Thursday, September 3, 2015

ስብሰባ በማወክና በማነሳሳት የተከሰሱት መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት ለ3ኛ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው


᎐ተከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል አራቱ ሴቶች
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ለእስር ተዳርገው ‹‹ስብሰባ በማወክና በማነሳሳት›› የተከሰሱት እነ ሚካኤል ያሬድ ለሦስተኛ ጊዜ መከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 8/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡
ዛሬ ነሀሴ 28/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የቀረቡት በእነ ሚካኤል ያሬድ የክስ መዝገብ 14 ሰዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ መካከል አራቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በዚህ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት በአጠቃላይ 19 የነበሩ ሲሆን አምስቱ ከአንድ ወር በፊት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ተሰናብተዋል፡፡
ቀሪዎቹ 14 ተከሳሾች ግን ተከላከሉ በተባሉት መሰረት መከላከያ ምስክሮቻቸውን ቢያቀርቡም ዳኛው ‹‹ቀጠሮ ለመስጠት ነው የተሰየምኩት›› የሚል ምክንያት በመስጠት ተከሳሾችን በቢሮ አስጠርተው ለ3ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተውባቸዋል፡፡
በክስ መዝገቡ የተካተቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣
1. ሚካኤል ያሬድ
2. እስማኤል ዳውድ
3. ዮርዳኖስ አለማየሁ
4. ታሪኩ ፍቅረማርያም
5. ስንታየሁ ዮሐንስ
6. ንጉሱ ታደሰ
7. ቸርነት ደመቀ
8. በኃይሉ በቀለ
9. በሱፍቃድ አሰፋ
10. ፋሲል ዮሐንስ
11. ወ/ሪት ማህሌት ኤርሶዶ
12. ወ/ሪት ምስለ ኃይሉ
13. ወ/ሪት ረሃማ ጀማል
14. አንዱዓለም መሃሪ
15. ሙከሚል ሁሴን
16. አይተነው ቀለመወርቅ
17. አብዱልከሪም ሽኩር
18. ወ/ሪት ቤዛዊት ግርማ፣ እና
19. ሰለሞን ካህሳይ፣ ናቸው፡፡
ከእነዚህ ተከሳሾች መካከል አምስቱ ማለትም፣
1. በኃይሉ በቀለ
2. ከሚል ሁሴን
3. ንጉሱ ታደሰ
4. አይተነው ቀለመወርቅ
5. ቸርነት ደመቀ፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ከእስር ተለቅቀዋል፡፡
ቀሪዎቹ 14 ተከሳሾች ግን ለእስር ከተዳረጉበት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀምሮ ዋስትና ተከልክለው በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment