Wednesday, March 18, 2015

የታንዛንያ ፖሊስ ሐገሬ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብተው ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው ያላቸውን 63 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ገለጸ


ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በትብብር ባደረገው ዘመቻ ስደተኞቹን ለመያዝ እንደቻለና በሂደቱም አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሕይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል. ስደተኞቹ ሊያዙ የበቁት የአካባቢው ማሕበረሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሆኑም ተዘግቧል.
ዘገባው አክሎም ስደተኞቹ ይጓጓዙበት የነበረው መኪና ተበላሽቶ እንደቆመ. በዚህም ወቅት የመኪናው አሽከርካሪ ስደተኞቹን ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንዲጠብቁት ማድረጉና ከዚያም ጥሏቸው መጥፋቱ ተጠቅሷል.
ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በተያዙበት ወቅት በረሀብ እና በጤና ችግር ተጎሳቁለው እንደነበር; ረሀብ የጠናባቸው አንዳንዶቹም ማሳ ውስጥ በመግባት ረሃባቸውን ለማስታገስ መሞከራቸውን, ሌሎቹም የአካባቢውን ሕዝብ ምግብ ሲለምኑ እንደነበር የዴይሊ ኒውስ ዘገባ ያስረዳል.
source –.diretube77024212

No comments:

Post a Comment