Wednesday, September 30, 2015

በሆድ እቃቸው ውስጥ 156ሺህ ዶላር(3ሚሊዮን ብር) የደበቁ ሰዎች “እንዲተፉት” ተደረጉ


ሰሞኑንን ከወደ ምእራብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ የተሰማው አሰገራሚ ዜና በዙዎችን ወቸው ጉድ! ፣ምን አይነት ዘመን ላይ ደረሰን? ማለቱ አይቀረም። የአገሪቱ ጸረ -የአደንዛዥ እጽ እና የሀገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ግበረ ሃይል ሰሞኑን ከመዲናይቱ ሌጎስ አይሮፕላን ጣቢያ አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ ዘመናዊ ሆቴል ውስጥ ድንገተኛ አሰሳ ሲያደረግ ከሆቴሉ አንደኛው ክፍል ውስጥ የተሰባሰቡ ፣ እንግዳ እና ያለተለመደ በሆነ ሰራ ተጠምደው ከነበሩ ሰደስት ግለሰቦች ጋር ይፋጠጣል።
አንድ የወጪ ገንዘብ ምንዛሬ ቤሮ ሰራተኛ ( Burea De Change operator ) እና የሆቴል ቤቱ ዋና ሰራ አስኬያጅ ጨምሮ ሰደሰቱ ሰዎች ግምቱ 156 ሺህ ዶላር ወይም 32 ሜሊዮን ኒየራ(የአገሪቱ ሕጋዊ ገንዘብ ነው ) በኢትዮጵያ ብር ደግሞ( ወደ3 ሚሊዮን 120 ሺህ ብር) የሚገመት ገንዘብ እጅግ ፕሮፊሽናል በሆነ ሰው አማካኝነት በመጠቅለል እና በመዋጥ ከሆድ እቃቸው ውስጥ በማኖር በሁለት የ ብራዚል ዜግነት ባላቸው ተጠርጣሪዎች አቀናባሪነት ገንዘቡን ወደ ብራዚል ለማሸጋገር ሲጣደፉ “ደረሼባቸዋለሁ” ሲል ፖሊስ ተናግሯል።
እንደ መርማሪዎቹ ዘገባ ከሆነ አንደኛው ተጠርጣሪ ብቻውን 120 ሺህ ዶላር ወደ ሆድ እቃው ሰዷል። ሌላኛው ደግሞ 111ሺህ ዶላር ያካተቱ 74 ጥቅል ዶላሮችን እንደዋጠ እና ሶስተኛውም 45ሺህ ዶላር ለዚህ ስራ ተብሎ በመጣ በአንድ ፕሮፊሽናል የጌጣጌጥ ወረቀት ጠቅላይ ሰው አማካኝነት ውጠው ለብራዚል ጉዟቸው ሲሰናዱ እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።አንዳንድ የናይጄሪያዊያን ዘራፊዎች ከዚህ ቀደም የሚታወቁት ኢትዮጵያ አየር መንገድን ጭምሮ የተለያዩ ደንበሮችን እና የአየር ክልሎችን በመጠቀም አደንዛዥ አጾችን በሆድ እቃዎቻቸው እና በብልቶቻቸው ሳይቀር ሸሽገው ለማሸጋገር ሰሞክሩ በቁጥጥር ሰር ዋሉ መባላቸውን ነበር።
የናይጄሪያው አዲሱ ፕ/ት መሃመዱ ቡሃሪ በቅርቡ “ሙስናን ካልገደልነው ሙሰና እኛኑ ይገድለናል ።ማለታቸውን ተከተሎ በርካታ ወገኖች “ሙሰኞች እና ዘራፊዎች እንደ ቻይና፣ እንደ ህንድ እና እንደ ደ/አፍሪካ በሞት ይቀጡልን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከ 12 -15 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት የ ናይጄሪያ መናገሻ ከተማ የሆነቸ ሊጎስ ብቻዋን አመታዊ ገቢዋ ወደ 50 ቢሊዮን ዶላር ሲገመት ይህም ሃብቷ ሌጎስ ከተማ አንድ የአፍሪካ አገር ብትሆን ሰባተኛዋ በኢኮነሚ የበለጸገች አፍሪካዊ አገር ትሆን ነበር። የሚያሳዝነው ግን የሌጎስ ከተማ ባለሰልጣናቶቹዋ ለቁጥር የሚከብድ ገንዘብ በሰበብ በአስባቡ የሚዘርፉባት መነሃሪያ መሆኗ ነው።ሰኞ እለት ኔዮርክ(አሜሪካ)ላይ በተካሄደው 70ኛው የተመድ ጉባኤ ላይ የተገኙት ፕ/ት ቡሃሪ “ከ አፍሪካ አሕጉራችን ተዘርፎ በምእራባዊያን ባንኮች ተደላድሎ የተከማቸው ግዙፍ ገንዘባችን ይመለሰልን ዘንድ ተባበሩን” ሲሉ የሙሰኞች እና የዘርፉት ገንዘብ መሸሸጊያ የሆኑት ከበርቴ እገሮችን በጽኑ ተማጽነዋል።
የዚህ ሙሰና ነገር ከተነሳ ኢትዮጵያም ቢሆን ፈርጣማ የሆኑ ሙሰኞች እና በጠራራ ጸሃይ የሕዝብ ሃብት ዘራፊዎች እያቆጠቆጡባት እንደመጡ የተለያዩ ዘገባዎች የናገራሉ “ጥርስ አልባው አንበሳ” የሚሉት የጸረ ሙስና መ/ቤት ሳይቀር በመግለጫዋቹ አልፎ አልፎ ይነግረናል።ታዲያ እኛስ ብንሆን ሙስናን ቀይ ምንጣፍ አንጥፈን እንቀበለው?፣ወይስ እንደ ሰሞኑ የናይጄሪያው የጸረ አደንዛዥእጽ እና ሕገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ግብረሃይል ዘርፊዎችን የዋጡትን የሕዝብ ገንዘብ አንዲተፉት አናድርጋቸው? አሊያም የኮሚኒስት ቻይና ተሞክሮን አ/አ(ኢትዮጵያ) ላይ ተግባራዊ እናደርገው? ለነገሩ ሙስናን የሚዋጋ ሃሞት ያለው አገዛዝ ጠፋ እንጂ ሁለመናችን ቻይናዊ ከሆነ ውሎ አድሮ የለ?!።

የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች


ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ክፍል አንድ
በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2ኛ ነገሥት 5፤ ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡

አሁን በያዝነው ዘመን አያሌ ‹አጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡
1. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት፣ ክህነታዊ ሕይወት፣ የጸሎት ሕይወት ወይም ሌላ አንዳች ተጋድሎ ሳይኖረው ማጥመቅ ብቻ ሥራው የነበረ ክርስቲያን የለም፡፡ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች የሌላው መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውጤት ወይም ነጸብራቅ ነበር እንጂ ሥራቸው እየዞሩ ማጥመቅ አልነበረም፡፡ የሐዋርያት ሥራን ብናነብ ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ሲሠማሩ በአንድ በኩል አሕዛብን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት በሌላ በኩል የአንደበት ትምህርታቸውን በእጃቸው ተአምር ለማጽናት ተአምራትን ያደርጉ ነበር እንጂ በአንድ ከተማ ውስጥ ሲያጠመቁ ውለው ያደሩበት፣ ወይም ከወንጌል አገልግሎት ተለይተው አጥማቂ ብቻ የሆኑበት፣ ወይም ደግሞ በዚህ ቦታ ፈውስ እንሰጣለንና ተሰብሰቡ ብለው ያስነገሩበት አንድም ማስረጃ የለም፡፡ በገድለ ቅዱሳንም ቅዱሳን ጸጋ እግዚአብሔር ሲያድርባቸው፣ ሥጋቸውንና ሰይጣንን ድል ሲነሡ፣ በክርስትናቸው ሲበስሉ ተአምራት ይከተሏቸዋል እንጂ እንዲሁ ማጥመቅና መፈወስ ብቻ ሕይወቱ የነበረ ቅዱስ የለም፡፡ ሰው ያለ ተጋድሎ እንዴት ጸጋ ያገኛል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ከተራ ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ ሕይወት የሌላቸው ሁሉ እየተነሡ አጥማቂ ሊሆኑ የቻሉበት አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡
2. በገድለ ቅዱሳን ውስጥ ቅዱሳን በገዳማዊ ሕይወት፣ በሰማዕትነት፣ በክህነታዊ አገልግሎት ሲሠማሩ እግዚአብሔር ምእመናንን ለመጥቀም ወይም ክብረ ቅዱሳንን ለመግለጥ በእነርሱ ላይ ተአምራትን ያደርጋል፡፡ እነርሱ ግን ይህ ክብር እንዳይገለጥባቸው ሲሸሹ፣ እኔ አላደረግኩም ሲሉ ወይም ስለራሳቸው ደካማነት ሲነገሩ እናያለን እንጂ ‹ኑ እንፈውሳችኋላን› ብለው ዐዋጅ ሲናገሩ አይተንም፣ አንብበንም አናውቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ወጥተው ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሄዱበት ዋናው ምክንያት በገዳሙ እያሉ በፈወሱት አንድ በሽተኛ ምክንያት ስማቸው ከፍ በማለቱ፣ ብዙ ሰዎችም በመሰብሰባቸው የተነሣ ነው፡፡ ታላቁ አባት መቃርዮስ ገዳሙን ትቶ ወደ አንዲት መንደር መጥቶ የኖረው በገዳሙ ክብሩ በመገለጡና ተአምራቱ በመታየታቸው ከከንቱ ውዳሴ ለማምለጥ ነበር፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው አካባቢውን ትቶ የጠፋው ተአምር አድራጊነቱ በመታወቁ ምክንያት ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚህ በተቃራኒው ሰዎች እናጠምቃለን፣እንፈውሳለን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩበት፣ ካሴት የሚሸጡበት፣ ፖስተር የሚሰቅሉበት ዘመን ነው፡፡
3. ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ ድንግል ማርያም ማን እንደሆነች፣ ቅዱሳን መላእክት ማን እንደሆኑ ሌሎቹም ቅዱሳን ማን እንደሆኑ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰዎች ሰጥታ አታውቅም፡፡ ቅዱሳንን ከፈጣሪ አስበልጣ አታወቅም፡፡ የቅዱሳን መገኛና መሠረት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን ታምናለች፣ታስተምርማለች፡፡ ለእግዚአብሔር የማይቻል ለቅዱሳን ይቻላል፣ በእግዚአብሔር የማይሠራ በቅዱሳን ይሠራል ብላ አታምንም፣ አታስተምርም፡፡ በዘመኑ አጥማቂዎች ዘንድ የምናየው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ በክርስቶስ ስም የማይወጣው ሰይጣን የቅዱስ ሚካኤልን ስም ሲጠሩበት ይወጣል፡፡ በክርስቶስ ስም የሚያሾፍ ሰይጣን የድንግል ማርያምን ስም ሲጠሩበት ተቃጠልኩ ይላል፡፡ ይኼ ፈጽሞ ክህደት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት አይደለም፡፡ ‹‹በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ›› ብላ ያስተማረች ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹በክርስቶስ ስም አንወጣም፣ በማርያም ስም ግን እንወጣለን›› እያለ አጋንንት ወጣ የሚል ትምህርት ማስፋፋት ክህደት ነው፡፡
4. መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት መቀስቀሻና ማስታኮቻ የሚውል ነው፡፡ ምእመናን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፣ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ፣ ኪርኤ አላይሶን የተባሉትን የምሕላ ጸሎቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተመደበላቸውን ቁጥር ሳይስቱ እንዲጸልዩ የተሠራ ሥርዓት ነው፡፡ በጸሎት ጊዜ ዝንጋኤ እንዳይገጥማቸው ኅሊናቸውን ለመሰብሰብም ይረዳል፡፡ አንድ ቅዱስ ለብዙ ዘመን የጸለየበት መቁጠሪያ፣ የተደገፈበት መቋሚያ፣ የቆመበት ምድር፣ የለበሰው ልብስ፣ የተጠቀመበት መጽሐፍ ተአምራት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸውም ለልብሳቸው፣ የልብሳቸው ለጥላቸው ተርፎ አይተን እናውቃለንና(የሐዋ. 5፣12-17፤ 19፣ 11-12)ከዚህ ውጭ ግን የሚሸጥ መቁጠሪያ ሰይጣን የሚያስወጣበት፣ ሰው ራሱን በመቁጠሪያ ስለደበደበ ከዲያብሎስ እሥራት የሚፈታበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሰይጣን በጾምና በጸሎት እንጂ በመቁጠሪያ ድብደባ አይለቅም(ማቴ.17፣21)፡፡ ያ መቁጠሪያ ተአምር የሚሠራ ቢሆን እንኳን አንድ ቅዱስ የተጋደለበት፣ ከዚያ ቅዱስም በረከት ያተረፈ መሆን አለበት፡፡ ልክ የቅዱስ ጳውሎስ የጨርቁ እራፊ ይፈውስ እንደነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም የትኛውም አባት መቁጠሪያ ሲያድልና በመቁጠሪያ ሰይጣን ታወጣላችሁ ብሎ ሲያስተምር አልታየም፡፡
5. ጌታችን በሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አስተምሯል፡፡ በጌንሳሬጥ ምድር አምስት ሺ(ማቴ 1413-21)፣ በገሊላ ባሕር አጠገብ አራት ሺ(ማቴ 15፣32-39)፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይቶ ይኼድ ነበር እንጂ ሰይጣን አድሮበት በአንድ ጊዜ የጅምላ ጩኸት ሲጮህ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ግን እየቀረቡ ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ አግኝተዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢሆን መድኃኒት ያደረገብሽ፣ ድግምት ያስደገመብህ፣ መተት ያስመተተብህ እገሌ ነው የሚል ሰይጣን አልተሰማም፡፡ ዛሬ ግን በአንድ ቦታ ለጥምቀት የሚሰበሰቡ ሰዎች አብዛኞቹ ይጮኻሉ፡፡ ሁሉም በሰይጣን ተይዘዋል ይባላሉ፣ ሁሉም ድግምት፣ መተት፣ መድኃኒት፣ ጥንቆላ እንደተደረገባቸው ይነገራቸዋል፡፡ ሰይጣንን አምነው ከባሎቻቸው፣ ከሚስቶቻቸው፣ ከእኅት ወንድሞቻቸው፣ ከጎረቤቶቻች፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ይጣላሉ፡፡ ከባቴ አበሳነትን ፈጽሞ የረሳ፣ ከፍቅር ይልቅ ጠላትነትን ለማስፈን የመጣ፣ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነው ከመፋቀር ይልቅ ሰይጣንን አምነው እንዲጣሉ የሚያደርግ የሰይጣን አሠራር ነው፡፡ ለመሆኑ ይህንን ሁሉ ሕዝብ ሰይጣን ሲቆጣጠረው ክርስቶስ የለምን? የተጠመቅነው የልጅነት ጥምቀት፣ የቆረብነውስ ቁርባን አይሠራምን? ገና ወደ ክርስትና ያልመጡ የገሊላ ክርስቲያኖች እንኳን በጩኸት አልተደበላለቁም እንኳን እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ የተባልነው፡፡ ይህ አሠራር የክርስቶስን ነገረ ድኅነት የሚፃረርና ከማዳን ሥራውም የወጣ ነው፡፡ ከክርስቶስ ክብርና ኃይል ይልቅ የሰይጣንን ኃይል ለማሳየት የሚሠራም ነው፡፡
6. ለመሆኑ ስመ እግዚአብሔርን የሚጠራ ሁሉ ትክክለኛ ነውን? አንዳንድ ምእመናን እንዲህ ይላሉ ‹እግዚአብሔርን ይጠራሉ፣ እመቤታችንንም ያከብራሉ››፡፡ ልክ ነው ሰይጣን ለአመሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ይባላል፡፡ ሰይጣን ምንም እንኳ የሐሰት አባቷ ቢሆንም (ዮሐ. 8፣44) ሙሉ ውሸት ግን አይናገርም፡፡ በከፊል እንጂ፡፡ ሔዋንን ‹ንግሥተ ሰማይ ወምድር› ሲላት ከፍሎ ነው የዋሻት፡፡ ንግሥተ ምድር ናት፤ ንግሥተ ሰማይ ግን አልነበረቺም፡፡ በወንጌል ውስጥ አጋንንት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ያውቃሉ፡፡ ሰይጣን ጌታን ሲፈትነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሶ ነው(ማቴ 4)፤ ጌታችን በጌርጌሴኖን ያገኛቸው አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ‹የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡ ንግግራቸው ልክ ነው፡፡ እነርሱ ግን አጋንንት ናቸው፡፡ ጌታም አስወጣቸው እንጂ ማን ድግምት እንዳደረገባቸው አላናዘዛቸውም፡፡ በሌላ ቦታም በምኩራብ ሲያስተምር አንድ ሰይጣን ያደረበትን ሰው አመጡለት፡፡ ሰይጣኑም ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ‹ ብሎ ነበር የጠራው፡፡ ጌታ ግን ‹ዝም ብለህ ወጣ› አለው እንጂ መድኃኒት ማን እንዳደረገ ተናገር አላለውም(ማር. 1፣21-28)፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ ስላለውም ሰይጣንነቱን አልቀየረውም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስተምር ፊልጵስዩስ የተባለ ከተማ ደረሰ፡፡ በዚያም አንዲት በርኩስ መንፈስ የተያዘች ሴት እየተከተለቺው ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› አለች፡፡ ሴትዮዋ የተናገረቺው ምንም ስሕተት የለውም፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን መንገድ ያስተምራሉ፡፡ የልዑል አምላክ ባሪያዎችም ናቸው፡፡ ይህ ትክክል ስለሆነ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ዝም አላለም፡፡ መንፈሱን አስወጣው እንጂ(የሐዋ.16፣16-18)፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚነግሩን አንድ ሰው ስመ እግዚአብሔርን ወይም ስመ ቅዱሳንን ስለጠራ ብቻ ትክክል መሆኑን እንደማያሳይ ነው፡፡ እርስ በርሱ የማይጣረስ ርቱዕ የሆነ እምነትም ያስፈልገዋል፡፡ ርቱዕ የሆነ ሕይወትም ያሻዋል፡፡ በክርስትና አንድ ሰው መንገዱ ትክክል ሳይሆን ውጤቱ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ያለ ትክክለኛ እምነት፣ ያለ ትክክለኛም መንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ ተአምራት ሊኖረው አይችልም፡፡ በሲኦል በኩል ወደ ገነት ሊገባ አይችልምና፡፡
7. ተአምራት ማድረግ ብቻውን የቅድስና ማሳያ አይደለም፡፡ ተአምራት ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት ሲመነጩ እንጂ፡፡ ተአምር ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት የመጣ ሲሆን ‹ስም በመንግሥተ ሰማያት በመጻፉ እንጂ በድንቅ ነገር ማንም ደስ አይለውም››(ሉቃ. 10፣ 17-20)፡፡ ተአምራትን ሲከተሉ መኖርም የአሕዛብነት ምልክት እንጂ የክርስትና ምልክት አይደለም(ማቴ. 12፣ 39)፡፡ የክርስትና ዋና መሠረቱ ክርስቲያናዊ ትምህርት፣ ክርስቲያናዊ እምነትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ናቸው፡፡ አንዳንዶች በማርቆስ ወንጌል መጨረሻ ላይ(ማር 16) ‹‹ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል›› የሚለውን ይጠቅሳሉ፡፡ እዚህ ላይ ያመኑት የተባሉት ‹የበቁት› ማለት ነው፡፡ ያማ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ተአምር ስናደርግ መኖራችን ነበር፡፡ አምነናልና፡፡ ደግሞም ያመኑት የሚለው ለሁላችንም ይሠራል ካልን እስኪ መርዝ ጠጥተን ምንም ሳንሆን ፣እባብም ጨብጠን ስንተርፍ እንየው፡፡ ይህ ሁሉ ግን በእመነት ለበሰሉ የሚቻል ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራም በሐዋርያት እጅ ያመኑት ሁሉ ተአምር ሲሠሩ አናይም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ድንቅ ሲሠሩ የምናያቸው ክርስቲያኖችም በጸሎት የተጉ፣ በሐዋርያነት አገልግሎት ሰማዕትነት የከፈሉ፣ በገድል የተቀጠቀጡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ሕይወቱ በተአምራት ከመገለጡ በፊት በሱባኤ የተወሰነ ነበረ(የሐዋ. 13፣ 1-3) የዛሬ አጥማቂዎች ግን ማጥመቅ ፕሮፌሽናቸው እንጂ የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መገለጫ አይደለም፡፡ እንዲህ ባለው ገዳም በገድል የኖሩ፣ እንዲህ ያለ መሥዋዕትነት ለክርስትና የከፈሉ ወይም ለምእመናን አርአያ የሚሆን እንዲህ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ናቸው ተብሎ የማይመሰከርላቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ ናቸው፡፡
8. የሰይጣን ምትሐትም አለ፡፡ የሙሴ ጸጋና ሕይወት ድል እንዲሆኑ ባያደርጋቸው ኖሮ የፈርዖን ጠንቋዮች ብዙ አስደናቂ ነገር ሠርተው ነበር(ዘጸ. 7፣8- 13)፡፡ በዘመነ ሳዖል የነበረቺው ሟርተኛም የሙታንን መንፈሶች ትጠራ ነበር(1ኛ ነገሥት. 28፣ 8-24)፡፡ አይሁድም አጋንንትን ያወጡ ነበር(የሐዋ. 19፣13)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የሐሳዊ መሲሕን አመጣጥ ሲያስተምረን ‹‹የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች፣ በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመጽም ማታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው›› ይላል (1ኛ ተሰ. 2፣9)፡፡ ይህም ከመንፈሳዊ ብቃት የማይመጣ ተአምር፣ ድንቅና ምልክት ምንጩ ከሰይጣን እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡ ዛሬ በእነዚህ ይህንን ያህል የምንታለል ከሆነ ነገ ሐሳዊ መሲሕ ከዚህ የሚበልጡ አስደናቂ ተአምራትን ሲያደርግ ጨልጠን ገርኝተን መከተላችን የማይቀር ነው፡፡ ‹‹የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ›› ተብሏልና፡፡
9. ምሥጢረ ቀንዲል መሠረቱን መጽሐፍ ቅዱስ ያደረገ(ያዕቆብ. 5፣13) ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የሚፈጸመው በካህናት ሲሆን የራሱ የሆነ የጸሎትና የመቀባት ሥርዓት አለው፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ምሥጢረ ቀንዲልን ማንበብ ይጠቅማል፡፡ አሁን የምናየው ግን በጀሪካል ቅባት ይዞ ማከፋፈል፣ ምእመናን ከአጥማቂዎች ‹ቅብዐ ቅዱስ› ወስደው እንዲጠጡና እንዲቀቡ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያልነበረ፣ በምሥጢረ ቀንዲል ያልተፈቀደና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ የሌለ ነው፡፡ አንዳንድ አጥማቂዎችም ‹‹ከኢየሩሳሌም የመጣ ነው›› ይላሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የሚመጣ የተለየ ቅባት የለም፡፡ አንድን ቅባት ቅዱስ የሚያደርገው ጸሎቱና ሥርዓቱ አንጂ የተሠራበት ከተማ አይደለም፡፡ ኢየሩሳሌም ውስጥ ግሪክ ኦርቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ሌሎችም አሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የመጣ ማለት ከየት የመጣ ነው? ምእመናን ለኢየሩሳሌም በጎ ኅሊና ስላላቸው ‹‹ከኢየሩሳሌም ተባርኮ የመጣ ›› ይባላል፡፡ ማን ባረከው? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡
10. ከአክባሪው ይልቅ ከባሪው፣ከሰጭው ይልቅ ተቀባዩ፣ከጌታው ይልቅ አገልጋዩ የሚከብርበት ሥራ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማክበር፣ አሕዛብም እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ከመንገድ ጠራጊውም ይልቅ መንገዱን እንዲያገኙት ማስቻል ነው፡፡ አሁን የምናያቸው ‹አጥማቂዎች› እና ‹ተአምራት› አድራጊዎች ግን ራሳቸውን የሚያከብሩ፣ እግዚአብሔርን የሚሸፍኑ፣ ሕዝቡ ቅዳሴና ትምህርት እየተወ እነርሱን በየሜዳው እንዲከተል የሚደርጉ፣ ሕዝቡ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወ ደሙ ከመቀበል ይልቅ የእነርሱ አድናቂና ካዳሚ እንዲሆን የሚስቡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ስለ ራሱ ሲናገር ‹እኔ ዝቅ ዝቅ ልል፣ እርሱም ከፍ ከፍ ሊል ይገባል›. ነበር ያለው (ዮሐ. 3፣29)፡፡ ለእነ ቅዱስ ጳውሎስም በልስጥራ እግሩ የሰለለውን ሰው በፈወሰው ጊዜ ሕዝቡ ተደንቆ እንደ አምላክ ሊሠዉላቸው ወድደው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹እንደ እናንተ ሰዎች ነን›. እያለ ለምኖ አስተዋቸው፡፡ ሕዝቡንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መለሳቸው፤ የእግዚአብሔርም ስም እንዲከብር አደረገ(የሐዋ 14፣8-18)፡፡
በእነዚህና ቤሎችም ምክንያቶች በዘመናችን የተነሡትን ‹አጥማቂ ነን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩትን፣ መቁጠሪያና ቅብዐ ቅዱስ የሚያከፋፍሉትን፣ በየሜዳው ሕዝብ ሰብስበው ምትሐት የሚሠሩትን ሰዎች መቀበል አለብን ብዬ አላምንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸጋው ግምጃ ቤት ናት፡፡ በጸሎት የሚተጉ፣በእምነት ሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች በየምሕረት አደባባዮች ምሕረትን ያገኛሉ፡፡ በቤተ ሳይዳ መልአኩ ውኃውን ይባርከው እንደነበር ሁሉ የጠበል ቦታዎችን ራሱ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ባርኳቸዋል፡፡ የተለየ አጥማቂ አያስፈልገቸውም፡፡ የክህነት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው እንጂ፡፡ ደግሞም ሁሉም ሕመም መዳን የለበትም፡፡ ደዌ ዘእሴት(ለበጎ የሚሰጥ ሕመም) አለ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የብዙዎችን ሰይጣን እያስወጣ እርሱን ግን የሚጎስመው ሰይጣን ነበረው፡፡ ጌታን ሲለምንም ‹‹ተወው›› ነው የተባለው(2ኛቆሮ. 12፣ 7)፡፡ የዛሬ አጥማቂ ነን ባዮች ግን ሁሉም ሕመም ይድናል ይላሉ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ ያልተቻለ ተቻላቸውን? ከሐዋርያት አንዱ የነገረው ያዕቆብ እግረ በሽተኛ ነበር(ዜና ሐዋርያት፣ በእንተ ያዕቆብ ሐዋርያ)፤ እርሱ ግን ብዙዎችን ይፈውስ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ምሕረት አገኘን የምንለውም ስንፈወስ ብቻ መሆን የለበትም፤ የምንታገሥበት ዐቅም ስናገኝም ጭምር እንጂ፡፡ ልመናችንም ለፈውስ ብቻ ሳይሆን ለመታገሥ ዐቅም እንዲሰጠን መሆንም አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ለመፈውስ የሚችል ቢሆንም ሁሉንም ግን አይፈውስም፡፡ ለበረከት፣ ለተግሣጽ፣ ከከንቱ ውዳሴና ከትዕቢት ለመከላከል የሚፈቅደው ደዌም አለ፡፡ ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ይህ ተሰጥቶት ነበር(ዘፍ. 32፣31)፡፡ ክርስትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመኖር፣ በንስሐ መንገድ በመመላለስ፣ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመሳተፍ እንጂ በድንቅና በተአምራት የሚኖር አይደለም፡፡
አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ‹‹ገንዘብ ይሰበስባሉ፣ ገቢ ያስገኛሉ›› ብለው እነዚህን ሐሳውያን እንደሚደግፉ ይታወቃል፡፡ ምእመናንም ‹‹ታድያ አቡነ እገሌ ለምን ፈቀዱ›› ይላሉ፡፡ እኛ ግን መሠረት ማድረግ ያለብን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ታሪከ ቤተ ክርስቲያንን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ማንም ከዚህ የወጣ ቢኖር ትምህርቱን ለመቀበል አንገደድም፡፡ ታላቅነት በእምነት እንጂ በሥልጣን አይገኝምና፡፡ ታላቁ አባት ዲዮስቆሮስ በ451 ዓም የኬልቄዶን ጉባኤ የልዮንን የሁለት ባሕርይ ትምህርት አልቀበል ሲል የሮም ባለ ሥልጣናት ‹‹እርሱኮ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የተቀመጠ የሮም ፖፕ ነውና አለቃህ ነው›› ባሉት ጊዜ ‹‹ሰይጣንም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበረ›› ብሎ ነው የመለሰላቸው፡፡
ሳንድያጎ፣ ካሊፎርንያ

የትጥቅ ትግልና ግራ የሚያጋባ አስተያየት – በፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

በኢትዮጵያ ትከሻ ላይ የተቆለፈውን ቀምበር ለማላቀቅ ቍልፉ የትጥቅ ትግል መሆኑ በተነሣ ቍጥር ከአንዳንድ ሰዎች የሚሰጠው አስተያየት ግራ የሚያገባ ነው። ገዢዎቹና ደጋፊዎቻቸው ቢቃወሙ ይገባኛል። የሚሰጡት አስተያየት ግን ሕፃንን ሳይቀር የሚያሥቅ ነው። “ጦርነት በቃን” ይላሉ። “አትንኩን” ማለታቸውን የማናውቅ ይመስላቸዋል።
ጦርነት ካላስፈለገ፥ ለምን ከንጉሣዊው አስተዳደር ጋር ተዋጉ? ለምን ከደርግ ጋር ተዋጉ? ጨቋኝ ገዢ የት አገር ነው በሌላ መንገድ ሥልጣን ለሕዝብ ሲለቅ የታየው? የምሥራቁ ዓለም ጨቋኞች የወደቁት በሕዝብ ዐመፅ ነው ማለት፥ የምዕራቡን ዓለም ከባድ እጅ ሚና መርሳት ይሆናል።
የኛዎቹ ጦርነት ከመረራቸው፥ ሕዝብን ወደጦርነት የሚመራ በደል አይሥሩበት። ምን ጊዜም ቢሆን የትጥቅ ትግል የመጨረሻው አማራጭ ነው። የትጥቅ ትግል የሚያደርሰው ጉዳት በአንዱ ወገን ላይ ብቻ አይደለም። መሣሪያ የሚያነሣ መሣሪያ ማንሣት የሚያመጣበትን ጉዳት ሳያውቅ አይነሣም።
ሰው ሆኖ እንደከብት መገዛት ያልቻለ ሰው በቃኝ ሲል፥ ክብሩን በመጠበቁ ከተቀመጡበት ተነሥቶ “ነወር” የሚባል እንጂ፥ በባርነት ጥላ ሥር ተቀምጦ የሚተች አይደለም። “ጦርነት መርሮናል” የሚለውን ምክር መገዛት ለመረረው አይመክሩም።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ግራ አጋቢ አስተያየት “ጦርነትስ አስፈላጊ ነው፥ ግን . . .” የሚለው ነው። ይህ አስተያየት በቅን አሳብ፥ የተሰጠ ሊሆን ይችላል። ግን አዛኝ መስሎ፥ ቀምበረኛውን ለመደገፍ የተሰጠ አስተያየት አለመሆኑ በምን ይታወቃል? እውነተኛ አሳቢና ሠጊ ሰው አስተያየቱን የሚሰጠው ሲጠየቅ፥ ካልተጠየቀም በግሉ ትጥቅ ያነሡትን ፈልጎ በጨዋ ደምብ መንገር ነው። ሳይጠየቁ ተነሥቶ በይፋ ምክር መስጠት ግን ሰሚው ሕዝብ ትግሉን እንዳይደግፍ መገፋፋት ነው። የትጥቅ ትግል ከታመነበት እንዲፋፋም የማይፈለግበት ምክንያት ምንድን ነው?
ትጥቅ ትግል የራስን ሕይወት ለወገን ነፃነት መሥዋዕት ማድረግ ነው። ሌላ ዓለማ የሌለው ሰው መሣሪያ ሲያነሣ፥ እንዴት ይኸንን የሚሰነዘርበትንና የሚሰነዘርለትን ምክር ሳያስብበት ራሱን ለመሥዋዕትነት ያቀርባል? የሚካኼደው የትጥቅ ትግል የሚያዋጣ የመሰለው እርዳታውን ያቅርብ፤ የማያዋጣ የመሰለው ለምንድን ነው የሚቃወመው? ተቃውሞው ማንን ለመጥቀም ነው? ለታጋዮቹ አስቦ ከሆነ፥ ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው። “የኔን ያህል የማሰብ ችሎታ የላችሁም” ማለት ነው። እንዴት ነው ለታጋዮቹ ያልተገለጠ ሥጋት ለምክር ሰጪዎቹ የተገለጠው?
አንዳንዱ ደግሞ፥ “ይኸው እንታገላለን ሲሉ ዓመታት አሳለፉ፥ ግን አንዳች ውጤት አላሳዩም” ይላል፤ ውጤት እንዲያሳዩ የቀጠራቸውና ካልሆነላቸው የሚያሰናብታቸው ሹም ይመስል። አርፎ መቀመጥ ስንት ውጤት አሳየ? ሌሎችን ሙከራዎችም “አንዳች ውጤት አላሳዩም” ብለን እንንቀፋቸዋ! ውይስ ውጤት አሳይተዋል?
“በመካሄድ ላይ ያለው የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” ከተባለ፥ እርግጥ ሊታሰብበት ይገባል። ግን አሳሳቢው ምክንያት ሊቀበሉት በሚገባ መልኩ አልተሰጠንም።
ይህ ትግል የሚያመጣው ጉዳት ከተሸከምነው ቀምበር ይበልጥ ሊከብድ እንደሚችል አሳዩን። የወያኔ ቀምበር መሰበር አለበት የምንል ሁሉ በመሰለንና በተቻለን መንገድ እንታገል። ካልተቻለን፥ ካልመሰለን፥ አርፈን እንቀመጥ፤ ታጋዮችን አለማደናቀፍ፥ እንደ ትግል እንዲቈጠርልን።

ሰበር ዜና ! ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !


የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ። ጋዜጠኛ ግሩም ላለፉት ሶስት ቀናት ሲታደን መቆየቱን የጠቁሙኝ ምንጮች ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውልኛል !
የጋዘጠኛ ግሩም መታሰር እንደሰማሁ ወደ የመን ስልክ በመደዎል ያነጋገርኳት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ በየነንየጋዜጠኛ ግሩምን መታሰር አረጋግጣልኛለች ። ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ከዚሁ ጋር አያይዛ ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት ” ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎች ስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ ” የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።
በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተው በማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛ ወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያን የስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ “የሞት ጉዞ ” የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም !
በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት እስራት ዙሪያ ስላሉት አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልኩ መረጃ የማቀርብ መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

በረሃብ የተጠቁ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ፤

ኢሳት ዜና ፦ በኤልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕፃናትን ጨምሮ ከ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑንና አፋጣኝ የሆነ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአውስትራሊያው ቻይልድ ፈንድ በሪፖርቱ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ያለው የርሃብ ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና በተለይ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች ለአስከፊ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ህጻናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ድርጅቱ አትቷል።
.
ቻይልድ ፈንድ አገልግሎት እየሰጠባቸው ባሉ አካባቢዎች እስከ 211 ሺህ ሰዎች ከዚህ ውስጥ ደግሞ 74 ሺህ የሚሆኑት ህጻናት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፍልጋቸው ገልጿል። ለሶስት ወራት የምግብ ድጋፍ ለማድረግ ቢያንስ 3.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልገውም አስታውቋል። ለሁለት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ወቅቱን ጠብቆ ዝናብ ባለመጣሉ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ለችግር መጋለጣቸውንና የችግሩ ዋናው ገፈት ቀማሾች ደግሞ ሕፃናት መሆናቸውንና አፋጣኝ የሆነ እርዳታ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ካልቀረበ ችግሩ አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችልም ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

Tuesday, September 29, 2015

ሑመራ ከተማ የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነው የገበያ ማእከል በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ወድሟል።


ቃጠለው ሓሙስ 13/ 01 / 2008 ዓ/ም ሌሊት ያጋጠመ ሲሆን የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ንብረት በቃጠለው መውደሙ ታውቋል።
ህብረተሰቡ ቃጠለው ለማጥፋት የተቻለው ቢጥርም ሊሳካ እንዳልቻለ ኑዋሪዋሪዎች ገልፀዋል።
ከሁሉም በላይ ሒመራን የምታክል ትልቅ ከተማ የእሳት ማጥፍያ መኪና መንግስት ባለማዘጋጀቱ ቅሬታቸው ኣሰምተዋል።
የቃጠለው መነሻ እስካሁን ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም።
መንግስት ለተለያዩ ምክንያት መሬቱ ሲፈልገው እሳት የማስገባት ልምድ እንዳለው ይታወቃል። ለምሳሌ በመቐለ ኢንዳስትሪ ቀበሌ በተነሳው ቃጠሎ ሱቃቸው የወደመባቸው ሰዎች መልሰው ለመገንባት ሲሞክሩ መንግስት ቦታው ለሌላ ስራ ስለፈለገው መስራት ኣትችሉም ተብለው ተከልክለዋል።
ሑመራ እነሞላ ኣስገዶም የገቡበት መንገድ ስለሆነ የጣሉት ወይም የተንጠባጠበ ቢሆንስ ማን ያውቃል።
ንብረታቸው ቃጠሎ ያወደመባቸው ዜጎቻችን ፅናት እንመኝላቸዋለን።
ህዝባችን በስንት ይቃጠል ባካቹ…?
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO……!
 Amdom Gebreslasie
Amdom Gebreslasie's photo.

ሰበር ዜና ሁለት የአሜሪካ ከፍተኛ የጦር አማካሪዎች ኤርትራ ገቡ።


በ 1960 ዎቹ አመተ ምህረት አካባቢ ወደ ቬትናም ሄዶ ሲያሰለጥን የነበረዉ የአሜሪካዉ ምርጥ እንዲሁም ኤኮ 31 በመባል የሚታወቀዉ ሐይል U.S. Army Special Forces and Echo 31 ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል በትናንትናዉ እለት ከኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ተቀማጭነታቸዉ በኤርትራ በሆኑ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር በተለይም ከርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋ መክሯል የተባለዉ ይህዉ ቡድን አመጣጡ ተቃዋሚዎችን ለመርዳት ነዉ ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ኮምባት አማካሪዎችን (combat advisors) አጣምሮ ኤርትራ የተከሰተዉ ኤኮ 31 የጦር አማካሪ ቡድን ወደመጣበት ይመለሳል በካባቢው ላይ የአል=ሸባ ሐይሎችንና በኤርትራ ደሴቶች ዙሪያ ለሚኖሩ የሽብር አደጋዎች የመከላከል ስልጠና ሊሰጥ ነዉ ቢባልም ቡድኑ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሐይሎች በተለይም ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር መምከሩ ለሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ቡድን እራስ ምታት ሳይሆን አይቀርም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው


‪አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ‪‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡ ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡ ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ በህዝብ ላይ ሴራ በማቀነባበር የሚታወቀው ህወሓት ራሱ ግንብቶ ለግለሰቦች ያከራየውን የንግድ ማዕከል ነው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል ከህዝብ ለመነጠል ሲል ነው በተቀነባበረ ሂደት በእሳት የለቀቀው ፡፡
በህወሓት የተቀነባበረ ሴራ የተከሰተው ከባድ የእሳት አደጋ የደረሰው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሲሆን ከ40 በላይ ሱቆች ተበልተው ወደ አመድነት ተቀይረዋል፤ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ንብረትም ወድሟል፡፡ ህወሓት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱት የቦንብ ፍንዳታዎች ትግራይ ሆቴልን ጨምሮ እጁ እንዳለበት የአሜሪካ ኤምባሲ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከውን ደብዳቤ በዋቢነት ጠቅሶ ዊክሊክስ የተባለው ድረ-ገፅ ማጋለጡ የሚታውስ ነው፡፡

Monday, September 28, 2015

ሥርዓቱ በሁለት ጫፍ የተሳለ አደጋ አፍጦበታል፤


በብዙ መልኩ ዴሞክራሲያዊ ገፅታን ያልተላበሰው ኢሕአዴግ ራሱን በገዥ መደብነት «አመቻችቶ» አስቀምጧል። ግንባሩ በቀደመው ዓመት አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በዝግ በማካሄድ እንደተለመደው ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቋል። በዚሁ ጉባኤ፣ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ጉባኤዎች በተለይም በ1994 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከተካሄደው አራተኛው የድርጅቱ ጉባኤ ጀምሮ ይነሱ የነበሩ አጀንዳዎች ቅርፃቸውን ብቻ በመቀየር ይዘታቸውን እንደጠበቁ እስከ አስረኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ድረስ ዘልቀዋል። በተለይም የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና ጉዳይ ከድርጅቱ ጋር አብረው የተፈጠሩ እስኪመስሉ ድረስ ችግሮቹ ገንግነዋል። በ1994ዓ.ም የአዲስ አበባው ጉባኤ አብይ አጀንዳ በመሆን ጉባይተኛው የተወያየበት አጀንዳ «ጥገኛ ዝቅጠት አስተሳሰብ» የስርዓቱ አደጋ መሆኑን ነበር። የቃላት ሃብታሙ ኢሕአዴግ፣ «ጥገኛ ዝግጠት አስተሳሰብ» የሚለውን ሃረግ «ኪራይ ሰብሳቢ» በሚል አገላለጽ በመተካት በቅርቡ እስከተካሄደው አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ድረስ ይህንኑ አጀንዳ ሲመክርበት ኑሯል። ከግንባሩ ነገረ ታሪክ መረዳት እንደሚቻለውም ድርጅቱ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ይሄው አጀንዳ (ኪራይ ሰብሳቢነት) ሲነሳና ሲወድቅ እንደሚኖር እሙን ነው። ርግጥ ይህ ጉዳይ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እየታየ ካለው የመልካም አስተዳደር እጦት ጋር በተያያዘ የማታ ማታ የግንባሩን ፍጻሜ የሚያቀርበው ይሆናል። በርግጥም ግንባሩ እንደሚለው «ኪራይ ሰብሳቢነት የሥርዓቱ አደጋ ነው»፡፡ ከዚህ አኳያ ሥርዓቱ በሁለት ጫፍ የተሳለ አደጋ አፍጦበታል።
.
«ኪራይ ሰብሳቢነት» ሲባል ኪራይ ሰብሳቢነት ሲባል ያልተገባ የኢኮኖሚ ጥቅም በማጋበዝ ብቻ የሚተረጎም ሳይሆን ከዚህ ባለፈ የፖለቲካ ጥቅም ትስስር (ኔት ወርክ) እና ቡድንተኝነትን መሰረት ያደረገ የስልጣን መደጋገፍንም የሚጨምር የትርጉም ይዘት አለው። የአደጋው መንታ መልክም ይሄው ነው። የስርዓቱ መሪዎች ለማመን በሚከብዱ የሙስና መረቦች በመተብተባቸው በህዝቡ ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ቅሬታዎችን መሰረት አድርጎ ሊፈጠር የሚችለው ህዝባዊ አመፅ የአደጋው አንዱ ገጽታ ሲሆን፤ ሁለተኛው የአደጋው መልክ ደግሞ ባለስልጣናቱ እንደ ቡድን በሚዘረጉት የሙስና መረብ ከጥቅም ትስስራቸው ጋር በተያያዘ እንደ መንግስታዊ መዋቅርም ሆነ እንደድርጅት የሚመጡ ግምገማዎችን በጋራ የሚመክቱበት እንዲሁም ባለስልጣናቱ የራሳቸውን የቡድን አባል ወደ ተሻለ የስልጣን ከፍታ ለማውጣት የሚያደርጉት ርብርብ የቡድን ፍላጎት የሚታይበት በመሆኑ፣ ፍላጎቱ ከሌላው ቡድን ጋር የሚጋጭ ከሆነ በዚህ መሀል የሚፈጠረው ልዩነት ከስርዓቱ አልፎ ለአገርም አደጋ የሚሆንበት እድል ይኖራል። በዚህ አግባብ ኢሕአዴግ በሁለት ጫፍ የተሳለ አደጋ አፍጦበታል።
.
‹የግንባሩን ቀጣይ እጣ ፈንታ ከሚወስኑት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ኪራይ ሰብሳቢነት ነው› የመባሉ እውነታም ከዚህ የመነጨ ነው። በተለይም የፖለቲካ ኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያ ብሄርን መሰረት ያደረገ ቡድንተኝነት የሚንፀባረቅበት በመሆኑ አደጋው ጠባብነትን መታያው አድርጎ የሚከሰት ሲሆን ፤ ይህን ተከትሎ የሚፈጠረው ችግር ከሥርዓቱ አልፎ ለአገርም የከፋ መሆኑ የሚያከራክረን ጉዳይ አይደለም። ስርዓቱ «ኪራይ ሰብሳቢነት ለመታገል ጥረት እያደረኩ ነው» እያለ ዲስኩሩን ቢያሰማም፣ ችግሩ ከመባባሱ ውጭ ጠብ ያለ ለውጥ በአደባባይ ሊታይ አልቻለም። እጅግ አስደንጋጭ የሙስና ሪከርዶች በተወካዮች ምክር ቤት በኩል በሪፖርት መልኩ ሲታለፍ ማየት የሚደንቅ አይደለም። በመሬትና በፍትህ አስተዳደር እንዲሁም በመንግስት ንብረት ግዢና ሽያጭ ላይ እየታዩ ያሉ ግልጽ የስልጣን መባለጎችን ስናስተውል አገሪቷን እንደ «መንግስት» እያስተዳደራት ባለው ገዢው ግንባር ላይ እምነት እንድናጣ ያደርገናል። ባገባደድነው አመት የፌዴራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ሃያ አምስት የሚሆኑ የፌዴራል መስሪያ ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ህጋዊነት የሌለው የንብረት ግዢና ሽያጭ መካሄዳቸውን፣ ሥራቸውን የለቀቁ ሰራተኞች በሌሉበት እስከ ስድስት ወር የሚደርስ ደመወዝ እንደተከፈላቸው፣ ያለ ጨረታ የኮንስትራክሽን ግንባታ ስራዎች ለተለያዩ ተቋራጮች እንደተሰጠ፣ ህጋዊ የደመወዝ ጭማሪ ላልተደረገላቸው ሰራተኞች በህገ-ወጥ መንገድ ተጨማሪ ክፍያ የከፈሉ መስሪያ ቤቶች መኖራቸውን ያመለከተው ይሄው ሪፖርት፣ በዚህም እንደ አገር ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ያልተመሳከረ ሒሳብ መኖሩን ይጠቁማል። ሪፖርቱ የፌዴራል መስሪያ ቤቶችንና የተወሰነ ዩኒቨርስቲዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፤ በየክልሉ ያለውን ምዝበራ ከዚህ ሪፖርት አኳያ ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። የፌዴራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የንብረት ግዢና ሽያጭ ችግር አለባቸው፣ ህጋዊ የፋይናንስ አሰራር አልተከተሉም በሚል በሪፖርቱ የጠቆማቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶችም ሆኑ ችግሩ የታየባቸው የዩኒቨርስቲ አመራሮች በህግ ሲጠየቁ ለማየት አልታደልንም። በርግጥ በኢህአዴግ ቤት ፖለቲካን እንጂ ገንዘብን መሰረቅ የስርዓቱ አንዱ ገጽታ ነውና የተለየ እርምጃ አይጠበቅም። ይሁንና እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ከገንዘብ ባለፈ የፖለቲካ ፍንገጣ ያሳዩ ቀን ‹ፋይላቸው› ከመሳቢያ መውጣቱ አይቀሬ ነው። በኢህአዴግ ቤት፣ ከሁሉም የሙስና አይነቶች ከባዱ ሙስና የመሬት ወረራን ተከትሎ እየተፈጠረ ያለው ምዝበራ ዋናው ተጠቃሽ ነው። በዚህ ዘርፍ እየታየ ያለው ሙስና «ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል» እንዲሉ የከፍተኛ አመራሮችን ፈለግ በመከተል ቀበሌ ድረስ ያሉ አመራሮች «ከድርሻቸው» በላይ በወዳጅ ቤተ ዘመድና በሙታን ስም ሳይቀር የመሬት ወረራዉን ተያይዘውታል። የታችኛው አመራር ምዝበራ አይን እያወጣ በመምጣቱ «ኪራይ ሰብሳቢነትን እየተዋጋሁ ነው» የሚለው ኢሕአዴግ፣ ለአስመሳይ ፖለቲካው ማሳያ ይሆን ዘንድ አልፎ አልፎ የታችኛውን አመራር ጭዳ ሲያደርገው ይታያል። ነገሩ ‹የኪራይ ሰብሳቢዎች መተካካት› አይነት ነገር ነው፡፡ የበላ ይሻራል፡፡ ያልበላ ይሾማል፡፡ ኡደቱም በዚህ መልኩ እየቀጠለ ያለ ይመስላል፡፡ ለዚህ ማሳያ ሆኖ የሚቀርበው ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሞክሮ ነው። የከተማ አስተዳደሩ የከተማ ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆነው አቶ ኃየሎም ጣውዩ በነሐሴ ወር ሦስተኛ ሳምንት ለንባብ ከወጣው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠየቅ በ2007 የሥራ ዘመን ከመሬት ጋር በተያያዘ ብቻ በየደረጃው ያሉ 315 (ሦስት መቶ አስራ አምስት) አመራሮችና ፈፃሚዎች ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ፣ ከእነዚህ ውስጥ በህግ የሚጠየቁ ኃላፊዎች እንዳሉ ተናግሯል።
.
በተመሳሳይ መልኩ ከተማ አስተዳደሩ 221 (ሁለት መቶ ሃያ አንድ) አመራሮችንና 4100 (አራት ሺህ አንድ መቶ) የሚሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን ከሥራ ሊያሰናብት እንደሆነ፣ በህግ የሚጠየቁ መኖራቸውንም ለፋና ብሮድ ካስት አስታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የካቢኔ ሹም ሽር እስከማድረግ የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሆነም መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ መካከለኛ አመራሮች ከሙስና ጋር በተያያዘ ከሥራ የሚሰናበቱበት አዲስ አበባ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ‹አንገት አልባ› አመራሮችን ተሸክማ በማዝገም ላይ ትገኛለች፡፡ ነገሩ «ጉልቻ ቢቀየር …..» አይነት ነገር ነው። የበላ ይሻራል። ያልበላ ይሾማል። ዑደቱም ይቀጥላል….ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ በተለይም ሀሰተኛ የመሬት ባለይዞታነት መረጃ በማዘጋጀትና ህጋዊ ቅድመ ሁኔታ ላላሟሉ ሰዎች በጥቅም ትስስር መሬት የመስጠቱ ሁኔታና የአመራሩ የመሬት ቅርምት ከአዲስ አበባ ከተማ በከፋ መልኩ በሌሎች የክልል ከተሞች እንዳለ ከአንባቢ የተሰወረ አይደለም። በፍትህ አስተዳደር በኩልም አስደንጋጭ የሙስና ተግባር እየተከሰተ እንዳለ የአደባባይ ምስጢር ነው። ከ30 ሺህ እስከ 350 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ በመቀበል በሀሰተኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፍርደኞችን የለቀቁ የፌደራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች መካከለኛ አመራሮችን እንዲሁም ከሙስና ጋር በተያያዘ የዳኞችን ክስ/ስንብት መስማት ከአመት አመት እየተለመደ መጥቷል።
.
እንግዲህ በ«ሕግ በምትመራ» አገር ላይ ከአመት አመት አስደንጋጭ የሙስና ዜናዎችን በሪፖርትም፣ በክስም መልክ እየታየ በመሆኑ «መንግስት» የሚባለው አካል ምን እየሰራ እንዳለ መጠየቅ ግድ ይለናል። የመሬትና የፍትህ አስተዳደርን እንደ ማሳያ አንስተን ተመለከትን እንጂ በሌሎች መንግስታዊ ተቋማቶች ዘንድ ምን አይነት ጉድ ሊፈጸም እንደሚችል መገመት የሚከብድ አይደለም። በቅርቡ እንኳ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበረው አቶ ወንድሙ ቢራቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የ500 (አምስት መቶ) ሚሊዮን ብር ኦዲት እየተጣራበት ይገኛል። የምርመራው ውጤት ምን ይሁን ምንም አንድ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣን በዚህን ያህል የብር መጠን በሙስና ወንጀል መጠርጠሩ (ኦዲት መደረጉ) ሥርዓቱ በምን ያህል መጠን እንደ ነቀዘ ጥሩ ማሳያ ይሆነናል። በየአመቱ ተዝቆ ከማያልቁ መንግስታዊ ጉዶች መካከል ጥቂቱን ቆንጥሮ የሚያሳየን የፌደራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንቅስቃሴ ከአሳ ነባሪዎች ይልቅ ትንንሽ አሳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ «መረቡ»ን የጣለ በመሆኑ፣ አህአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ሙስና የምንግዜም ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ ይኖራል። ገዢዉ መደብ ኢህአዴግ፣ በጉምቱ ባለሥልጣናቱ ላይ የሚታየውን ሙስና ከመቅረፍ ይልቅ «ሂስና ግለ ሂስ» በሚል ድርጅታዊ ቀኖናዉ ለጉዳዩ ከሚያሳየው መለሳለስ የተነሳ የሙስና ጉዳይ ለፖለቲካዊ አለመግባባቶች የመፍትሄ ማፈላለጊያ እየሆነ መጥቷል። ግንባሩ እንደሁልጊዜው ሁሉ በአስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤው «የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ኪራይ ሰብሳቢነት ሚናን በልማታዊ አስተሳሰብ በመተካት የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናረጋግጣለን» ቢልም፣ ጉዳዩ ከተለመደው የአቋም መግለጫነት የዘለለ ጠብ የሚል ነገር እንደማይኖረው የድርጅቱ የቀደመ ተሞክሮ ይነግረናል።
.
እንደ-መዉጫ
.
በመቶ ብሮች የሚቆጠር የወር ደመወዝተኛ በበዛባት አትዮጵያ፣ በየመስሪያ ቤቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ምዝበራ መካሄዱን፣ ይህን ተከትሎ እንደ አገር ቢሊዮን ብሮች በየዓመቱ በመንግስት ሌቦች መመዝበሩን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ከመንግስታዊ ተቋማት ጭምር መስማት መደበኛዉን የትራፊክ አደጋ ሪፖርት የመስማት ያህል እንኳን አላስደነግጠን ብሏል። በፖለቲካና በነጻ ተቋምነት መሃከል የዋልሉ ተቋማት አሁን አሁን የጠቅላዩ ኢህአዴግ ክንፍ መሆናቸዉን በተግባር እያሳዩን ነዉ። መንግስት በከሳሽነት በሚቀርብባቸዉ ፖለቲካ-ቅብ የክስ ጉዳዮች ተሸናፊ ሆኖ የታየበት አጋጣሚ የለም። የፍርድ ቤት ዉሳኔ በማረሚያ ቤት አመራሮች ሳይፈጸም ሲቀር የታዘብንባቸዉ አጋጣሚዎች ከጥቂት በላይ ናቸዉ። «ፍትህ»ን በብረትና በገንዘብ የገዙ አካላት አንገታቸዉን ቀና አድርገዉ በሚሄዱባት ኢትዮጵያ፣ የግፉአን ድምጽ በርክቶባታል። ጎን ማሳረፊያ ያጡ ዜጎች በበረከቱባት ሃገር፣ ከግማሽ ደርዘን በላይ ቪላ ቤቶች በተለያዩ ግለሰቦች ስም ያለዉ የኢህአዴግ መካከለኛ አመራር ፈልጎ ማግኘት ያን ያህል የሚከብድ አይደለም። በቦታ ርቀት፣ በግንዛቤ ማነስ፣ ከበቂ የምግብ አቅርቦት እጦት ጋር በተያያዘና መሰል ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተነሳ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ህጻናትና ወጣቶች በየአመቱ ትምህረታቸዉን ለማቋረጥ በሚገደዱባት አትዮጵያ፣ ልጆቻቸዉን ከአንድ ቀበሌ የግማሽ አመት በጀት ጋር የሚስተካከል የዉጭ አገር ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ የአህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ቁጥር እንደ ኢኮኖሚ «እድገቱ» ሁሉ በሁለት አሃዝ የሚገለጹ ናቸዉ፡፡ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ያጣ ህዝብ በበረከተባት አገር፣ የአልኮል መጠጥ ፋብሪካ በአክሲዮን ስም የገነቡ፤ ሚለዮኖች የዕለት ጉርሳቸዉን ያጡበት ሁኔታ የግል ባንክ ባለቤት የሁኑት ባለስልጣናት የደም እንጀራ እየጎረሱ እንደሆነ ሊረዱት አልቻሉም። የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ነገረ-ስራ በቅጡ ያስተዋለ ሰዉ የሚከተለዉ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻለዋል። እርሱም፡- ‹ማንኛዉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከህግ በላይ ናቸዉ። የትኛዉም የህዝብም ሆነ የአገር ሃብት የባለስልጣናቱ እንጂ የህዝብ አይደለም› ባልተጻፈ ህግ እየተተገበረ ያለዉ እዉነታ ይህ ነዉ። ኢህአዴግ «የ አስራ ሦስት ወር ጸጋ» የተባለላትን አገር ወደ አስራ ሦስት ወር የፖለቲካ ጭቆናና የኢኮኖሚ ብዝበዛ አሻግሯታል።
.
የአገሪቱ ማህበራዊ ቀዉስ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አላየንም። አይነ ስዉሩን ደርግ ሸኝተን ደንቆሮዉን አህአዴግ ተክተናልና ዛሬም እንደ ትላንቱ በደል የማንነት አካል ሆኗል፡፡ አስር፣ እንግልት፣ ስቅየት፣ ስደት፣ ሞት … ከገዥዉ መደብ በተቃራኒ የተሰለፉ ኢትዮጲያዉያን እጣ ፋንታ መሆኑን ሩብ ክፍለ-ዘመን ያካለለዉ የአገዛዙ ተሞክሮ ጮሆ ይመሰክራል። ገዥዉ መደብ በብዙ መልኩ ኮረብታዉ እርቆት ቁልቁለቱን በሚገርም ፍጥነት ተያይዞታል፤ የአይቀሬዉን አብዮት ማፍጠኛ የተጫነዉ ኢህአዴግ የህልዉናዉ ማክተሚያ ጊዜ ሩቅ አይደለም። በየአመቱ እንደ «መንግስት» አዋጂ አዲስ ዓመት መግባቱን በሚዲያ ስንሰማ ኑረናል። አዲስ ነገር በማናይበት ሁኔታ «አዲስ ዓመት» ብሎ ነገር ምናችን ነዉ?! እኛ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አመት ሳይሆን አዲስ ስርዓት እንሻለን!!
.
(የዚህ ጦማር አቅራቢ ጋዜጠኛ ሙሉዓለም ገ/መድህን ሲሆን በቅርቡ «የኢሕአዴግ ቁልቁለት» በሚል ርዕስ የጻፈው መጽሀፍ ለንባብ በቅቷል፡፡ ይህ ጽሁፍ በተለይለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተላከ ነው፡፡)

የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሶች በዝግ ይመክራሉ


የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት አባቶች፣ በሃይማኖታዊ ጉዳዮችና በማኅበራዊ ግንኙነቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ እንደሚመክሩ ተገለጸ፡፡
በእስክንድርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ ከሚመራው ልኡክ ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የሚካሔደው ምክክር፤ የኹለቱን አገሮችና አብያተ ክርስቲያናት የቆየ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ግንኙነት አጠናክሮ በማስቀጠል ወደ ከፍተኛ መተማመን እንዲያመራ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፤ ተብሏል፡፡
በክርስትናው አስተምህሮ ባላቸው የትምህርተ ሃይማኖት አንድነት፣ “እኅትማማች” የሚባሉት ኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት፣ የጋራ ተልእኮዎቻቸውን በአንድነት በመፈጸም ጥንታዊውንና ታሪካዊውን ግንኙነታቸውን ለማዳበር የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም የኢትዮጵያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባለፈው ዓመት ጥር ባደረጉት የግብጽ ይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት ጠይቀዋል፡፡
የግብጹ አቻቸው ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስም ጥያቄውን በመቀበል፤ በሃይማኖታዊ፣ በጤና እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር አብሮ የሚሠራና በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ኮሚቴ ለመሰየም ዝግጁ መኾናቸውን አስታውቀው እንደነበር ተወስቷል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ፈለገ ግዮን ተብሎ የሚታወቀውና ኹለቱ አገሮች በጋራ የሚጠቀሙበት ተፈጥሯዊው የዓባይ ውኃ የማኅበራዊ ትስስሩ መሠረት ሲኾን በዝግ በሚካሔደው የኹለቱ ቅዱሳት ሲኖዶሳት ምክክርም ዐቢይ ትኩረት እንደሚያገኝ ተጠቁሟል፡፡
የዓባይ ውኃን በመተማመን ከተጠቀሙበት ከኹለቱ አገሮች አልፎ ለመላው አፍሪካ የሚበቃ የአምላክ በረከት እንደኾነ ለግብጽ ባለሥልጣናት የተናገሩት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ “የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አንድ የሚኾኑት የእግዚአብሔር ጸጋ በኾነው በዓባይ ነው፤ እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ደግሞ ሰው ሊለያየው አይችልም፤” ያሉ ሲኾን ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስም፤ “እኛ የግብጽ ሕዝቦች ከዓባይ ወንዝ አንድ ብርጭቆ ውኃ በጠጣን ቁጥር ኢትዮጵያን እናስታውሳታለን፤” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡
በወቅቱ ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በ2008 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዲገኙ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በቀረበላቸው ግብዣ፣ ትላንት ሌሊቱን ዘጠኝ አባላት ያሉትን የሃይማኖት አባቶች ልኡክ በማስከተል ዐዲስ አበባ የገቡ ሲኾን ከዛሬ ጀምሮ የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡  ለጉብኝቱ የወጣው መርሐ ግብር እንደሚያመለክተው ፓትርያርኩ፣ ትላንትና መስከረም 14 ቀን ሌሊት 9፡00 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የፕሮቶኮል ባለድርሻ አካላት አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ፣ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 2፡30 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የመንበረ ፓትርያርኩና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ የእንኳን ደኅና መጡ ፕሮግራም ይደረግላቸዋል፤ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋርም ይወያያሉ ተብሏል፡፡
ጠዋት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራት፣ ሥርዐተ ቅዳሴውን የሚያከናውኑ ሲኾን ከቀትር በኋላም በመስቀል ዐደባባይ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር የመስቀል ደመራ በዓልን ያከብራሉ፡፡
ከመስከረም 17 – 19 ቀን የርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮን ማርያምን፣ የጎንደርን፣ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትንና ታሪካዊ ስፍራዎችን፣ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን እንዲኹም በአዲስ አበባ የሰበታ ጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ወጠባባት ገዳምንና የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመጎብኘት ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚባርኩ ታውቋል፡፡ በግብፅና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ የኹለቱ እኅትማማች አብያተ ክርስቲያናት ትብብር እንደ ድልድይ ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራሷን ፓትርያርክ በ1951 ዓ.ም እስከሾመችበት ጊዜ ድረስ ለ1600 ዓመታት ከግብጽ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሾሙ ጳጳሳት ስትመራ ቆይታለች፡፡ በሀገራቱ መንግሥታት ምክክር ጭምር የመንበሩ ነጻነት ከተገኘም በኋላ የሚካሄዱ ፕትርክናዊ ጉብኝቶች ለውጭ ግንኙነታቸው መጠናከር አስተዋፀኦ እንዳለው ይታመናል፡፡addisadmas

በማይጨው 11ሉኳንዳ ቤቶች ታገዱ!


በማይጨው ከተማ ያሉት 11 ሉኳንዳ ቤቶች ለከተማዋ ኑዋሪ የሚያቀርቡት ስጋ ለማሳረድ ወደ ማይጨው ቄራ የተዘጋጁት ከብቶች ይዘው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
የመታገዱ ምክንያ በቄራው የከብቶች ምርመራ የሚያካሂድ ዶክተር “ለእርዱ የሚበቃ ውሃ ስለ ሌለ ከብቶቻቹ ይዛቹ ተመለሱ” የሚል ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ መሆኑ ባለሉኳንዳዎች ገልፀዋል።
በመስቀል በዓል የማጨው ህዝብ የሚቀመስ ስጋ ማግኘት ኣልቻለም።
በውሃ እጥረት ምክንያት ማይጨው በኣለ መስቀሉ በጎመን እያለፈች ነው።

Wednesday, September 23, 2015

በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጂት መቀላቀላቸውን ከማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።


በደረሰን መረጃ መሰረት የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መቀላቀላቸውን የገለፀ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
1 ተክላይ ታፈረ ገብረዋሂድ ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት ወረዳ አዲ ላኪያን ቀበሌ አዲ በዛ አካባቢ
2 በሪሁ ገብረየሱስ ሃድጉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ቀበሌ አዲስ ተስፋ ሰፈር ደንጎሎ ከተባለው መንደር
3 ነፀረ-አብ አባዲ ፍስሃ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህዳይ አድያቦ ወረዳ ገመሃሎ ቀበሌ ሁመር ከተባለው ሰፈር
4 ፍስሃ ገብረስላሴ ገብረ መድህን ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቤተ ገበዝ ቀበሌ ዝባን እንዳቦይ ገብራት ከተባለው አካባቢ
5 ጉዑሽ ሃይለ ገብረስላሴ ከስሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ማይ አድራሻ ከተባለው ቀበሌ
6 አወት ገዛኢ ፈዳይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎመከዳ ወረዳ ዛላንበሳ ከተማ
7 ክብሮም ገብረ ፃድቅ ረዳ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አድፍታው ቀበሌ አዲ ቀረዲሂም ከተባለ መንደር
8 በሪሁ አብረሃ ተላ ከትግራይ ደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ስስት ቀበሌ ከታረ ከተባለው ሰፈር
9 በረከት ገብረ ኪዳን ወልደማሪያም ከትግራይ ማኦከላዊ ዞን ናአዴር አዴት ወረዳ አዲ ለኪያን ከተባለው ቀበሌ
10 ሚኪኤሌ ካህሳይ በርኸ ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ አዲ ፀፀር ከተባለው ቀበሌ
11 ፀጋይ ሃፍታይ ከምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላሎ ወረዳ ፅጌረዳ ቀበሌ
12 ከድር ወህበይ አብራር ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ አድ ብዘት ከተባለው ቀበሌ ብዘት አካባቢ እምቢሉ ከተባለው መንደር
13 ሃጎስ ገብረ ዮሃንስ ንጉሴ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አወት ቀበሌ
14 ግደይ ወልደሚካኤል ወልደማሪያም ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽረ ወረዳ ሰመማ ቀበሌ
15 አሸናፊ ገብረየሱስ ወልዱ ከምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ አዲ ገናህ ከተባለው አካባቢ
16 ዘነበ አለም ገብረ ሚካኤል ከሰሜን ምዕራብ ታህታይ አድያቦ ወረዳ ባድመ ቀበሌ
17 ገብረ ሂወት ጉዕሽ ገብረ መስቀል ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ራማ ቀበሌ ሰፈር 03
18 መብርሃቶም ሃዲሽ ተክለ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ አድክልተ ቀበሌ ገዛ ስቃ ከተባለው መንደር
19 ክብሮም ተሾመ ክንፈ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዳምበራይ ቀበሌ አዲገባ እና ሌሎችም ሲሆኑ በተለይ ፍስሃ ገብረ ስላሴ ስርዓቱን እንዲቃወም ያስገደደውን ምክንያት ሲናገር ስርዓቱ አገዛዙን ለማስረዘም ሲል ብድር በመስጠት ሞዴል ተሸላሚ ናችሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ተገልብጦ በተላላኪዎቹ ተጠቅሞ አቶ ገብረእግዜር ጋዕሲ የተባለውን ንፁህ ዜጋ የቀፎ ንቡን በማላታይን ሲያጠፉ በማየቱ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰልጣኝ ጉዕሽ ሃይሉ ገብረስላሴ በበኩሉ ባለፈው ምርጫ አረና የተባለውን ድርጂት የመረጡ ዜጎች ከመሬት እደላ እንደተከለከሉ ከገለፀ በኋላ ቀደም ሲልም በብድር የተሰጡ ወገኖችን ጊዜው ሳይደርስ መልሱ እያሉ እያሰሩ ያሰቃዩአቸው እንደነብር ገልፀዋል።
source: TPDM

ጦርነቱ ከሰሜን እስከ ኦጋዴንና ጋምቤላ ተፋፍሞ ቀጥሏል።


ጦርነቱ ከሰሜን እስከ ኦጋዴንና ጋምቤላ ተፋፍሞ ቀጥሏል።ይህ በንዲህ እንዳለ እንደውስጥ አወቅ ምንጮች ኤርትራ ወያኔን ለማንበርከክ የዛተች ሲሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ የሚከተለውን ያክብሮት መልክት አስተላልፋለች።
“ወያኔ በሉኣላዊት አገር ኤርትሪያ ጦርነት ቢያውጅ
የ ኤርትራ ህዝብና መንግስት ሊወስደው የሚችለው
እራስን የመከላከል እርምጃ የሚያነጣጥረው ወንድሙ እና እህት በሆነው
የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሳይሆን በህወዓት ላይ ብቻ መሆኑን ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘብልን እንወዳለን፥፥”

ጦርነቱ እንደቀጠለ ነዉ ከትግራይ ማይ ሁጻ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ተንቀሳቅሰዋል፤


ከትግራይ ማይ ሁጻ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ተንቀሳቅሰዋል! ከአዲ ሐገራይ የጦር አየር መንደርደሪያ የወያኔ ሄሊኮፍተሮች በተለያየ አቅጣጫ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች የቆሰሉ ና የሞቱ ወታደሮችን በማንሳት ተጠምደዋል… አነስተኛ የቃኘዉ ሚጎች በአዲግራት ጠረፍና በሁመራ አካባቢዎች እያንጃበቡ ነዉ። በዚያዉ አካባቢ ከአዲ ሐገራይ ከ5—7 ኪ.ሜ እርቀት ላይ የሚገኘዉ በተራራ የተሸፈነዉ የግንባር ሆስፒታል በቁስለኛ እየተጨናነቀ ይገኛል ህክምናዉን ለማገዝ ከመከላከያ ወታደራዊ ነርሶች ከመሐል ትግራይ ተንቀሳቀሰዋል በሁመራ አካባቢና በጠገዴ የተደራጁ የአርበኞች ግንቦት 7 ናቸዉ ተብሎ የተገመቱ ሐይሎች ከ 71 በላይ የወያኔ ቃኘው ጸረ ሽምቅ ሐይሎችን አጥቅተዉ 24 ኛ ክ/ጦር ወደ ስፍራዉተወርዉሯል።
.
ጦርነቱን በአንድ አቅጣጫ ለመምራት የህወሃት የጦር አመራሮች ግራ ተጋብተዋል ወታደራዊ የጦር መሐንዲሶችም ብቃታቸዉን በሚፈትን ሁኔታ ማጠፊያዉ አጥሯቸዋል። ወያኔ ለህዝብ ማሳወቅ ግድ የሚልበት ወቅት አይኑን አፍጥጦ የመጣ ሲሆን ወታደራዊ ደህንነቱ «ሞላ አስገዶም በመክዳቱ የተበሳጩ ጥቂት የሻዕቢያ ታጣቂዎች ለማጽዳት» በሚል ሰበብ የጦር ነጋሪቱ ይመታልኝና ሐይል የተላበሰ እርምጃ ይወሰድ ቢልም የጦር አመራሮች በአንድ አቅጣጫ የማይመጣዉንና የቱ ጋር እንኳ እንዳለ የማናዉቀዉን ሽምቅ ዉጊያ እንዴት ብለን ነዉ የምንዋጋዉ በማለት እየተናታረኩ ነዉ።
.
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Tuesday, September 22, 2015

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !


“መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡
በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡
አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ ተላልፏል፡፡
“ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡
ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡
አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡
ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡
ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡
ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

የወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትቴር ዛቻ!!

ሐይለማሪያም ደሳለኝ የተባለዉ ግለሰብ ኤርትራ ዉስጥ የተደራጁ ሐይሎችን እያየን የምንታገስበት ምክንያት የለንም ሲሉ ቃዥተዋል በአመታታት ዲስኩራቸዉ በኤርትራ ምንም አይነት የተደራጀ ሐይል የለም ይሉ የነበሩት ወያኔያዉያን የቁርጡ ቀን ሲመጣ የተደራጁ ሐይሎችን ለመደምሰስ ኤርትራን እንወራለን ኢያሉ እየዛቱ ይገኛሉ ይገኛሉ።
ህወሃቶች ትናንት የሰሩትን ስህተት ዛሬም የመድገም ህልም አላቸዉ ትናንት ኢትዮጵያዊያንን በባድሜና ሽራሮ ድንጋይ ላይ እንዳስጨረሱት ዛሬም ያንን የመድገም ህልም አላቸዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ቂል አይደለም አሁን የነጻነት ጥያቄ ነዉ ጦርነቱ በኛ በኢትዮጵያዊያንና በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መካከል ነዉ። እኛ ያለነዉ ኤርትራ በረሐ ነዉ! ስለነጻነታችን ስንቃትት ያስጠለለችን እህት ሐገር ኤርትራ! አዎ ትፈነዱም እንደዉ ፈንዱ!! ታዲያ ጸቡ በኛ በነሳነት ጥመኞቹና በእናንተ በወያኔዎች መካከል ሆኖ ሳለ ኤርትራን እንወራን እያላችሁ ትደነፋላችሁ። ” ሞክሩን ” እናንተ ወደ ኤርትራ ስጥመጡ እኛ ወደ ኢትዮጵያ እንደምንገሰግስ ስለምናዉቅ ሞክሩን ነዉ የምንለዉ!! ይልቅ ጨዋታዉ በርግጥ ገሐድ ከመዉጣቱ በፊት አሁንም ጊዜ ስላላችሁ ስልጣን ለህዝብ አስረክቡ ያለበለዛ ታልቃላችሁ!!ታልቃላችሁ!!ታልቃላችሁ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ጉድሽ ወያኔ

የአቶ ነሃምን ዘለቀ ከኤርትራ መልስ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቆይታ




ዜና ሰበር ጦርነቱ እንደቀጠለ ነዉ. ክትግራይ ማይ ሁጻ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ተንቀሳቅሰዋል


ክትግራይ ማይ ሁጻ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ተንቀሳቅሰዋል! ከአዲ ሐገራይ የጦር አየር መንደርደሪያ የወያኔ ሄሊኮፍተሮች በተለያየ አቅጣጫ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች የቆሰሉ ና የሞቱ ወታደሮችን በማንሳት ተጠምዷል አነ ስተኛ የቃኘዉ ሚጎች በአዲግራት ጠረፍና በሁመራ አካባቢዎች እያንጃበቡ ነዉ. በዚያዉ አካባቢ ከአዲ ሐገራይ ከ5_7 ኪ / ሜ እርቀት ላይ የሚገኘዉ በተራራ የተሸውፈነዉ የግንባር ሆስፒታል በቁስለኛ እየተጨናነቀ ይገኛል ህክምናዉን ለማገዝ ከመከላከያ ወታደራዊ ነርሶች ከመሐል ትግራይ ተንቀሳቀሰዋል በሁመራ አካባቢና በጠገዴ የተደራጁ የአርበኞች ግንቦት 7 ናቸዉ ተብሎ የተገመቱ ሐይሎች ከ 71 በላይ የወያኔ ቃኘው ጸረ ሽምቅ ሐይሎችን አጥቅተዉ 24 ኛ ክ / ጦር ወደ ስፍራዉ ተወርዉሯል. ጦርነቱን በአንድ አቅጣጫ ለመምራት የህወሃት የጦር አመራሮች ግራ ተጋብተዋል ወታደራዊ የጦር መሐንዲሶችም ብቃታቸዉን በሚፈትን ሁኔታ ማጠፊያዉ አጥሯቸዋል ወያኔ ለህዝብ ማሳወቅ ግድ የሚልበት ወቅት አይኑን አፍጥጦ የመጣ ሲሆን ወታደራዊ ደህንነቱ ሞላ አስገዶም በመክዳቱ የተበሳጩ ጥቁት የሻቢያ ታጣቂዎች ለማጽዳት በሚል ሰበብ የጦር ነጋሪቱ ይመታልኝና ሐይል የተላበሰ እርምጃ ይወሰድ ቢልም የጦር አመራሮች በንድ አቅጣጫ የማይመጣዉንና የቱ ጋር እንኳ እንዳለ የማናዉቀዉን ሽምቅ ዉጊያ እንዴት ብለን ነዉ የምንዋጋዉ በማለት እየተናታረኩ ነዉ. ለኢትዮጵያ ህዝብ ድል ጉድሽ ወያኔ

የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል፡፡


ከዳባት አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው መንገድ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሳኔ መታጠፉ ተገለፀ፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም መንገዱ የሚገነባበትን አካባቢ ህዝብ ማለትም ከዳባት እስከ ጠገዴ ለሚገኘው ነዋሪ መንገድ ሊገነባለት ዕቅዱ እና በጀቱ አልቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ቃል ከመግባት አልፎ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ አድርጎ ነበር፡፡ የይስሙላሁ ጠ/ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሰላኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በፊት ጎንደር ተገኝቶ “ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ የሚደርስ መንገድ በፌድራል መንግስቱ ወጭ እንገነባለን…” ሲል ቃል ገብቷ፡፡ ነገር ግን ከሰሞኑ ዕቅዱ መሰረዙ ለወረዳው ባለስልጣናት ከፌድራል አገዛዙ ባለስልጣናት በቀጥታ ተገልፆላችዋል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ድረስ ሊሰራ የተከለለው መንገድ ግንባታ ዕቅድ የታጠፈው መንገዱ ጠገዴ ከደረሰ በቀላሉ ከወልቃይት ጋር ይገናኛል በሚል ምክኒያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ የህወሓት አገዛዝ የወልቃይትን ህዝብ ያለፍላጎቱ ከጎንደር ገንጥሎ ከትግራይ ጋር በመቀላቀል በኃይል አፍኖ ረግጦ እየገዛው መሆኑ የሚታወቅ ነው በመሆኑም መከረኛው የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ በዕቅድ ተይዞ የወልቃይትን ህዝብ ለመነጠል ሲባል ብቻ የተሰረዘው መንገድ እንዲገነባ በህዝቡ የተጠየቀው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር፡፡
የአካባቢው ህዝብ መንገዱ አይሰራም በመባሉ ብቻ ሳይሆን አገዛዙ ዕቅዱን ለመሰረዝ የተነሳሳበት ምክንያት እጅግ በጣም እያበሳጨው እንደሆነ እና ለለውጥ ለመታገል ውስጥ ለውስጥ መደራጀት መጀመሩን የአርበኞች ግንቦት 7ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

Monday, September 21, 2015

ዶ/ር አረጋዊ በርኼ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ከህወሃት በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብላቸውም እንዳማይቀበሉት ገለፁ፤


የቀድሞው የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አባል የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ህወሃት ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፣ ከድርጅቱ የለቀቁ የቀድሞ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጅታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል።
ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ የውስጥ ችግር መዳከሙን የሚገልጹት ዶ/ር አረጋዊ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እርሳቸውም ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በተደጋጋሚ እንዳናገሯቸው ይሁን እንጅ እርሳቸው የሚታገሉለት አላማ ጥሪውን እንዳይቀበሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
.
ዶ/ር አረጋዊ «በቅርቡ የትህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሞላ አስጎዶም ወደ ህወሃት መመለሳቸው ወይም ሌሎች የቀድሞው ታጋዮች ወደ ድርጅቱ መመለሳቸው ለህወሃት ኢህዴግ ትንሽ ስትንፋስ ይሰጠው ካልሆነ ችግሩን አይቀርፍለትም» ሲሉ ያክላሉ። በእርሳቸውና አቶ ሞላ አስገዶም ይመሩት በነበረው ትህዴን መካከል የቆየ ግንኙነት አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር አረጋዊ፣ ኮሎኔል ፍሰሃ ድርጅቱን ይመሩ በነበረበት ወቅት ግንኙነት እንደነበራቸው ይሁን እንጅ አቶ ሞላ አመራሩን ከያዙት በኋላ ግንኙነቱን ማቋረጣቸውንና አቶ ሞላ በተደጋጋሚ ሊቀርቧቸው ቢሞክሩም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ገልጸዋል።
.
ዶ/ር አረጋዊ ፣ አቶ ሞላም ሆኑ ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ አባላት ወደ ድርጅቱ ተመልሰው መግባታቸው የትግራይ ህዝብ ሊወቀስ እንደማይገባው፣ የትግራይን ህዝብ በደፈናው ከህወሃት ጋር ደምሮ ለማየት የሚደረገው ሙከራ ፣ እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዘረኛ መሆንና በትግራይ ውስጥ ያለውን ብሶት ላለማየት ከመፈለግ የሚመጣ ነው ብለዋል። ዲሞክራሲያዊ መሰረት ያለው ስርዓት ለመገንባት እንታገላለን የሚሉ ሃይሎች የኢህአዴግን አገዛዝ ለማስወገድ መተባባር ይኖርባቸዋል ሲሉም ዶ/ር አረጋዊ ተናግረዋል። ሙሉውን ቃለምልልስ እንደደረሰ እናቀርበዋለን።

የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።


Getachew Reda sitt bilde.
ሥግብግቦቹ የብአዴን መሪዎች ከወያኔ ጋር አብረው የዐማራ ሕዝብን እያጠፉ ይገኛል
የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን። እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

Thursday, September 17, 2015

ሰበር ዜና በህብረቱ ሐይሎችና በወያኔ መካከል ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው

ዛሬ በ17/09/2015

በአርበኞች ግንቦት 7 በትህዴን እንዲሁም በህብረቱ ሐይሎች ከፍተኛ ድል የተደረገ ነዉ አማጽያኑ ገዢ መረት ተቆናጠዋል ህዝባዊ ወያኔ የሚመራዉ ሰራዊት በመበታተን እየሸሸ ነዉ፤
ምንጮቻችን ኢእንደሚገልጹት ከሆነ የአማጺያኑ ሰራዊት በእልህና በድፍረት ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ነዉ፤ የከባድ መሳሪያ በማዕሉባ ወረዳ ላይ እየተምዘገዘገ ነዉ፥፡
በኤርትራ ውስጥ በሁመራ ድንበር አካባቢ ከአምሓጀር ከተማ በስተ ጀርባ ማዕሉባ ከማለዳው 4:30 ጀምሮ እስከ አሁንዋ ሰዓት ድረስ በከፍተኛ ደረጃ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን ከነብስ ወከፍ እስከ ከባድ መሳራ ልውውጥ እየወረደባት ነዉ ከተማዋ በወያኔ ፌደራል እና የአካባቢ ሚሊሻ እንዲሁም መከላከያ ትርምስምስ ዉስጥ ገብታለች 
ድል ለኢትዮጵያዊያን !! ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 እና ለህብረቱ ሰራዊት!!!

Wednesday, September 16, 2015

አራት ጥይት የተፈረደባት አንዲት ነፍስ!


የሟች እናት ለቅሶ ነበር … ይሄ ግን የአንዲት እናት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ጥያቄ ነው ለእኔ ….ይታያችሁ ይች ትላንት ህልፈቷን የነገርኳችሁ ወጣት ሶሎሜ ጉልላት ….ስትገደል አብራት የነበረችው ጓደኛዋ እንደገለፀችው ….. የታመመ ሰው ለመጤቅ ጆሞ ቁጥር 1 ወደሚባለው ኮንዶሚኒየም ይሄዳሉ … የሄዱበትን ጉዳይ ጨርሰው ወደአንድ ካፌ ይገቡና ሲወጡ ወደመፀዳጃ ቤት ይሄዳሉ ….መፃዳጃ ቤቱ ውስጥ ክላሽንኮቭ የታጠቀ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰ ሰው ቁሟል አልፈውት ገብተው ሲመለሱ የመፀዳጃ ቤቱ የውጭ በር ተቀርሮ መታጠቢ ክፍሉ ውስጥ ሰውየው ቁሟል …
ሟችን ጠርቶ ‹‹ሰላም በይኝ›› ይላታል …ሰላም ለማለት ፈቃደኛ አልሆነችም …እናም ይህ ሰው በቦክስ ሟችን ይመታትና መሬት ላይ ይጥላታል ….ቀጣዩ ጉዳይ ለማመን የሚቸግር ነበር …ጓደኛዋ ወደአንዱ መፀዳጃ ክፍል ገብታ ከውስጥ ቀረቀረችው … ወዲያው ግን አካባቢው በተኩስ ድምፅ ተናወጠ …አራት ጥይቶች ተተኮሱ ሰውየው በሶስት ጥይት ሶሎሜን ነበር የደበደባት …በመጨረሻም ራሱ ላይ ተኮሰ … ሶሎሜ ህይወቷ ወዲያው ሲያልፍ ገዳይ ይሙት ይትረፍ አልተረጋገጠም !!
እንግዲህ መሳሪያ የታጠቁና የመንግስት እና ህዝብ አደራ የተሸከሙ ሰዎች የግል ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሃላፊነትን ከግል ጉዳይ መለየት ካልቻሉ ምን እንላለን ! ከዚህ በፊት ባህር ዳር ላይ በተመሳሳይ የወደድኳት ልጅ ተወችኝ በሚል ምክንያት በርካታ ሰዎችን ተኩሶ በመግደል ራሱን ስላጠፋው የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ተብሏል ….ለመሆኑ ለእንደዚህ አይነት ለህዝብም ህዝብ እጠብቃለሁ ለሚለውም አካል አሳፋሪና አሳቃቂ የሆነ ድርጊት ተጠያቂው ማነው ? በቃ የሆነው ሆነ ተብሎ ዝም ማለቱስ እስከመቸ??
Alex Abreham's photo.
Alex Abreham's photo.

” ከእንካሰላንታው ባሻገር” ኤርሚያስ ለገሰ


የሰሞኑን የኢትዬጲያ ፓለቲካ ለተከታተለ ሰው የትግሉ ጫፍ ወዴት እየሔደ እንደሆነ ለመገመት አያዳግተውም። …በአንድ በኩል ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት የበላይነቱን ያስጠበቀው አናሳ እና ዘረኛ ቡድን አሁንም ከማንም በላይ የደም ሀረጉን በመምዘዝ ለመሰባሰብ እየተጋ ያለበት ነው። …በሌላ በኩል ሁሉን አቀፍ ትግል የመረጡ በብሔርም ሆነ በሕብረ ብሔራዊነት የተደራጁ ሀይሎች ሀይላቸውን በማቀናጀት በጋራ ለመስራት እየተመካከሩ ያለበት ሁኔታ ነው። እነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች ከፓለቲካ ፓርቲ እና የድርጅት ህልውና ባሻገር ከኢትዬጲያ ህዝብ የነጳነት ትግል መቀጠልና ወደ ኃላ መመለስ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ርግጥም የእነዚህ ሁለት አካላት የፍልሚያ ውጤት የወደፊቱን የኢትዬጲያ እጣ ፋንታ የመወሰን እድሉ ከፍተኛ ነው።
1• ” አናሳ እና ዘረኛው ቡድን”
የመጀመሪያው እድል ከፓለቲካ ፕሮግራም እና ብቃት ይልቅ የማንነት ደም ያስተሳሰራቸው አናሳ ቡድኖች በኢትዬጲያ ህዝብ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው፣ እንደ በረሮ(?) ከክብደታቸው በላይ የሚበሉበት ሁኔታ መፈጠሩ ነው። ያለማጋነን የዛሬይቱ ኢትዬጲያ በጥቁር ደም በተሞሉ መዥገሮችና ቁንጣን በያዛቸው በረሮዎች ተወራለች። የአናሳው ቡድን ተስፈኞችም ህዝባችን ላይ የተጋረጠ አደጋ በማለት ወደዚህ ቡድን እየተሰባሰቡ ነው። የትግራይን ህዝብ ካባ በማጥለቅ የራስን የስልጣን ፍላጐት ለማርካት ጥረት እየተደረገ ነው። በተባራሪ እንደሰማነው የተቃዋሚ አመራሮች ነን የሚሉና ብሄራዊ ማንነታቸው ሁሌም የበላይ እንደሆነ እንዲቀጥል የሚፈልጉትም በዚህ ጐራ የሚካተቱ ናቸው። አንዳንድ ምልክቶችም እየታዩ ነው።በህውሀት ጉባኤ አንዱ ተነስቶ ውይይት የተደረገበት እነዚህን ተቃዋሚዎች ( አቤ ቶኪቻው “የስጋ ዘመዶች ” ይላቸዋል) በመለየት ቢያንስ የማለዘብ ስራ የመስራት አስፈላጊነት መሆኑ የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ። መጀመሪያ በሀገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ስያሜ የተሰጣቸው ቡድኖች የቅድሚያ ትኩረት አግኝተዋል። በማስከተል ወደ ተለያዩ ሀገሮችም አማላይ ቡድኖችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው። በቅርቡ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥተው የነበሩ ግብረሀይሎች አንዱ ተልእኮ ይህ እንደነበረ ይገመታል። ወደ አውሮፓም የሚሄዱ ( በተለይም የቀድሞ ህውሀት አመራሮችን የሚያናግሩ) የህውሀት ቡጅሌዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።
ይሔ በአናሳ ብሔር ስም የተሰባሰበ ቡድን በአሁን ሰአት እየተከተለ ያለው ስትራቴጂ ዋነኛ ማጠንጠኛ የትግራይ ህዝብ እና ሌላው የኢትዬጲያ ማህበረሰብ በባላንጣነት እና ጠላትነት እንዲተያይ ማድረግ ነው። ይሄ ቡድን ለዘር ማጥፋት እንደ አንድ ምልክት ተደርጐ የሚቆጠረውን ” እኛ እና እነሱ!” የሚለውን አባባል ወደ ተግባር ለመለወጥ ወገቡን ታጥቆ እየሰራ ነው። ይህ አናሳ ቡድን ኃላቀር በሆነ የፓለቲካ ባህል የተተበተበ በመሆኑ የትግራይን ህዝብ ለማደናገር በዘረኝነት እየቀሰቀሰ ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዬጲያዊ በመለያየት እና በማናቆር አገዛዛቸውን ለማራዘም ወገባቸወን ጠበቅ አድርገው እየሰሩ ነው። ይህ አናሳ ቡድን የተቀረው የኢትዬጲያ ህዝብ እንዲያውቅላቸው የሚፈልጉት ነገር አለ። ይኸውም እርስ በእርሳቸው ቅራኔ ቢፈጠር እንኳን ” በአንድ ጐጆ ስር” የተፈጠረ ልዩነት አድርጐ የኢትዬጲያ ህዝብ እንዲወስድ ይፈልጋሉ። ለዚህም ነው ከአስርተ አመታት በላይ በኤርትራ የመሸገውን የትግራይ ንቅናቄ በአሸባሪነት በፓርላማ እንዲፈረጅ ያላደረገው። በተቃራኒው ከእሱ ያነሰ እድሜ ያለው ግንቦት ሰባት በአሸባሪነት እንዲመደብ ያደረገው። …
…ለዚህም ነው ኤርትራ የመሸገውን ደህሚት “የኤርትራ ሀይል ( የኢሳያስ ጠባቂ)” የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያደረገው። …ለዚህም ነው ደህሚት ያሉት አባላት ከ300 አይበልጡም የሚል አሰልቺ ፕሮፐጋንዳ ለተራዘመ አመታት እንዲስተጋባ ያደረገው።…ለዚህም ነው አይኑን በጨው አጥቦ በግላጭ የተናገረውን በማጠፍ ዛሬ ደግሞ በሶስት እጥፍ ቁጥራቸውን አሳድጐና አጀግኖ ነገሪት እየጐሰመ ተቀበልኳቸው የሚለን። …ለዚህም ነው እነዚህ ትግሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሻገር ያቃታቸው ” የጦጣ ዘር አቀባዬች” መንገዋለላቸውን አውቀው ቅሬታ ሲያዝሉ መንገድ ላይ አፈፍ አድርጐ ” ለእኛ እና እነሱ” የውድመት ስትራቴጂው የተጠቀመበት። …
…ለዚህም ነው በተቀረው ኢትዬጲያውያን ዘንድ ” ዘሮች ሁሉ እኩል ናቸው፣ አንዳንድ ዘሮች ግን የበለጠ እኩል ናቸው” የሚለው አባባል ገዥ አስተሳሰብ እንዲሆን ያደረገው። …ለዚህም ነው ” ፕሮፌሰሩ ወደ ጫካ እንዲገባ ያደረግነው እኛ ነን!” ያለው አንደበታቸው ሳይዘጋ ” ኢሳያስ ፕሮፌሰሩን ወደ ሜዳ እንዲወርድ አደረገው” የሚል ቅጥፈት ሲናገሩ የማይሸማቀቁት። እኔ እምለው ኢሳያስ አፈወርቂና አባይ ወልዱ (ዶክተር ደብረጲዬን) እየተመካከሩ መስራት ጀመሩ እንዴ?…መቼስ ” የአህያ በሬ!” የሆነው “ደ -ሳአ -ለ -ኝ!” እና ሌሎች ባለሟሎች የዚህ አካል ነው ብሎ ማመን ከቧልት አይዘልም ብዬ ነው።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ አንዳንድ በሚኒስትር እና ፓርላማ ደረጃ ያሉትን ባለሟሎች ሁለት ጥያቄ ልጠይቅ። ክቡር ሚኒስትሮች! ለመሆኑ ” የፀረ ሽብርተኝነት ግብረሀይል አባላት” እነማን እንደሆኑ ታውቃላችሁ?… ክቡራን ሚኒስትሮች እና የሸንጐ አባላት ደእሚት የሽብርተኝነት አዋጁ ከመውጣቱ ስድስት እና ሰባት አመት በፊት የተቋቋመ እንደሆነ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል። ታዲያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት፣ በወይዘሮ አስቴር ማሞ አንባቢነት፣ በተከበረው ፓርላማ አጵዳቂነት ለምን በሽብርተኝነት አልተፈረጀም??
2• ” The Law of the Few!”
ሁለተኛው እድል አምባገነናዊ ስርአቱ እየደቀነ ያለውን አደጋ በአግባቡ በመረዳት የስርአት ለውጥ መምጣት እንዳለበት ያመኑ ሀይሎች ቅሌን ጨርቄን ሳይሉ በትብብር የሚሰሩበት ሁኔታ መፍጠር ነው። ትብብርም እንበለው ንቅናቄ የመጨረሻው ግቡ በጠመንጃ ስልጣን ያለመያዝ፣… በኢትዬጲያ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት መደላድል መፍጠር፣ …ሁሉን የሚያቅፍ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እስከሆነ ድረስ በጋራ ለመስራት የሚያስቸግረው አይደለም። የትብብር አላማ እና ግቡ ግልጵ እስከሆነ ድረስ በጥቂቶች ቢጀመርም (“The Law of the few”) ነገ እልፎችን የሚያሰልፍ ጥቂቶችን እያራገፈ የሚሄድ መሆኑ ሳይንሳዊ ነው። በተጨባጭም እየታየ ያለው እውነታ የዚህን ሳይንሳዊ አባባል የሚያፀና ነው።
እንደ እውነቱ ከሆነ የሰሞኑን የጥቂት የለውጥ ሀይሎች እንቅስቃሴ ስመለከት የሚያስታውሰኝ የማልኮም ግላድዌል የሚባለው ፀሀፊ የጳፈው የሊደርሺፕ መጵሀፍ ነው። ማልኮም ” Tipping point: How little Things make Big Differences” በሚለው መጵሀፋ ህዝባዊ ንቅናቄ (ማእበል) የሚቀሰቀሰው በጥቂት የቆረጡ ሰዎች እንደሆነ ያስረዳል። በእሱ እምነት መሰረት መሰረታዊ የለውጥ ሂደት ( ህዝባዊ ንቅናቄ) ለማቀጣጠል ወሳኞቹ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ እነዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጣሪዎች ራእይ ያላቸው፣ ራእያቸውን ለማስፈፀም ስትራቴጂና አቅጣጫ የመንደፍ ክህሎት፣ የማደራጀት ብቃት፣ በህዝባዊ ማእበል ሊያነሷሷቸው ከሚፈልጉት ማህበረሰብ ጋር የተሻለ ተቀባይነት፣ እንዲሁም አለም አቀፍ እና አገራዊ ሁኔታውን ለመተንተን የሚያስችላቸው ብቃት ያላቸው ሊሆን ይገባል።
ከላይ የተቀመጠውን ሀልዬት መሰረት በማድረግ እነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀይሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሶስት አበረታች ውጤቶችን ያስመዘገቡ ይመስለኛል። እነዚህም፣
2•1 ምን አይነት ትግል
በእነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀይሎች ከአመታት በፊት ሲቀነቀን የነበረው ” በኢትዬጲያ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉን አቀፍ ትግል መካሔድ አለበት” የሚለው የፀና አቋማቸው በኢትዬጲያ ምድር ላይ ገዥ መሬት ተቆናጦ የአብዛኛው አስተሳሰብ ወደ መሆን ተቀይሯል። በዛሬይቱ ኢትዬጲያ አናሳው ዘረኛ ቡድን የበላይነቱን እስከያዘ ድረስ የምርጫ ፓለቲካ እንደ እባብ አፈር ልሶ የመነሳት እድሉ አልቦን በአልቦ የማባዛት ያህል ሆኗል። ከእንግዲህ በኃላ ብረት እና ህዝባዊ እንቢተኝነት ተዋህደው (Synergy) ፈጥረው እስካልተንቀሳቀሱ ድረስ በሌላ መንገድ ለውጥ አመጣለው የሚለው አካሄድ የተዘጋ ፋይል ሆኗል። እንደ እውነቱ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ” ብሔራዊ መግባባት”፣ ” ህገ መንግስት”፣ ” ምርጫ ቦርድ”፣ ” ተፎካካሪ ፓርቲ” …ወዘተ የሚሉ አባባሎችና ተቋማት ” ከኢቲቪ እና የመለስ አካዳሚ” ከሚባሉት ስፍራዎች የዘለለ ቦታ የላቸውም። ዛሬ በኢትዬጲያውያን ዘንድ ያለው አስተሳሰብ በጉልበት ረግጦ የሚገዛ ሀይል የሚወገደው በጉልበት ብቻ እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል።
2•2 የለውጥ ሀይሎችን ማብዛት
እነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀዋርያዎች በወሰዱት እርምጃ ባልተጠበቀ ሁኔታ የደጋፊያቸውን ሀይል ማሳደግ ችለዋል። በርካታው ህዝብ ( የሚቃወሟቸውን ሳይቀር) በወሰዱት እርምጃ አክብሮት እንዳለው ማሳየት ችለዋል። እነዚህ የለውጥ ሀይሎች የሚታመኑ እና የሚሰሙ በመሆናቸው መላውን ኔትወርክ ለመቆጣጠር ችለዋል። ዛሬ አብዛኛው ማህበራዊ ድረገጶችና ሚዲያዎች የተሸፈኑት በእነዚህ ሰዎች የእለት እንቅስቃሴ ሆኗል። በመላው አለም እነሱን ለመደገፍ የሚጠሩ ስብሰባዎች የህዝብ ማእበል እያጋጠማቸው ነው። እናቶች የጣት ወርቃቸውን አውልቀው እስከመስጠት ደርሰዋል። በየአህጉሩ ጠንካራ ተከታዬችን በማፍራት ላይ ናቸው። ባጭሩ ትንሹ መዘውር ትልቁን ማንቀሳቀስ ጀምሯል። ትልቁ መዘውር በተሟላ ሁኔታ መንቀሳቀስ ከጀመረ የሚያቆመው አይኖርም…The law of few!
እዚህ ላይ አንድ ነገር ላንሳ። እነዚህ በአናሳ ብሔር ገዥ መደብ ዙሪያ የተሰባሰቡ ዘረኞች እና ባለሟሎቻቸው ዘወትር ከአፋቸው የማትጠፋ የፕሮፐጋንዳ ቃል አለች። ይህቺም ” የዲያስፓራወን ገንዘብ አታሎ ለመውሰድ! ” ትላለች። እንደ እውነቱ ከሆነ ይሕቺን ቃል ከድሮ የትግል ጓደኞቼ አፍ ስሰማ ከመጠን በላይ እሸማቀቃለሁ። በአንድ በኩል አዳራሽ እየሞላ የሚፈሰውን ዲያስፓራ (በውጭ የሚኖር ኢትዬጲያዊ) ማገናዘብ የማይችል በነዱት የሚነዳ ማህበረሰብ አድረገው እየቆጠሩት ነው። ርግጥ ነው አዲሳአባን ተራራ ላይ ሆኖ ሲያያት በምሽት ፀሀይ የወደቀችበት መሰለኛ ያለው የትላንት ታጋይ ( የዛሬው በአሜሪካ ኤምባሲ ንግግር ለማድረግ የሚጋበዝ ኮረኔል) ይህንን ቢል የሚያስከፋ አይደለም። ነገር ግን የውጭውን አለም ከሚያውቁት እነ አምባሳደር ግርማ ብሩ አፍ ሲወጣ ግን ያሸማቅቃል። በነገራችን ላይ በቅርብ ጊዜ የለውጥ ሀይሎቹን ለመደገፍ በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ተገኝቼ ነበር። እናም በስብሰባው ላይ የለውጥ ሀይሉን ለመደገፍ ከመጡት ኢትዬጲያውያን ሁለቱ የህግ ዶክትሬት ነበራቸው።… ሁኔታው ስለገረምኝ ወደ አዱገነት በሀሳብ ሄድኩኝ። መልስ ባጣ አምባሳደሬን መጠየቅ ፈለኩ። እንዲህ በማለት ብጠይቅስ፣
ጋሽ አምባሳደር ግርማ ብሩ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስንት የህግ ዶክትሬት ያላቸው መምህራን እንዳሉ እንድትነግረን ከማክበር ጋር እጠይቃለሁ!!
2•3 የለውጥ ተውሳኮችን ማንገዋለል
ጥቂቶቹ የለውጥ ሀይሎች ያስመዘገቡት ሁለተኛ ውጤት ትግሉን ወደ ፊት ማራመድ የተሳናቸውን የበረሀ አመራሮች በአጭር ጊዜ ማንገዋለል መቻላቸው ነው። ሞላ አስክዶም እንደነገረን ላለፋት አስራ ምናምን አመታት በወር ሀያ ምናምን ሺህ ብር እየተከፈለው፣ የፈለገውን ምግብ እየበላ፣ ከአንደኛው አልጋ ወደ ሌላኛው እየተዘዋወረ ( ስንት ጊዜ ከአልጋ እንደወደቀ የህማማት እለት እንደምንሰማ ተስፋ አድርጌ!) የኖረ ሰው ነው። በሌላ በኩል በእሱ ስር ባሉት ሰፊ ጦር ምክንያት በሌለው አቅሙ የወታደራዊነት (Militarism) አመለካከት እንዲያዳብር አድርጐታል። በመሆኑም ትግሉን ፈቀቅ ማድረግ ተስኖት በቁጥር ተኮፍሶ የመኖር ሂደቱትን ገፍቶበታል። የዘር ምንጩም ሆነ አስተዳደጉ ከህውሀት ነውና ለእሱ የትምህርት፣ችሎታና ብቃት ጉዳይ ከግምት የሚገባ አይደለም። ሁሉም ዘሮች እኩል ናቸው፣ ሌሎች የበለጠ እኩል ናቸው እንዲሉ!…እንግዲህ ይህ የጓድ ሞላ አይብን( cheese) ጠብቆ የመኖር ህልውና በለውጥ ሀይሎች ተሰናከለ። የእሱን አባባል እንደ ወረደ ልውሰደውና ሀያ ምናምንቴ ሺህ ብር የነበረችው ደሞዝ ልትቀር ሆነ! …በየጊዜው የምትታረደው ጥቦት ልትቀር ነው!…ከአልጋ አልጋ እየተገላበጡ መውደቅ ልትቀር ነው! …ታዲያ ምን ይዋጠው!…ለማንኛውም “Who moved Molla’s cheese?” ብዬ ብሰናበት ምን ይለኛል??

‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እየደረሰብን ነው ያሉትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ‹‹የሽብር ተከሳሽ ስለሆንን ብቻ ህክምና ተከልክለናል፤ በማንነታችን ጥቃት እየተፈጸመብን ነው›› ሲሉ ችሎት ፊት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይ ያለውን በማስጠራት ‹‹ማስታወሻ ያዝና አጣራ›› በማለት አልፎታል፡፡
በሌላ መዝገብ የሽብር ተከሳሽ የሆነው በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ በፍቃዱ አበበ በበኩሉ ቀሪ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ለህዳር 16/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

Tuesday, September 15, 2015

“ሞላ ለጥቂት አመለጠን” የትህዴን ጊዜያዊ ሊቀመንበር ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ዛሬ ለኢሳት ይናገራሉ።

”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ”
”ይዞ የወጣው ታጋይ ቁጥሩ ተጋኗል። ያም ቢሆን ለስራ ተብለው(የኪነት ቡድኑ ለበዓል) የተታለለ ነው። በተቻለን መጠን አብዛኛውን መልሰናል። የተዋጋው ከእኛው ጋር ነው። ከሻዕቢያ ጦር ጋር የሚባለው ፈጠራ ነው።”
“ሞላ ለጥቂት አመለጠን”

ሰሜን ጎንደር ዞን የሚኖሩ አስተዳዳሪዎችና የህዝብ ተወካዮች መሬትን በተመለከተ ስብሰባ ማካሄዳቸው ታወቀ።

በሰሜን ጎንደር ዞን ወረዳዎች መተማ ሳንጃና ጭልጋ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የሚሊሻ ኮማንደሮችና ከ40 በላይ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች በተገኙበት ነሓሴ 24 / 2007 ዓ/ም ስብሰባ ማካሄዳቸውን የገለፀው ሪፖርቱ የስብሰባው ዋና አጀንዳም ከኢህኣዴግ የምናገኘው ለውጥ የለም፤ መሬታችን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን? መሬታችን አሳልፈን አንሰጥም? የሚሉና ሌሎችን እንደነበሩ ታውቋል።
በስብሰባው ከተሳተፉ የስርዓቱ ወገኖች ከሆኑ ስሞችን ለመጥቀስ ያህል የሳንጃ ወረዳ ኮማንደር እንዳርጋቸው አለሙና ሌሎችን የሚገኙባቸው እንደተሳተፉ ሲገልፅ በዚህ ሁኔታ የሰጉ አንዳአንድ የስርኣቱ ካድሬዎች ደግሞ “በዚህ ስብሰባ ፀረ-መንግስት ተቃውሞ የሚያነሱ ያሉ የአርበኞች ተላላኪዎች ሰርጎ ስለ ገቡ ነው” ሲሉ እንደተሰሙና በዛን ቀን ደግሞ በመቐለ ከተማ የኢህአዴግ ጉባኤ እየተካሄደ እንደነበር የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስታውቋል።

ፕሮፌሰር ቴድሮስ ኪሮስ ኢሕአዴግን ይጠይቃሉ – የሚሊዮኖች ድምጽ


ፕሮፌሰር ቴድሮስ በሃርቨርድ የፖለቲካ ፍልስፍና ምሁር ናቸው። በርካታ መጽሐፍትን ጽፈዋል። በተለይም አሁን በኢትዮጵያ የተዘረጋው የጎሳ ፌዴራሊዝም ለአገሪቷ ትልቅ ችግር እንደሚፈጠር ብዙ ጊዜ የተከራከሩ ምሁር ናቸው።
በኢትዮጵያ አለ ያሉትን የልማት እንቅስቃሴዎችን ፕሮፌሰር ያደንቃሉ። ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጵያዉያን የዚህ የልማይት እንቅስቃሴው አካል መሆን እንዳለባቸው የሚያሳስቡት ፕሮፌሰር ቴድሮስ ኪሮስ፣ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና እርቅ፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ፣ በአሳታፊነት ዙሪያ መሰረታዊ ለዉጥ ማድረግ እንዳለበት ለማሳየት ጥያቄዎች ለአገዛዙ ያቀርባሉ።
ገዢው ፓርቲ የሚቃወሙትን ሽብርተኞች እያለ በመፈረጅ በኢትዮጵያዉያን መካከል የበለጠ መካረር እያመጣ እንደሆነ ይታወቃል። በርካት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ሃብታሙ አያሌው ያሉ ሽብርተኞች ተብለው በግፍና በጭካኔ በወህኒ እየማቀቁ ነው።
ፕሮፌሰር ቴድሮስ ግን የተቃዋሚ መሪዎች ን ለአገራቸው ለመሞት የተዘጋጁ፣ አገር ወዳዶች እንደሆኑ በመግለጽ፣ ኢሕአዴግ ስር ነቀል በሆነ መንገድ ዴሞክራቲክ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ፣ ተቃዋሚዎችን ማነጋገር እንደሚገባው ለማሳየት ሞክረዋል።
ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ኪሮስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለኢሕአዴግ ያቀርባሉ፡
I have a serious of questions, however, which I would like to address to the leaders. They are the following.
1. Note that the opposition is also composed of patriotic Ethiopians who love their country are ready to die for it. How is your regime going to engage the opposition in a peaceful and radically democratic style and invite to return home and shape the bright future of Ethiopia?
2. Ethiopian investors who want to participate in the developmental project are being rejected left and right, unless they are card holding party members. When and how is this corrupt practice going to be corrected?
3. What is preventing the party from inviting its highly educated Ethiopians in the diaspora to return home and work peacefully and productively according to the expertise, which they can bring to their country, instead of aging and leaving unfulfilled lives in foreign lands? When is this going to be changed, since this is time sensitive and would have to be acted on before these national treasures and professionals die with broken hearts?
4. How are you going to equalize the lives of those Ethiopians who work, when they are employed, from dusk to dawn, for meager wages, and still block those who manage to save and build homes for their families by erecting bureaucratic walls which they cannot penetrate, and when they fail, they leave their beloved Ethiopia and die in foreign lands?

ሰበር ዘና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ ወንጀለኛዉ ቡድን በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኤርትራዉያንን ሊሰበስብ ነዉ።


ይህዉ የኢትዮጵያና የኢትያዊያን ጠላት ወያኔ በተለይም ከፍተኛ የሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎችና አባላት አሉበት በሚባሉ የአለም ሐገራት የሚገኙ ተቃዋሚ ኤርትራዊያንን ኢላማ ያደረገ ሚስጢራዊ ስብሰባ ለማድረግ መወሰኑን እንዲሁም ከብሐራዊ መረጃ ለየሐገራቱ የኢትዮጵያ ኢንባስሲ ሰራተኞች ትእዛዝ መተላለፉን የደረሰን መረጃ አመለከተ።
17/09/2015 በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረዉ ይህዉ ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ በኖርዌይና ስዊድን እንደሚቀጥል ታዉቋል። በመሆኑም ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለነዚሁ ኤርትራዊያን ልብ ማማለያ ይሆን ዘንድ ወደ ሐገር ቤት የሚገቡበት ፓስፖርት (travel document) ፣ የገንዘብ ድጎማ፣ የመሬት አቅርቦት እና የንግድ ፈቃድ (work permit) ፣ የአስመጪ እና ላኪ ፍቃድና እገዛ (import and export license) የሚሰጥ ሲሆን በተለየ መልኩ ዋና ትኩረቱ በኤርትራ መንግስት ላይ አለም አቀፍ ተቃዉሞ ለማስነሳት መሆኑ ታዉቋል
ወያኔ ኤርትራዊያኑ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ የሚሰጡ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች የኤርትራን መንግስት እድሜ በማራዘም እያገዙት ነዉ በሚል አጀንዳ ተቃዋሚያኑ ከሀገራችን ይዉጡ በማለት ሰልፍ እንዲወጡ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ የሚኖረዉን የኤርትራ ተቃዋሚ ሐይል እንዲያግዙ ለማድረግ በወያኔ በኩል ተቃዥቷል ይላል መረጃችን።
ወያኔ ተቃዋሚዎቹ እጅግ ሰልጥነዉና በሚገባ ታጥቀዉ ሊፋለሙት በጀመሩበት በዚህ በመጨረሻዉ የመዉደቂያዉ ሰአቱ አለኝ የሚለዉን ተንኮሉና ሴራዉን እያደረገ ቢሆንም ተቃዋሚ ሐይሎቹ እጅግ ከሚገመተዉ በላይ ወደፊት እየገሰገሱበት ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈናቀልበትና በረሐብ አለንጋ በሚገረፈበት በዚህ በዘመነ ወያኔ ወቅት ይህዉ ቡድን የሐገራችንን አንጡራ ሐብት ለፖለቲካ ጥቅሙ እያባከነዉና እያፈሰሰዉ ይገኛል ሆኖም አንዳንድ ያነጋገርናቸዉ አርትራዉያን በስፍራዉ በመገኘት ተቃዉሞዋቸዉን እንደሚያሰሙ ለማወቅ ተችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ይዉደም!!!

ሄሊኮፕተራችንስ መቸ ነው የምትመለሰው ?? (አሌክስ አብርሃም)


ባለፈው ግምቱ ከ30 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ የኢትዮጲያን የጦር ሄሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ ገቡ የተባሉት ‹‹ከሃዲው››አብራሪና ረዳት አብራሪዎች …. ከብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት እና ከፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብር ሀይል ‹‹የተሰጣቸውን ተልእኮ›› ሲጨርሱ በሱዳን በኩል ወደአገራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ አለኝ፡) አብራሪዎቹ ባይችሉ እንኳን ሄሊኮፕተሯን በፒካፕ መኪና በሱዳን በኩል ይላኩልን፡)
እንበልና ሄሊኮፕተራችን ስትመለስ ኢቢሲ ምናይነት ዜና ሊሰራ እንደሚችል እንጠርጥር እንዴ …
‹‹ የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት እና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብር ሀይል ስለላውን በምድር እንዲሁም በአየር ለማቀላጠፍ ሆነ ብሎ ወደኤርትራ የላካት ሄሊኮፕተር ተልእኮዋን በመፈፀም በሱዳን በኩል ወደአገሯ በሰላም ገብታለች …በአሁኑ ሰዓት ኤርትራ የቀሩት …ሲሄዱ ‹‹ከሃዲ›› የሚል የሽፋን ስም የተሰጣቸው ዋና አብራሪውና አንዳንድ ረዳት ፓይለቶች ብቻ ናቸው››፡)
የቀልዱ ቀልድ ነው ….ወደቁም ነገሩ ስንመለስ ጥያቄም አለኝ … ይሄ ለኢትዮጲያ ሲሰልል ነበር የተባለው ደሚህት የተባለው ድርጅት በኢትዮጲያ አንዳንድ አካባቢዎች ጥቃት እያደረሰ ኢትዮጲያዊያ ውስጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ ሲባል ከዚህ በፊት ሰምተናል …ታዲያ በራሳችን ‹‹ሰላዮች›› ለደረሰብን ጉዳት ካሳ የሚከፍለን ማነው ….ከምር ፖለቲካ እንዲህ እቃቃ መሆኗ ይገርማል!!
ለማንኛውም መንግስታችን አቶ ሞላ እንደገና ‹‹የኢትዮጲያ ተልእኮውን›› ጨርሶ ወደኤርትራ እንዳይመለስ ጥንቃቄ እንዲያደርግልን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንጠይቃለን !! (የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ገፀ ባህሪ ስእላይ በርሄን ማስታወሱም ደግ ነው !!) እንግዲህ ጀግኖቻችንን እንቀበላቸው ዘንድ መስቀል አደባባይ ሰልፍ ብንጠራና ተሰልፈው ቢያልፉ በዛውም ከ‹‹ስምንት መቶ ጀግኖቻችን›› ምንም አለመጉደሉን በህዝብ አይን ቆጥረን ብናረጋግጥ ‹‹ህዝብን አስፈቅዶ ለሚወሰደው እርምጃ ›› ፈቃድ ለመስጠት ያመቸናል፡)

Monday, September 14, 2015

ብስሉ ከጥሬው ገና ከጅምሩ የተለየበት እውነትም አገር አድን!


የአፋር ሕዝብ ንቅናቄ፣ ት ህዴ ን፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት ፯ የጋራ አገር አድን ንቅናቄ መመስረታቸውን በተመለከተ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በኢሳት ራዲዮ ተጠይቀው በድርጅቶቹ አባላት መሃል ማፈግፈግ ቢከሰት እንኳ አገር አድን ሰራዊቱ እንደሚታደገው አብራርተዋል። ለዚህም ካስረኛው የቃለመጠይቁ ደቂቃ በኋላ እንደተረዳነው ከሁሉም ድርጅቶች ተውጣጥቶ ከተቋቋመው አገር አድን ሰራዊት ተመልሶ ወደ እናት ድርጅቱ ልመለስ ማለት አይቻልም።
አራቱ ድርጅቶች በጋራ ንቅናቄው ሰራዊት ይዋጣሉ እንጂ ለምሳሌ ት ህዴ ን ብዙ ሰራዊት ያለኝ እኔ ነኝ እና በኔ ስም ተጠሩ ቢል የሚሰማው የለም።ሞላ አስገዶም ትግሉን የከዳውም ጥዴንን እንደንብረቱ ቆጥሮ መሪ ካላደረጋችሁኝ ብሎ ከሌሎች ጋር ተጣልቶ ከሆነም ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም የነፕሮፌሰር ብርሃኑ ምሁራዊ አካሄድ የህወሃትን ካባ ለብሰው ኤርትራ ለመሸጉት ቅጥረኞች አልተመቻቸውም። የተደላደለ የ አሜሪካ ኑሯቸውን ትተው እነ ኤፍሬም በረሃ ይወርዳሉ ብለው እነ ወዲ አስገዶም አልጠበቁትም። ህዝቡ ለውጥ እንደሚፈልግ ተረዱት።ነገም ዛሬም የሚወተውቱት ስለ እውነተኛ ዲሞክራሲ ነውና ሆዳሞች ጨነቃቸው።ስለዚህ ሳይነቃባቸው ፈረጠጡ።
በመጨረሻም የ አርበኖች ግንቦት ሰባት አመራሮች ኤርትራ ከገቡ የተሰበሩ ሁለቱን የህወሃት ሴራዎች እንይና ለዛሬ ይብቃን።ዙሩ ከሯል። ሃምሌ 10 እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ገብተው ሃምሌ 20 የኤርትሪያውንን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብል ለበርካታ ዓመታት የኖረ እና በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረ የመላዋ ኤርትሪያ የፀጥታ ኃላፊ በቁጥጥር ስራ ውሏል። ያኔ ከአሜሪካ የሄዱት አመራሮች ያለደህንነት ስጋት እንዲንቀሳቀሱ የወያኔ ቀኝ እጅ የነበረው የጸጥታ ሃላፊ መያዝ ፍንጭ ሰጥቶ ነበረ።
አሁን ደሞ የተቃዋሚ ጦር ሰራዊት የት ህ ዴን መሪ በመሆን ለህወሃት ሲሰራ የነበረው ሞላ አስገዶም ተጋልጧል።ይህ እንግዲህ ብስሉ ከጥሬው ገና ከጅምሩ የተለየበት፤ ምርቱ ከ እንክርዳዱ በመጀመሪያው የውህደት ወንፊት የተጣራበት ወቅት ነው።
ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም!!!( አብርሃም ታየኝ )

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ, TPDM መግለጫ ሰጠ፥


ድርጅታችን ትህዴን በየካቲት 1993 ዓ/ም ብረት አንስቶ ትግል ሲጀምር አላማው ግልፅና የማያሻማ ነበር።
እሱም በሃገራችን የገነነው አፋኝ ስርዓት ህዝባችንን ከፋፍሎ ሰብኣዊ መብቱን ረግጦ ለመግዛት በሚያመቸው መንገድ ይጓዝ ስለነበር ድርጅታችን ትህዴን ችግሩን ለመፍታት ኩሁሉም በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ድርጅቶች በመተባበር ህዝባዊ ስርአት ለመትከልና አንድነቷ የተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት የሚል አላማ አንግቦ የህወሓት-ኢህ አዴግ ስርዓትን በመቃወም ነፍጥ አንስቶ በትጥቅ ትግል መፋለም ከጀመረ 14 ዓመታት ሆኖታል።
በነዚህ 14 ዓምታት የትግል ጉዞ ድርጅታችን ትህዴን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መስክ ከፍተኛ ድሎችን እያስመዝገበ መጥቷል። ትግል ሲባል ቀላል እንዳልሆነ ካሳለፍነው የትግል ታሪክ እየተማርን መጥተናል።
ድርጅታችን ትህዴንም በዚህ አጭር እድሜው ክፍተኛ ድሎችን ሲጎናጸፍ የተለያዩ መስናክሎችን በመሻገር ነው።
በቅርብ ጊዜ የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለስቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛኛው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈኛ ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል።
የተከበርከው ሰፊው ህዝባችን እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው ያደሩ እንጂ ትህዴንን የሚወክሉ አይደሉም። የእነዚህ ስዎች ከትግሉ መክዳት ደግሞ ድርጅታችን ትህዴን የቆሸሸውን በመጥረግ ጥንካሬውን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያጎለብተዋል እንጂ ትግሉን ለሰክንድም ቢሆን አያደናቅፈውም።
ትህዴን ይዞት የተነሳ ዓላማ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ስለሆነ ሊቅበለውም ውይም ላይቅበለውም የሚችለው ህዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። ትግላችን ደግሞ በሃገራችን ያለውን ፀረህዝብ ስርዓት ከስልጣኑ ተወግዶ ህዝባችን የጀመረውን የትጥቅ ትግል ግቡን ሳይመታ ለአፍታም ቢሆን አይቆምም።
ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ስፊ ህዝብ ይህንን ተረድተህ እንደበፊቱ ሁሉ በልጆችህ እይተካሄደ ባለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፍ መላው የትህዴን ታጋይ ጥሪውን ያቀርባል።
ፍኖተ ትህዴን ፍኖተ ድል ነው!
ድል ለጭቁኖች!!
"የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ, TPDM የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለስቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛኛው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈኛ ስላጡ,,,,,ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል። ሲል ድርጅታዊ መግለጫ ሰጠ፥ 
ዓየ የሞላ ነገር ዓሁን ባለቀ ሰዓት እንዲህ ይሁን በጣም ያሳዝናል፥"

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ (ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ)


በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።
የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።
ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።
ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።
ይህአዲስ የፖለቲካ አዝማሚያ ምቾት የማይሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ ድርጅት ከሰሞኑ ሞላ አስገዶምን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ኃይሎች ተሰባስበው እንዳይታገሉና ስርዓቱን እንዳይፈታተኑ የማያደርገው ጥረት የለም። በዚህ በህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀላሉ መጠቀሚያ የሚሆኑት በጋራ የሚደረግ ትግል በግለሰብ ደረጃ ያሳጣናል ብለው የሚፈሩት “የግል ጎጆና” ጥቅም የሚያስጨነቃቸው ደካማ የፖለቲካ መሪዎች ነን ባዮችን ነው። ባንጻሩ በየድርጅቶቹ ውስጥ በሚገኙት ብዙሀኑ ሩቅ አሳቢ መሪዎች ጥረትና በተለይም ደግሞ ይህን ትግል ለአላማ እንጂ ለሌላ ምንም አይነት የግል ጥቅም ያልተቀላቀሉና በትግሉ ሂደትም ትልቁን ሚና በሚጫወቱት ብዙሀን ታጋዮች አልበገር ባይነት እንዲህ አይነት ደካማ መሪዎች ተከታይ በማጣት ሲዳከሙና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በድርጅታቸው ውስጥ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻላቸው በቀላሉ እየተፍሸለሸሉ ከመራገፍ በስተቀር በድርጅቶቹ ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ ይከስማሉ።
በህወሓት/ኢህአዴግ “የስለላ ድርጅት አቀናባሪነት” በሞላ አስገዶም መሪነት ከሰሞኑ የተሞከረው የማፍረስ ንቅናቄ ከሽፎ ወደ ተስፋ መቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ የተቀየረው የሰሞኑ ሙከራም የዚህ አጠቃላይ ሂደት አካል ነው። በዚህ የከሸፈ ሙከራ ውስጥ እጅግ የሚገርመውና የትህዴንን ብዙሀን አመራሮች ብስለት፤ የድርጅቱን መዋቅራዊና ድርጅታዊ ጥንካሬ፤ እንዲሁም ብዙሀኑ ታጋይ ለጋራ ትግል ያለውን ቆራጥ አቋም ያስመሰከረው፤ ይህንን የማፍረስ ሙከራ የመራውና ሳያሳካለት በመጨረሻም በጣም ጥቂት ተከታዮቹን ብቻ ይዞ የከዳው ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት የመክዳት ሂደት ባጭር ጊዜ በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጥረውን አስጨናቂ ስሜት የምንረዳው ቢሆንም ከዚያ በላይ ልንረዳው የሚገባው ግን በእንዲህ አይነት ከፍተኛ ያመራር ቦታ የነበረ ሰው ሙከራ አለመሳካት በእርግጥም የሀገራችን ፖለቲካ እየበሰለ፤ ከግለሰብ አመራሮች ተጽእኖ እየተላቀቀ፤ አዲስ የተባብሮ መታገል አቅጣጫን እያበሰረ እየሄደ መሆኑንና በትናንሽ ሰዎች መግተርተር ይህ ሂደት የማይቀለበስ መሆኑን የሚያመለክት የረጅም ጊዜ ግኝት መሆኑን ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ ለትህዴን ብዙሀን አመራርና ለሰፊው ታጋይ በመርህ ላይ ለተመሰረተው አቋማቸውና መርሃቸውን ለማስጠበቅ ለሚያደርጉት ቆራጥ ትግል ያለውን ጓዳዊ አክብሮት ይገልጻል። በመግለጫቸው ላይ በግልጽ ያስቀመጡት መርሆአቸው የኛም መርሆ መሆኑን ስንገልጽላቸው በታላቅ ኩራት ነው። ድርጅታቸውን እያጸዱ የተመሰረቱበትን መርሆ ጠብቀው ለመጓዝ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ወደፊትም በሚያደርጉት ትግል ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንንና ጓዳዊ ድጋፋችን ምንጊዜም እንደማይለያቸው በዚህ አጋጣሚ ደግመን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም ይህ ትግል ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሳያደርግ የማይቆምና እንዲያውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለኢትዮጵያ ህዝብም በየጊዜው በሚፈጠሩ እንቅፋቶች ላይ ሳያተኩር ትግሉን በሙሉ ልብ እንዲደግፍ ያደረጉት ጥሪ የኛም ጥሪ ነው።
አንድነት ኃይል ነው!!!
አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

Sunday, September 13, 2015

የአባይ ወልዱ ሚስት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ስልጣን ለመልቀቅ አሻፈረኝ አሉ


የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ስለተገመገሙ ከሃላፊነታቸው መውረድ አለባቸው ሲሉ የህወሓት ጉባኤተኞች የወሰኑትን ውሳኔ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተተገበረ ተገለፀ።
እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአባይ ወልዱ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም ላለፉት አመታት የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆነው በሰሩበት ጊዜ በመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ለውጦች ባለማምጣታቸው የተነሳና ጊዜው ያለፈው አስራር በየጽህፈት ቤቱ በነበረበት መሰረት እንዲቀጥል በማድረጋቸው እንደተነቀፉና ሌሎች በፍትህ ቢሮ በተደረገ ግምገማ በከባድ ሙስና የሀገርና የህዝብ ሃብት በማጠፋፋት ስለተገመገሙ በህወሓት ጉባኤተኞች ከሃላፊነታቸው እንዲወርዱ ወስኖ እያለ ባለሉበት የስልጣን እርከን በመቀጠል ላይ እንዳሉ ታወቀ።
አግባብነት የሌለውን የትግራይ ክልል የአስተዳደር አሰራር የታዘቡት አገር ወዳድ የመንግስት መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ምሁራን ወ/ሮ ትርፉ ቀድሞም የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆኖው የተመደቡበት ምክንያት በአቅም በልጠው ሳይሆን የአባይ ወልዱ ሚስት በመሆናቸው ነው። አሁንም በፈፀሙት ጥፋት ከሃላፊነታቸው ተወግደው ጉዳያቸው በህግ ፊት መጣራት እየተገባው በሃላፊነታቸው መቀጠላቸው የስርአቱን አመጣጥ የሚያመለክት እንደሆነ እየገለፁ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል