Thursday, March 5, 2015

በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ የሶስት ህፃናትን ሀይወት አጠፋ


ትናንት በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት ከአስር አመት በታች የሆኑ ልጆች ህይወታቸው አለፈ።
እሳቱ ሌሊት 6 ሰዓት ከ 38 ደቂቃ አካባሲ የተነሳ ሲሆን፥ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ሲደርሱ መኖሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ወድሞ ነበር፡፡
ቤት ውስጥ የነበሩትን ሶስት ልጆች የእሳት አደጋ ሰራተኞች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ማውጣት ተችሎ ነበር፡፡
ሆኖም ልጆቹ በከፍተኛ ጭስ ታፍነው ስለነበር እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ዘነበ ወርቅ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም፡፡
በእሳት ቃጠሎ 500 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ የተገለጸ ሲሆን፥ የቃጠሎ መነሻም ተለኩሶ የተረሳ ሻማ እንደሆነ ነው የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የገለፀው።
ህብረተሰቡ ቤት ውስጥ ለእሳት መነሻ ለሆኑ ነገሮች ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ጽህፈት ቤት አሳስቧል።

No comments:

Post a Comment