Wednesday, March 11, 2015

ዛሬ እነ አበራሃ ደስታ ፍርድ ቤት ያደረጉት ነገር ሁሉም የህሊና እስረኞች ሊያደርጉት የሚገባ ነገር ነው!

11035502_771235849624393_3401706099381023667_n
ሲመስለኝ,,,,,
ዛሬ እነ አበራሃ ደስታ ፍርድ ቤት ያደረጉት ነገር ሁሉም የህሊና እስረኞች ሊያደርጉት የሚገባ ነገር ነው!
አዎ ዛሬ እነ አብራሃ ደስታ በማጨብጨባቸው የካንጋሮ ፍርድ ቤቱን ደፍራቹአል ተብለው የ7 ወር እስራት ሲበየንባቸው፣ በድጋሜ በማጨብጨብ ፍርድ ቤቱን በድጋሜ ደፍረውት፣ ለዚህም ድፍረታቸው እንደገና ሌላ እስር ለመወሰን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥተዋል፣ እና ሳስበው ሁሉም የህሊና ፍርደኞች፣ ለተወሰነ ውሳኔ እንደሞኝ ጊዜና ጉልበት ከመጨረስ በቃ እንዲህ ፍርድ ቤቱን በመድፈር እና ፍርድ ቤት ሳይሆን፣ የህወሀት መቀለጃ ቤት መሆኑን ማሳየት ዳኞችም ዳኞች ሳይሆኑ አሻንጉሊቶች መሆናቸው ማሳየት ነው የሚያዋጣው,,,, እስቲ አስቡት አንድ ዳኛ ማዕከላዊ ነው የምልክህ ብሎ አብራሃን ማስፈራራት ምን ማለት ነው ? እንዳላስገርፍህ እያለው እኮ ነው! እና ከነዚህ ዳኞች ምን ዓይነት ውሳኔ ነው የምንጠብቀው? ይህ ለታሪክ የሚባለውም ነገር እርግጠኛ ነኝ ህወሀት ፋይሎችን በሙሉ እንደሚያጠፋቸው። ስለዚህ እንደሚያሾፉብን እናሹፍባቸው ፣ የተወሰነ ፍርድ እስኪነግሩን አንጠብቅ!
• ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ
• ‹‹ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው›› የሺዋስ አሰፋ
• ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፣ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› ዳንኤል ሺበሽ

No comments:

Post a Comment