በስምንት ግራም ቶሪየም 100 አመት ያህል መኪና ሊያስነዳ የሚችል ማዕድን አግኝቼያለሁ. ሃኪም ንጉሴ አሰፋ.
“አገር አቀፍ የባህል መድኃኒትና የህክምና ቀን” በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትንና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአለም የጤናድርጅት ጋር በመተባበር ከትላንት በስቲያን በሃርመኒ ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ ላይ ላለፉት ሃያ አመታት በባህል የህክምና ሙያ ላይ የቆዪት ሃኪም ንጉሴ አሰፋ ላለፋት 15 አመታት በቶሪየም ማዕድን ላይ ጥናት ካደረጉ በሆላ በስምንት ግራም ቶሪየም ማዕድን አንድ መቶ አመት መኪና ሊያስነዳ የሚችል ማዕድን በምርምር ማግኘታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገለፁ.
የምርምሩንም ውጤት ለማዕድን ሚንስቴር አቅርበው ተቀባይነትን ማግኘታቸውን የገለፁ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅቤት የምርምሩን ውጤት ለማቅረብ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል.
የ 64 አመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት ሃኪም ንጉሴ አስፋ የአራት ልጆች አባትና በትምህርታቸውም ከስምንተኛ ከፍል እንዳልዘለሉ አስረድተዋል.

No comments:
Post a Comment