካሄደበትም ተመልክቷል።
ዘወትር ሃሙስ የዝዋይ ማረሚያ ቤት የጽዳት ቀን በመሆኑ፣ የአትክልት መቆፈሪያና መኮትኮቻ መሳሪያዎች የሚወጡበት ቀን ተጠብቆ ድርጊቱ እስረኞች መሃል ሲፈጸም ተቃውሞ ይቀሰቅሳል በሚል የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ በህሙማን ማገገሚያ ክፍል እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ድርጊቱ መፈጸሙ ታውቋል።
ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በሳምንቱ ቀናት ከሚገኙበት ዘመዶቹ ሃሙስ ዕለት ሊጠይቁት የመጡትን ጎብኝቶ ሲመለስ በህሙማን ማገገሚያ አካባቢ አድፍጦ የጠበቀው ግለሰብ ድርጊቱን መፈጸሙን የኢሳት የዝዋይ እስር ቤት ምንጮች አብራርተዋል።
ድርጊቱን የፈጸመው የ12 ዓመታት እስራት የተፈረደበት ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ነው በማለት የወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች ከተጠያቂነት ለመሸሽ እየሞከሩ ቢሆን፣ የግድያ ሙከራ ያደረገው ግለሰብ የእዕምሮ ጤና ችግር የሌለበት፣ በእስር ቤት ውስጥ እስረኛውን ለመሰለል ከተመለመሉ አንዱ መሆኑ በእስረኞቹ ዘንድ እንደሚታወቅም ተመልክቷል። በዝዋይ ወህኔ ቤት የአእምሮ በሽተኛ እንደማይታሰር በመግለጽም፣ የወህኔ ቤቱ ሃላፊዎች ምክንያቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑም የኢሳት ምንጮች አብራርተዋል።
በኡስታዝ ኑር ቱርኪ ላይ የግድያ ሙከራው የተቀነባበረው በወህኒ ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይቅርታ እንጠይቅም በማለታቸው በግድያ ከማለቃችሁ በፊት ጠይቃችሁ ውጡ የሚል በቤተሰብና የወዳጅ ግፊት ለማስከተል እንደተቀነባበረ ተምኖበታል።
ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰረው ሙባረክ፣ የደሴ ከተማ ተወላጅ ድንገት በዚሁ ወህኒ ቤት መሞቱንም የኢሳት ምንጮች ያስታውሳሉ። በትኩሳት ህመም ላይ የነበረው ሙባረክ ለምርመራ ወደ ሃኪም ቤት ሲሄድ በሰጡት መርፌ፣ ወዲያውኑ ህይወቱ ማለፉን ተገልጿል። በእስር ቤቱ ውስጥ መርዝ ወግተው እንደገደሉት ሁኔታውን የተከታተሉት የኢሳት ምንጮች ያምናሉ።
በነፍስ ማጥፋት በዘረፋና መሰል ከባድ ወንጀል የተፈረደባቸው ግለሰቦች የወህኒ ቤት ሃላሃፊዎች እስረኛውን እንዲሰልሉ እንደመለመሏቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በእነዚህ ግለሰቦች አማካኝነት የፖለቲካ የህሊና እስረኞችን ማጥቃት ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ እየተዘወተረ መምጣቱም ታውቋል።
የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት የነበረው አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በዚህ ሁኔታ መደብደቡ ሲታወስ፣ የኦሮሞ ህዝቡ ኮንግሬስ /ኦህኮ/ አመራር የነበረው አቶ ኦልባና ሌሊሳም በተመሳሳይ ዘርፍ በታሰረ ግለሰብ ድብደባ ተፈጽሞበታል።
መንግስትን በሃይል ለመጣል ተንቀሳቅሳችኋል በሚል የዛሬ 5 አመት በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከታሰሩት ተከሳሾች ውስጥ ኮ/ል ደምሰው አንተነህ እና ኮ/ል ዓለሙ ጌትነት በጥር ወር 2007 በወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች በጥይት የተደበደቡ ሲሆን፣ በተለይ ኮ/ል ደምሰው አንተነህ የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ለቤተሰቦቻቸው ሊያመልጡ ሲሉ ነው የተተኮሰባቸው የሚል ምክንያት መስጠታቸው ይታወቃል።
Norway Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy's photo.

ወያኔ የጋምቤላዉን ጭፍጨፋ ተገን በማድረግ የከዱ ከፍተኛ የጦር አባላቶችን እያሰሰ ነዉ!!


የህወሃት መከላከያ ከፍተኛ የሰራዊት እጥረት ገጥሞታል።
በአራቱም የሐገሪቱ መእዘናት ድንበሮችን መቆጣጠር የማይታሰብ እየሆነ መጥቷል! በሰሞኑ በጋንቤላ ክልል ኢትዮጵያዊያን ላይ የተቀናበረዉን ጭፍጨፋ ወያኔ በዋና አዘጋጅነት እንደተወነዉ ምንጮች እየገለጹ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ላይ የሐገሪቷን ድንበር ለማስጠበቅ ከመካከለኛዉ እዝ ሰራዊት ለመመልመል ቢሞከርም የመካከለኛዉ እዝ ሰራዊት በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ልጆቻችን ለማጽዳት በወንጀል ላይ ይገኛል!
የምስራቅ ኮከብ የሚባል ስም የተሰጠዉ የምስራቁ እዝም እጅግ ተመናምኗል በተለይም ይህ እዝ በተተኪ ሐይሎች ምክንያት እና በሰራዊት ክዳት እጥረት ገጥሞታል!
የምእራብ እዝ የሚባለዉ ወደ ሰሜኑና ወደ ምስራቅ እዝ ክፍተቶችን ለመሙላት በብዛት በመዘዋወሩ ከፍተኛ የሰራዊት እጥረት ፈጥሯል።
ህወሃት የአየር ሐይሉን ለማመን የሚችልበት ሁኔታ እጅግ አናሳ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አሁን የጋምበላን ድንበር ተሻግሮ ለመምታት የሚያስችል አቅም በማጠሩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ከሱዳን ጋር ድርድር ተይዟል።
ድርድሩ በኑሜር ብሔረሰቦች የተጠለፉ ሕጻናት እንዲመለሱልን እንፈልጋለን ስለዚህም ይህን አሰሳ ለማድረግ ሱዳን እዉቅና ትስጠን ነዉ።
ደቡብ ሱዳን ዉስጥ የሚኖሩ ወገኖቻችንን በሰጡት መረጃ መሰረት ህጻናቱን ማግኘት የማይታሰብ ጉዳይ ነዉ ይላሉ።
ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር ጥሰዉ ይገባሉ በሚል መነሻ ሐሳብ የመከላከያ ሐይሏን ወደ ስፍራዉ አስጠግታለች! በተቃራኒዉ ግን የወያኔ ሚዲያዎች የሐሰት መረጃዎችን ተያይዘዉታል።
በተጨማሪ የወያኔ ወታደራዊ ሰላዮች የጋምቤላዉን ጭፍጨፋ ተገን በማድረግ በድርድር ሰበብ የትግራዩን ነጻ አዉጪ ቡድን ከድተዉ ሱዳን ዉስጥ ተሸሽገዋል ያላቸዉን 6 ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች እንዲሁም 11 ወታደራዊ ደህንነቶችንና 3 የፌድራል ፖሊስ አዛዦችን ማፈላለጉን የተያያዘዉ ሲሆን ነገር ግን በትናንትናዉ እለት ሁሉም በሰላም ከደቡብ ሱዳን መዉጣታቸዉን ለማወቅ ተችሏል።
ድል ለኢትይጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )
 

Wednesday, April 20, 2016

ሰበር ዜና የሱዳ ወና ከተማ ካርቱም በተቃውሞ ሰልፍ እየተናጠች ነው

የሱዳ ወና ከተማ ካርቱም በተቃውሞ ሰልፍ እየተናጠች ነው የተቃውሞ ሰልፉ መንስዔ 1ዶላር 9 ጂኔህ ነበር የሚዘረዘረው በቅስፈት 1 ዶላር 14 ጂኔ ከ50ሳኒቲም መግባቱ እና የመሳሰሉ የወጋ ግሽበቶች እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል ተቃውሞ ሰልፍ እተካሄደበቸው የሉ ቦታዎች የካርቱም የገበያ መዕከላት ናቸው ኡንዱርማን ሻቢ ፣ ሱቅ በህሪ ፣
ሱቅ ሊቢያ ፣ ሱቀል አረቢ እና ካርቱም ሸቢ ለይ ነው እኚ የጠቀስኳቸው ቦታዎች ትላልቅ የገበያ መዓከል ነቸው ልብ በሉ የ1ዶላር ምንዛሬ 9ጂኔህ የነበረው 14ጂኔህ 50ሳንቲም ለምን ገባ ብለው ነው የተቃውሙ ሰልፍ የወጡት እኛስ?

አሰቃቂው የጋምቤላ ጭፍጨፋና የፀጥታ ኃይሎች አሠላለፍ


• ራሱን ‹‹የደቡብ ሱዳን ቡድን›› በማለት የሚጠራው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂ ቡድን የደቡብ ሱዳንን ወታደራዊ ዩኒፎርም በመልበስና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በመታጠቅ መቼ እንደተነሳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይገኝም፣ ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቅዳሜ አጥቢያ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጋምቤላ ደረሰ፡፡
• ታጣቂው ኃይል ከደቡብ ሱዳን ግሬት ስቦር ግዛት ተነስቶ፣ በሁለት መንገዶች (ጆር እና ኦኛላ) 175 ኪሎ ሜትር አቋርጦ በኑዌርና በአኙዋ ዞኖች በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች ተሰማራ፡፡
• ‹‹የደቡብ ሱዳን ቡድን›› እያለ ራሱን የሚጠራው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂ ኃይል በወታደራዊ ሬዲዮ መረጃ እየተለዋወጠ በተመሳሳይ ሰዓት በከፈተው ተኩስ፣ ምናልባትም በታሪክ ዘግናኝ የሚባል ግድያ በሰው ልጆች ላይ ፈጽሞ ግዳዩን ይዞ በድል ዜማ ታጅቦ ወደመጣበት መመለሱ ተነግሯል፡፡
• ለአራት ሰዓታት በቆየው የሙርሌዎች ዘግናኝ ጭፍጨፋ 182 የኑዌር፣ የአኝዋ እንዲሁም ደገኛ ወገኖች ሕይወት፣ እንዲሁም ከሚያዚያ 7 ግድያ ቀደም ባሉት ቀናት 26 ንፁኃን የተገደሉ በመሆኑ በድምሩ የሟቾች ቁጥር 208 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
• ጋምቤላ ከእንቅልፏ ሳትነቃ በተከፈተው በዚህ የሙርሌዎች የጥቃት ተኩስ፣ በተለይ እናቶችና ሕፃናት አስከፊ ጭፍጨፋ ተካሂዶባቸው እዚህም እዚያም ወድቀው ታይተዋል፡፡
• በግፍ ከተጨፈጨፉት ወገኖች በተጨማሪ ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት እስከ ስምንት ዓመት የሚደርሱ ምንም የማያውቁ 36 ሕፃናት በዕለቱ ታፍነው ከመወሰዳቸው በተጨማሪ፣ ቀደም ባሉት ቀናት 72 ሕፃናት ታፍነው በመወሰዳቸው በድምሩ የታገቱ ሕፃናት ቁጥር 108 ደርሷል፡፡
• ከዚህ ዘግኛኝና ተቀባይነት ከሌለው ድርጊት በተጨማሪ 72 ንፁኃን ወገኖች ቁስለኛ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በንብረት በኩል በርካታ መኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን፣ ከ2,000 በላይ ከብቶች ተዘርፈዋል፡፡ በአጠቃላይ በአደጋው 20,000 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
• የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ደረጃ፣ ጭፍጨፋ የፈጸሙት የሙርሌ ታጣቂዎች ያቀዱትን አሳክተው ሕፃናቱንና ከብቱን እየነዱ ወደመጡበት መመለሳቸው፣ የጋምቤላ ነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ክስተት ሆኗል፡፡
• የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት፣ ጨፍጫፊው ቡድን ያቀደውን ካሳካ በኋላ በዜማ ታጅቦ መመለሱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡
• ‹‹ራሱን የደቡብ ሱዳን ቡድን›› እያለ የሚጠራው ኃይል ዕልቂት ፈጽሞ በድል አድራጊነት ስሜት ወደመጣበት ተመልሷል፤›› ብለዋል፡፡
• በእርግጥ አቶ ጋትሉዋክ ባይቀበሉትም ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የጋምቤላ ነዋሪ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ይህ ዕልቂት ከመድረሱ በፊት ጫካ ውስጥ ፀጉረ ልውጦች መታየታቸውን ለአካባቢው የአስተዳደር አካላት ከኅብረተሰቡ ጥቆማ ደርሷል፡፡
• እኝህ ግለሰብ እንደሚሉት ይህ መረጃ ጥቅም ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ይህ አሳዛኝና በዚህ ዘመን ሊታሰብ የማይገባው ዕልቂት ላይደርስ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን አቶ ጋትሉዋክ ፀጉረ ልውጦች ስለመታየታቸው የሚገልጽ ምንም ዓይነት መረጃ ለመንግሥት እንዳልቀረበ አስተባብለዋል፡፡
• ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. እና ከዚያ ቀደም ባሉት ቀናት ሙርሌዎች በኑዌርና በአኙዋ ዞኖች በሚገኙት ጅካዎ፣ ላሬ፣ ሙከይ፣ ጆርና ጎግ ወረዳዎች በሚገኙ 13 ቀበሌዎች ጥቃት ፈጽመዋል፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ እንደሚሉት፣ ከዚህ ቀደም አልፎ አልፎ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት የሚፈጽሙ መሆኑ ቢታወቅም፣ ይኼኛው ግን እጅግ የከፋ ነው፡፡ይህ ጥቃት የከፋ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲያስረዱ፣ የመከላከያ ሠራዊት ዕልቂቱ በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በፍጥነት ባለመድረሱና የጋምቤላ ልዩ ኃይልና የፖሊስ ኃይል ትጥቅ እንዲፈቱ በመደረጉ ነው ይላሉ፡፡
• ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የሙርሌ ጎሳዎች ጥቃቱን አድርሰው የተመለሱት በተሽከርካሪዎች አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ከብቶችና ሕፃናት በመያዛቸው ፈጥነው ሊጓዙ አይችሉም፡፡
• ‹‹መከላከያ ሠራዊታችን በፍጥነት ቢሰማራ አንዳቸውም ሊያመልጡ አይችሉም ነበር፤›› በማለት አንድ ነዋሪ ቁጭታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
• ከዚህ ባሻገርም የጋምቤላ ልዩ ኃይል ትጥቅ ፈትቶ በመከላከያ ካምፕ እንዲገባ መደረጉንም ለአስከፊውና ለአሰቃቂው ጥቃት መንስዔ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ እንደተናገሩት፣ የመከላከያ ሠራዊት ጦር ሠፈር ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች በግምት 60 ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል፡፡
• ‹‹ጥቃቱ የተፈጸመባቸው አካባቢዎች የመንገድ መሠረት ልማት የሌላቸው በመሆናቸው መከላከያ ሠራዊታችን መጠነኛ መዘግየት ነበረበት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ፈጥኖ በመድረስ ዕርምጃዎች እየወሰደ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
• በጥር 2008 ዓ.ም. በኑዌርና በአኙዋ ብሔረሰቦች መካከል ተከስቶ የነበረውን የእርስ በእርስ ግጭት ለመቆጣጠርና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት፣ የፌዴራል መንግሥት ከክልሉ ጋር በመሆን ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች ውስጥ የመጀመርያው ለግጭቱ መባባስ በጋምቤላ ልዩ ኃይል ውስጥ የሚገኙ የኑዌርና የአኙዋ ተወላጆች አስተዋጽኦ አለበት በማለት ልዩ ኃይሉን ትጥቅ ማስፈታት አንዱ ነበር፡፡ በተመሳሳይ ምክንያት የፖሊስ ኃይሉም ትጥቅ እንዲፈታ ተደርጓል፡፡
• በዚህም መሠረት የጋምቤላ ልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ ፈተው እዚያው ጋምቤላ ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ጦር ካምፕ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
• ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የፌደራል ጉዳዮችና የአርብቶ አደሮች ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው በወቅቱ ልዩ ኃይሉ ትጥቅ እንዲፈታ መደረጉን ለሪፖርተር ገልጸው ነበር፡፡
• ከዚህ በተጨማሪም የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ ድንበር የሚዋሰን በመሆኑ ሕገወጥ የጦር መሣርያ ዝውውር መኖሩ መረጃ መድረሱን፣ ይህ ሁኔታ ለጋምቤላ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አካባቢዎች ችግር እየሆነ በመምጣቱ የታጠቀውን ዜጋ ትጥቅ የማስፈታት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ሙሉጌታ መናገራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
• ይህ ዕርምጃ ከተወሰደ ከሦስት ወራት በኋላ የተከሰተው የሙርሌዎች ጭፍጨፋ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ራሱን መከላከል በማይችልበት ወቅት እንደተፈጠረ ይታመናል፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይልና ፖሊስ ትጥቅ እንዲፈቱ መደረጉን፣ በዚህ ምክንያት ጥቃት በተሰነዘረባቸው አካባቢዎች የጥበቃ ኃይል ባለመኖሩ ክፍተት መፍጠሩን አምነዋል፡፡
• የጋምቤላ ክልል ለግጭት የተጋለጠ ከመሆኑ በተጨማሪ መረጋጋት ከተሳነው ደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ ድንበር የሚዋሰን በመሆኑ፣ ዘወትር ትንኮሳ እንደማያጣው ይነገራል፡፡
• የፌደራል መንግሥት ከዚህ በመነሳት በጋምቤላ ክልል ቋሚ የመከላከያ ሠራዊት ጦር ካምፕ እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ ነገር ግን መንግሥት ጥቃቱ በደረሰባቸው ቦታዎች ቀደም ብሎ ኃይል ለማሰማራት ባለመቻሉ፣ አሰቃቂው ጭፍጨፋ ከመፈጸሙም በላይ ሙርሌዎች ሕፃናትንና ከብቶች እየነዱ ተረጋግተው መሄዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጨ እየተነገረ ነው፡፡
• ከዚህ በተጨማሪ ደቡብ ሱዳን የተረጋጋና ዘላቂ ሰላም የሰፈነበት አገር ባለመሆንዋ፣ ለኢትዮጵያ ፀጥታ አሥጊ ልትሆን የምትችልበት ዕድል ሰፊ መሆኑ ይታወቃል፡፡
• ከዚህ በመነሳት በሁነኛ መንገድ ድንበሩ ባለመጠበቁ፣ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ብቻ ሳይሆን ከዚያም በፊት ባሉት ቀናት የንፁኃን ሕይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡
• የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ባላት ጉርብትና የጎላ ችግር አጋጥሟት አያውቅም፡፡ ‹‹ነገር ግን የከብቶች ዝርፊያ አለ፡፡ መከላከያ ሠራዊት ምላሽ የሚሰጠውም ሪፖርት ሲደርሰው እንደመሆኑ ሪፖርት እንደደረሰው ምላሽ ሰጥቷል፤›› ብለዋል፡፡
• ‹‹ከዚህ ውጪ ግን ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው ድንበሩ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ታጥሮ ይጠበቃል ማለት አይደለም፤›› ብለው ‹‹ሕፃናት የታገቱ በመሆኑም የሚወሰደው ዕርምጃ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መሆን ይኖርበታል፤›› በማለትም አክለዋል፡፡
• መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ በወሰደው ዕርምጃ 60 ያህል የሙርሌ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ጋር በጋራ ኦፕሬሽን ለማካሄድ ንግግር መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
• የሙርሌ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ወተደራዊ ዩኒፎርም ለብሰውና ዘመናዊ መሣሪያዎች ታጥቀው ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫው ወቅት እንዳብራሩት በጉዳዩ ላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ታጣቂ ኃይሎቹ እንደሌሉበት ነው፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ ‹‹እስካሁን የፖለቲካ አጀንዳ መኖር አለመኖሩ አልተረጋገጠም፤›› በማለት ጉዳዩ ገና እየተጣራ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ የታገቱትን ሕፃናት ሙርሌዎች ምን ያደርጓቸዋል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹የከብት እረኛ ያደርጓቸዋል፡፡ ታጋቾቹ ሕፃናት እንደመሆናቸው የሙርሌ ቋንቋ እንዲለምዱ አድርገው እዚያው የእነሱ አካል ያደርጓቸዋል፤›› ብለዋል፡፡
• አቶ ጋትሉዋክ ድንበር ሰብረው የገቡ የሙርሌ ታጣቂዎችን ቁጥር መገመት ባይችሉም ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑን ግን ያምናሉ፡፡ ታጣቂዎቹ ጉዳት ያደረሱባቸውን ነዋሪዎች በማሰባሰብ ድጋፍ ለመስጠት እየተሞከረ መሆኑን ሥጋት ለገባቸው ነዋሪዎችም መንግሥት በማፅናናት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
• የደረሰውን ግድያና አፈና ኢትዮጵያውያን በማውገዝ ላይ ሲሆኑ፣ መንግሥትም ብሔራዊ የሐዘን ቀን ከማወጁም በተጨማሪ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
• መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ መንግሥት ዜጎችን ትጥቅ በማስፈታት ራሳቸውን የሚከላከሉበትን ዕድል ነፍጓል በማለት ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ ‹‹ባዶ እጃቸውን በቀሩበት ሁኔታ ለደኅንነታቸው ተገቢው ጥበቃ ስላልተደረገላቸው ነው፤›› በማለት ችግሩ እንደተከሰተም ገልጸዋል፡፡
• የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ባወጣው መግለጫ የመከላከያ ሠራዊት የአገር ዳር ድንበርና የዜጎችን ሰላም የማስጥበቅ ኃላፊነቱን ከምንጊዜውም በበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን፣ መንግሥት ከአካባቢያቸው ታግተው የተወሰዱትን ዜጎች ሕጋዊም ሆነ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አድርጎ እንዲያስመልሳቸው ጠይቋል፡፡

Tuesday, April 19, 2016

የወያኔ ባለስልጣን የሆነው ቴድሮስ አድሀኖም በስዊድን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

በፍርድ ቤት ነፃ ተብለው የተፈቱት ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ ከእስር ቤት ከወጡ ከሰዓታት በኋላ በድጋሚ ታሰሩ


ከስድስት መቶ ቀናት በኋላ በፍርድ ቤት ነፃ ተብለው የተፈቱት ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ ከእስር ቤት ከወጡ ከሰዓታት በኋላ በድጋሚ ታሰሩ። ሁለቱ ወጣቶች በነ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ የክስ መዝገብ የኢንተርኔት ደህንነት ስልጠና ለመውሰድ በማመልከታቸው “የሽብር ስልጠና ወስደዋል” በሚል ተከሰው 647 ቀናት እስር ቤት አሳልፈዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፍርድ ቤት በነፃ እንዲለቀቁ ያሰናበታቸው ሲሆን ዛሬ ሰኞ ከቂሊንጦ እስር ቤት እንደወጡ በድጋሚ ታስረው ወደ ማዕከላዊ ተወስደዋል። የታሰሩበትን ምክንያት አልተገለፀም።

በሳውዲ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ፍላጎት ከፍ ብሏል !


* ሳወዲዎች ይወዱናል ፣ ይጠሉናል
… የባለጸጎች ቤት ያለ በቂ የቤት ሠራተኛና ኦና ነው። የሳውዲ ወይዛዝርትና ልጃገረዶች መኪና መንዳት አይፈቀድላቸውምና እንዳሻቸው መውጣት መግባት ሲፈልጉ ውሎ አዳራቸው ያለ ሹፊር የሰመረ አይሆንም። በአጠቃላይ ያለ ቤት ሠራተኛና ሹፊር ኑሯቸው የሚመሰቃቀልባቸው ሳውዲዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መንግሥትታቸው የሠራተኛ አቅርቦቱን እንዲያፋጥን እየወተወቱ ይገኛሉ። ባሳለፍነው ሳምንት የወጣው ታዋቂ ጋዜጣ ሳውዲ ጋዜጥ የቤት ሠራተኛ ፍላጎት መጨመሩን በመጠቆም Housemaids’ black market booms ብሎ የድለላውና የሕገ ወጥ ሠራተኛ አቅርቦቱ ገበያ ስለ መድራቱ ዘርዘር ያለ መረጃ አቅርቧል። በጥቁር ገበያ የአንድ ሰዓት ክፍያ እስለ 40 ሪያል ማሻቀቡን ጋዜጣው ጠቁሞ አንድ ሠራተኛ በወር በአማካኝ እስከ 9 ሽህ ሪያል ገቢ እንደሚያገኙ በዝርዝር ያስረዳል። ጋዜጣው በሳውዲ ቤተሰቦች ተመራጭ ካላቸውን የቤት ሠራተኞች መካከል በአንደኝነት የኢንዶኖዥያ ዜጎች ሲጠቀሱ በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ተመራጭ መሆናቸውንም አልደበቀም።
************
የተዘጋው የሠራተኛ አቅርቦት ጉዳይ ከወራት በፊት መነሳቱን የሳውዲ መንግሥት ሲያስታውቅ ከኢትዮጵያም በኩል አዲስ የሥራ ስምሪት ተረቆ መጽደቁ ይጠቀሳል። ጸደቀ በተባለው ረቂቅ ባለድርሻ ከሚባሉት መካከል በስደት የችግሩ ዳፋ ቀማሽ ስደተኛ እንዲመክርበት ያልተደረገው ረቂቂ ለሳውዲ መንግሥትት ከቀረበ ወራት ቢቆጠርም ከሳውዲ በኩል ሠራተኛ ስምሪቱን ለመጀመር በተፈለገው ፍጥነት ይሁንታን አልተገኘም። በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፋዎችን ዋቢ በማድረግ ደጋግነው “ስምምነቱ ጫፍ ላይ ደርሷል” ቢሉም የሥራ ስምሪት ስምምነት እስካሁን አለመፈረሙ ይጠቀሳል።
ስምምነቱ እንዳይፈረም ዋናው ምክንያት የሆኑት የሳውዲ አልሹራ የምክር ቤት አባላት መሆናቸው ሲያስታውቅ ከአንድ አፍሪካ አገር ጋር ለሳውዲ ምክር ቤት የቀረበውን ረቂቅ ተከትሎ የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት ከኢትዮጵያ ጋር ሊጀመር የታሰበውን ስምምት መቃወማቸው ባሳለፍነው ሳምንት አረብ ኒውስ አስነብቦናል፡፡ በጋዜጣው የቀረበው መረጃ እንደሚያስረዳው ሱልጣን አል ሱልጣን የተባሉት የሳውዲ አልሹራ ምክር ቤት አባል ከዚህ ቀደም ስለተደረገው የቤት ሠራተኛ ቅጥር አንስተው “ማኅበረሰባችን ከአፍሪካ በቀጠርናቸው ሠራተኞች እጅግ አስፈሪና ሰቅጣች የሆነ ድርጊት ማየታችን አንርሳ ” ብለው መናገራቸው ተጠቅሷል። ሌላው የምክር ቤት አባል ናስር አልዳውድ “እንደኔ ተሞክሮ በተጠቀሰው አገር የመጡ ሠራተኞች በሽብርና በወንጀል ተሳታፊዎች እንደነበሩ አውቃለሁ” በማለት ተናግረዋል።
አስፍ አቡ ተንያን የተባሉት ሌላው የአልሹራ ምክር ቤት የቅጥር ጉዳይ አስተዳደር ባልደረባ በበኩላቸው “ይህ ከሆነ እውነቱ ከዚህች አገር ሠራተኞችን ለማስመጣት ማሰቡስ ለምንስ አስፈለገ ?” ብለው በመጠየቅ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሠራተኞች በሚፈጽሙት ወንጀል ከፍ ያለውን ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያን መሆኗ በጋዜጣው ተመልክቷል፡፡ በሠራተኛ ስምሪቱ ዙሪያ አስተያየት የሚሰጡ ሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው ሲናገሩ “ካለፈው አልተማርንም፤ ዛሬም በቂ ዝግጅት አልተደረገም ፤ ነገም ማዘናችን አይቀርም፡፡ ሌላ ስምሪት በከፋው ስማችን መባቻ አያዋጣም። በመላ ሳውዲ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደጨው ተበትነው ይገኛሉ። አንዳንዶች መዳረሻቸው አይታወቅም። ማንነታቸውን መለየት ሳይቻል ቀርቶ የተቀበሩ አሉ። የጅዳ ቆንሰልና የሪያድ ኢንባሲ ወደ ሳውዲ ስለመጡት ዜጎቻቸው አያያዝ መዳረሻቸው የሚያውቁት የለም። የሚታወቂት ቁጥር በጣም ትንሽ ነው። አደረ ራሻቸው የጠፋ፣ ታመው ማንነታቸው ሳይታወቅ ያሸለቡት፣ አብደውና ተሰናክለው ያሉበት የማይታወቀውን ቁጥር ቤቱ ይቁጠረው” ካሉ በኋላ ስለ አዲሱ ስምሪት ሲናገሩ “አሁንም ከበፊቱ አልተማሩም፤ ሥራው ሁሉ ለብለብ ነው፤ የቤት ሠራተኞች መብት ማስከበር የሚችል አደረጃጀት የለንም፡፡ የዜጎችን መብት ለማስከበር ክህሎቱ ያለው በቂ የሰው ኃይል በጅዳ ቆንስልና በሪያድ ኢንባሲ የለም። ገጽታችን ለመገንባት ከተፈለገ አሁንም ዝግጅቱ ይቅደም ” ሲሉ መንግሥት አሁንም እየሠራው ያለው ስህተት ብዙ እህቶችን ከቤተሰብ የሚለያይና የሚያሳዝን ፍጻሜ እንዳይሆን በውል ሊገነዘብ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል !
ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ

የወያኔ መንግስት የጋምቤላ ወገኖቻችንን መገደል ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው ተባለ


በትናንትናዉ እለት የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች ተወያይተዋል!!
ዉይይቱ እጅግ የሱዳናዊያን ብቻ ነበር የሚመስለዉ ያሉት ዉስጥ አዋቂ መረጃችን….
ተቆርቋሪነታቸዉ ለሱዳናዊያን የሙርሌ ብሔር ወንጀለኞች የሆኑ ሁለት ወታደራዊ አመራሮች በተለየ መልኩ በድንበር ማስጠበቁ እና የድንበር ማካለሉ ስራን አስረግጠዉ አስቀምጠዋል
” እንደዚህ ያሉ የብሔር ግጭቶች በሰሜኑ የሱዳን ድንበርና ኢትዮጵያ መካከልም ይፈጠራል ያሉት የኛዎቹ የመከላከያ ጀኔራል ጉዶች ድንበር እስኪካለል ድረስ የሰሜን ሱዳናና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አብረዉ በጥምረት እየሰሩ እንደሆነና የደቡብ ሱዳኑም ያንኑ እንዲያደርግ ሐሳብ አቅርበዋል” 
የጋምቤላ ወገኖቻችንን ከ10 ቀበሌዎች በላይ ዘልቀዉ በመግባት የገደሉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ወይም ወንጀለኞቹ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እንዲሁም ታፍነዉ በተወሰዱት 103 ሕጻናት ዙሪያ እና የደቡብ ሱዳኑ መንግስት ካሳ እንዲከፍል በመጠየቅ በኩል ያልተሳተፈዉ የወያኔ መንግስት ነገሩን ሆን ብሎ እንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከስብሰባዉ መንፈስ ለመረዳት ተችሏል።
በመጀመሪያ ደረጃ ጋንቤላን በፌደራል መንግስት እጠቀልላለዉ ያለዉ ህወሃት የክልሉን መከላከያ ሰራዊት በመበረዝ ከቦርደር ላይ እንዲነሱ በማድረግና በምትካቸዉ ምንም አይነት ሰራዊት ሳያመጣ መሰንበቱ! እንዲሁም በሁለቱ ብሔሮች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት አዲስ እንዳልሆነና በማንኛዉም ወቅት እንዲህ ያለ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል መረጃ እያለዉ ጉዳዩን በቸልተኝነት ያለፈዉ የድንበር ማካለሉን ጉዳይ ከጋምበላ ወደ ጎንደር ለመዉሰድ የታለመ ሳይሆን እንዳልቀረ ተንታኞች እየገለጹ ነዉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂ የተባሉት ወታደራዊ አቋም ያላቸዉና ልዩ ስልጠና የወሰዱ የደቡብ ሱዳን ወታደርዊ ዩኒፎርም እንዲሁም አንዳንዶቹ የኢትዮጵያን መከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ግድያዉን ከፈጸሙ በኃላ የኢትዮጵያ መከላከያ ፈጽሞ ያለመኖሩን የተገነዘቡት የጋንቤላ ህዝቦች በመተባበር የሙርሲ ብሔር የተባሉትን ነፍሰ ገዳዮች በማሳደድ የመልሶ ማጥቃት እንደፈጸሙ ምንጫችን አረጋግጠዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
 

Monday, April 18, 2016

በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በኑዌር ብሔረሰብ አባላት ላይ የተፈጸመውን ግዲያ በሚመለከት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ፡


ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ ም በጋምቤላ ክልል ነዋሪ በሆኑ ሰላማዊ የኑዌር ብሔረሰብ አባላት ላይ በጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን ነዋሪ በሆኑ ታጠቂዎች የተፈጸመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመስማታችን መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ እጅግ ልብ የሚሰብር ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡
ከመንግሥት ባገኘነው መረጃ መሠረት ብቻ 208 ዜጎቻችን በዚሁ ጭፍጨፋ በአንድ ሌሊት ሕይወታቸውን ማጣታቸውና 102 ሕፃናት ታፍነው መወሰዳቸው በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛና ዘግናኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ዜጎቻችን ለዚህ ያህል ትልቅ ጥቃት የተዳረጉት ደግሞ ቀደም ሲልም ጥቃት ሲፈጸሚባቸው እንደነበረ እየታወቀ የኢህአዴግ መንግሥት እራሳቸውን የሚከላከሉበትን ትጥቅ በማስፈታቱ የመከላከያ መሣሪያ እንዳይኖራቸው በመደረጉና ባዶ እጃቸውን በቀሩበት ሁኔታ ለደህንነታቸው ተገቢው ጥበቃ ስላልተደረገላቸው መሆኑን መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ይገነዘባሉ፡፡ ከዚህም ሌላ ቀደም ባሉት መንግሥታት በየጠረፉ አከባቢዎች ይመደብ የነበረው ጠረፍ ጠባቂ ኃይል እንዳይኖር በመደረጉ የውጭ ሀገር ታጣቂዎች እንደፈለጉ ድንበር ጥሰው የሚገቡበትና ወገኖቻችን ላይ ጥቃት የሚያደርሱበት ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል፡፡ ስለዚህም፡-
1ኛ፡- በጥቃቱ ምክንያት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ላጡ የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ለሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንደዚሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፡፡
2ኛ፡- በአጥቂዎቹ ታፍነው የተወሰዱት ሕፃናት በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መንግሥትና የዓለም ማሕበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ተገቢውን ጥረት ሁሉ እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
3ኛ፡- ለወደፊቱ በጋምቤላም ሆነ በሌሎች ክልሎች በጠረፍ አከባቢዎች በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ሕዝቡ ራሱን መከላከል የሚያስችልበትና ተገቢውን የደህንነት ጥበቃ የሚያገኝበት ሁኔታ በአስቸኳይ በመንግሥት በኩል እንዲመቻች አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ሰላም ለሕዝባችን!!
ድል ለሕዝባዊ ትግላችን!!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ
ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ

ባልታወቀ ምክንያት ሁለት ጥንዶች ከያዙበት አልጋ ሞተው ተገኙ


ዛሬ ደግሞ 09.08.2008
ባልታወቀ ምክንያት ሁለት ጥንዶች ከያዙበት አልጋ ሞተው ተገኙ
የሞቱትን ጥንዶች ለምርመራ ይዘው የሄዱት ቤተሰቦቻቸውና አብረው የሄዱት ሰወች ጋር ከመቀሌ ሲመለሱ ቆቦ ከተማ
ሲደርሱ የተሳፈሩበት ሚኒባስ ከተሳቢመኪና ጋ በመጋጨቱ በአደጋው ግማሾቹ ለሞት ተዳርገዋል።
ነፍስ ይማር።
ሞትን ሞት
ባኮረፈ ሰማይ በጋ በዋለበት
በተረገመ አፈር ሀፅያት በበዛበት
ጭጭ ባለው ባህር ውሃ ጥም ተድሶ
የማያቋርጥ ሞት ሂዶ ሂዶ ፈሶ
የዝምታ ኩሬ ምንጩ ደፈረሰ
ልክ እንደታቻምና ዛሬም ተለቀሰ
ቢጨለፍ እማያልቅ ሀዘን ተወረሰ
በፍቅር ተቃቅፈው እስከዚያ ሲያሸልቡ
የሞት ፅዋ ቀምሰው አልቃሽን ሲራቡ
ሞትን ሞት ሊቀብር ተከታይ አዘለች
ሀገሬም አኩርፋ በሞት ቂም ይዛለች
ሞታችሁ ሁላችንንም አሳዝኖናል ።ለመላ ቤተሰብ መፅናናትን
እመኛለሁ።
መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.

የአርማጭሆ ሕዝብ ለብአዴን ማስጠንቀቂያ ሰጠ

በመላው አርማጭሆ የሚኖረው ህዝብ ብአዴን አመራር ውስጥ አማራ መስለው ገብተው ህዝቡን በዘር የሚያጋጩ፣ ታጋዮችን እየጠቆሙ የሚያስይዙ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያን ለም መሬት ለሱዳን ለማስረከብ በስወር የሚሰሩ፣ የወያኔሰላዎች እየበዙ መምጣታቸውን እያወቀ ብአዴን ምንም እርምጃ ሊወስድ ማለመቻሉ ህዝቡ ተቆትቷል። በዚህም ምክንያት፣ ህዝቡ በቁጣ ለብአዴን መሪዎች ከወያኔ አሽከርነት ነጻ እንዲወጡ ጠይቋል። በተጨማሪ ማንኛውም የብአዴን ባለስልጣን ፣ የጎንደር ደንበር ተከዜ መሆኑን የማይቀበል ከሆነ እንዲሁም፣ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱን የማይቃወም ከሆነ ጠላታችን መሆኑን ታወቆ ከአባቢው እንዲነሳልን ብለው ጠይቀዋል።
በመጨረሻም፣ ብአዴን ለራሱ ቢል ከህዝቡ ጎን ይሰለፍ ካልሆነ ግን “ያለ ብአዴን ሀገራችንን እናስከብራለን፣ ድሮም አርማጭሆ ራሱን ይችላል ተብሎ ተቀኝቶለታል” በማለት ምክርና ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ


በክልሉ የተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማስታወቃቸው ይታወሳል።
አዲስ አበባ —
በኦሮሚያ በየደረጃው የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ከደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሰሩ የማድረግና ከሀላፊነት የማንሳት እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
በክልሉ የተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ልጆቻቸውን በነፍሰ ገዳዮቹ እንዳይወሰዱ የተከላከሉ የኑዌር እናቶች እዚያው በጥይት ተገድለዋል።


“ልጆቻቸውን በነፍሰ ገዳዮቹ እንዳይወሰዱ የተከላከሉ የኑዌር እናቶች እዚያው በጥይት ተገድለዋል። እናቶቹ ራሳቸውን ከግድያ: ልጆቻቸውን ከአፈና ሳያድኑ ቀርተዋል። እነሱም ተገደሉ። ልጆቻቸውም ተወሰዱ።”
“አራት ልጆቼን ገደሉብኝ። ከዚህ በኋላ ለእኔ ህይወት ምንድን ናት?” የኑዌር አባት የተናገሩት
ከኑዌሩ ግድያ ጋር በተያያዘ ከተሰሙት
” መንግስትና መከላከያ ሰራዊታችን ከ200 በላይ ዜጎቻችንን የገደሉትን ደቡብ ሱዳናውያን ጥቃት ፈፃሚዎች ተከታትሎ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል ! ”
ይሄ አረፍተ ነገር ከሞላ ጎደል ከሃይለማሪያም ደሳለኝ የሃዘን መግለጫ ንግግር የተወሰደ ነው።
ይሄ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ግን መቼ ይሆን ንግግር የሚማረው ? የሚባለውንና የማይባለውን የሚለየው መቼ ነው ?
.
“አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ” ሲል ምን ማለቱ ነው ?
ገዳዮቹን ከደቡብ ሱዳን ዞኖች ወይም ወረዳዎች ግምገማ አድርገን ስልጣን ካላቸው በሌላ እንተካለን ማለቱ ነው ??smile emoticon
ኢትዮጵያ በየትኛው የአለም አቀፍ የህግ አግባብ ነው በሌላ ልኦላዊ ሃገር ጣልቃ ገብታ አስተዳደራዊ እርምጃ የምትወስደው ?? ነው ወይስ ደቡብ ሱዳንን ኦሮሚያ ክልል ወይም አፋር ክልል አደረገው ?
ይሄ ጠቅላይ ሚንስትር መቼ ነው ትንሽ እንኳን ፖለቲካ የሚገባው ??
እረ ይሄን ለወረዳ አስተዳዳሪነት እንኳን የሚመጥን አጠቃላይ ፖለቲካዊ ግንዛቤ የሌለው ጠቅላይ ሚኒስትራችሁን አንድ በሉት እባካችሁ ? ለነገሩ ሌሎቹም ከሱ የባሱ ናቸው መሰለኝ።

Sunday, April 17, 2016

ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ።


ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ። በዚህም መንግስት በተገደሉት 140 ዜጎች ዙርያ ገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲያቋቁምና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል። በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የተነተነውን የፓርላማውን መግለጫ ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ።
having regard to the press release on the meeting between the High Representative/Vice-President Federica Mogherini and the Minister of Foreign Affairs of the Federal Republic of Ethiopia, Tedros Adhanom, 13 January 2016

–   having regard to the statement by the EEAS Spokesperson on elections in Ethiopia, 27 May 2015
–   having regard to the press release of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015

–   having regard to press briefing note of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015

–  having regard to the universal Declaration of Human Rights

–   having regard to the African Union Charter of Human and Peoples’ Rights

–   having regard to the UN the International Covenant on Civil and Political Rights,

–   having regard to Rule 123(2) its Rules of procedure

A.whereas over the past two months , Ethiopia’s largest region, Oromia, has been hit by a wave of mass protests over the expansion of the municipal boundary of the capital, Addis Ababa which has posed risks for farmers eviction from their land;
B.whereas security forces used excessive lethal force and killed at least 140 protesters and injured many more, in what may be the biggest crisis to hit Ethiopia since the 2005 election violence;
C.whereas on the 14 January 2016 the government decided to cancel the disputed large scale urban development plan ; whereas if implemented, the plan will expand the city’s boundary by 20 times its current size; whereas Addis Ababa’s enlargement has already displaced millions of Oromo farmers and trapped them in poverty;
D.whereas the ethnic Oromos continue to suffer particular discrimination and human rights violations in efforts to suppress potential dissent in the region;
E.whereas the Ethiopian authorities arbitrarily arrested a number of peaceful protesters, journalists and opposition party leaders in the context of a brutal crackdown on the protests in the Oromia Region; whereas those arrested are at risk of torture and other ill-treatment;
F.whereas the government’s labelled largely peaceful protesters as ‘terrorists’ deploying military forces against them ;
G.whereas on December 23, the authorities arrested Bekele Gerba, deputy chairman of the Oromo Federalist Congress (OFC); Oromia’s largest legally registered political party; whereas Mr Gerba was being taken in a prison known for torture and other ill-treatment practices and shortly after he was reportedly hospitalized; whereas his whereabouts are now unknown, raising concerns of an enforced disappearance.
H.whereas other senior OFC leaders have been arbitrarily arrested in recent weeks or are said to be under virtual house arrest.
I.whereas last December leading activists such as Getachew Shiferaw (Editor-in-Chief: Negere Ethiopia), Yonathan Teressa (an online activist) and Fikadu Mirkana (Oromia Radio and TV) have been arrested arbitrarily though yet to be charged by the Ethiopian authorities.
J.whereas the current protests echo the bloody events of April and May 2014, when federal forces fired into groups of largely peaceful Oromo protesters, killing dozens; whereas at least hundreds more students were arrested, and many remain behind bars
K.whereas Ethiopia’s government has regularly been accusing people who express even mild criticism of government policy of association with terrorism; whereas dozens of journalists, bloggers, protesters, students and activists have been prosecuted under the country’s draconian 2009 Anti-Terrorism Proclamation.
L.whereas Ethiopia’s government imposes pervasive restrictions on independent civil society and media; whereas according to the Committee for the Protection of Journalist’s (CPJs) 2014 prison census found that Ethiopia was the fourth worst jailer of journalists in the world, with at least 17 journalists behind bars, whereas Ethiopia also ranked fourth on CPJ’s 2015 list of the 10 Most Censored Countries
M.whereas the Ethiopian authorities have routinely summoned to court the “Zone 9 bloggers” with terrorism charges for their writing over the past 2 years.
N.whereas numerous prisoners of conscience, imprisoned in previous years based solely on their peaceful exercise of their freedom of expression and opinion, including journalists and opposition political party members, remained in detention.; whereas these included some convicted in unfair trials, some whose trials continued, and some who continued to be detained without charge, among others Eskinder Nega, Temesghen Desalegn, Solomon Kebede, Yesuf Getachew, Woubshet Taye, Saleh Edris, and Tesfalidet Kidane
O.whereas severe restrictions on external funding continue to undermine the work and effectiveness of non-governmental organisations (NGOs) under the 2009 Charities and Societies Proclamation.
P.Whereas Ethiopia rejected recommendations to amend the Charities and Societies Proclamation and the Anti-Terrorism Proclamation that several countries made during the examination of its rights record under the Human Rights Council Universal Periodic Review in May 2014.
Q.Whereas Andargachew Tsige, a British-Ethiopian citizen and leader of an opposition party living in exile, was arrested in June 2014 while in transit through Yemen’s main airport and forcibly removed to Addis Ababa; whereas Tsige had been condemned to death several years earlier in his absence, and has been in death row practically incommunicado since then; whereas Juan Mendez, the UN special rapporteur on torture, has written to the Ethiopian and UK governments saying he is investigating the treatment of Tsige, following claims that Tsige is being deprived of sleep and held in isolation;
R.Whereas the Ethiopian government has de facto imposed a widespread blockade of the Ogaden region in Ethiopia, rich in oil and gas reserves; whereas attempts to work and report from the region by international media and humanitarian groups are seen as criminal acts, punishable under the anti-terrorist proclamation; whereas there are reports of war crimes and severe human rights violations perpetrated by the Army and government paramilitary forces against the Ogaden population;
S.whereas The Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), the ruling party coalition, won all 547 parliamentary seats in the May 2015 elections, due in part to the lack of space for critical or dissenting voices in the election process; whereas May’s federal elections took place in a general atmosphere of intimidation, and concerns over the lack of independence of the National Electoral Board;
T.Whereas Ethiopia enjoys political support from western donors and most of its regional neighbours, mostly due to its role as host of the African Union (AU) and its contribution to UN peacekeeping, security and aid partnerships with Western countries;
U.whereas Ethiopia receives more aid than any other African country – close to $3bn per year, or about half the national government budget
V.whereas for decades the government have been authorizing big development projects to foreign investors, which have been leading to severe land grabbing and millions vulnerable people often forcibly evicted and insensitively resettling; whereas often the government does not offer the local communities any alternative to permanent settlement and had not fully consulted groups before evicting them.
W.whereas some donors, including UK’s Department for International Development (DFID) and the World Bank, rechanneled funding from the problematic Protection of Basic Services (PBS) program in 2015 which was associated with the abusive “villagization program,” a government effort to relocate 1.5 million rural people into permanent villages, ostensibly to improve their access to basic services; whereas some of the relocations in the first year of the program in Gambella region in 2011 were accompanied by violence, including beatings and arbitrary arrests, and insufficient consultation and compensation
X.whereas Ethiopia is experiencing its worst drought in decades, deepening food insecurity and severe emaciation and unusual livestock deaths; whereas with 640 000 refugees, Ethiopia is the country in Africa with the highest number of refugees; whereas nearly 560 000 people are internally displaced due to floods , violent clashes over scarce resources and drought
Y.whereas the current political situation in Ethiopia and the brutal repression of dissent put a serious risk the security, development and stability in the country;

1.Strongly condemns the recent use of excessive force by the security forces in Oromia and in all Ethiopian regions, the increased cases of human rights violations and abuses, including violations of people’s physical integrity, arbitrary arrests and illegal detentions, the use of torture, and violations of the freedom of the press and of expression, as well as the prevalence of impunity;
2.Calls for an immediate end to violence, human rights violations and political intimidation and persecution;
3.Urges for the immediate release of all those jailed for exercising their rights to peaceful assembly and freedom of expression, including students, farmers, opposition politicians, academics, bloggers and journalists ;
4.Calls on the government to carry out a credible, transparent and impartial investigation into the killings of protesters and other alleged human rights violations in connection with the protest movement, and to fairly prosecute those responsible, regardless of rank or position;
5. Welcomes the government’s decision to completely halt the Addis Ababa and Oromia special zone master plan, that plans to expand the municipal boundary of Addis Ababa. Calls for an immediate inclusive and transparent political dialogue, including the government, opposition parties, civil society representatives and the local population preventing any further violence or radicalisation of the population; takes the view that such dialogue, conducing to the democratisation of the country, is not possible under the current political conditions;
6.Calls on the Government of Ethiopia to respect the Universal Declaration of Human Rights and the African Union Charter of Human and Peoples’ Rights, including the right to peaceful assembly, freedom of expression and association;
7.Urges the government to immediately invite the UN Special Rapporteur on the rights to freedom of association and peaceful assembly and other UN human rights experts to visit Ethiopia to report on the situation;
8.Calls on the government to stop suppressing the free flow of information, including by jamming media broadcasts and harassing media, including through intrusive surveillance programs, and facilitate access throughout Ethiopia for independent journalists and human rights monitors;
9. Calls on the government to include local communities in a dialogue on the implementation of any large scale development project and ensure equal distribution of future benefits to the population ; to ensure that farmers and pastoralists are adequately compensated, preventing them from any arbitrary or forced displacement without consultation and adequate compensation.
10. Expresses its concerns on the government’s forced resettlement program, known as “villagization program”.
11.States that respect for human rights and the rule of law are crucial to the EU’s policies to promote development in Ethiopia and throughout the Horn of Africa;
12.Call on the EU to effectively monitor programs and policies to ensure that EU development assistance is not contributing to human rights violations in Ethiopia, particularly programs linked to displacement of farmers and pastoralists, and develop strategies to minimize any negative impact of displacement within EU funded development projects;
13. Further calls on the EU and Member States to react promptly to the escalation of violence and the deterioration of the human rights situation in the country by publicly and privately condemning the use of excessive force by security forces in Oromia and call on the government to exercise restraint in its response against protests and the exercise of basic freedoms by the Ethiopian people;
14. Stresses that financial support to Ethiopia from the EU should be measured attending to the country’s human rights record and the degree to which the Ethiopian government promotes reforms towards democratisation, as the only way to ensure stability and sustainable development;
15.Instructs its President to forward this resolution to the Government and the Parliament of Ethiopia, the European Commission, the Council, the Vice-President of the Commission/High Representative of the Union for Foreign Affairs and Security Policy, the institutions of the African Union and the Secretary-General of the United Nations

በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱት እነ ዓለማዬሁ ለሳምንት ተቀጠሩ


ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከ20/07/08 ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ አንድነት የዞኑ ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ፖሊስ የጠየቀባቸውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጨርሰው ዛሬ በ05/08/08 ፍርድ ቤት ቀርበው ለመጪው ሃሙስ ( ሚያዝያ13/08) መቀጠራቸው ታውቋል ፡፡ በችሎት ላይ የተገኙት የኦህዲኅ አባላትና የታሳሪዎች ቤተሰቦች እንደገለጹት ፖሊስ መረጃ የማሰባሰብና የምርመራ ሥራዬን ስላላጠናቀቅሁ የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ‹‹ ጥያቄው አግባብ ያለመሆኑን ባልተሰበሰበ መረጃና ባልተደረገ ምርመራ ተጠርጣሪዎችን ማሰርም ሆነ እዚህ ድረስ ማምጣት አልነበረባችሁም ፣ ይህ በህግ አሰራርም ሆነ ከሰብዐዊ መብት አኳያ አግባብ አይደለም ›› ብሎ ከገሰጸ በኋላ ‹‹መዘንጋት የሌለበት እነዚህ ሰዎች በጠባብ ቦታ ነው ያሉት ፣ እኛ ደግሞ በሰፊው፣ ስለዚህ የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ምን የተለየና ተጨማሪ ነገር ለማድረግ ነው ?›› ሲል ጠይቋል፡፡ ፖሊስ ሰጠው መልስ የሰው ማስረጃዎችና ተጨማሪ መረጃዎች እያሰባሰብን ያለነው ከዞኑ- ጂንካ በመሆኑ ከቦታው ርቀትና ከዞኑ ፖሊስ ጋር ስለምንሰራ ነው፣ ስለዚህም የተጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት አስረድቷል፡፡ አቶ ዓለማዬሁ በበኩላቸው ‹‹ ከጅምሩ የታሰርነውና ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ወደሌለበት ያመጡን ያለአግባብ ነው፣ አሁን እየተጠየቀ ያለው የጊዜ ቀጠሮም ምንም በሌለበት እንዲሁ ለማንገላታት ነውና ፖሊስ አለኝ የሚለውን ማስረጃና የምርመራ ውጤት ያቅርብ ፣ ይህ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በነጻ ያሰናብተን ዘንድ እንጠይቃለን››ሲሉ አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ካደመጠ በኋላ ‹‹ የአንድ ሳምንት ጊዜ ይበቃችኋል›› በሚል ለመጪው ሃሙስ ሚያዝያ 13/08 ዓ.ም. ፖሊስ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቦ፣ ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርብ ሲል ቀጠሮ ሰጥቷል ፡፡ በተጨማሪም በዛሬው ችሎት ታሳሪዎች ከመያዛቸው አስቀድሞ ቤታቸው ሲፈተሸ የነበሩ እማኞች በችሎት ያለመቅረባቸው ተረጋግጧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢሳት እነ ዓለማዬሁ ከመታሰራቸው ጥቂት ቀናት በፊት በዞኑ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸመውን የመሬት ቅርምት፣ ይህም በዞኑ ልማት ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖና የመሬት ቅርምቱ ከ98 ከመቶ በላይ የተፈጸመው በህወኃት አባላትና ደጋፊዎች መሆኑንና በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ዓለማዬሁና የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ አስተያየት መስጠታቸውን መዘገቡ ይታወሳል ፡፡

ሰበር መረጃ . . የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ወታደራዊ መኮንን ኮበለሉ.


በምእራብና በምስራቁ እዝ ዉስጥ ከ1991 አመተ ምህረት አንስቶ ሲያገለግሉ የነበሩ የወያኔ ወታደራዊ አመራር ሻምበል መላኩ የትግራይ ነጻ አዉጪዉን ቡድን የመከላከያ ሰራዊት ከድተዉና ዉድ ሐገራችዉን ጥለዉ ከወጡ ሰንበትበት ብለዋል አዎ በአንድ ዘር የበላይነት ላይ የተመሰረተዉን ሰራዊት ከማገልገል መነጠል ይሻለናል ብለዋል ወጣቱ መኮንን ።
ሻምበል መላኩ በሶማሌያና በጎንደር እንዲሁም በምስራቁ እዝ ላይ ያገለገሉ የነበረ ሲሆን በተለይም ከሶማሌያ የተመለሰዉንና አዘዞ ላይ የፈረሰዉን የ 43ተኛ ክ/ጦር ሰራዊት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት
” እጅግ አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል ” አዎ እጅግ በጣም ዘግናኝና አሰቃቂ በደል ተፈጽሞብናል! እንደ ከንቱ ሸቀጥ ነበር ሙት ወታደሮች በከባድ መኪና ሸራ ለብሰዉ ተጭነዉ የሚወሰዱት! ወታደሮቻችን ሲሞቱ ለቤተሰቦቻቸዉ እንክዋን በቅጡ መሰዋታቸዉ አይነገራቸዉም! ካሳም ሆነ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘውት የዘር ሀረግ ይመዘዝ ነበር! በሶማሌያ ላይ የተደረገዉ ወንጀል ህዝብ ቅነሳ ካልሆነ በስተቀር አንድ እራሱን እንደ መንግስት የሚመለከት አካል ሊሸከመዉ የማይችል ጉዳይ ነዉ “።
” በተለይም ከአዘዞ ወደ ቀብሪ ደሐር ተላልፈን ሁለተኛ ሜካናይዝን ካቋቋምን ወዲህ የብረት ለበሱ የመከላከያ መሳሪያዎች ወደ ሶማሌያ ተወስደዋል።
ባጠቃልይ ከወያኔ ጋር የሚደረግ አብሮነት እጅግ አደገኛ ነዉ! ህዝብንና ሐገርን ከመጉዳቱም በላይ ለተጠያቂነት ይዳርጋል ነገ የወያኔ መንግስት መዉደቁ አይቀርም እዉነት ግን እዉነት ነች ሁሉም በሰራዉ ወንጀል ይጠየቃል በመሆኑም ለመላዉ የመከላከያ ሰራዊት የማስተላልፈዉ መልእክት ቢኖር ከወያኔ ጋር ያለዉን ማለትም የተሳሰረበትን ገመድ በመበጠስ ለህዝብ ከቆሙና ከሚታገሉ ጋር አብሮ እንዲቅም ነዉ ” ።
ፎቶ የሙሉ መቶ አለቃ በነበሩበት ወቅት የተነሳ ሲሆን ሻምበል መላኩ የህዝብ ልጅነታቸዉን በማስመስከር ኢትዮጵያዊነታቸዉን አንጸባርቀዋል!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
 

የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ሃይሎች በኢትዮጵያ ጉዳት አደረሱ

ከደቡብ ሱዳን የተነሱ ሀይሎች ባደረሱት ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተዘገበ፡፡ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው የተባሉቱና ከሙርሌ ጎሳ እንደሆኑ የተገመቱት እነዚህ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ጥቃት የፈጸሙት ሀይሎች በኢትዮጵያ ባሉ የኑዌር ጎሳዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸውንና ቁጥራቸው እስከ 170 የሚደርሱትን ሳይገድሉ እንዳልቀረ ተዘግቧል፡፡ ጥቃቱ በደረሰበት ጋምቤላ ህይወታቸው የተረፈ ሰዎች እንደተናገሩት ከሆነ ከደቡብ ሱዳን የተነሱቱ ሀይሎች በጄኮውና በኒያንያንግ ወረዳዎች አስር መንደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈታቸውን፤ ካጠፉት የሰው ህይወት በተጨማሪም በቤት እንስሳትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡……

Friday, April 15, 2016

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት አለመሻሻሉን ገለጸ

የ2015ትን የአለም የሰብአዊ መብት አያያዝን የሚተነትነው ሪፖርት በኢትዮጵያ የሚታየው አፈናና ዜጎችን በእስር ቤት ማሰቃየት መቀጠሉን ይተነትናል፡፡
የአሜሪካ መንግስት በያመቱ በሚያወጣው የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ተቃዋዎችን ፣ ደጋፊዎቻውንና ጋዜጠኞችን እንደሚያሳድዱ፣ እንደሚያስሩ፣ በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድደባ እንደሚፈጽሙ፣ እንዲሁም በህግ ስም ፖለቲካዊ ክስ እንደሚመሰር ዘርዝሮአል፡፡
ያለ ህግ እንደፈለጉ መግደል፣ ማሰር፣ ለፍርድ ቤት ሳያቀርቡ ዜጎችን ለረጅም ጊዜ በእስር ማቆየት፣ ለህይወት አደገኛ በሆነ እስር ቤት ውስጥ ማሰቃየት፣ በተራዘመ የፍርድ ሄደት ማሰቃየት፣ በዳኞች ላይ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳረፍ፣ የግለሰቦችን መብት መዳፈር፣ ህወገጥ ብርበራ ማካሄድ እንዲሁም በመንግስት የሰፈራ ፕሮግራም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈ‹ም የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡
ሀሳብን በመግለጽ በኩል የሚታየውን አፈና ሲዘረዝር ደግሞ በህትመትና በኢንትረኔት አገልግሎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ፣ መሰብሰብ፣ መደራጀትና በነጻ መንቀሳቀስ የተገደበ መሆኑን፣የትምህርት ነጻነት መጥፋቱን፣ በሃይማት ጉዳይ ጣልቃ መግባት መቀጠሉ እንዲሁም በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር መጠናከሩን ያትታል፡፡
ዜጎች መንግስታቸውን፣ አስተዳደራቸውን፣ ፖሊሲንና በሙስና የተዘፈቁ ዳኞችን በሰላማዊ መንገድ የሚለውጡበት እድል አነስተኛ መሆኑን የሚጠቅሰው ሪፖርቱ፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸመው የመብት ጥሰትና መገለልም ቀጥሎአል ብሎአል፡፡
በኢትዮጵያ ዋናው ችግር ተጠያቂነት የሚባል ነገር አለመኖሩ ነው የሚለው የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት፣ መንግስት በአብዛኛው ከሙስና በስተቀር ሌሎች ወንጀሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናትን ለፍርድ እንደማያቀርብ ገልጾአል፡፡
ሪፖርቱ ካለፈው ምርጫ ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውን፣ እንዲሁም ከምርጫው በሁዋላ በሃመር ወረዳ በመንግስት እና በጸጥታ ሃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት 48 ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሶአል፡፡ የግጭቱ መንስኤ ህዝቡ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አለመሆኑ፣ የተፈጥሮ የግጦሽ መሬታቸውን መነጠቃቸው፣ መንግስት የሚያካሂደው የስኩዋር እርሻ ልማት የአካባቢውን ነዋሪዎች መሬት አልባ ማድረጉ እንዲሁም የአደን ክልከላ መሆናቸውን ሪፖር አመልክቶአል፡፡
በአማራ ክልል በጭልጋ ወረዳ ደግሞ ከቅማንት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ 6 ሰዎችን የገደለ ሲሆን፣ በርካቶችን አቁስሎአል፡፡
በህዳር ወር ደግሞ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ፣ በኦሮምያ በተነሳው ተቃውሞ የጸጥታ ሃይሎች ከመጠን በላይ ሃይል መጠቀማቸውንና ግጭቱም ሪፖርቱ እስከተጠናከረበት እስከ ጥር ወር መቀጠሉን ጠቅሶአል፡፡
በጥቅምት 2014 ደግሞ በጋምቤላ የታጠቁ ሃይሎች 126 ፖሊሶችንና ነዋሪዎችን የገደሉ ሲሆን፣ ግጭቱም በመዠንገር ተወላጆችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል መካሄዱን ገልጾአል፡፡
በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አሰቃቂ ድብደባ በመፈጸም፣ እስረኞች መረጃዎችን እንዲያወጡ ይገደዳሉ የሚለው ሪፖርቱ፣ እስረኞቹ እጆቻቸው ለፊጥኝ ታስሮ እንደሚንጠለጠሉ፣ ለርጅም ጊዜ እጆቻቸው በገመድ እንደሚታሰሩ፣ ውሃ እየፈሰሰባቸው እንዲሰቃዩ እንደሚደረጉ፣ የቃላት ማስፈራያ እንዲደርሳቸው ና ለብቻቸው ተነጥለው እንዲታሰሩ እንደሚደርግ ጠቅሶአል፡፡
ምንም እንኩዋን አገሪቱ 6 የፌደራልና 120 የክልል እስር ቤቶች ቢኖሩዋትም፣ ሌሎች ይፋ ያልሆኑ እስር ቤቶች በደዴሳ፣ ብር ሸለቆ፣ ጦላይ፣ ሆርማት፣ ባሌ፣ ታጠቅ፣ ጅጅጋ፣ ሆለታና ሰንቀሌ ይገኛሉ ብሎአል፡፡
መንግስት ከውጭ የሚተላለፉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ማፈን መቀጠሉን ሪፖርቱ ገልጾአል፡፡ መንግስትን ይቃወማሉ የሚባሉ ድረገጾች መዘጋታቸውን ከእነዚህም መካከል የግንቦት7፣ ኦነግ እና ኦብነግ ድረገጾች እንደሚገኙበት የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ አልዘጂራና ቢቢሲ ሳይቀሩ አልፎ አልፎ ይዘጋሉ ብሎአል፡፡ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመሰለል ፊን ፊሸር የሚባል ሶፍት ዌር መግዛቱም በሪፖርቱ ተጠቅሶአል፡፡
መንግስት ለስርአቱ ታማኝ ለሆኑት ብቻ የትምህርት እና የስራ እድል እንደሚሰጥ ሪፖርቱ አመልክቶ፣ የፓርቲ ስብሰባዎችን አንሳተፍም ያሉ መምህራን ከስራ እንደሚባረሩ እንዲሁም የተለያዩ እድገቶችና ጥቅሞች እንደሚቀርባቸው አትቶአል፡፡ በኦሮሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም እስራት መቀጠሉን ሪፖርቱ አመልክቶአል፡፡
በአገር ውስጥ የሚታየው የህዝብ መፈናቀል ከዚህ በፊት ከነበሩት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ እስከ ጥር ወር ድረስ 505 ሺ 104 ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡
በሪፖርቱ የቀረቡት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እጅግ በርካታ በመሆናቸው ለወደፊቱ እንዳስፈላጊነቱ እየጠቀስን እናቀርባለን፡፡

በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…


በኦሮሚያ እና አማራ ክልል በነበረው ረብሻና ሁከት ምክንያት ዘንድሮ ብሄራዊ ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች እንዳሉ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ…
ችግሩ በርትቶ ትምህርት እስከ መዝጋት የደረሱ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ቀደም ሲል በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው የፈተና ሰሌዳ መሰረት አያስፈትኑም ተብሏል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የህዝብ ተወካዮች ዛሬ ላነሱላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡
ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት እና ረብሻ ተማሪዎች ተሳታፊ ነበሩ፣ የስነ ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ለመሆኑ ምን ፈይደዋል ሲሉ ሚንስትሩን ጠይቀዋል፡፡
አንድ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ትምህርቱ መወቀስ የለበትም የሚል ምላሽ የሰጡት አቶ ሽፈራው ተማሪዎቻችን ጥያቄ ማንሳታቸው እና መሞገታቸው ስህተት የለበትምብለዋል፡፡
በመላው ሀገሪቱ 40 ሺ ትምህርት ቤቶች አሉን የሚሉት አቶ ሽፈራው ሁከትና አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረው በኦሮሚያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ብቻ ነበር ብለዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 13 ትምሀርት ቤቶች ትምህርት ለማቋረጥ ተገድደዋል ብለዋል፡፡
ተማሪዎቻችን መስታወት እንኳን አለሰበሩም፣ ድንጋይም አልወረወሩም፣ ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ ነው ያቀረቡት ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ትምህርታቸውን ተረጋግተው ላልተማሩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የብሄራዊ ፈተና መውሰጃ ጊዜው ይራዘማል ተብሏል፡፡
ከክልሎቹ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ሰበር ዜና…የወያኔ ወታደራዊ አመራር መረጃ ይዘዉ ጠፉ

ተግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ እየፈለጋቸዉ ይገኛሉ በትዉልድ ኦሮሚያ የሆኑት ኮረኔል ንጉሴ በሰራዊቱ ዉስጥ በአስከፊ ሁኔታ የተንሰራፋዉን የዘር የበላይነት በመጥላት ሐገራችዉን ጥለዉ በሰላም ጎረቤት ሐገር ገብተዋል።
የ43ተኛ ክፍለ ጦርን አዘዞ ላይ ካፈረሱና ምንም አይነት ብረት ለበስ ወይም ሜካናይዝድ ጦር ላልነበረዉ የምስራቁ እዝ ቀብሪ ደሐር ላይ የሁለጠኛ ሜካናይዝድ ካቋቋሙ ወዲህ የተሰወሩት ኮረኔል ንጉሴ…..
” በወያኔ ስር ሆነህ ኮረኔል ወይም ጄኔራል ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ትግሬ የሆነ ተራ የመቶ አለቃ ያዝሐል!! መመሪያ ሲወርድ አንተ አናት ላይ ተቀምጠህ ተራ የትግሬ ወታደር ቀድሞህ ይደርሰዋል!! ለመሞት ወደ ዉጊያ ስትሄድ ግን ከፊት ትሰለፋለህ!! በቃ ምንም መብት የሌለው እንሰሳ ነዉ የምትሆነዉ!! ”
በማለት የገለጹ ሲሆን የምስራቅ እዙ ብቸኛዉ የሁለተኛ ሜካናይዝድ ጦር ታንኮችና መድፎች እንዲሁም ከባድ የሚባሉ መሳሪያዎች በብዛት ወደ ሶማሌያ ተወስደዉ ለአልሸባብ መሸጣቸዉን ኮረኔሉ ጨምረዉ ገልጸዋል።
የትግራይ ነጻ አዉጪዉን ቡድን ወታደራዊ ሰነድ ይዘዉ የተሰወሩት ኮረኔል ከእርሳቸዉ ጋር 8 ወታደሮች እና አመራሮች እንዳሉ መረጃችን የጠቆመ ሲሆን በተመሳሳዩ የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት እነዚህን ጀግኖች በቁጥጥር ስር ለማዋል ላልተፈለገ የሰዉ ሐይልና የገንዘብ ወጪ ከመዳረጉ አልፎ በጠፉበት መረጃዎቹ ምክንያት ወታደራዊ ስልቶችን ለመቀየር ተገዷል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

የቀድሞው ደህንነት ባለስልጣን አቶ ወልደስላሴ ከቀረበባቸው 12 ክሶች በሰባቱ ጥፋተኛ ተባሉ


የቀድሞው የሀገር ውስጥ ደህንነት ባለስልጣን አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም እና ምንጩ ያልታወቁ ሃብት በማፍራት ከቀረበባቸው 12 ክሶች በ7ቱ ጥፋተኛ ተባሉ።
በክስ መዝገቡ የተካተቱት ወንድምና እህታቸው ደግሞ በሶስት ክሶች ጥፋተኛ ተብለዋል።
በኢንቨስትምንት ስም በወንጀል የተገኘ 6 ሚሊየን ብር ሰውረዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ዶሪ ከበደ ክሱን በበቂ ሁኔታ በመከላከላቸው በነፃ ተሰናብተዋል።
የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በቀድሞው የሀገር ውስጥ ደህንነት ሰራተኛ አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ ወንድማቸው አቶ ዘርአይ ወ/ሚካኤል፣ እህታቸው ወ/ሪት ትርሀስ ወ/ሚካኤል እና የቅርብ ጓደኛቸውና በንግድ ስራ በሚተዳደሩት አቶ ከበደ ዱሪ ላይ 12 የተለያዩ ክሶች ላይ ነው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጅል ችሎት ዛሬ ብይን የሰጠው።
ከክሶቹ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል፣ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት ማፍራትና ታክስ ስወራ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
1ኛ ተከሳሽ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በ2002 ዓ.ም “ቴረሪዝም ኢን ኢትዮጵያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ” የተሰኘ መጽሃፍ ባሳተሙበት ወቅት፤ ይህንን መጽሃፍ በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገ/መስቀል የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ።
መጽሃፉ በመስሪያ ቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላም እንዲሁም የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ አድርገዋል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍል መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው።
አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ወቅት ሃላፊነታቸውን ተጠቅመው፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ በማድረጉ ስልጣናቸውን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል 1ኛ ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል።
እንዲሁም በ3ኛ ክስ የተሰጠውን ስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከ1998 እስከ 1999 ባሉት ጊዜያት ወይዘሮ ግርማነሽ ይኹኑአምላክ ለተባሉ ግለስብ ለግል ጉዳይዋ በአዲስ አበባ ከተማና ውጪ ስትንቀሳቀስ የመስሪያ ቤቱን ተሽከርካሪ ነዳጅ በመሙላት እና ሰራተኛ በመመደብ እንድትገለገል አድርገዋል ይላል ክሱ።
እንዲሁም ተከሳሹ ለግላቸው ራሳቸው ማስፈፀም ያለባቸውን ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኛና ተሽከርካሪ ለሁለት ወራት ለተለያዩ ጉዳዮች በመጠቀማቸው ጥፋተኛ ተብለዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል በሚለው 4ኛ ክስም ጥፋተኛ ሆነዋል።
ከ2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትመው ከሸጧቸው መጻህፍት ካገኙት ገቢ ላይ መክፈል የነበረባቸውን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አሳውቀው ባለመክፈል ህግን በመጣስ 5ኛ ክስም ጥፋተኛ ተብለዋል።
በተጨማሪም በ8ኛው ክስ ከተለያዩ ሽያጮች መክፍል የሚገባቸውን የተርን ኦቨር ታክስ ባለመክፈል የተመሰረተባቸውን ክስ ፍርድ ቤቱ በሁለት ተመልክቶታል።
በአመት አንድ የሚከፈለው ግብር ተከሳሹ እጃቸው የተያዘው ነሐሴ 2005 ዓ.ም በመሆኑና የግብር መክፈያ ጊዜ እስከ ጥቅምት 2006 ዓ.ም በመሆኑ አያስጠይቃቸውም።
ሆኖም በየወሩ የሚከፈለውን ግብር ከግንቦት ወር ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት የሶስት ወር አለመከፈሉ ጥፋተኛ አስብሏቸዋል።
9ኛ፣ 10ኛ እና 11ኛ ክስ ላይ በተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ በተመሳሳይ የህግ ድንጋጌ ሊጠቃለሉ የሚችሉ በመሆናቸው በ9ኛ ክስ ተጠቃለው ጥፈተኛ ተብለዋል።
ተከሳሹ በሁለተኛ ክስ ከ26 ተቋማት መጽሀፍ ሸጠው ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላ ዳግም አስገድደው መጽሐፉን ወስደዋል የሚለውና ከታክስ ጋር ተያይዞ በክስ 6 እና 7 የቀረበባቸው ክሶችን ጨምሮ በአራቱ ነፃ ሆነዋል።
2ኛ ከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ወስደው ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርገው በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝተዋል በሚለውም ጥፋተኛ ከተባሉበት ሶስት ክሶች ተጠቃሽ ነው።
3ኛዋ ተከሳሽ እህታቸው ትርሃስ ወልደሚካኤል የታተመውን መጽሀፍ የሽያጭ ዋጋ 399 ሺህ ብር በባንክ ሂሳባቸው አስገብተዋል በሚለውና በሌሎች ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተብለዋል።
በኢንቨስትምንት ስም በወንጀል የተገኘ 6 ሚሊየን ብር ሰውረዋል ተብለው ክስ ተመሰርቶባቸው የነበረው አቶ ከበደ ዶሪ ክሱን በበቂ ሁኔታ በመከላከላቸው በነፃ ተሰናብተዋል።
ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግና ተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ለማድመጥ ለሚያዚያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ኢንባሲ አንባሳደር በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያኑን እያመሱ ያሉት ግንቦት 7ቶች ናቸዉ በማለት ወነጀሉ


ደቡብ አፍሪካ ጆሓንስበርግ የሚገኘዉ የመድሓኒያለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤና አስተዳደሩ ወዳልተፈለገ መጠቃቃት እየሀዱ ይገኛሉ ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጉዳዩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየወሰደዉ ሲሆን የትግራይ ተወላጆችን በመጠቀም አንድ ሌላ ግሩፕ እንዲፈጠር እያደረገ ነዉ 17 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸዉ በፖሊስ እየታደኑ ሲሆን 3 ግለሰቦች…. 1 ሔኖክ ገ/ሚካኤል 2. ታምሬ ተምትሜ 3. አቶ ኤፍሬም በጆሓንስበርግ ሴንትራል ፖሊስ ጣቢያ ( Johannesburg central police station ) በትናንትናዉ እለት በቁጥጥር ስር ሲዉሉ ሁለት ማንነታቸዉን ለመጥቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች ከተላኩባቸዉ ዘራፊዎች የግድያ ሙከራ አምልጠዋል በኢትዮጵያ የሚገኘዉ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ ሉቃስ የአጎት ልጅ እና የወያኔ ብሔራዊ መረጃ ባልደረባ የሆኑት አባ ጾመ ልሳን ሰበካ ጉባኤዎችን ምድረ ፌስታል ሻጭ ሁሉ ይህ መነኩሴ የሚገድል ህዝብ ነዉ አዉቃለዉ በማለት የተሳደቡበት የድምጽ መረጃ እጃችን የገባ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንባሲ አንባሳደር በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያኑን እያመሱ ያሉት ግንቦት 7ቶች ናቸዉ በማለት ወንጅለዋል። አባ ጾመ ልሳንና የኢትዮጵያ ኢንባሲ በመተባበር ቤተ ክርስቲያኗን መሪ አልባ ያደረጓት ሲሆን በጆሐንስበርግ የሚኖረዉን መሐበረሰብ በሰፍርና በዘር እየለዩ በመጥራት እያባሉትና እያጋጩት ይገኛሉ። አብዛኛዉን ሕዝበ ክርስቲያን ይህ ሁኔታ እጅግ ያሳዘነዉ ከመሆኑም በላይ በገዛ ገንዘባችን እኛዉ በለግሰዉ እንደዚህ የሚባሉ ከሆነ ምን ልንሰራ እንሄዳለን በማለት ቅሬታቸዉን የገለጹ ሲሆን እለት በእለት እየተፈጠረ የሚገኘዉን ይህን አሳሳቢ ጉዳይ የሚያበርድ አባት ወይም ሽማግሌ በመጥፋቱ ምክንያት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ መጤፋፋት ኢያመራ ይገኛል።

Thursday, April 14, 2016

አስቸኳይ የሆነ የአቋም ለዉጥ በኢትዮጵያ በኩል እስካልተደረገ ድረስ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚሰረዝ ማሳስጠንቀቂያ ተሰጠ


ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ስጌ ለትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ እራስ ምታት ሆኗል።
የተከበሩት የቀድሞ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ በወያኔ እጅ በግፍ ተላለፈዉ ሲሰጡ የእንግሊዝ የደህንነት አካላት ያዉቁ እነደነበር እና የየመን የጸጥታ ሐይሎች እንዲሁም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በመተባበር እገታዉን እንዳካሄዱት ዛሬ ከብሔራዊ መረጃ ምንጭ ተገኝቷል።
የእንግሊዝ ከፍተኛ የደህንነት አባላትን ጨምሮ አጣብቂኝ ዉስጥ የከተቱት አንዳርጋቸዉ ጽጌ በአምነስቲ ኢንተርናሽናልና በሌሎች ሁለት ከፍተኛ ተደማጭነት ባላቸዉ የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም በወላጅ አባታቸዉ የሚጎበኙ ሲሆን የተለያዩ የወያኔን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዲስኩር ያዘሉ መጽሐፎች፣ እና መጽሄቶች በተለይም የክቡሩን ታጋይ ሞራል በሚነካ መልኩ አንዳንድ አልባሌ ጽሁፎችን ያካተቱ መጣጥፎችም ሆን ተብለዉ እንዲሰጡት ቢደረግም በጀግናዉ አንዳርጋቸዉ ላይ እየታየ ያለዉ አልበገር ባይነት በወያኔያዊያን ላይ የበላይነቱን ይዟል።
በተልይም የደህንነት ቢሮዉ ሚስጥራዊና ልዩ ስብሰባ ያካሔደ ሲሆን የእንግሊዝ ባለስልጣናት እራሳቸዉን ከተጠያቂነት ባሸሸ መልኩ በተገላቢጦሹ ታጋይ አንዳርጋቸዉን እንድንፈታ እያስገደዱን ነዉ። ” ሰባዊ መብት ጥሰቱ እስካልቆመና አንዳርጋቸዉ ጽጌ ካልተፈታ ወይም አስቸኳይ የሆነ የአቋም ለዉጥ በኢትዮጵያ በኩል እስካልተደረገ ድረስ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚሰረዝ ማሳስጠንቀቂያ አዘል ትእዛዝ ተሰጥቶናል ” በሚል አጀንዳ ተንተርሶ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድኖች ጭንቅ ዉስጥ ገብተዋል።
እንዳይለቁት እሳት እንዳይዙት መአት!!! ይሏል ይህ ነዉ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

የኢህኣዴግ ውጥረትና የኣቦይ ስብሓት ጭንቅ


ሰሞኑን ኢህኣዴግ በኣዲስ ኣበባ ስብሰባ ማካሄድ ጀምሮ ነበር።
ስብሰባው ከተጠበቀው በላይ ውጥረት የተሞላበትና የድርጅቶች ሞቧደን የታየበት ነበር። ቡዱኖቹ ህወሓትና ደህዴን በኣንድ በኩል፤ ብኣዴንና ኦህዴድ በሌላ መስመር ተሰልፈው ሲወቃቀሱ ነበር።
ሊቀ መንበሩ ሃይለማርያም ደሳለኝ የቡዱናዊ መንገድ ከተመለከቱ በኋላ የኢህኣዴግ ስብሰባ ኣቁመው የድርጅቶቹ በግላቸው ገምግመው እንዲመለሱ በማለት መላው ቀይረው ጉብኝት ለማድረግ ብለው ወደ ምዕራብ ኣፍሪካ ሄደዋል።
በኢህኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ለመሳተፍ የሞከሩት ኣቦይ ስብሓት ነጋና ኣቶ ኣባይ ፀሃየ “ስብሰባው ለኢህኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ብቻ የሚመለከት ስለሆነ ኣዳራሹ ለቃቹ ውጡልን” ተብለው በብኣዴን፣ ኦህዴድ ድርጅቶችና በነ ኣባይ ወልዱ የሚመራው ኣንጃ ተቃውሞ ስለ ደረሰባቸው በብስጭት ሳይወዱ በግድ ከስብሰባው ወጥተዋል።
ኣቦይ ስብሓት ነጋ በራሳቸው የደረሳቸው ጠንካራ ተቃውሞና ህወሓት በኢህኣዴግ የነበረው ተሰሚነት ማሽቆልቆሉ ኣስደንግጧቸዋል።
ለዚህ ጭንቀታቸው መፍትሄ ብለው የመረጡት መንገድ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ፕ/ጀነራል ሳሞራ ዮንስና የብሄራዊ ደህንነት ሃላፊ ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋ በሽምግልና እየያዙዋቸው ይገኛሉ።
የኣቦይ ስብሓት ተማፅኖ “መንግስታችን የቆመው በ60 ሺ መስዋእትነት ነው እያልን የመጣነው ለፕሮፖጋንዳ እንዲመቸን ነው(ህዝቡን ዋሽተነዋል) እንጂ በትጥቅ ትግል የተሰዋው ከ200 ሺ በላይ ውድ የሰው ሂወት ነው” ካሉ በኋላ “ይህ ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለበት ትግላችን እያየነው ወደ ጠላቶቻችን እጅ እየገባ ነው፣ ድርጅታችን ከዚ ውድቀት ለማውጣትና ስርዓታችን ከውድቀት ለማዳን ኣስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ኣለባቹ” የሚል ሓሳብና ተማፅኖ ኣቅርቦውላቸዋል።
በኣዲስ ኣበባ ለስብሰባ የተቀመጠው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ እየደረሰበት ያለው ተፅእኖ ለማብረድ በማሰብ “በትግራይ እየተካሄደ ያለው ልማት የሚቃወም ማንኛውም ሰው ከኣፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ…”የሚል መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።
የኣቦይ ስብሓት በትጥቅ ትግል ስለ ተከፈለው የሂወት መስዋእትነት ለ25 ዓመታት 60 ሺ ሲሉን ቆይተው ኣሁን ደርሰው 200 ሺ ነው የተከፈለው በማለት ስርዓቱ ለማቆየት ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው በመፈለግ ነው።
ስለ ኣጠቃላይ የድርጅቱ ንትርክ መረጃው ሲደርሰን እናካፍላቹሃለን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

እንደ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ዘገባ በኢትዮጵያከሚኖረው ሕዝብ ከአምስቱ አንዱ ርኃብ አደጋ ላይ ነው።


ወገኖቻችን በረሃብ እያለቁ ነው ልንደርስላቸው ይገባል===

እንደ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ዘገባ በኢትዮጵያከሚኖረው ሕዝብ ከአምስቱ አንዱ ርኃብ አደጋ ላይ ነው። ዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት – ዩኒሴፍም ዘገባውን ስያጠናከር በኢትዮጵያ የስድስት ሚልዮን ሕፃናት ሕይወት አደጋ ላይ ነው ብሏል።በሌላ በኩል በከተማ የሚኖረው ሕዝብ የኑሮ ውድነቱጣርያ ነክቶበታል።የብሔራዊ ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው የዋጋግሽበቱ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 12% ደርሷል።ዓለም አቀፍየረድኤት ድርጅቶች የ90 ቀናት የእርዳታ ማሰባሰብያ መርሃ ግብርአዘጋጅተዋል።በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን በይፋእንዳይጠይቁ ታግደዋል። (Ethiopian government stops fundraising campaign by UN agencies) ይህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ወንጀልም ነው።ምግብ ከመኖር ህልውናበላይ የሰብአዊ መብት ጉዳይም ነው። መንግሥታት፣ግለሰቦች እናኩባንያዎች ሰዎች ምግብ እንዳያገኙ ለሚያደርጉት ማናቸውም እንቅስቃሴ እና ኃላፊነት ያለመወጣት ተግባር ሁሉ በሕግእንዲጠየቁ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ
ከተጀመረ ጥቂትአመታት ተቆጥረዋል።

ምግብ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው (Right to food) የሚለውንመመርያ በአገራቸው ለተግባራዊነቱ ሥራ ከሚሰሩት አገራትውስጥ ኤልሳ ልቫዶር፣ዮርዳኖስ እና ህንድ ይገኙበታል።የምግብ መብት ዓለም አቀፍ ሕግ የማድረግ እንቅስቃሴ የመነጨው ከተባበሩት መንግስታት የምጣኔ ሀብት፣የማኅበራዊ እና የባሕል መብት ፅንሰ ሃሳብ ሲሆን እኤአቆጣጠር በ2012 ዓም 160 አገራት ጉዳዩን ከፍ ወዳለ ዓለም አቀፍ ሕግ ቅረፃ ለማሳደግ የመግባብያ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።የመግባብያ ሰነዱ አገራቱ ምግብ የመብት ጉዳይ መሆኑን የሚያሳይ ፖሊሲ በአገራቸው እንዲያወጡ እና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተግባራዊ እንዲሆን ያሳስባል። በእዚህም መሰረት በ20013 እኤአ ህንድ የምግብ መብት ሕግን በብሔራዊ ሕግ ውስጥ አካተተች።ምግብ የመራብ እና አለመራብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መንግሥታት ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግዴታቸውን የመወጣታቸው እና ያለመወጣታቸው ጉዳይም ጭምርም ነው።ለአንድ ሕዝብ ምግብ እንዳይደርሰው ማድረግ ከዘር ማጥፋት ወንጀል እኩል ያስጠይቃል።የምግብ ጉዳይ የኢትዮጵያቴሌቭዥን ሲመቸው ስለረሃብ ሳይመቸው ዘፈን የሚያቀርብበት ጉዳይ አይደለም።በኢትዮጵያ የሰው መብት ከሚታሰበው እና
ከሚገመተው በላይ በአምባገነኑ ስርዓት ስለተረገጠ ጉዳዩን አቅልሎ የማየት አዝማምያ ይስተዋላል።ሆኖም ግን ጉዳዩ ቀላል ጉዳይ አይደለም። የሚወራው ስለ ሚልዮኖች ሕይወት ነው።የተራበው የኖርዌይን ሕዝብ ሶስት እጥፍ የሚሆን ሕዝብ ነው።ይህ ሕዝብ እንደ ምንም ነገር ዝም ሊባል
አይገባም። የምግብ መብት ጉዳይ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ በአገራት የውስጥ ፖሊሲከመግባት ባለፈ መንግሥታት ፍርድ ቤት አስቁሞ አስፈርዷል።በኔፓል1998 የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መንግስቱን ምግብ ለሕዝቡባለማዳረሱ ምግብ እንዲያከፋፍል ፈርዶበታል።በህንድም በተመሳሳይመልክ የእርዳታ ድርጅቶች ተሰብስበው የህንድን መንግስት ለሕዝቡ ምግብባለማድረሱ የሚል ክስ መስርተው አስፈርደውበታል።
በመጨርሻም ምግብ ለሕዝብ እንዳይደርስ የማድረግ ሂደት ከቢሮክራሲያዊድክመት ባለፈ በአገር ውስጥ የሚፈጥረው የውስጥ ቅራኔ ቀላልአይደለም።በአሁኗ በህወሓት የጎሳ ፖለቲካ የተከፋፈለች ኢትዮጵያውስጥ ምግብ እንዳይደርስ የተደረገው አካባቢ ከጎሳ ጭቆና አንፃርሊመለከተው ስለሚችል ጉዳዩ ውስብስብ ችግር ይዞ
መምጣቱአይቀርም።በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት እየደበቀ ያለውን ርኃብበግልፅ በአደባባይ በመቃወም የተሻለ ብሔራዊ መግባባት እና
አንድነትመፍጠር ይችላል።የተራበው አካባቢ ሕዝብ በርቀት የሚኖረው ወገኑእንደሚያስብለት የማሳያው እና ሌላው አንድነትየመፍጠርያ አጋጣሚም
ነው።ስለተራበው ሕዝብ የዩንቨርስቲተማሪዎች፣ምሁራን፣የከተማ ነዋሪዎች እና ገበሬዎች ሁሉ መጮህካለባቸው ወቅቱ አሁን ነው።ሚልዮኖች
ከመርገፋቸው በፊት ለኢትዮጵያሕዝብ እንድረስለት።