የወያኔ ቅጥር ሰራዊት የሽምቅ ሐይል ስምሪት ክፍል በሶስት አቅጣጫዎች በተለይም በትግራይ ጠረፍ በአብረሐ ጅራ በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ በባሌ በኩል ከባድ ዉግያ እንደገጠመዉ የሚጠቁሙ መረጃዎች ትናንት ማምሻዉን በስቸኳይ መልእክት ለበላይ አካላት የተላለፉ ሲሆን፡ እንዲሁም በአርማጭሆ ህዝብ እና በሰራዊቱ መካከል እየተጧጧፈ የሚገኘዉ አለመግባባት ከአሳሳቢነቱ በመዝለል በየትኛዉም አቅጣጫ በሽምቅ ዉጊያ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ወታደሮቻችን ወደ ኋላቸዉ በመሸሽ ላይ ባሉበት ሁኔታ የራሳችን ሰላማዊ የተባለዉ ህዝብ እርምጃ እየወሰደባቸዉ ግራና ቀኝ ፊትና ኋላቸዉን ማመን ተስኗቸዉ እየተጎዱ ይገኛሉ በማለት ሲያሳስብ አያይዞ በሽምቅ ዉጊያዉ እየደረሰብን ያለዉን ድንገተኛ ጥቃት መልሰን ለመከላከል እንዳንችል የወልቃይትና የአርማጭሆ ህዝብ ከለላና ድበቃ በማድረጉ ምንም ዉጤት ልናመጣ አልቻልንም ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ አስጊ እንደሚሆን በመጠቆም በተደጋጋሚ ለበላይ ወታደራዊ አካላት ያደረገዉ ጥሪ መልስ አልባ መሆኑን አክሎ ገልጿል።
ይህንን መረጃ ከስፍራዉ በመሆን የላኩልን የጸረ ሽብር አባላቱ አካል ” የአርበኞች ግንቦት ሰባት የጥቃት አካሄድ ከሽምቅ ዉጊያ ወደ ማጥቃት የመሸጋገር ሁኔታ ይታይበታል የሚል አዲስ ወታደራዊ መረጃ እንደደረሳቸዉና በርከት ያለ የልዩ ሐይልና ፌደራል ፖሊስ አባላት ጸረ ሽምቁን ለማገዝ ቢቀላቀሉም ዉጤት አልባ እንደሚሆን ከወዲሁ አሳዉቀዋል።

No comments:
Post a Comment