Tuesday, March 31, 2015

አሳዛኝ ዜና በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ከ60 በላይ ቆሰሉ


ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም በዛ ካምፕ ውስጥ የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊን መሆናቸው ግን የታወቀ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሄጄ ካምፑን እንዳየሁት እኔም የማውቀው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ብቻ እንደሚያርፉበት ነው፡፡ የሞቱትን ነፍስ ይማር!!!! የተቀሩት ኢትዮጵያዊያንስ እጣ ፋንታ ምን ይሆን?
ግሩም ተ/ሀይማኖት

ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ተፈተው እንደገና ዛሬ ታስረው ሞጆ ላይ ተለቀቁ


አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ:: ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::
አቶ በቀለ ገርባ 26 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልሳን መምህር የነበረሱ ሲሆን የሰውነት አቋማቸው ግን ገና 26 ዓመታትን የሚሰሩ ያስመስላቸዋል።
የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::
*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት ፖሊሶች ወደ አቶ በቀለ መጡና “መጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይወሰዳሉ” አሉ:: ቤተሰብም አቶ በቀለም ቀልባቸው ተገፈፈ:: ደስታቸው ብን ብሎ ጠፋ!
*በደንጋጤ የተዋጡት ወይዘሮ ሀና ይህንን ጉዳይ ለኦፌኮ አመራሮች አሳወቁ። የኦፌኮ አመራሮች በፍጥነት አቶ በቀለ ይሄዳሉ ወደተባሉበት ቃሊቲ እስር ቤት ተጓዙ።
*ሆኖም ቢጠበቅ-ቢጠበቅ አቶ በቀለ ብቅ ሳይሉ ቀሩ
*አቶ በቀለን ይዘው የነበሩት ጠባቂዎች ታሳሪውን ይዘው ሞጆ አካባቢ ለቀቋቸው።
ውዥንብሩ ለምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ዋናው ደስታው ነውናን ቤተሰባቸው አቶ በቀለ ገርባን ይዞ ወደ አዳማ ናዝሬት ይዞ ሄደ። አቶ በቀለና ሴት ልጃቸ ቦንቱን ኢሳት በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::
በካንጋሮው የሕወሓት ፍርድ ቤት “በሽብርተኝነት” ክስ ጥፋተኛ ተብለው 3 ዓመት ከ7 ወር የተፈረደባቸው አቶ በቀለ በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 5 ዓመት ማስደረጋቸው ይታወቃል:: በየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ በኣመክሮ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም መከልከላቸው ይታወሳል:: እስር ቤትም ህክምናም ሳያገኙ ብዙ ተሰቃይተዋል:: አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::10956995_1805760096315126_4661105567449755265_n

Monday, March 30, 2015

የመረጃ ግብአት … በ5 ኛው ቀን ዘመቻ …በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል


የመረጃ ግብአት … በ5 ኛው ቀን ዘመቻ …
የዘመቻ ” ወሳኙ ማዕበል ” አበይት ክንውኖች ዳሰሳ !
================================
* በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል
* የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል
saudi vs yemen
* ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል
* በጦርነቱ መካከል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ። በጥብቅ በታጠረው የሳውዲ ድንበር ወዲህና ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጦረነቱ እሳት መካከል በአጣብቂኝ ውስጥ ስለ መሆናቸው በግል የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ
* በሳውዲ የመን ድንበር በባህር ጠረፎች ከፍተኛ የእግረኛና የባህር ኃይል ሰራዊትና የሜካናይዝድ ጦር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል
* በሳውዲ ድንበር ፣ በጀዛን እና በኤደን የባህር ወሽመጥ በባብ አልመንደብ አካባቢ የባህር ኃይልና የምድር ጦር ዝግጅቱን አስመልክቶ የተጠየቁት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ” በጦርነት ውስጥ እያለህ ይህ መሰሉ ዝግጅት የተለመደ ነው! ” ብለው መልሰዋል
* የምድር ጦር በሚመለከት በአንድ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዠን የተጠየቁት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ በሳውዲ በኩል የምድር ጦር ለማዝመት እስካሁን ውሳኔ አለመደረሱን ጠቁመዋል
* የየመን ፕሬ አብድልረብ መንሱር በሳውዲ ስደት ላይ ሆነው በኢምሬት የየመን አንባሳደር አድርገዋቸው የነበሩትን አህመድ አሊ አብደላ ሳላህን ከስልጣን አባረሩ ። አህመድ አሊ በአባታቸው የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የጦር መኮነን ነበሩ ። በኢምሬት አምባሳደር የተሰጣቸው በፕሬ አብድልረቡ ሲሆን ከነበሩበት ቁልፍ የጦር መሪነት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦታ ለማሸሸት ታስቦ ነበር ። አህመድ የፕሬ አብድልረቡ ወዳጅና የአሁን ሁነኛ ባላንጣቸው የሆኑት የቀድሞው ፕሬ የአሊ አብደላ ሳላህ የብኸር ልጅ ናቸው ፣ ከቅርብ ወራት ጀምሮ አህመድ ከአባታቸው ጋር ሆነው ፕሬ አብድልረቡን ለማውረድ የሁቲ አማጽያንን በመደገፍ መሪውን አሽቀንጥረው የመንን ለዛሬ መከራ እንደዳረጓት ይወነጀላሉ
* ባሳለፍነው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2007 በግብጽ ሻርማ ሸክ የተደረገው የአረብ ሊግ ስብሰባና ውጤቱ የአረብ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው እየተዘገበበት ይገኛል
* እዚህም እዚያም የቃላት ጦርነቱ ተጋግሟል …
===========================
* የሁቲ አማጽያን የሳውዲ መራሹን የጦር አውሮፕላን ጣልን ይላሉ ፣ የሳውዲ መራሹን ጦር ቃል አቀባይ በአንጻሩ የሁቲ አማጽያን ከዚያ የሚያደርሰውን አቅም በመጀመሪያ ቀን የአየር ድብደባ ብቻ አክሽፈነዋል በማለት በተዋጊ ጀቶቻቸው ላይ ጥቃት አለመድረሱን በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል
* በየመን የሁቲ አማጽያንን በሳውዲ መራሽነት የተጀመረው የአየር ድብደባ እንዲያቆም ከሚፈልጉት ሀገራት መካከል ቀዳሚ የሆነችው የራሻው ፕሬ ፑቲን ለአረብ ሊግ ስብሰባ በላኩት ደብዳቤ አረብ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ሰላምን ለማምጣት ከጦርነት ውጭ ያለውን የሰላማዊ መንገድ አማራጭ ይጠቀሙ ዘንድ መክረዋል
* የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዑድ አል ፈይሰል ግን የፑቲንን መልዕክቱን ተቃውመዋል ። በኢራን የሚደገፈውን በሶርያ የአሳድን መንግስት የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ በራሽያ ስንቅና ትጥቅ ይደገፋል ሲሉ የራሻን ተቃርኖ መንገድ ላይ የሰላ ሂስ ያቀረቡት ልዑሉ የራሻው ፕሬ ፑቲን ከአረብ ሀገራት ጋር የቆየ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ንግግራቸውን አርመው አቋማቸውን ይፈትሹ ዘንድ አሳስበዋል።
* ከኢራን እርዳታ በማግኘት የሚታሙት የሽምቅ ተዋጊው የሀማስ መሪዎች ሳውዲን ጭምሮ የ10 አረብ ሀገራትን ዘመቻ ሲደግፉ የኢራንና የሶርያ መንግስት ደጋፊ የሊባኖሱ የሂዝቦላህ መሪ ሸህ ሀሰን ነስርአላህ የሳውዲ መራሹን ዘመቻ በማውገዝ በተለይ በሳውዲ መንግስትን መወረፋቸው የሳውዲን መንግስት አስቆጥቷል
* በሊባኖስ የሳውዲ አምባሳደር አሊ አዎድ አሲሪ ጭብጥ የሌለው ሀሰት ነው ያሉት የሂዝቦላሁ ሀሰን ነስርአላህ ንግግር ሂዝቦላህ የሚወክለውን የኢራን አቋም የተንጸባረቀበት አሳሳች መልዕክት እንደሆነ ለአረብ ኒውስ አስረድተዋል
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።


በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።
በብሔራዊ የደህንነት መዋቅር ውስጥ መሰላቸት፣ አለመተማመን፣ ጫና እንዲሁም ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ የሚደረግባቸው ክትትል ጤና የነሳቸው ተበራክተዋል። በተለይም የህወሃት ያልተማሩ ነባር /አንጋፋ ባለሥልጣናት/ ታጋዮች የሚሰጡት ቅጥ ያጣ መመሪያና ወሬ ለቃሚዎቸ ከየመንደሩ ለብር እያሉ የሚያቀረቡት የሰላማዊሰዎችን ህይወት የሚያናጋ መርጃ ዕረፍት እንደነሳቸው የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።
“በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ተቀምጠው የሚያገለገሉ ባብዛኛው ደስተኛ አለመሆናቸው በገሃድ ስለሚታወቅና የመውጫው ቀዳዳ ስለተዘጋ” በሁሉም አቅጣጫ መሹለኪያ ፈላጊውና በሰላም መኖር የሚመኘው ክፍል እንደሚያይል ያመለከቱተ ዜና አቀባዮች “የኢህአዴግ ዙሪያ መለሱ ቆሽሾዋል፤ የእርስ በርስ መተማመኑም ኮስሷል” ብለዋል። በማያያዝም በርካታ አመራሮች አገር ለቅቀው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (ሚያዚያ 2፤2006ዓም/April 10,2014) “ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው፤ “አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል”” በሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለአንባቢያን እንዲረዳ ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ።
ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው “በደህና ጊዜ ተገላገልክ” በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው።
የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች “አሁን ያለው ኢህአዴግ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል” በማለት አንድ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ እያገለገለ ያለ የቀድሞ ጓደኛቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ለስራ እንኳን ካገር መውጣት የማይችሉ ባለስልጣኖች እንዳሉ ዘጋቢያችን አመልክቷል። በተቀመጡበት ሃላፊነት ወደ ውጪ የሚያስኬድ አጋጣሚ ሲኖር የሚከለከሉ እንዳሉም ያገኛቸውን መረጃዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ለሃላፊዎቹ ደህንነት ሲባል የሚሰሩበትን ተቋምና ስም መናገር እንደማይችሉ በመጥቀስ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች “ባለስልጣኖቹ በመካከላቸው እርስ በርስ መተማማን ስለማይችሉ ችግራቸውን መወያየት እንኳን አይችሉም” ብለዋል፡፡“በጣም የሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ገንዘብ ወደ ውጪ እንድወስድላቸው እስከመጠየቅ ደርሰዋል” ሲሉ የገለጹት የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣን፣ ፓርቲው በሙስና ስም ያካሄደው የሽግግር ወቅት የማጥራት ርምጃ የፈጠረው ስሜት አሁን ድረስ እንዳለ ጠቁመዋል።
ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ያቀኑ የቀድሞ የኢህአዴግ ሰው በማግኘት ተመሳሳይ መረጃ ያሰባሰበው ዘጋቢያችን “ኢህአዴግ በከፍተኛ የመበስበስ አደጋ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ካድሬው ተዥጎርጉሯል” ሲል ሪፖርት አድርጓል። ኢህአዴግ በውስጥ ያለበትን ችግር ለማድበስበስ የአባይ ግድብ ላይ ትኩረት በመስጠት “የንቅናቄ ሃይል” በማስፋፋት ላይ እንደሆነም ጠቁሟል።
ድፍን ህዝብ የአባይ ግድብን አስመልክቶ ያለው ስሜት በበጎ መልኩ የሚታይ በመሆኑ ኢህአዴግ ይህንኑ የህዝብ ስሜት ለቅስቀሳና ለበሽታው መደበቂያ ለማድረግ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተጠቁሟል። የህጻናት ፕሮግራሞች ሳይቀሩ አባይ ላይ ያነጣጠሩ ቅስቀሳዎች እያስተላለፉ መሆናቸውን ያመለከቱት ሰው፣ “ስለ አባይ ግድብ የሚባለውና የሚሰራው ፕሮግራም ችግር የለውም። በአግባቡ ቢሰራበት ብሔራዊ ስሜት ሊገነባበትም በተቻለ ነበር። ይሁን እንጂ ዓለማው የችግር ማለባበሻ እንዲሆን መደረጉ ነው” ብለዋል።
“መለስ ኢትዮጵያን ቢወድ ኖሮ ከባድመ ጦርነት በኋላ የፈረሰውን ብሔራዊ አንድነትና መግባባት መልሶ መትከል ይቻል ነበር” በማለት የተናገሩት እኚሁ ሰው “በወቅቱ ይህንን ሃሳብ ያነሱ ሰዎች ነበሩ” ሲሉ ቁጭታቸውን ይሰነዝራሉ። በማያያዝም ኢህአዴግ የአባይን ግድብ ተንተርሶ ብሔራዊ አንድነት የሚገነባበት፣ መቀራረብና በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ብሔራዊ መግባባት የሚደረስበት፣ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጣልበት ቢያደርገው እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ለመተካት ህዋሀቶች የሚያደርጉት ሽርጉድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርት መቅረቡ ተሰምቷል። ይኽው ሪፖርት የቀረበላቸው ክፍሎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት የህወሃትን ከፍተኛ አመራሮች በማነጋገር ስህተት እንዳይሰሩ እየወተወቱ ነው።
source:ጎልጉል

ኢትዮጵያዊቷ የISIS ሙሽራ እና “ጽንፈኛ” ሆነው የተገኙት አባቷ


አስደንጋጭ ዜና ነው። ራሱን የእስልምና ግዛት ISIS ብሎ የሚጠራው አክራሪ እና ጭራቂዊ ቡድንን ለመቀላቀል ከሁለት ጓደኞቿ ጋ ከለንደን ወደ ሶሪያ የሄደችው የ15 ዓመቷ አሚራ አባት የሆኑት አቶ አባስ ሁሴን Innocence of Muslims የሚለው ፊልም እስልምና እምነትን አዋርዷል በማለት በለንደን አሜሪካ ኤምባሲ ፊት-ለ-ፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ አሜሪካ ትቃጠል፣ ሙስሊም ክሩሴድን ያጠፋል አሜሪካንና እንግሊዝን ጨምሮ…. የሚሉ መፈክሮች ጀርባ በስሜት መፈክር ሲያስተጋቡ የሚታዩበት ቪዲዮ ይፋ ሆኗል።
መፈክር ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንና እስራኤል ባንዲራ ሲቃጠል አቶ አባስ አጃቢ ናቸው።
ልጃቸው ወደ ሶርያ ለመግባት በቱርክ በኩል ስታቋርጥ በካሜራ እይታ ውስጥ ከገባችና ሁኔታው በእንግሊዝ መንግስት በገሊ ከተነገረ በኋላ አቶ አባስ የእንግሊዝን ፖሊስ ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ በብሪታኒያ ፖሊስ ማዕከል ስኮትላንድ ያርድ ቃለምልልስ ሲሰጡ ልጃቸው ስለአክራሪነት ፈጽሞ የምታውቅበት መንገድ ይፈጠራል ብለው እንደማያምኑ ሳግ እየተናነቃቸው ሲናገሩ ሰምተናል።
ነገር ግን አሁን ቀስቱ ወድሳቸው ዞሯል። ከ3 ዓመታት (2012) በፊት የዛሬን ጦስ ሳያስቡት እንግሊዝን ባስበረገገው የጽንፈኞች ሰልፍ ላይ ተዋናይ መሆናቸው በቀላሉ የማይታይ፣ ለልጃቸው የISIS ነፍሰ ገዳይ ለመሞሸር ድንበር ማቋረጧ በቀጥታ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው። አሜሪካንም ሆነች እንግሊዝ ጉዳዩን በቀላሉ አያዩትም። ለዚህ ምክንያቴ አቶ አባስ:–
1. የአሜሪካኑን 911 እና የእንግሊዙን 7 July 2005 የሽብርተኞች ጥቃትን በአደባባይ የደገፈው ብሪታኒያዊው አካራሪ፣ አክቲቪስትና የሙስሊም ማህበረሰብ ጠበቃዎች ሊቀመንበር አንጀም ቾዳሪ የመራው ሰልፍ ላይ መገኘታቸው
2. በዛ ሰልፍ ላይ ከታደሙት መካከል Michael Adebowale የተባለ ወጣት ከዚያ የጽንፈኞች ሰልፍ አንድ ዓመት በኋላ የብሪታኒያን ወታደር Lee Rigbyን በደቡብ ምሥራቅ ለንደን በጠራራ ፀሐይ በመኪና ገጭቶ በስለት ወጋግቶ የገደለ መሆኑ
ልጃቸውን ከማጣታቸው ጋር ተደማምሮ የአቶ አባስን ቀጣይ ሕይወት መሪር ያደርገዋል።
ሆኖም ሰው የዘራውን ማጨዱ አይቀርም ቢባልም በልጃቸው ማንነት ላይ የነበራቸውን ሚና እርግጠኛ ሆኖ መናገር አዳጋች ነው።
ሆኔታው ግን ለጅምላ ፈራጆች ትልቅ ሲሳይ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴን በጎሪጥ ለሚያዩ ሰዎች፣ ህወሓት የሚሰራው ፕሮፓጋንዳ ለኀይማኖታቸው፣ ለብሔራቸው… በሚመች መልኩ በትሪ ጠረጴዛቸው ላይ ቁጭ ሲቀርብ ተስገብግበው ለሚሻሙ ሰዎች ለቁንጽል መረጃቸውና ድምዳሜያቸው ግዙፍ ርዕስ አግኝተዋል።
ድምጻችን ይሰማ በዚህ ውዥንብር ሳይደናገር ላለፉት 3 ዓመታት ያሳየንን ሰላማዊ እና ስልጡን ተቃውሞ እንደሚቀጥል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም።
Kassa Hun Yilma10403460_969626446381572_5554302589652916277_n

በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ማሰር እንደሚከለከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው አስታወቁ!


በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ማሰር እንደሚከለከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው አስታወቁ!
የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖና የፀረ አክራሪነት አጀንዳ ተገን
በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ርእዮታዊ
እና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን በማስተጋባት የሚታወቁት ሚኒስትር
ሺፈራው፣ ይህን መናገራቸው የተጠቆመው፣ ከነሐሴ 18ቀን 2006 ዓ.ም.
ጀምሮ እስከ መስከረም 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በዘለቀውና በኹለት ዙሮች በተካሔደው የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ ነው፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደውና 800 ያህል መካከለኛ አመራሮች
በተሳተፉበት የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ
መንግሥት ግንባታና ፈተናዎቹ›› የሚለውን ሰነድ የሚያብራራና በፓወር
ፖይንት የተደገፈ ጽሑፍ ያቀረቡት ሚኒስትሩ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ መነሻ ያደረገ ነው የተባለ ጥያቄ ከአንዲት ተሳታፊ ቀርቦላቸዋል፡፡
እንደ ስብሰባው ምንጮች፣ የተሳታፊዋ ጥያቄ፣ ‹‹በቢሮ ፊታቸውን
ተሸፍነው የሚመጡ ሙስሊሞችን አለባበሳቸው ከቦታው አንፃር ያለውን ተገቢነት በማንሣት እንዲያወልቁ ስንጠይቃቸው ‘እኛ ይኼን የምናወልቅ ከኾነ ኦርቶዶክሱም ክሩን ይበጥስ’ ይሉናል፤ ይኼን እንዴት ነው የምንታገለው?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹መንግሥታችን ሴኩላር ነው›› ሲሉ በጠያቂዋ የተጠቀሰውን ዐይነት
አለባበስ የተቹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ማተቡም ቢኾን የጊዜ ጉዳይ
ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤›› የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተገልጧል፡፡
ማዕተብ÷ የሲኦል መሠረት የተናወጠበት፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ለዘመናት ለያይቷቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበት፣ የሞት ኃይሉ ተሽሮ የትንሣኤ መንገድ የተከፈተበት መስቀል ትእምርት በመኾኑ በተሳሳተ የሴኩላሪዝም ግንዛቤ ‹‹ማዕተቡም ሊወልቅ ይችላል›› ማለት፣ ‹‹ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፤ ጉዳዩንም ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ታሪካዊ ትውፊት እንደማፋለስ የሚታይ ነው!
ሁላችንም ምዕመናን ማዕተባችንን ጠበቅ በማድረግ ለእምነታችንን ያለንን ፍቅር እስከ መስዋዕትነት የምንገልጽበት ጊዜ ቀርቧል!
ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ
እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ
ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋላኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽቱ
የተዋህዶ ልጆች አሁነ ነው ሰዓቱ
አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ሚስጢር
ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የጥንት ነሽ የአናትና አባቴ
ማህተቤን አለበጥስም
ትኖራለች ለዘላለም!
ሼር በማድረግ ለሁለም ሰው መረጃውን እናድርስ!!

በየመን ኢትዮጵያውያኖች በጭንቅ ላይ ናቸው


ግሩም ተ/ሀይማኖት (ከየመን)ISIS_organs
ረቡዕ ሌሊት 8፡30 ላይ የተጀመረው የአየር ድብደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የመን ነዋሪ የሆነ ሁሉ በፍርሃት ርዷል፡፡ በተለይ በትላንትናው ሌሊት የነበረው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡ ላይ የጣለው ፍርሃት ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ “በሁቲይን አማጽያን ሚሊሻ ላይ የተጀመረው የአየርጥቃት አሁንም በድርድሩ ካልተስማሙ ወይ ሰነዓ ከተማን ለቀው እስካወጡ አያቆምም!” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ገልጸዋል፡፡ ይህን አባባላቸውን ተከትሎ እግረኛ ሰራዊትም ሊንቀሳቀስ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ 20.000 እግረኛ ወታደር ተዘጋጅቶ ድንበር ላይ መሆኑን የየመን መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ተጀምሮ የነበረውን ድርድር እንዲቀበሉ ለሁቲይን አማጺዎች ከትላንት ወዲያ የ3 ቀን እድሜ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉትም፡፡
በሳዑዲ ሰብሳቢነት የአረብ ሊግ ሀገራት መንግስታት በየመን ጉዳይ ለመመከር ግብጽ ሻርማ ሸኸ ተሰብስበው ነው ያሉት። በዚህ ስብሰባ ላይ የአየር ጥቃቱ የዘመቻ መሪ ሀገር የሳዑዲ አረቢ ንጉስ ሰልማን ሀቲይን የተባሉት አማጽያን ለቀው እስኪወጡና የመን እስክትረጋጋ ድረስ የተጀመረው ጥቃት ቀጣይ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት የየመኑ ቶውራ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የየመኑ መሪ አብድረቡ መንሱር ሀዴ ተገኝተዋል፡፡ ህዝቡ ግን ሀገራችንን እያስደበደበ ያለው ፕሬዘዳንታችን ነው በማለት ጥስ እየነከሰባቸው ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላ ድርድሩን እንደሚቀበሉ ቢገልጹም ተቀባይነት ያገኙ አይመስልም፡፡
ዛሬ ሌሊት በሳውዲ የተመራው የአስሩ ሀገራት ህብረት ጦር በሰንዓ ፈጂ አጣን የተባለው ቦታ ጋራ ላይ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ያለ የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ማውደሙ ታውቋል፡፡ ይህ የመሳሪያ ክምችት በተመታበት ወቅት መላ ከተማው የተርገደገደበት የመሬት መንቀጥቀጥ አይነት ሁኔታ ነበር፡፡ አንዳንድ ህንጻዎች መስታዎታቸው ሁሉ ርግፏል፡፡ ነዋሪው ሲነጋ እንቅልፍ አጥቶ መደሩ ዋነኛው ርዕስ ነበር፡፡ በተለይ ስደተኛ ኢትዮጵያዊን ከፍተኛ ፍርሃት ተውጠን እንዳለን በርካታ ያናገርኳቸው ወገኖቼ ገልጸውልኛል፡፡ በእርግጥ ሌላውስ ወገን የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት እያሰባቸው ይሆን?
የተመታው ካምፕ ላይ የሚቃጠለው መሳሪያ ፍንዳታም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከሌሊቱ 8፡20 ጀምሮ ጠዋት ድረስ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ነበር፡፡ የሁቲይን አማጺያን ድብደባውን በዝምታ እያዩት አይደለም፡፡ ከየአቅጣጫው በአየር መቃወሚያ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ እንደ አባባላቸው ከሆነ የአየር ጥቃቱን ከሚያደርሱት ጀቶች እስካሁን ሁለት መምታታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ሌሊት ሰነዓ ላይ ድብደባው ቀነስ ቢልም ሁዴዳና ሌሎች ደቡባዊ የመን ላይ ጠንከር ያለ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሁቲይኖቹም ከየአቅጣጫው የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራቸው በዛሬው ሌሊት ቀንሶ ታይቷል፡፡ ሰነዓ ያለ ኢትዮጵያዊ በጭንቅ ውስጥ ሲሆን አደን የተባለው ሁለተኛ ከተማ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቡ ነው፡

ከአፍሪካ በምሁራን ፍልሰት ቀዳሚ መሆኗ በጥናት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ ምሁራኗን መግፋት ቀጥላለች።


የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሣይንስ መምህር ዶ/ር መረራ ጉዲና እና የፍልስፍና መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋን ማባረሩን በይፋ ገለፀ።
===================================
የዩንቨርስቲ ምሁራን ለእረጅም ጊዜ በማስተማር እና በምርምር በቆዩ ቁጥር የበለጠ ተፈላጊ እየሆኑ እንደሚሄዱ ይታወቃል።ልምድ፣የማስተማር ጥበብ እና የምርምር ችሎታ በአገልግሎት በቆዩባቸው ጊዜያት ሁሉ መምህራኑ የሚያዳብሯቸው ክህሎቶች ናቸው።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የፖለቲካል ሣይንስ መምህር ዶ/ር መረራ ጉዲና እና የፍልስፍና መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋን ከስራ ሲያባርር የሰጠው ምክንያት ”መብቴ ነው” ከማለት ያልተለየ ነው።ዶ/ር መራራ ጉዲና ለእረጅም ዓመታት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ያስተማሩ፣በተማሪዎች መካከል በሚነሱ የጎሳ ግጭቶች ተማሪዎቹን በመምከር ታላቅ ሃገራዊ ሥራ የሰሩ፣በዩንቨርሲቲው እና በተማሪዎች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን ሲዳኙ የኖሩ ምሁር ናቸው።
ዶ/ር መራራ የፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን ዩንቨርስቲው እንደያዘባቸው ለኢሳት በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወቃል።ዶ/ር ዳኛቸው ባለቤታቸውን እና ልጃቸውን ትተው ከስድስት ዓመት ላላነሰ ጊዜ ከቤተሰብ ተለይተው ለሀገሬ አስተዋፅኦ ላድርግ ብለው ደፋ ቀና የሚሉ ምሁር ናቸው።
ዛሬ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ”ማባረር መብቴ ነው” መሰል መግለጫ ሲሰጥ ብዙ መምህራን አሉኝ ማለቱ ህዝብን አስገርሟል።።
ኢትዮጵያን ያህል ለድህረ ምረቃ ትምህርት ወደውጭ ከምትልካቸው ተማሪዎች ከአስሩ ስምንቱ የሚቀሩባት ሀገር ሌሎች አስተማሪዎች ስለበዙልኝ የረጅም እድሜ ያስቆጠሩትን ዶ/ር መራራን እና ዶ/ር ዳኛቸውን አባረረኩ ማለቱ ከፌዝ ያነሰ አነጋገር አይደለም።
ኢህአዲግ/ወያኔ ስልጣን እንደያዘ መጀመርያ ስራውን የጀመረው ከአርባ በላይ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህራንን በማባረር መሆኑ ይታወሳል።

የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ .


ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !
የዛሬዋን አጠር ያለች የማለዳ ወጌን እንድሞነጫጭር ምክንያት የሆነኝ ትናንት መጋቢት 20 ቀን 2007 የልጆች ምርጫ Nickelodeon’s 28th Annual Kids’ Choice የተሰኘውን አመታዊ የሽልማት ስነ ስርአት አዋርድ በማሸነፍ ተሸላሚ የሆነችው የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ሽልማት አይደለም። ሰብዕናዋ ፈቅዶ የዘራችው አጎምርቶ ለደስታዋ ድርብ ደስታ መሆኑን በማየቴ እንጅ …ቅዱስ መጽሐፉ ” የዘራቸውን ታጭዳላችሁ! ” እንዳለው ከመከራው ኑሮ አቅፋ ደግፋ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በአሳዳጊ እናታቸው አንጀሊና ጆሊ ማሸነፍ እየፈነደቁ ሲያቅፉና ሲስሟት የተሰማኝ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ያህል ነበር ብዕሩን መጨበጤ …
የተጨበጨበላት ድንቋ የፊልም ተዋናኝ ፣ ደራሲና በጎ አድራጊዋ አንጀሊና ጆሊ ሽልማቷን ስትቀበል ባሰማችው ንግግር ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” ነበር ያለችው … አዎ ልዪነተ መልካም ነገር ነው ! አንጀሊና እንዳለችው ልዩነት መልካም ነገር ነው ፣ ልዩነት ጌጥ መሆኑን አምኖ በሚያስማማው ነገር ተስማምቶ መኖር ይቻላል ።
አንጀሊና እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2005 ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በጉዲፈቻ ወስዳ ያሳደገቻት ዘሐራ ተለውጣለች ። እነሆ አሳዳጊ እናቷ ስትሸለም ከእቅፍ ወርዳ ከጎኗ ተቀምጣ ደስታዋን የምትጋራ የጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት አድምቃታለች ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” እኔም እላለሁ በፍቅር እንድትዋጅ ፍቅርን ስጥ … ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ”
ደስ ሲል: )
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም
Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.Nebiyu Sirak's photo.

Thursday, March 26, 2015

(ዜና ፎቶ) የኦሮሞን ሕዝብ “ልክ እናስገባዋለን” ያሉት አባይ ጸሐዬ በኦህዴድ ስብሰባ ላይ እንቅልፋቸውን ተኙ


በቅርቡ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ማስፋፋት ተከትሎ የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞና መንግስታቸው ሕዝቡን በመግደል ጭምር እርምጃ በመውሰድ ተቃውሞውን ለማርገብ የሞከሩት የሕወሓቱ ቁልፍ ሰው አባይ ጸሐዬ ካሁን በኋላ የኦሮሞ ሕዝብ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ጥያቄ ቢያነሳ “ልክ እናስገባዋለን; ያሰብነውንም እናደርጋለን” ማለታቸው በድምጽ ወጥቶ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ እና በተለያዩ ድረገጾች ላይ መውጣቱ አይዘነጋም:: ሕወሓቱ አባይ ጸሀዬ ከኦህዴድ አመራሮች ጀርባ ሆነው የኦሮሚያ ክልልን የሚያሽከረክር ሲሆን ሰሞኑን ኦህዴድ 25ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዓል ተገኝተው ነበር:: አባይ ጸሐዬ ሕዝቡን ልክ እናስገባዋለን ማለታቸው ሳያንስ የንቀታቸው ንቀት በስብሰባው ላይ የኦህዴድ አመራሮች ንግግር ሲያደርጉ እንቅልፋቸውን ለጥጠውታል:: ይህም በፎቶ ግራፍ  ተካፈሏቸው:-abay-Tsehaye1 abay-Tsehaye

ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ግንባታን በየደረጃው የሚቆጣጠረውን ስምምነት ፈረመች


ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በጋራ የፈረሙት አዲሱ ስምምነት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ በሙሉ ነጻነት የምትሰራውን ስራ እንደሚገድብ ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው ሰነድ አመልክቷል።
ሰነዱ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት በምታደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴና በየትኛውም የግንባታ ደረጃ ላይ አለማቀፉ አጥኝ ቡድን ለሚሰጠው አስተያየት ተገዢ በመሆን እንድትተገብር ይገልጻል። አጥኝ ኮሚቴው የግድቡ ግንባታ የግብጽንና ሱዳንን የውሃ ድርሻ መጠን
ይቀንሳል ወይም በግብጽና ሱዳን አካባቢያዊ ሁኔታ ላይ ተጽአኖ ያመጣል የሚል ድምደማ ላይ ከደረሰ ካሳ እስከመክፈል የሚያደርስ ግዴታም መጣሉ ተመልክቷል።Blue-Nile-2
አጥኚ ቡድኑ የመጨረሻውን የጥናት ውጤት ይፋ ካደረገ በሁዋላ ሶስቱም አገራት እንደሚቀበሉት የተስማሙ ሲሆን፣ ምናልባት አጥኝ ቡድኑ ግድቡ በግብጽና ሱዳን ላይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ያስከትላል ብሎ ቢወስን ኢትዮጵያ የግድቡን ቅርጽ እስከመቀየር ልትደርስ ትችላለች።
ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ፣ ከግብጽና ሱዳን የውሃ ማጠራቀሚያዎችን የሚጎዳ ከሆነም ኢትዮጵያ አገራቱን ፈጥና የማሳወቅና ለውጥ ማድረግ እንደሚኖርባትም ስምምነቱ ይገልጻል።
የስምምነቱ አብዛኛው ክፍል ኢትዮጵያ ስለምትፈጽማቸው ግዴታዎች ትኩረት ያደረገ ነው። ግብጽና ሱዳን ለአባይ ወንዝ የሚያበረክቱት የውሃ ድርሻ ካለመኖሩ አንጻር ስምምነቱ በዋነኝነት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን መብት የሚገድብ ብቻ ሳይሆን፣ የአባይ ግድብ
ግንባታ እጣ ፋንታን ከኢትዮጵያ እጅ አውጥቶ በአለማቀፍ አጥኚዎች እጅ እንዲሆን የሚያደርገው ነው በሚል ትችት እየቀረበበት ነው።
ይሁን እንጅ ሶስቱም አገራት ስምምነቱን በማወደስ ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ


• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹አማራጫችን እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
10854971_685322414926753_8423503827339637126_o10854971_685322414926753_8423503827339637126_o

ድምፃችን ይሰማ 2ኛውን የሰላማዊ ተቃውሞ ይፋ አደረገ * “ሳንቲም በመሰብሰብ በራስ ላይ እቀባን በማድረግ ለመንግስት ተቃውሞን መግለጽ”


2ኛው አነስተኛ የትብብር መንፈግ ተቃውሞ መርሃ ግብር
ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ
ረቡዕ መጋቢት 16/2007
በሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ትብብር የመንፈግ እና የቦይኮት ተቃውሞ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ሳይፋጠጡ እና አካላዊ ግጭት ውስጥ ሳይገቡ ትብብርን በመንፈግና የቦይኮት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በደል እያደረሰ ለሚገኘው አካል የተቃውሞ መልእክት የማተላለፍ ስልት ነው፡፡ የትብብር መንፈግ ተቃውሞዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓይነቶች ያሏቸው ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ የሚገባንን የዜግነት መብት እስክናገኝ ድረስ ለመታገል ቆርጠን በገባንበት ታላቅ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ካሁን ቀደም እምብዛም ሳይሞከር ቆይቷል፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቃውሟችን ወደቦይኮት እና ትብብር የመንፈግ ስልቶች እንደሚሸጋገር፣ ይህም አደባባይ ተኮር በሆኑ ተቃውሞዎች የገዛ ህዝቡ ላይ ጥይት ለመተኮስ የማያመነታው መንግስት ጡጫ እንዳያሳርፍብን ለመከላከል እንደሚያስችል መገለጹ ይታወሳል፡፡ እስካሁንም በጥቂት አጋጣሚዎች በቀኑ ክፍለ ጊዜ ስልክን በማጥፋት እና በአስገዳጅ ሁኔታዎች ውስጥ ካልሆነ ባለመጠቀም ውስንና አነስተኛ የቦይኮት ተቃውሞን በኢትዮ ቴሌኮም ተቋም ላይ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ አሁን ደግሞ ትንሽ ከፍ ያሉ የትብብር መንፈግ ስልቶችን ቀስ በቀስ ወደመላመዱ እና ወደመተግበሩ፣ ቀስ በቀስም ወደማሳደጉ መግባት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ባለፈው ጁሙዓ እየገባንበት ያለውን የትግል ስልት ስኬታማ እንዲያደርግልን እና መሪዎቻችንንም ከእስር ነጃ እንዲልልን በአገሪቱ በሚገኙ መስጂዶች ተሰባስበን ዱዓ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ከፊታችን ጁሙዓ መጋቢት 18/2007 ጀምሮ ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ወደማስተላለፍ እንቅስቃሴ የምንገባ ይሆናል፡፡
መንግስት በገዛ ህዝቦቹ ላይ በሃይማኖታችን ምክንያት እያደረሰብን የሚገኘው ከፍተኛ በደል የሚሳለጠው ከእኛው በሚሰበሰብ ግብር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ህዝቡን እየደበደቡ እና እየገደሉ ያሉት የመንግስት ኃይሎች ደሞዛቸው የሚከፈለውም ከህዝቡ ኪስ በሚወጣ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም እንደዜጋ ገንዘባችንን በራሳችን ላይ ኢንቨስት ያለማድረግ የዜግነት መብታችንን በመጠቀም የሳንቲም ዝውውሩ ላይ እጥረት ስንፈጥር በእርግጥም ከእኛ ኪስ የሚገኘው ገንዘብ ላይ እኛም እንደህዝብ የተወሰነ ስልጣን እንዳለን ለመንግስት ግልጽ እናደርጋለን። ጥያቄዎቻችንን ባለመመለሱም የተቃውሞ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት አንዲትን ሳንቲም ከዓለምአቀፍ የገንዘብ አምራች ተቋማት ሲያሰራ ከዋጋዋ በላይ አውጥቶባት ነው፡፡ ለሳንቲም ማሰሪያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ በመሆኑም ሳንቲም ዝውውሩ ላይ ችግር ሲፈጠር ከፍተኛ ጫና ይደርስበታል፡፡ ምናልባት መንግስት ክፍተቱን ተጨማሪ ሳንቲም በማተም ለመሙላት ቢሞክር እንኳን የሰበሰብነውን ሳንቲም መልሰን ወደ ገበያው በማስገባት የዋጋ ዝቅጠት መፍጠር የምንችልበት አጋጣሚ የሚኖር መሆኑም ከግንዛቤ የሚገባ ነው፡፡ በዚህ የተቃውሞ ዘዴ ልናሳካው የምንሻው ጊዜያዊ ዓላማ ለሶስት ዓመታት ‹‹የፍትህ ያለህ!›› ስንል ቆይተን ከተጨማሪ በደል ውጭ መልስ ላልሰጠን መንግስት እንደህዝብነታችን አቅም እንዳለን እና ተጽእኖ ማሳደርም እንደምንችል ማሳየት ነው – ያለህዝብ ይሁንታ የመንግስት ህልውና ቢዘግኑት የማይዘገን ጉም መሆኑን ማስመስከር!!
ሳንቲም ሰብስቦ የመቆጠቡ ተቃውሞ አተገባበር
1/ የምንሰበስበው እና ቆጥበን የምናስቀምጠው እጃችን ላይ የገባውን ሳንቲም በሙሉ አይደለም! ይልቁንም ለኑሯችን አስገዳጅ የሆነውን ያክል ብቻ በመጠቀም ቀሪውን ማስቀመጥን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም እጃችን ላይ ከሚገቡት ሳንቲሞች የግድ አስፈላጊ የሆነውን ያክል ብቻ በመጠቀም ቀሪውን በማስቀመጥ ብቻ እንወሰናለን፡፡
2/ ሳንቲም ቆጥቦ የመሰብሰብ ተቃውሞው የሚካሄደው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እና ከተሞች ነው፡፡
3/ ሳንቲም ቆጥቦ የመሰብሰብ ተቃውሞው የሚጀምረው የፊታችን አርብ መጋቢት 18/2007 ጀምሮ ሲሆን በዚሁ ገጻችን ማብቃቱ እስኪገለጽ ድረስም ላልተወሰነ ጊዜ ይቀጥላል፤ በአላህ ፈቃድ!
አዎን! እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሃይማኖታችን ምክንያት በመንግስት ከፍተኛ በደል እየደረሰብን ያለን ሰላማዊ ዜጎች ብንሆንም መንግስት ከበደሉ ሊቆጠብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለዓመታት ሰላማዊ ትግል ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ሰላማዊነታችንን ለመግለጽ ነጭ ጨርቅ እያውለበለብን በአደባባይ በተገኘን ቁጥር መንግስት አስፈራርቶናል፤ ዘልፎናል፤ ደብድቦናል፤ ዘርፎናል፤ አስሮናል፤ ገድሎናል፡፡ እኛ ነጭ ሶፍት ይዘን ሰላማዊነታችንን በአደባባይ ስንዘምር መንግስት ደግሞ ዝናሩን ታጥቆ በጥይት እሩምታ ተቀብሎናል፡፡ የማይጠፋ ጠባሳ የጣለ ጥቁር ሽብር ፈጽሞብናል፤ ፈርመን የላክናቸውን ወኪሎቻችንን በግፍ እስር እና በከፍተኛ ቶርቸር አሰቃይቶብናል፡፡ እስካሁንም ነጻነታቸውን ነፍጎ የምርጫ ቅስቀሳ መጠቀሚያ እያደረጋቸው ነው። እንግዲህ አሁን ላይ መንግስት ጥይት ሊተኩስበት በማይችለው ሜዳ ሰላማዊ ተቃውሟችንን ከመቀጠል ውጭ ሌላ ምርጫ ያለን አይመስልም፡፡ ዛሬ ይፋ ያደረግነው የትብብር መንፈግ ተቃውሞ ዋነኛ ዓላማም መንግስት ጥይት የሚተኩስበት ዒላማ የማያገኝበትን የትግል ድባብ በመፍጠር መብታችንን የማጎናጸፍ ግዴታውን እንዲወጣ የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ ነው፡፡ ወደፊትም አንድ ብርና ከዛም በላይ ያሉ የብር ኖቶችንም ከመሰብሰብ ጀምሮ ሌሎች በአተገባበራቸውም ሆነ በእንድምታቸው ጠንክረው እያደጉ የሚሄዱ የትብብር መንፈግ እና የቦይኮት ስልቶችን ቀስ በቀስ በመለማመድ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች እንቀጥላለን፡፡ ከአላህ ፈቃድ ጋር ይሳካልናል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
yisema

Tuesday, March 24, 2015

ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም! አርበኞች ግንቦት7

Ginbot 7ከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ። ሆኖም ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዢዎች በከፋ መልኩ የሚገዛ የጥቁር ፋሺስቶች አገዛዝ በመሆኑ የሚሰራቸዉ ስራዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈርማቸዉ ዉሎችና ስምምነቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም የሚጻረሩና የሚጋፉ ድብቅ ስምምነቶች ናቸዉ።
ይህ የወያኔ መሪዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ ተሸሽገዉ የሚሸርቡት የድብብቆሽ ሴራ ዛሬ የተጀመረ አዲስ ክስተት አይደለም። ባለራዕዩ መሪ የሚል አላስፈላጊ የቅጽል ስም የተሰጠዉ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓም ሐምሌ ላይ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ዜናዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረዉ በነኀሴ ወር ማለቂያ ላይ ነበር እሱም ቢሆን ሞትን ያክል ነገር ደብቆ ማቆየት ስለማይቻል ነዉ እንጂ አይነግሩንም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በሰሜናዊዉ የአገራችን ከፍል ወያኔ ከጎረቤት አገር ጋር የተዋዋለዉ መሬት ቆርሶ የመስጠት ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ የተደረገ ዉል ወይም ስምምነት ነዉ።
አርበኞች ግንቦት ሰባት አገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ብቻ ሳይሆን ከግዛቷ ተነስተዉ ወደ ጎረቤት አገሮች በሚፈሱ አለም አቀፍ ወንዞቿና በሌሎችም የአገር ዉስጥ ወንዞቿ ላይ ግደብ የመስራት ማንም ሊጋፋዉ የማይገባ የተፈጥሮ መብት አላት ብሎ ያምናል። በሌላ በኩል ደግሞ አባይን በመሳሰሉ ድንበር ዘለል ወንዞች ላይ የሚሰሩ ምንም አይነት የልማት ፕሮጀክቶች በዛቻና በማንአለብኝነት ሳይሆን በመግባባት፤ በመመካከርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በሚያዳብሩ መልኩ መሰራት አለባቸዉ ብሎም ያምናል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ይህንን የሚለዉ ደግሞ መሠረታዊ ኑሯቸዉ በአባይ ወንዝ ላይ አገሮች ሊያደርሱ የሚችሉትን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ጫና በመፍራት ሳይሆን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመጀመራቸዉ በፊት ፕሮጀክቶቹን አስመልክቶ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ልዩነቶች መወገድ አለባቸዉ፤ ልዩነቶችን ለማስወገድ ደግሞ የተሻለና አዋጭ የሆነዉ አማራጭ ዲፕሎማሲ ነዉ የሚል ጽኑ አምነት ስላለን በቻ ነዉ።
የወያኔ አገዛዝ እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2011 ዓም የህዳሴዉን ግድብ ስራ ሲጀምር ከአራት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ወይም 96 ቢሊዮን ብር በላይ የተገመተዉ ግዙፍ ግድብ ስራ ሙሉ በሙሉ ከአገር ዉስጥ የገንዘብ ምንጮች በሚገኝ ገንዘብ እንደሚሰራና አገዛዙ ግድቡንና የግድቡን ስራ አስመልክቶ ምንም አይነት ድርድር ከማንም አገር ጋር እንደማያደርግ ለለህዝብ ቃል ገብቶ ነበር። የግድቡ ስራ በተጀመረ በጥቂት አመታት ዉስጥ የግድቡ ግንባታ የአገሪቱን የካፒታል ጥሪት ሙጢጥ አድርጎ በመብላቱና በሌሎች በተጀመሩና ሊጀመሩ በእቅድ በተያዙ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በግልጽ የሚታይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማድረግ በመጀመሩ አለም ባንክ፤ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና አያሌ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን የግድቡ ስራና ግድቡ ላይ የሚፈሰዉ የካፒታል ብዛት እንደገና እንዲታሰብበት ምክር ለግሰዉ ነበር፤ ሆኖም ምክሩ የተሰጠዉ የሚሰማ ጆሮ ለሌለዉ ለወያኔ ነበርና ሰሚ ታጣ። ዛሬ ግድቡ ከተጀመረና ወያኔም በህዳሴዉ ግድብ ላይ ከምንም ከማንም አልደራደርም ካለ ከአራት አመታት በኋላ አንደኛ የግድቡ ፕሮጀክት ስራ በገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ ተደርጓል፤ ሁለተኛ ወያኔ የህዳሴዉን ገድብ አስመልክቶ ከግብፅና ከሱዳን መንግስታት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የፊታችን መጋቢት 14 ቀን ስምምነቱን ለመፈረም ጎንበስ ቀና እያለ ነዉ።
ለመሆኑ ይህ ወያኔ ከሱዳንና ከግብፅ ጋር የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ የሚፈራረመዉ የስምምነት ዉሳኔ ይዘት ምንድነዉ? ዉሳኔዉ በሦስቱ አገር መሪዎች ፊርማ ከመፅደቁ በፊት ለምንድነዉ የዉሳኔዉ ባለቤት የሆነዉ የኢትዮጳያ ህዝብ እንዲያዉቀዉ ያልተደረገዉ? ባለፉት አራት አመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ ምንም አይነት ገቢ ከሌላቸዉ ከተማሪዎችና ከአረጋዉያን ጀምሮ እስከ ቀን ሰራተኛዉ ድረስ ለህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ገንዘብ አዋጣ ወይም ቦንድ ግዛ እየተባለ በሩ ያልተንኳኳ ኢትዮጵያዊ የለም። ታዲያ ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ በራሱ ገንዘብ ለዕድገቴና ለብልፅግናዬ መሠረት ይሆነኛል ብሎ የሚያሰራዉ ግድብ ስራዉ በገንዘብ እጥረት ሲተጓጎልና በዚሁ ግድብ ዙሪያ ከዉጭ መንግስታት ጋር አለም አቀፍ ስምምነቶች ሲደረጉ ምንም የማይነገረዉ ለምንድነዉ?
የወያኔ መሪዎች ከሱዳንና ከግብጽ መሪዎች ጋር የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ የተዋዋሉትን ዉል እንመራዋለን ብለዉ ከሚናገሩት ህዝብ ቢደብቁም ካርቱምና ካይሮ ወስጥ ሾልከዉ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግብፅ የህዳሴዉ ግደብ ፕሮጀክት ላይ የቁጥጥርና የማነጅመንት ድርሻ አንደሚኖራት እየተነገረ ነዉ። እንደዚህ አይነቶቹ ከዚህ ቀደም በፍጹም የማይሞከሩ ወይም የማይታሰቡ ናቸዉ ተብለዉ ሲነገሩ የነበሩ ስምምነቶችና ዉሎች ዛሬ ተደርገዉና የሶስትዮሽ ስምምነት ተደርሶባቸዉ በፊርማ የሚጸድቁት ግድቡን ሰርቶ ለመጨረስ የሚያስፈልግ ገንዘብ ለማግኘት ነዉ ወይስ ሌላ ድብቅ አላማ አለዉ? ደግሞስ ግድቡ የሚሰራዉ ለህዝብ ግድቡን የሚሰራዉም ህዝብ ሆኖ ሳለ ለምንድነዉ ይህ በዉድም በግድም ገንዘብ ካላዋጣህ ወይም ቦንድ ካልገዛህ እየተባለ ቀንና ማታ ሲጠየቅ የኖረ ህዝብ በዚህ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ዉሎችንና ስምምነቶችን እንዳያዉቅና ጭራሽ እንዳይሰማ የተደረገዉ? ካይሮና ካርቱም ዉስጥ እንደሚነገረዉ ግብፅ በህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ዙሪያ የማነጅመንትና የቁጥጥር ሚና ይኖራታል የተባለዉ ዜና እዉነት ከሆነ እኛ እራሳችን አገራችን ዉስጥ በምንሰራዉ ግድብ ግብፅ ሊኖራት የሚችለዉ የማነጅመንትና ቁጥጥር ድርሻ ዬት ድረስ ነዉ የሚሆነዉ …ለምንስ እንዲህ አይነት ሚና እንዲኖራት ተደረገ?
አርበኞች ግንቦት ሰባት የሶስቱ አገሮ መሪዎች ስምምነቱን በፊርማ ከማጽደቃቸዉ በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ለእንደነዚህ አይነት ቁለፍ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለበት ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያን አስመልከቶ የሚደረጉ ምንም አይነት ዉሎችና ስምምነቶች ብቸኛዉ ባለቤት ነዉና ከዚህ ህዝብ ተደብቆ የሚደርግ ምንም አይነት ስምምነት ሊኖር አይገባም። ስለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህ ከዚህ በላይ ያነሳናቸዉ ጥያቄዎች ጥርት ባለ መልኩ እንዲመለሱለት የወያኔን አገዛዝ ማስጨነቅ አለበት፤ አለዚያ ይህ ጉዳይ ዉሎ ካደረ በኋላ የሚደረገዉ ሩጫ ሁሉ “ቁጭ ብለዉ የሰቀሉትን ቆሞ ማዉረድ ያቅታል” እንደሚባለዉ ይሆናል።
ግብፅና ሱዳን የረጂም አመታት ወዳጅነትና አመታት ያስቆጠረ ወተዳራዊ ስምምነት ያላቸዉ ተጎራባች አገሮች ናቸዉ። እነዚህ ሁለት አገሮች በቅርቡ ከወያኔ ጋር የደረሱበትን ስምምነት “የግብፅን ፍላጎት የሚያረካ” ስምምነት ነዉ እያሉ ካርቱምና ካይሮ ዉስጥ አስተያየት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን ሁሉም ነገር ህዝብ እንዳያዉቀዉ በሚስጢር መያዙ እየታወቀ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት “አዲስ ምዕራፍ” ተከፈተ እያለ የፈረደበትን የኢትዮጵያ ህዝብ መሸንገል ጀምሯል። በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ሱዳንና ግብፅ በቅርቡ ካርቱም ላይ የደረሱበት ስምምነት እዚያዉ ካርቱም ዉስጥ የፊታችን ሰኞ በሦስቱ አገሮች መሪዎች ፊርማ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ የዉጭ ጉዳይና የዉኃ ኃብት ልማት ሚኒስተራቸዉን አስጠርተዉ ሦስቱ አገሮች የደረሱበትን ሰነድ መርምረዉ ሪፖርት እንዲያቀርቡላቸዉ ማዘዛቸዉ ከወደ ካይሮ ተደምጧል። እንግዲህ ይታያችሁ እኛ ኢትዮጵያዉያን የሦስቱ አገሮች ስምምነት ምን እንደሆነ እንኳን ሳናዉቅ ግብፅ እሷ እራሷ የደረሰችበት ስምምነት አልጥም ብሏት ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣት ጠይቃለች። ይህ የሚያሳየን አገሮች ለብሄራዊ ጥቅማቸዉና ደህንነታቸዉ ምን ያህል እንደሚጨነቁና አርቀዉ የሚመለከቱ አስተዋይ መሪዎች ደግሞ የሚጨንቃቸዉና የሚያሳስባቸዉ ይህ አሁን የሚመሩት ህዝብ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በተከታታይ የሚመጣዉ ትዉልድ ጭምር መሆኑን ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ለእንደዚህ አይነት መሪዎች አልታደልንም። የኛ መሪዎች እንኳን ለሚመጣዉ ትዉልድ ሊጨነቁ ለዛሬዉም ትዉልድ “እኛ ከሞትን ሠርዶ አይበቀል” የሚሉ ስግብግቦች ናቸዉ።
ወያኔ ከራሱ ዉጭ ማንንም የማይሰማ፤ልዩነትን የማያስተናግድና የሌሎችን ሃሳብ ከሱ ሀሳብ የተሻለ መሆኑን እያወቀም ቢሆን የማይቀበል ችኮ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቶናል። ዛሬ ላይ ቆመን ወደ ኋላ ዞር ብለን የትናንቱን ስንመለከት ወያኔ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያም ገና ከጥንስሱ ጀምሮ ያሳየን ይህንኑ ችኮነቱንና “እኔን ብቻ ስሙ” ባይነት ዕብሪቱን ነዉ። በተለይ የህዳሴዉን ግደብ በተመለከተ አባይ ወንዝ ላይ የሚገነባዉ ግድብ ከዚህ ቀደም በማንም ኢትዮጵያዊ ያልታሰበና የልተወጠነ ፍጹም አዲስ የሆነ ወያኔ ለኢትዮጵያ ያበረከተዉ ገጸ በረከት መሆኑን ለማሳየት ብዙ ጥሯል፤ አንዳንድ የዋሆችን ደግሞ አሳምኗል።ወያኔ ሁሌም ቢሆን ጥረቱና ፍላጎቱ እራሱን ከብጤዉ ከደርግ ጋር እያወዳደረ የተሻለ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነዉ እንጂ የተሻለ ስራ መስራት ስላልሆነ በህዳሴዉ ግድብ ላይም አብዛኛዉን ግዜ ያጠፋዉ “አባይን የደፈረ” ተብሎ ለመጠራት ስለሆነ ዛሬ ግድቡ ግንባታዉ አልቆ አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበት ወቅት የግድቡ ስራ ከመጀመሩ በፊት ተሰርተዉ ማለቅ የነበረባቸዉን ስራዎች እየሰራ ነዉ።
በቅርቡ አንድ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ቡድን ግድቡ የሚሰረባት ቦታ ድረስ በመሄድ የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ ጥናት አትንቶ የግድቡ ስራ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ ይዘገያል ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ጉዳዩን በቅርብ ለምናዉቀዉ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ግን እዉነቱ ከዚህ በላይ ነዉ። የህዳሴዉ ግደብ የሚዘገየዉ በገንዘብ እጥረት ብቻ አይደለም። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት ድህረ ጥናት ሁኔታዎችን የላጤነና ቅደም ተከተሎችን ያላገናዘበ ጎደሎ ጥናት ነበር፤ ከዚህ በተጨማሪ ሩጫዉና ግርግሩ የተጀመረዉ የህዳሴዉን ግደብ የመሰለ ግዙፍ የ96 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት በይድረስ ይድረስ ሰርቶ ለመጨረስ ነበር።
የብዙ አለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ኤክስፐርቶች ግምት በግልጽ እንደሚጠቀመዉ የህዳሴዉን ገድብ ግንባታ ጨርሶ አግልግሎት የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ፕሮጀክቱ በዕቅድ ከተያዘለት በጀት ከሃምሳ በመቶ በላይ ሊያስፈልገዉ ይችላል። ይህ ደግሞ ዛሬ ወያኔን ስለምንቃወም የምናወራዉ ተራ የፕሮፓጋናዳ ጨዋታ ሳይሆን የዛሬ አራት አመት ወያኔ ከበቂ ጥናትና ዝግጅት ዉጭ አባይን እገድባለሁ ብሎ ሲፎክር የዛሬዋ ቀን እንደምትመጣ አዉቀን በተከታታይ ያስጠነቀቅነዉ ማስጠንቀቂያ ስለሆነ ነዉ። ይህ ሁሉ የሚያሳየን ወያኔ አስቀያሚ መልኩን ለማሳመር ሲል ብቻ በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዝብና ጉልበት የህፃን ጨዋታ መጫወቱን ነዉ። ሆኖም ዛሬ የሚያስፈራን ይህ ወያኔ የተጫወተበት መጠነ ብዙ የህዝብ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ግድቡን ሰርቶ ለመጨረስ ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት የሚያደርገዉ አጉል መቅበዝበዝ ነዉ። በእኛ እምነት የህዳሴዉ ግደብ ተሰርቶ ሲያልቅ ኢትዮጵያን ከጥገኝነት ነፃ ማዉጣት ነዉ ያለበት እንጂ ሌላ አላስፈላጊ የሆነ የፖለቲካ ጥገኝነት ዉስጥ ይዞን መግባት የለበትም። ለዚህም ነዉ አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔ፤ ግብፅና ሱዳን በአባይ ወንዛችን ላይ የሚሰራዉን ግድብ አስመልክቶ ደረስን የሚሉትን ስምምነት ምኑም ሳይደበቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ መነገር አለበት እያለ ህዝብንም ወያኔንም የሚያስጠነቅቀዉ። የግብፅና የሱዳን መንግሰታት አገራቸዉ ዉስጥ ህዝብ የሚወዳቸዉ ወይም የሚጠላቸዉ መንግስታት ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም ከዉጭ መንግሰታት ጋር በሚያደርጉት ምንም አይነት ድርድርና ዉይይት ሽንጣቸዉን ገትረዉ የሚቆሙት ለአገራቸዉ ጥቅም ብቻ ነዉ እንጂ ሌላ ከህዝብና ከአገር የተለየ አጀንዳ የላቸዉም። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ በተለይ ባለፉት ሃያ አራት አመታት ብቻዉን ስልጣን ተቆጣጥሮ የኖረዉ ህወሓት ግን ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘለቄታዊ ጥቅም የተለየ የራሱ የሆነ አጀንዳ አለዉ። አርበኞች ግንባት 7 ህወሓትንና ይህንን ከህዝብና ከአገር የተለየ አጀንዳዉን የማቆሚያዉ ግዜ ዛሬ ነዉና ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፤ ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ፤ እዉቀት ያለህ ደገሞ በእዉቀትህ ነገ ሳይሆን ዛሬ ህዝባዊዉን ትግል ተቀላቀል እያለ አገራዊ ጥሪ ያስተላልፋል።

ትጥቅ ትግል ፣ ሰላማዊ ትግል ፣ ሁለገብ ትግል (ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ)

11075125_351890231682989_1605144358791622863_n(አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ናቸው። ይህ ጽሁፍም ፓርቲን ወክለው ሳይሆን ራሳቸውን ወክለው የጻፉት ነው)
ወቅታዊ አጀንዳ እና በቁንፅል የሚተው ባይሆንኝ ነው – በትግስት አንቡልኝ
ጭቆና ሲበዛ ሰዎች ብዙ መንገድን ተጠቅመው መታገል ይሻሉ፡፡ የጭቆናውን ቀንበር ለመስበር ጨቋኙን ከመግደል አንስቶ ራስን እስከማቃጠል ድረስ የሚደርሱ በርካታ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ከአገዛዝ ሰንሰለት ራስን ነፃ ለማድረግ ብዙዎች ተጨንቀው ማሰብም አይፈልጉም፡፡ በቃ ገዢውን ወዲያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ነፃ መሆን (end of the story end of the oppression)! በተፈጥሮ ነፃ ሆኖ የተፈጠረ ሰው በሂደት እጅግ በተወሳሰበ የህይወት መስተጋብር ውስጥ ቢኖርም የጭቆናው ለከት ሲያልፍ ግን ቀስቃሽ ሳያሻው እንደቡድንም ይሁን በግል በነሲብ ወደ ነፃነት ትግል መግባቱ አይቀርም፡፡ ነፃነት ከብዙ ምክንያታዊነትም በላይ የስሜት ሀይሉ ከፍተኛ ገፊ በመሆኑ ለነፃነት የሚደረገውም እንቅስቃሴ በራሱ ድንገታዊነት ይበዛዋል፡፡ ‘መቼ’ እና ‘እንዴት’ን አያጠይቅም፤ ‘ለምን’ የሚለው ብቻ በቂው ነው፡፡
እንግዲህ እዚህ ጋር ነው የነፃነት ትግል መሪዎች ሚና ወሳኝ የሚሆነው፡፡ ጭቆናን ከምክንያታዊነት በላይ በስሜቱ ተፀይፎ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የተነሳን ሰው መንገዱን ማመላከት የመሪዎቹ ሚና ነው፡፡ መሪው የትግሉን ‘እንዴትነት’ ‘መቼ’ ምን መደረግ እንዳለበት አፍታቶ ማሳየት እና እምቅ የሆነውን የነፃነት ፍላጎት ሀይል በተጠናና በተገቢው ቦታ ጥቅም ላይ እንዲውል ማስቻል፤ በዚህም አኳኋን ታጋዮችን አስተባብሮ መምራት አለበት፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም የነፃነት ትግል መሪ ከስሜት በላይ እጅግ ምክንያታዊ እና በአስቸጋሪ ሁናቴዎች ውስጥም ለታለመው ግብ ሲባል በርካታ ፈታኝ ውሳኔዎችንም እንዲያሳልፍ ይጠበቅበታል፡፡
የዛሬን መጨቆን ሳይሆን የነገን የተጨበጠ ውጤት ቀድሞ ማለም ለዛም የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ መክፈል ግዴታው ነው፡፡ ከተራ ውሳኔ አንስቶ በሰዎች ህልውና ላይ እስከመወሰን የሚያደርስ ጠንካራ የዲሲፕሊን ሰው የመሆን ኃላፊነቱ የትግሉ መሪ ላይ ይወድቃል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ሂደቱ ከየት ተነስቶ የት እንደሚደርስ በጠራ ሁናቴ የሚያልም፤ ከግቡም ለመድረስ የቆረጠ፤ ተግባራዊ እና ለዛም ሁነኛ መላ ቀያሽ ብልሃተኛ መሪ ትግሉን ከጫፍ ለማድረስ ይቻለዋል፡፡
ትግል ተፈጥሯዊ ነው – በብልሃት ማስተባበር እና መምራት ደግሞ ትግልን ከፍሬ የሚያደርሱ ነገሮች ናቸው፡፡ ከዚህ ተነስተን በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄዱት የነፃነት ትግሎች እንፈትሽ፡፡ አዋጪነታቸውንና ኪሳራቸውን እንመዝን፡፡
NOTHING PERSONAL NOR DESTRUCTIVE!
ትጥቅ ትግል በኢትዮጵያ?
———————-
* በ21ኛው ክ/ዘመን የትጥቅ ትግል አለማቀፋዊ አንደምታው እጅግ የተወሳሰበና ከፍተኛ የሰው እና የሉዓላዊነት ዋጋ የሚያስከፍል ነው፡፡ ለነፃነት እሞታለሁ ብሎ የወጣን ሰው አስተባብረህ ከምታስጣጥቀው መሳሪያ ጀምሮ የተለያዩ ሎጀስቲክና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ ይላል (ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን የዓለም ሴራ ቀመስ ፖለቲካ ትተን)፡፡ እነዚህን ድጋፎች ለማግኘት ደግሞ በዓለም ላይ ከሚገኙ ታላላቅ መንግስታት ጀምሮ ገዢ መሬት ከሚሰጡህ አካላት ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውል መፈፀሙ አይቀርም፡፡
ህወሃት ትጥቅ ትግሉን ድል አድረጎ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ በሀገር እና በህዝብ ላይ እስከመደራደር ደርሷል፡፡ ለትጥቅ ትግሉ ስኬት ሲባልም ብዙ ታሪካዊ ስህተቶችም መፈፀማቸው ያልሻረ ቁስል ነው፡፡
በዚህ ዘመን ደግሞ በትጥቅ ትግል ኢህአዲግን ከስልጣን ማውረድ ከዓለም ነባራዊ ስርዓት አንፃር እጅግ አስቸጋሪ እና በአደጋ የተሞላ ነው (at this point there is no near-safe deal)፡፡ ስለዚህ ጥያቄው አህአዴግን ለማስወገድ ከተለያዩ ሀይሎች ጋር የሚደረጉት ስምምነቶች በእውነት ሚዛን ይደፋሉ ወይ? የሚፈፀሙት ስምምነቶች ህወሓት (ሊያውም በዘመነ ጦርነት) ካስከፈለን ዋጋ ምን ያህል ቢሻሉ፤ ምን ያህልስ የህዝባችንን እና የሀገራችንን ጥቅም ያስቀደሙ ወይም ከግምት አስገብተው የተፈፀሙ/ሊፈፀሙ ያሉ ናቸው? እነዚህ እና መሰል ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ እስካላገኙ ድረስ በዚህ ዘመን የሚደረገው የትጥቅ ትግል ለኢትዮጵያ የሚኖረው ፋይዳ ‘ከድጡ ወደማጡ’ ከመሆን ያለፈ አይሆንም!
* ከዚሁ ጋር በተዛመደ የኢትዮጵያ ታጣቂ ሀይሎች የመረጡት ገዢ መሬት የሙግቱ ዋና ማጠንጠኛ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ የሻቢያ ግዛት ኤርትራ፡፡ እዚህ ላይ ስለ ሻቢያ እና ወያኔ ፍቅርና ጠብ – አንድነት እና ልዩነት አሁን ስላላቸው ለክፉም ለደጉም የእርስ በእርስ መጠባበቅ ማውራቱ ‘አውቆ የተኛን . . .’ ካልሆነ በስተቀር ለማንም ምስጢር አይደለም፡፡ ምንአልባትም እነዚህ ሁለት ሀይሎች በኢትዮጵያም ይሁን በቀጠናው ጉዳይ ላይ የራሳቸው ቁማር እየተጫወቱ ስልጣናቸውን ለማስቀጠል ምንም ሊያደርጉ እንደሚችሉም ለሁሉም ሰው ግልፅ ነው፡፡
ይህን ካልን ዘንዳ ኢትዮጵያ ውስጥ በትጥቅ ትግል ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ሃይሎች ከሻቢያ ጋር በምን መልኩ ሰምምነት አካሂደው ገዢ መሬት አገኙ? በዚህ ትግል ውስጥ የሻቢያ ጥቅም ምንድን ነው? በየትኛው ስሌት የኢትዮጵያ ታጣቂ ሀይሎች ከሻቢያ ድጋፍ አግኝተው የኢትዮጵያን ጥቅም ያስጠብቃሉ? (በቀደም ለት የኤርትራው ፕሬዘዳንት ስለኤርትራ እና ኢትዮጵያ ስላለፈውና መሆን ስላለበት ሲያብራሩ እነዚህ ጥያቄዎች ይበልጡኑ አወዛጋቢና በትጥቅ ትግሉ የተሰማሩ ሀይሎች ግልፅ ሊያደርጓቸው እንደሚገቡም ጭምር ተገንዝቤያለሁ!)
ስለሆነም እነዚህ መሰረታዊ ነጥቦች ምላሽ ባላገኙበት ሁናቴ ኢትዮጵያ ልጆቿን ዳግም ወደ እርስ በእርስ ጦርነት የምትከትበት አሳማኝ ምክንያት አይኖርም (ምሬት እና ጭቆና ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ እደማይችል ከላይ በመግቢያዬ ያሰፈርኩትን ልብ ይሏል) – የጦረኞቹ የፖለቲካ ሰዎች ይህን መሰሉን ጉዳይ አፍታተው መዳረሻውን፣ ጥቅምና ጉዳቱን እስካሁን ማሳመንም ሆነ ደፍረው ለውይይት ሊያቀርቡት አለመቻላቸው በራሱ የትጥቅ ትግሉ አዋጪ እንዳልሆነ አመላካች ነው (there is something fishy behind the silence)፡፡ (እንዲህ አይነቱ ነገር መገለፅ የለበትም የሚል መከራከሪያ እኔ አልቀበልም – ሁላችንም በሀገራችን ጉዳይ ያገባናል!)
* እዚህ ጋር አብሮ መነሳት ያለበት ነገር ደግሞ – ይህን ትግል ለመቀላቀል የሚፈልጉ ሰዎች የሚከፍሉት አላስፈላጊ መስዋእትነት ነው፡፡ ገና ሳይጀመር በባዶ ሜዳ፤ በጉዞ ላይ እየተለቀሙ ዘብጥያ የወረዱትን እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ከምትታገልለት ህዝብ ውጪ ሆነህ ልታገኘው የምትችለው የሎጀስቲክና ሌላም መሰረታዊ ድጋፍ አናሳ ነው፤ ከናካቴውም ላይኖር ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል አሁን በኤርትራ ምድር ከሌላ ሀይል ጋር ውህደት የፈፀመው የአርበኞች ግንባር በተለይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ድጋፍን ማግኘት የቻለና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ ምከንያቱ ደግሞ ይታገል የነበረው በዛው በህዝቡ መሃከል ሆኖ መሆኑ ነው (ያ አደጋ የለውም እያልኩኝ አይደለም ቢያንስ ግን ከባህሩ የወጣ አሳ አለመሆን ያለው ጠቀሜታ ከጉዳቱ ይበልጣል)፡፡ በየትኛው መልኩ ጭቆናው በቃኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ‘መንገዱም ጨርቅ’ ለመቀላቀልም ቀና የነበረ ግንባር ነበር፡፡ አሁንስ?
* እርግጥ የህዝባችን ስነ ልቡና ለትጥቅ ትግል የቀረበ መሆኑ አይካድም፡፡ ታሪካችንም ቢሆን ስልጣን በጦረኞች እንጂ በሰላማዊ መንገድ ተቀይሮ አያውቅም፡፡ ያም ሆኖ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁናቴ የዚህን መሰሉን የህዝብ ስነ ልቡናዊ ዝግጁነት ጥቅም ላይ ሊያውል የሚችል አስማሚ አጀንዳም የለም፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ ደግሞ ራሱ በትጥቅ ትግል ያሉት የተበታተኑ ሀይሎች ናቸው፡፡ ይህ ችግርም ባልሆነ ነበር ግና ለነፃነት ዋጋ የሰጠና ለዛም ለመሞት የቆረጠው ምን ያህል ነው? አምናለሁ ነገርን የሚለውጡት ሚሊዮኖች ሳይሆኑ ጥቂቶች ናቸው – ቢሆንም በኔ እምነት እነሱም ከላይ በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች ሌላ አማራጭ እንዲጠቀሙ ይገፏቸዋል (ለዚህ ነው ብዙዎች ተስፋ ቢያስቆርጥ እንኳን ለሰላማዊው ትግል ቅድሚያ የሚሰጡት)፡፡ ወጣም ወረደ በዚህ ጉዳይ ላይ የማነሳው መሰረታዊ ጥያቄ ግን በጣም ግልፅ ነው – ይህን ታሪክ እና ባህል ይዘን እንቀጥል ወይስ እንቀይረው? እውን ትጥቅ ትግል በትጥቅ ትግል የሚቀያየርን የስልጣን አዙሪት መስበር ይችላል? የጦረኛን ህዝብ ስነ ልቡና በጦረኛ መቀየር ይቻላልን?
* ሌላው ደግሞ ጦርነት ለሰብዓዊነት ቦታ አለመስጠቱ ነው፡፡ የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ከገደለ በኋላ – ደም ካየ በኋላ ለሌላ ሰብዓዊ መብቶች ሊቆረቆር የሚችልበት ሩህሩህነት አይኖረውም፡፡ መግደልን የተለማመደ አንድ ሰው ጭካኔን እየተለማመደ መሆኑን ማንም አይክደውም፡፡ በዚህ ሁናቴ ስብእናው የሚገነባ ግለሰብም ሆነ ቡድን ደግሞ ለወደፊቱ ህልማችን አደጋ ነው፡፡ ሰው መጨከን የለበትም እያልኩኝ አይደለም (there may come critical times in life)- ሁሉም ነገር ግን የሚቃኝበት መንፈስ እንደ ነገሩ ተጨባጭ ሁናቴ መሆን አለበት፡፡ አሁን ላይ ይህን ያህል ርቀት መሄድ ይቻላል ወይም አለብን? መቀበል ይቸግረኛል!
ይህን የበለጠ ለማብራራት ሩቅ ሳንሄድ የሀገራችንን የትናንት ታሪክ እናንሳ፡፡ የህወሓት እና ኢህአፓ ታጋዮች ብረቱን እስኪጨብጡት ድረስ እንደሁላችን ሰዋዊ ባህሪያቸው እንዳልተለያቸው ምንም አጠያያቂ አይደለም – አንዴ ሞትን ተኩሰው ከተፉ በኋላ ግን የማያባራ እልቂት ሆነ፡፡ ሰብዓዊነታቸው ተሟጦ ግፉ ለኛም ተረፈ! ትጥቅ ትግል ይህ እንዳይሆን የሚሰጠን አንድም ዋስትና የለውም! በደም የታጠበ እጅ ህሊናው ለመፅዳት ትልቅ ፈተና አለበት፡፡ እረግጥ ሰብዓዊነት በፖለቲካ አውድ ውስጥ አሻሚ ትንታኔ ቢሰጥበትም በጥቅል ግን ከትጥቅ ትግል የፖለቲካ ትርፍ በላይ በማህበረስብ ስነ ልቦና ላይ የሚኖረውን ጠባሳ ከኛ በላይ ህያው ምስክር ያለ አይመስለኝም፡፡ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ አሁንም የአንድ አገር ሰው ወንድም በወንድሙ ላይ እጁን ማንሳቱ ነው፡፡
ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ?
————————
* ዓለም ዛሬ የምትመራበት መርህ እና ሴራው እየረቀቀ ቢመጣም አንድ እውነት ግን መቼም ሊሻር አይችልም! በሰላማዊ ትግል ውስጥ ማናቸውንም ሀይል ከጎን ለማሰለፍ ትለቁ ነገር አገዛዝን በህግ የበላይነት እና የሞራል ልዕልና ማጠየቅ ነው፡፡ መሳሪያ ደግኖ ሲመጣ ደረትህን ነፍተህ መጋፈጥ የመሳሪያውን ብረት በእቶን እሳት ከማቅለጥ ያነሰ አይደለም፡፡ ዛሬ አንተን ቢገድል፣ ነገ ጓድህን ቢደግመው – ቀጥሎ ቃታውን የመሰብ አቅም አይኖረውም – ምክያቱም ጓዶችህ በባዶ እጅ ገጥመው እየወደቁ ህሊናውን አሸንፈውታል፡፡ ገዳይህ ብቻም ሳይሆን ሌላውም ሀይል ይህን ቆራጥነትህን ከመቀበል እና ከመተባበር ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡
እርግጥ ጨካኞች የሞቀ ቤታቸው ውስጥ ናቸው፣ ይህን ቆራጥነትህን አያዩትም አይረዱትም ስሜትም አይሰጣቸውም – መጠቀሚያቸው ግን የሚልኩት ወታደርና ፖሊስ ነው፡፡
በሰላማዊ ትግልም የምታሸንፈው ይህንኑ ሀይል እንጂ ጨቋኞቹን አለመሆኑ እሙን ነው፡፡ አፈሙዙን አዙሮ ጨካኞችን ወደ ዘብጥያ እንዲያወርድ የሚገደድበት የትግል ስልት ቢኖር ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ልትገድለው ሳይሆን ሞትን ደፍረህ ለነፃነት ከምታደርገው ትግል በላይ ልቡን አቅልጦ ከጎንህ የሚያሰልፍው ሌላ መንገድም የለም፡፡ እንግዲህ ይህ የትግል ስልት በርካታ ጨቋኞችን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ስርዓቱን ጭምር እየተፈታተነ ያለ የትግል አይነት ነው፡፡
* በሌላ በኩል ይህ የትግል ስልት በኢትዮጵያ ያልተሞከረ በተግባርም እምብዛም ያልታወቀ ነው፡፡ የህዝባችን ስነ ልቡና በራሱ ለዚህ የትግል ስልት ዝግጁ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ኢህአዴግን በሰለማዊ ትግል ከማስጨነቅ ይልቅ ገና ከጅምሩ እዚህም እዚያም ትጥቅ ትግል የተጀመረው፡፡ ለዚህም ማሳያው ከ1998 በኋላ ከተፈጠረው ቡድን ውጪ ያሉት ታጣቂዎች ከጅምሩም በረሃ ወርደው የነበሩ መሆናቸው ነው (እርግጥ አንዳንዶቹ ከህወሓት ጋርም አብረው የገቡ ናቸው)፡፡ ከ1998 በኋላ ትጥቅ ትግልን የመረጠው ቡድንም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ እምብዛም አልጣረም፡፡ ኢህአዴግ እንከን የለሽ ምርጫ አደርጋለሁ አለ፤ ፓርቲዎች ተሰባሰቡ፤ እስካሁን ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ ቅንጅት ፈጠሩ፤ እንከን የለሽ ምርጫ ተካሄደ፡፡ ውጤቱ ግን ብዙዎችን ተስፋ አስቆረጠ፡፡ የዘመነ የምርጫ ፖለቲካም አበቃለት! ቀጠለና አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ትግል አካሂዳለሁ፤ ህዝብን የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ ብሎ ትግል ሲጀምር – ሌሎች ደግሞ አይ ህዝቡ የሰጠንን ድምፅ በመሳሪያ እናስመልሳለን ብለው ጦርነት አወጁ፡፡ በኔ እምነት ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ምድር ላይ አለመጀመሩን ብቻ ሳይሆን ለመጀመርም ያለውን ችግር ይህ ኩነት ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡
ምናልባትም የዚህ የትግል ስልት ትልቁ ተግዳሮት በህዝቡ ዘንድ አዲስ መሆኑና ለመቀበል እና ለመተግበርም እጅግ ድካምን የሚጠይቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ነፍጥ አልባ ትግል ለመምራት የሚነሱ መሪዎችም መጥፋት ነው፡፡ አንዱ ወደ እስር ሲጓዝ ሌላው በስሩ ተተክቶ ትግሉን ማስቀጠል ግድ የሚል የትግል ስልት መሆኑን ብዙዎች ይዘነጉታል መሰል አንዱ ሲነካ አስሩ ወይ ቤቱ ይቀመጣል ወይ ይሰደዳል ወይ ጦር ያነሳል፡፡ ይህ ትግል በቅብብሎሽ እንጂ በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃም ላይሆን ይችላል፡፡ እስክንድር ሲታሰር ተመስገን ይተካል ተመስገን ሲታሰር ሌላው ይቀጥላል እንጂ አለቀቀ ደቀቀ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ሊባል አይችልም፡፡ አንዷለም ሲታሰር ሃብታሙ ይተካል ሃብታሙ ሲታሰር እኛ እንቀጥላልን እኛ ስንገባ ሌላው ይከተላል፡፡ አንድነት ፈረሰ ሰማያዊ ይቀጥላል – ሰማያዊ ሲፈርስ ወይ ሌላ ፓርቲ ወይ በሌላ መልክ ትግሉ ይቀጥላል፡፡ መሪ ብቻ አያሳጣ!
* ነፍጥ አልባ ትግል በመውጣትና በመውረድ ውስጥ፤ በአድካሚና ተስፋ አስቆራች ጉዞ ዘላቂነት ያለው ድል ያስገኛል፡፡ በነፍጥ አልባ ትግል ብዙዎቻችን ሙሴን እንጂ ኢያሱን ልንሆን አንታደልም (የህወሓቶቹን ሳይሆን የቅዱስ መፅሃፎቹን)፡፡ እንቅፋቶችም ብዙ ናቸው – በመንገድ ተንጠባጥበው የሚቀሩ – በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የሚሰናከሉ በርካቶች ለትግሉ በጠላትነት ሊነሱበት ሁሉ ይችላሉ፡፡ ካዛም አልፎ በሌላው ዓለም እንደታየው ዘለግ ያለ ጊዜ መውሰዱ አሰልችነት ቢኖረውም ውጤቱ ግን በሂደቱ ሁሉ የተረጋገጠ ነውና ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ ህዝብን የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ማስቻል ብቻ ሳይሆን አመለካከቱንና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችንም በሂደቱ እየታገለና መልክ እያስያዘ ከግቡ ይደርሳል፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ይህን አድካሚ ጉዞ የሚያቃልል እና መንገዱንም የሚያሳጥር ምቹ ሁኔታ አለ፡፡ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት በደም መፋሰስ ውስጥ ያለፈ ህዝብ በስነ ልቦና ረገድ ያን ጊዜ ዳግም ለማየት ፍፁም አይሻም፡፡ ከዛም ሲያልፍ አዲሱ ትውልድና በእርስ በርስ ጦርነቱ ያልነበረው የህበረተሰብ ክፍል አሁን ላለው ዓለምአቀፍ ስርዓት ቀረቤታ ያላቸው መሆኑ ለአዲስ የትግል ስልት ዝግጁነታቸው ከፍተኛ የመሆን እድሉ ቀላል አይደለም (የድምፃችን ይሰማን እንቅስቃሴ ልብ ይሏል)፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጨቋኞቻችን ዘመኑን የማይመጥኑ በአዲሱም ትውልድ በዓለምም ዘንድ መቀይር እንዳለባቸው፣ በእድሜ መግፋትም ቢያንስ ጡረታ መውጣት እንዳለባቸው የጋራ ግንዛቤ መኖሩ የሰላማዊ ትግሉን የሚያፋጥን ነባራዊ እውነታ ነው፡፡
* ሰላማዊ ትግል በምርጫ ፖለቲካ የሚገደብ አይደለም፡፡ እርግጥ ምርጫን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀም ይችላል፡፡ ሂደቱ በራሱ ከአነስተኛ ነገሮች በመጀመር እያደገና እየረቀቀ ይሄዳል፡፡ በትግሉ ውስጥ በተጠና መልኩ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማቀፍ ባህሪም አለው፡፡ አውቀው ከሚተገብሩት ባልተናነሰ መልኩ ሳይሰማቸውና ሳያውቁት በትግሉ የሚሳተፉም እንዲኖሩ እድል ይሰጣል፡፡ በሕቡ እና በግላጭም ሊካሄድ ይችላል፡፡ ሰላማዊ ሆነው ህግን መጣስ ድረስም መሄድ ይቻላል – ለምሳሌ ያህልም በሩሲያ Pussy Riot (የሴቶች መብት ተሟጋቾች እንቅስቃሴ – በተከለከሉ ቦታዎች እና ነውር በሆነ ሁናቴ ጭምር ተቃውሞን ማሰማት)፣ በኢትዮጵያ በቅርቡ እየተደረገ ያለው በመገልገያ ብር ኖት ላይ ተቃውሞን በማስፈር ማሰራጨት . . . የመሳሰሉት . . .
* ሰላማዊ ትግል መነሻው እና መዳረሻው የታወቀ ነው፡፡ ጊዜው ምን ያህል ቢረዝም እንኳን ውጤቱ ግን ዘላቂነት ያለው ነው፡፡ ስልጣንን ከጨቋኞች የማውረጃ ትግል ብቻ ሳይሆን – የጦረኝነትን ባህልንና የህዝብ ስነልቦና መቀየር የሚችል ትግል ነው፡፡ ያለመሳሪያ ጨቋኞችን ከስልጣናቻው ማውረድ የቻለ ህዝብ በራስ የመተማመኑ መጠን ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ማንም መጣ ማን ያለምንም ስጋት የፈለገውን የመሻር የፈለገውን የመሾም አቅም እንዳለው – እንደሚችልም የሚተማመን ህዝብ ሊኖር የሚችለው በሰላማዊ ትግል በሚመጣ ለውጥ ብቻ ነው፡፡ በተለይ እንደኢትዮጵያ በበርካታ ታሪካዊ ትብታብ እና ግጭቶች ውስጥ ላለፉ ሀገራት ሰላማዊ ትግል የቱንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ እና አድካሚ ቢሆንም አማራጭ ግን ሊቀርብበት የሚችል አይመስለኝም!
* ሰላማዊ ትግል ጭቆናን ከማስወገድ ባለፈም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የመተማመን፣ የመተሳሰብና የመዋደድን ባህል ያሳድጋል፡፡ ሰብዓዊነትን ያጎለብታል፤ ለዓላማ መሞት እንጂ መግደልን ስለማያበረታታ ሰዋዊ የሆኑ እሴቶቻችንን ጠብቀን ስነምግባር ያለው ህብረተሰብ እንድንፈጥር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
ሁለገብ ትግል በኢትዮጵያ?
———————–
* ይህ አይነት ትግል በተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ ስኬታማ ሆኗል፡፡ በጥቅል ሲታይም ህዝባዊ እምቢተኝነትን (የነፍጥ አልባ ትግል አካል) እና ህዝባዊ አመፅ (የትጥቅ ትግል ደጋፊ ‘hot spot for armed struggle’) አቀላቅሎ የሚሄድ የትግል ስልት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁናቴ ሲቃኝ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚበዛ – የጨቋኞች አፈና እንዲጠናከር ሰፊ እድል የሚሰጥ ነው፡፡
* በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁናቴ የዚህ አይነት ትግል ዋነኛ እንቅፋት ደግሞ የቆሸሸው ፖለቲካ ባህላችን ነው፡፡ መተማመን የጠፋበት፣ አንዱ አንዱን ማጥፋት የሚፈልግበት፣ ሴራ የበዛበት እና በተጠና መልኩ መንቀሳቀስ ማናናቅ አዋቂ በሚያሰኝበት የፖለቲካ ባህል ውስጥ ውስብስብነት ያለውን ሁለገብ የትግል ስልት እንጠቀም ማለት ኢህአዴግ እድሜ ልኩን ሲገዛ ይኑር ከማለት አይተናነስም፡፡ ይህ ብቻ ቢሆን ደህና፤ ነገር ግን ሁለገብ ትግልን በሀገራችን ወቅታዊ ሁናቴ ለመተግበር አስቸጋሪ የሚያደርገው ሌላ መሰረታዊ ጉዳይ “የየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው” አይነት ለውጤቱ ብቻ ትኩርት የመስጠት ዝንባሌ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ግድ የለሽ ለሂደቱ ደንታ የሌለው አካሄድ በሁለገብ የትግል ስልት ከሚያስገኘው ውጤት በላይ ኪሳራው የትየለሌ ነው፡፡ ስለዚህ በዚሁ ዘግተነው ወደ ማጠቃለያችን እናሳልጥ!
ማጠቃለያ
———-
በዚህ ሀቲት ውስጥ ለማመላከት እንደተሞከረው ሀገራችን አሁን ባለችበት ሁናቴ ከሁሉም የትግል ስልት ይልቅ ሰላማዊ የትግል ስልት ውጤታማነቱ የሚያሻማ አይደለም፡፡ እርግጥ ማናቸውም መንገድ የራሱ የሆነ መጥፎና ጥሩ ነገሮች ቢኖሩትም ከሌሎች የትግል አይነቶች በተሻለ የተመጠነ ኪሳራ ነገር ግን ዘላቂና የሚጨበጥ ውጤት ያለው የትግል ስልት መሆኑም አያከራክርም፡፡ ትልቁ ኃይልም ህዝብ ብቻ መሆኑ ከተቀሩት በቀጠናው ላይ አይናቸውን ከጣሉ ዓለምአቀፍ ሀይሎች ጋር ሰጥቶ መቀበል ወይም በሌላ ሴራ የመጠለፍ አደጋው በእጅጉ የቀነሰ ነው፡፡
ነፍጥ አልባ የትግል ስልት በሀገራችን አዲስ ከመሆኑ አንፃር ገና ዳዴ በማለት ላይ ቢሆንም በጥቂት ጀምሮ እየሰፋና ከዳር ዳር እንደሰደድ በመስፋፋት ለሀገራችን ዘላቂ ለውጥን ለማምጣት ሰፊ እድል ያለው ነው፡፡
ባጠቃላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (በሀገር ቤትም ሆነ በውጪም) እነዚህን የተለያዩ የትግል ስልት አይነቶች ትርፍና ኪሳራ በመመርመር እና በማገናዘብ ለኢትዮጵያ የሚበጀውን መንገድ እንዲመርጥ እና እንዲደግፍ መልእክቴ ነው፡፡ ከመነሻዬም እንዳሰፈርኩት የትግል ፍላጎት፣ የነፃነት ስሜት ገፊ ሀይል እና ጭቆና ብቻውን ለለውጥ አያበቃምና ሀገራችን በተያያዘችው ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የሚደረግ ትግልን የምትመሩ ቡድኖችና ግለሰቦች ቆም ብላችሁ መንገዳችሁን ብትመረምሩ መልካም ነው፡፡ ከታናሽ ወንድማችሁ በሚሆን ምክርም ፅሁፌን ላብቃ – ብቻ ምንም እንወስን ለውሳኔያችን ቆራጥ፣ የተግባር ሰው እና ለሀገራችን እና ለህዝባችን ስንል ከተራ ሴራ፣ በከንቱ ውዳሴ ከመኮፈስ የፀዳን እንሁን!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊዋ ህወሓትን ከዳች

10314570_351899461682066_5292491014759542281_nከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በኢሕአዴግ አደረጃጀት ዉስጥ ትልቅ ቦታ የነበራት ናት። ከሴቶች አደረጃጀት ሃልፊ ነበረች። ከዚያም በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትሰራለች። በአዲስ አበባ ይለ የኢሕአዴግ አባል የማያወቃት የለም።
ከአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅቱ ጉዳይ ሃላፊነቷ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሴቶች መዋቅርም የአድን ክላስተር ሃላፊም ነበረች። አበባ ገብረ ሕይወት ትባላለች።
አበባ በቅርቡ ለአንድ ስብሰባ ወደ አሜሪካን አገር ባቀናችበት ወቅት አጋጣሚዉን በመጠቀም፣ የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደወሰነችና ወደ አገር ቤት የመመለስ ሀሳብ እንደሌላት ለርሷ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
በተለይም በኢሕአዴግ ዉስጥ ፍጹም የሆነ የሕወሃት የበላይነት ከመኖሩ የተነሳ፣ በሞያቸውና በእውቀታቸው የመወሰንና የማገልገል እድል የሌላቸውና፣ የታዘዙትን ብቻ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሌሎች የኢሕአዴግ አባላት ደስተኛ እንዳልሆኑ በስፍት ይነገራል። ብዙዎች ባላቸው አጋጣሚ ሁሉ ኢሕአዴግን እየከዱ እንደሆነ፣ ያሉት ደግሞ ከዉስጥ መረጃዎች በማቀበል ከአዝዙ ያላቸውን ጥላቻ በማሳየት ላይ መሆናቸው በግልጽ እየታየ ነው።
ከዚህ በፊትም ሚኒስቴር ዴታ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኤርምያ ለገሰን ጨምሮ ብዙዎች ኢሕአዴግ እንደከዱ ይታወቃል።

የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ?

አበበ ገላው (ከፌስቡክ የተወሰደ)
ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል።
ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን ውጤት ያሳያል ተብሎ የተለቀቀውም ፎቶ የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። አውራንባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ድብደባውን ማረጋገጡን የዘገበ ሲሆን ዘገባውም በፎቶ ማስረጃ የታጀበ ነው። ይሁንና ፎቶው የሚያሳው ኤርትራ ውስጥ የተኪያሄደውን የአየር ጥቃት ውጤት ሳይሆን ቢቢሲ በኦገስት 9 2013 አንድ የወያኔ አየር ሃይል የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ሞቃዲሹ ውስጥ ተከስክሶ ሲጋይ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃን ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው በሮይተርስ ሲሆን በቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ ከዜናው ጋር በክብር ታትሞ ይገኛል።
Ethiopian Air Force Jets Attack
 bisha-13
አውራምባ ታይምስ ግን ዜናውን እውነት ለማስመሰል ከርክሞ እውነተኛውን ምንጭ ሳይጠቅስ ለታዳሚዎቹ አቅርቧል። በዚህም ጥፋት የሚያሳይ ፎቶ የተደነቁ በርካታ ወያኔዎች “አየር ሃይሉን” በማወደስ አስተያየት ሰንዝረዋል። የካናዳው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ግን አንዳንድ ሰራተኞቹ የተወሰኑ ማሽኖች ሆን ብለው ማበላሸታቸውን እና ጥገና አድርጎ ስራ መቀጠሉን በይፋ ገልጿል።
መቼም አንድ ጋዜጠኛ በጄት ድብደባና በአውሮፕላን ወድቆ መከስከስ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ይገነዘባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አውራምባ ታይምስ ላይ በጭስ ተሸፍኖ የሚታየው ከተማ ሞቃዲሹ እንጂ አስመራ አለመሆኑን ከቢቢሲ ዘገባ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ነው ወይንስ ሶማሊያና ኤርትራ ሳንሰማ “ያለምንም ቅደመ ሁኔታ” ተዋሃዱ?

ለማንኛውም ቢቢሲ የአውሮፕላን መከስከስን አስመልክቶ ያቀረበው ዘገባ እስከ ፎቶው እዚህ ገጽ ላይ ይገኛል።
http://www.bbc.com/news/world-africa-23628549

(ይህንን ጥቆማ ያቀረበውን አንድ ወዳጃችንን ሳላመሰግን አላልፍም)