የአፋር ሕዝብ ንቅናቄ፣ ት ህዴ ን፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት ፯ የጋራ አገር አድን ንቅናቄ መመስረታቸውን በተመለከተ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በኢሳት ራዲዮ ተጠይቀው በድርጅቶቹ አባላት መሃል ማፈግፈግ ቢከሰት እንኳ አገር አድን ሰራዊቱ እንደሚታደገው አብራርተዋል። ለዚህም ካስረኛው የቃለመጠይቁ ደቂቃ በኋላ እንደተረዳነው ከሁሉም ድርጅቶች ተውጣጥቶ ከተቋቋመው አገር አድን ሰራዊት ተመልሶ ወደ እናት ድርጅቱ ልመለስ ማለት አይቻልም።
አራቱ ድርጅቶች በጋራ ንቅናቄው ሰራዊት ይዋጣሉ እንጂ ለምሳሌ ት ህዴ ን ብዙ ሰራዊት ያለኝ እኔ ነኝ እና በኔ ስም ተጠሩ ቢል የሚሰማው የለም።ሞላ አስገዶም ትግሉን የከዳውም ጥዴንን እንደንብረቱ ቆጥሮ መሪ ካላደረጋችሁኝ ብሎ ከሌሎች ጋር ተጣልቶ ከሆነም ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም የነፕሮፌሰር ብርሃኑ ምሁራዊ አካሄድ የህወሃትን ካባ ለብሰው ኤርትራ ለመሸጉት ቅጥረኞች አልተመቻቸውም። የተደላደለ የ አሜሪካ ኑሯቸውን ትተው እነ ኤፍሬም በረሃ ይወርዳሉ ብለው እነ ወዲ አስገዶም አልጠበቁትም። ህዝቡ ለውጥ እንደሚፈልግ ተረዱት።ነገም ዛሬም የሚወተውቱት ስለ እውነተኛ ዲሞክራሲ ነውና ሆዳሞች ጨነቃቸው።ስለዚህ ሳይነቃባቸው ፈረጠጡ።
በመጨረሻም የ አርበኖች ግንቦት ሰባት አመራሮች ኤርትራ ከገቡ የተሰበሩ ሁለቱን የህወሃት ሴራዎች እንይና ለዛሬ ይብቃን።ዙሩ ከሯል። ሃምሌ 10 እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ገብተው ሃምሌ 20 የኤርትሪያውንን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብል ለበርካታ ዓመታት የኖረ እና በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረ የመላዋ ኤርትሪያ የፀጥታ ኃላፊ በቁጥጥር ስራ ውሏል። ያኔ ከአሜሪካ የሄዱት አመራሮች ያለደህንነት ስጋት እንዲንቀሳቀሱ የወያኔ ቀኝ እጅ የነበረው የጸጥታ ሃላፊ መያዝ ፍንጭ ሰጥቶ ነበረ።
አሁን ደሞ የተቃዋሚ ጦር ሰራዊት የት ህ ዴን መሪ በመሆን ለህወሃት ሲሰራ የነበረው ሞላ አስገዶም ተጋልጧል።ይህ እንግዲህ ብስሉ ከጥሬው ገና ከጅምሩ የተለየበት፤ ምርቱ ከ እንክርዳዱ በመጀመሪያው የውህደት ወንፊት የተጣራበት ወቅት ነው።
ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም!!!( አብርሃም ታየኝ )
No comments:
Post a Comment