Wednesday, March 18, 2015

አንድነት ራስ ምታቱ ነበር ፣ አሁን ደግሞ ሰማያዊ ሆድ ቁርጠቱ ሆነ


የአንድነት አመራር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለዬ በኃላ በተሰጠው የሰባት ቀን እጩ የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች በ80 ምርጫ ክልሎች ተደራሽ በማድረግ 230 እጩዎችን ለማስመዝገብ ችለናል፡፡”
በምርጫ ቦርድ አሰራር፣ ለምርጫ የሚሰጡ የገንዘብ ድጎማዎች ፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ የሚቀርቡ የቅስቀሳ ጊዜያቶችን ፣ ፓርቲዎች ባቀረቡት ተመራጮች ቁጥርና አሁን በፓርላማ ባላቸው መቀመጫ ቁጥር እንዲሆን ነው የተደረገው። ይህ አሰራር በእጅጉ ሕወሃትን እንደሚጠቅም የታወቀ ነው።
በዚህ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ በሚደረገው ምርጫ 7 ጊዜ ለአሥራ አምስት ደቂቃ መቀስቀስ እንደሚችል ተገልጾለታል። «በቂ ባይሆንም ያን ያህል ኢቢሲ/ኢቲቪ መፍቀዱ ጥሩ ነው» ሊያስብል ይችላል። ሆኖም ሕወሃት በአንድ በኩል ሲከፍት በሌል በኩል እንዴት ለመዘጋት እንደሚሞከር እናሳይ፡
1) ሰማያዊ የሚያቀርባቸው የቅስቀሳ መልእክቶች ሳንሱር የሚደረጉ ናቸው። ከስድስት ጊዜ በላይ ኢቢሲ « ይሄን ካላስተካከላችሁ አናስተላልፍም» ብሎ መልሷል። እንድ ጊዜ እንደዉም አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ለም አደረጋችሁ በሚል ነው።
2) ሰማያዊ እንዲያቀርባቸው ከተፈቀደለት ሰባት ፕሮግራሞች አምስቱ እንዲተላለፉ የተወሰኑት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ( በፈረንጆች ነው። ወላጆች ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት ለመላክ ፣ ወደ እስራም ለመሄድ ደፋ ቀን በሚሉበት፣ ብዙዎች ከእንቅልፋቸው ሊነሱ በማይችሉበት ሰዓት ነው ።
የሕወሃቱ ኢቢሲ/ኢቲቪ ሆን ብሎ ሕዝቡ የሰማያዊ ፓርቲን መልእክት ለማዳመጥ እንዳይችል፣ ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ ለማከላከል ለምን ፈለገ ? መልሱ አጭር ነው። ሕወሃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ የፈራበትና በራሱ መተማመን ያልቻለበት ጊዜ ነው።10957136_792113257540277_1007416456643191723_n

No comments:

Post a Comment