Wednesday, September 2, 2015

ተሰዶም ለስደት ያልበቃ እድል


አብዛኛው ሰው በሀገሩ ኑሮ ሲጠበው፣ በሀገሩ ሰላም ሲያጣ ፣ በሀገሩ ነገሮች አልሆኑለት ሲሉ ራሱን ሊለውጥ አለያም ይደርስብኛል ሲል የሚሰጋበት ሰብአዊ መብት ረገጣ ሽሽት ወደስደት ይወጣል። አንዳንዱ እድለኛ ታስጠልለኛለች ብሎ ያላት ምድር ስቃ ትቀበለዋለች አንዳንዱን ደግሞ ህይወቱ የባሰ ቅጥአንባሩ ይጠፋውና ምነው በዚያው የሀገሬ ጅብ በበላኝ ሲል ይማረራል ለአንዳንዶች ግን ያስጠልለናል ካሉት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ይቀራሉ!
አንዱ አሳ ይበላዋል ከፊሉን ውሃጥም አቃጥሎ ያደርቀዋዋል ………ብቻ ስደት መከራው ብዙ ነው።
ዛሬ በሀገሩ ጦርነት ቢያሳድደው ስዴት ግን የበለጠ የገፋው ሶሪያዊ ህፃን ልጅ ፎቶ አለምን አሳዝኗል።
የዚህ ልጅ ስደት ወጥቶ ለስደት እንኳ ያልበቃ እድል ማጣት እኔንም አሞኛል፣ቅስሜን ሰብሮታል! እንደእናት ሆኘ ሳየው እና ሳስበውማ የሚሰማኝ ስሜት…… ያማል !!
ለማንኛውም ስሜቴን ወደራሴ አመጣሁት እና ይቺን ስንኝ አስታውሼ ደግሜ ለጠፍኳት
ሁሉን ያጣ
————
በዚች አለም ካለው የሰው ልጅ ፈተና፣
እጅግ የሚያሳዝን ህመሙ የሚጠና፣
ሳይፈቅድ ተወልዶ፣
ሳይስማማ በግድ ከኑሮው ተዛምዶ፣
ኖሮ ኖሮ ኖሮ፣
በኑሮ ተማሮ
ከመወለድ ወዲያ ከኑሮው ባሻገር ነፍስን የሚከፋት፣
ለዚሁም የሚያኖር እድል አጥቶ መሞት።
ይሄን እንኳ አትንፈገን!
Zehara Abdellah
Zehara Abdellah's photo.

No comments:

Post a Comment