Wednesday, March 18, 2015

“ኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) የህወሓት የአማርኛ ዲፓርመንት ነው”


የዚህን አባባል እውነትነት/ሐሰትነት ሊያረጋግጡልን የሚችሉት አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በፌስቡክ ላይ አሉ፡፡ ነገር ግን አቶ ያሬድ “ኢህዴን እንደዚያ የሆነው እኔ ከወጣሁ በኋላ ነው” የሚል እይታ ነው ያላቸው፡፡
እኔ አቶ ስየ አብረሃም “ህወሐት የአንድ ሰው አምባገነናዊ ድርጅት የሆነው እኛ ተገፍተን ከወጣን በኋላ ነው” ዓይነት ነገር ሲጠርቁልን ነበር፡፡ አምባገነን የተባለው ሰውዬ አሁን ሞቷል፡፡ እና አሁን ያለው ህወሐት ምን ሊባል ነው?…. አቶ ስዬ “እኛ እንኳን ታሪክ ጦርነት መስራት እንችላለን” በማለት ሲያፈራሩ እንደነበረ የረሳነው መስሎአቸዋል እንበል እንዴ?
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም “ኦፒዲኦ የተበላሸው እኔ ከድርጅቱ አመራር ጋር በ1993 ከተጣላሁ በኋላ ነው” የሚል አነጋገር ይደጋግማሉ፡፡ ወቼ ጉድ! ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ሆይ! እርስዎ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚመረጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያወቀው ገና በታሕሳስ ወር 1987 ላይ ነበር እኮ! ይህም ምርጫው ከመካሄዱ ከአምስት ወራት በፊት መሆኑ ነው፡፡
—-
እነዚህ የቀድሞ አውራዎች “ንስሐ ገብተናል! ከህዝቡ ጋር ወግነናል” ሲሉን ነበር፡፡ ህዝቡም እንደ ዜጋ የመኖር መብታቸውን ተቀብሎታል፡፡ ንስሐውን የእውነት ይሁን የውሸት ማጣራት የኛ ፈንታ አይደለም፡፡ ለራሳቸው ይያዙት፡፡ ይሁንና በየጊዜው የማይገባ ነገር እየለጣጠፉ ይነካኩንና “ዛሬም እንደ ድሮው ሳይሆኑ አይቀሩም” እያልን እንድንጠረጥራቸው ያደርጉናል፡፡

No comments:

Post a Comment