የህውሃት ሰዎች ጸጉረ ልውጥ ሰዎችን ለመከታተል የሚያመች አዲስ መረብ መዘርጋታቸውተደረሰበት ።
ዜና መረጃ ( ሄኖክ የሺጥላ )

በጎንደር ከተማ የሚገኙት ትላልቅ ሆቴሎች ( የሃ ፣ ጎሃ ፣ እና ተራራ ሆቴል ) ፣ በደንበኞች መቀበያ እና በሆቴል መስተንግዶ ክፍሎች ውስጥ የህውሃት ሰዎች ጸጉረ ልውጥ ሰዎችን ለመከታተል የሚያመች አዲስ መረብ መዘርጋታቸውተደረሰበት ። ከጎንደር በደረሰን መረጃ መሰረት ፣ የነዚህ ሆቴሎች የአልጋ ክፍል ( አከራይ ሰዎች ) ፣ ምንኛውም አዲስ ተጠቃሚ ሲመጣ ሙሉ ሱሙን ፣ ከተቻለ መልኩን በድብቅ ፎቶ በማንሳት እና የመኖሪያ አድራሻውን በፍጥነት ወደ ህውሃት የመረጃ መረብ እንዲልኩ የሚያስገድድ ነው ። ይህ የሆነው አርበኞች ግንቦት ሰባት በጎንደር ከተማ ይንቀሳቀሳል የሚለው ዜና ከተሰማ ወዲህ ሲሆን ፣ በይበልጥም የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ግንባር መግባት ተከትሎ የመጣ የህውሃት ትእዛዝ ነው ።
ከዚያው ከጎንደር ሳንወጣ ፣ የመከላከያ ሰራዊትና የጎንደር ሚሊሻ ወታደሮች ከዋና ከተማዋ ጎንደር ፣ ወደ ትክል ድንጋይ፣ አብርሃ ጅራ ፣ ሁመራ ፣ መተማ ፣ ወልቃይት ፣ አብደራፊ፣ ሳንጃ እና ዳንሻ የሚሄዱ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እያካሄዱ ሲሆን ፣ የይለፍ ወረቀት ካላመጡ ለስራም ቢሆን ወደተባለው ቦታ መሄድ እንደማይችሉ አንዳንድ የዚህ መጉላላት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሹክ ብለውናል ።
ህውሃት መርበትበት ጀምሯል ፣ ትግሉ ይቀጥላል ። መሬት ሰንጥቀንም ቢሆን ትግሉን እንቀላቀላለን የሚሉ ሰዎች ተበራክተዋል ።
<< በሊማ ሊሞ በኩል ሂዱ ፣ ነጥሎ መተኮስ የሰለቸን ነገር ነው ፣ ጀርባችንን በእሳት ሰንሰለት ገርፈን ነው እዚህ የደረስነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጥን ፣ እሳት የዋጥን ፣ ምናምን ፣ ምናምን >> እያለ ሲፎክር የነበረው ህውሃት መራሹ መንግስት ፣ ሀገር በወታደር አጥሮ ዘላለም ለመንገስ ያሰበ ይመስላል ። ቢያንስ ከራሱ የትግል ታሪክ መማር የማይችል ፣ ድውይ ስርዓት ለመሆኑ ጥሩ ማሳያ ነው ። እኔ በግሌ (ከልምድ): እንኳን ህዝብን ያህል ግዙፍ ነገር ይቅርና ፣ የ 10 ወር ህጻን ልጅን ፣ አጥር አጥረህ ለብዙ ጊዜ በአጥሩ ውስጥ ብቻ እንዲቆይ ማድረግ አትችልም ። ወይ ያፈርሰዋል ፣ ወይ ከአጥሩ ጋ መጋጨት ይጀምራል ። በኔው በራሴው ወንድ ልጅ ያየሁት ነው ! እምቢ ማለት ይችልበታል ። ስወደው !

ድል ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ።
No comments:
Post a Comment