


ሀላፊነት ከሚሰማው ዜጋ በውስጥ መልክት የተላከ ኡኡታ!
“ዘንድሮ በኢትዮዽያ ያለው ርሀብናድርቅ ከ1977ቱ አይተናነስም ሲሉ ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል መረጃ እየወጣ ነው።ሆኖም ለተጎጂወች እርዳታ ካለማቀፉ ማህበረሰብ እንዳይደርስ ወያኔ ባንድ ለናቱ ሚድያው የሚነዛው የውሸት የባለሁለት አሀዝ ዕድገት ፕሮፐጋንዳን የሚያጋልጥና የሀገር ገጽታ ግንባታን ያበላሻል በሚል መረጃው አይደለም ቀይ መስቀልና መሰል ዓለማቀፍ ድርጅቶች የኢትዮዽያ ህዝብ እንዳይሰማው አፍኖታል እባካችሁን ህዝብ በርሀብ እያለቀነው ጩኸታችንን አድርሱልን።”
ከዚህ መልክት ጋር ተያይዞ በደቡብ እና በምስራቅ ተግራይ ፣በወሎ ሙሉ በመሉ ፣በሰሜን ሽዋ ፣በአፋር፣ በሶማሌ እና በድሬ ድዋ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ ተከስቷል። በወሎ እና በትግራይ ሰብል ደርቋል።በአፋር እና በሶማሌ ከብቶች አየሞቱ ነው የመንግስት ባለስልጣናትም አይተው እንዳለዩ የሚያልፉ ሲሆን ሰውም መራብ ጀምሯል። በተመሳሳይ በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በተለይም ህጻናት በርሀብ እያለቁ ስለመሆኑ ቀጣዩ የፎቶ ማስረጃ ጠቋሚ ነው።በየአካባቢው ያለውን ሁኔታ በመቃኘት መረጃ ህይወት ነውና ያካፍሉ።
No comments:
Post a Comment