
የናዚ ወያኔ ስልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ወጣቶችንናሙህራንን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ አሳዷል፣አዋክቧል፣ዘግናኝ ሰቆቃና ግድያ ፈጽሟል።አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበታል።ወያኔወች ከስልጣን ለመውረድ የማይፈልጉት አንዱ ትልቁ ምክንያትም ይህ በየቦታው በፍጹም አረመኔያዊነት በገፍ የገደሏቸው እና በጅምላ የቀበሯቸው የንጹሀን ደም ጩኸት እያሸበረቸው እና የፈጸሙት ዘግናኝ ወንጀል ከተጠያቂነት የማያስመልጣቸው ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ(timebomb) መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁም ጭምር ነው።
በአማራ ሰሜን ሸዋ ብቻ በአገዛዙ ከ25ሺህ በላይ ወጣቶች ከየቦታው እየተለቀሙ መገደላቸውን፣እንዲሁም ባለፈው አመት አዲስ አበባ ጃን ሜዳ በሚገኘው የወያኔ የመከላከያ ቢሮ አጥር ግቢ ላይ መንገድን ለማስፋት በተደረገ ቁፋሮ ከምርጫ 97ጋር ተያይዞ የተገደሉ በርካታ የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ መቃብር መገኘቱ ይታወሳል።
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት በኦሮሚያ ባሌ ዞን ደምበል ከተማ አካባቢ በቅርቡ የተገኘ ሲሆን ወያኔ በስመ ኦነግ በጭካኔ የረሸነቸው ወጣቶችን ከሌላ ቦታ አምጥቶ የቀበረው ሊሆን እንደሚችል ያካባቢው ነዋሪዎች ግምታቸውን ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment