Wednesday, September 2, 2015

ሰበር መረጃ አ . አ. ዩ የፔንሲዩን አገልግሎት በስውር እየሰጠ ነው!

ወያኔ በመቶወቹ የሚቆጠሩ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙህራንን ጠራርጎ ካበረና በካደሬ ከሞላው ጀምሮ ዩኒቨርስቲው በሙስና ከመጨማለቁና የካድሬ መፈንጫ ከመሆኑ ባሻገር ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ኦዲት ተደርጎ የማይታወቅ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ የዩኒቨርስቲው ዶርሚተሪወች ወደ ግለሰቦች መኖርያና ክራይ እየተቀየሩ ስለመሆኑ ውስጥ አወቅ ምንጮች ዘግበዋል።ይህ በንዲህ እንዳለ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋየና ምክትላቸው ዶ/ር ጄሉ ኦመር ከሀገር መውጣታቸውን ተከትሎ ተወካዩም የኮበለሉ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው መሪ የሌለው ያለመችን ብቸኛ ተቋም መሆኑ ታውቋል።በወያኔው ካሳ ተብርሀን የቦርድ ሰብሳቢነት በካድሬ የታጨቀው ዩኒቨርስቲ ቀስበቀስ የፔንሲዩን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንና ጸረ እውቀት ትውልድ አጥፊው ከይሲ ቡድን የጥፋት ኢላማቸውን እያሳኩ ስለመሆኑ ውስጥ አወቅ ምንጮች ላፈትላኪ የዜና ምንጭ ጠቁመዋል።

No comments:

Post a Comment