Sunday, July 19, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት


11705147_1132823153411859_253212669174393629_n11249699_1132823486745159_3527348390337279840_n11229822_1132823303411844_3085414076884244111_n
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ዕለት ሀምሌ 12 2007 ዓ.ም ኤርትራ ገብቷል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ኤርትራ በገባ በጥቂት ሰዓታት ልዩት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፖለቲካ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ወደሚገኝበት ቦታ በማምራት ከህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አርበኛ ታጋዮች ጋር ምሳ በልቷል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አርበኛ ታጋዮች ባስተላለፈው መልዕክት 
“ከሁሉም ነገር ዓላማ ያስተሳሰረው ስለሚልቅ፤ ለእኔ ለአገሩ ህይወቱን መሰዋዕት ለማድረግ ከተዘጋጀ ሰው የሚበልጥ ምንም ነገር በምድር ላይ ባለመኖሩ ወደ እናንተ መጥቻለሁ፡፡ የመጣሁትም እናንተን ለማስተማር ሳይሆን ከእናንተ ለመማር ነው… ለነፃነታችን አብረን እንሞታለን…” በማለት ተናግሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 አመራርና የምክር ቤት አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ እና ሌሎች በርካታ የድርጅቱ አባላት ከዶ/ር ብርሃኑ ቀደም ብለው ኤርትራ ገብተው ውለው አድረዋል፡፡ ሌሎች አመራሮችና አባላት በቅርቡ እንደሚገቡም ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment