Sunday, July 12, 2015

እግዚአብሔር 10ቱን ለሙሴ የተሰጡትን ትእዛዝ እንዳሻሽላቸው አዞኛል “” የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ


Daniel Harar's photo.
የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ ሰሞኑን በላቲን አሜርካ ባደረጉት የስራ ጉብኝት በኢኮዶር በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች አዲስ መልእክት አስተላልፈዋል:: ጳጳስ ፍራንሲስ ካስተላለፉት አዳዲሶቹ መልእክቶች ዋናዎቹ እግዚአብሔር 10ቱን ለሙሴ የተሰጡትን ትእዛዝ እንዳሻሽላቸው አዞኛል:: ከ10 ትእዛዛት ውጪ 2 ሌላ አዲስ የእግዚአብሔር ትእዛዛት በ10ቱ ትእዛዛት ውስጥ በተጨማሪ የሚካተቱ መሆኑን ጳጳስ ፍራንሲስ አስታውቀዋል:: ከሚጨመሩት እና ከሚሻሻሉት ከ10ቱ አዳዲስ ትእዛዞች ውስጥ የግዜ እና የሰአት ለውጥ ፣ ሶዶማውያን በፍቅር መኖር እንደሚችሉ እና ሶዶማውያን በማደጎ የሚያሳድጓቸውን ልጆች በየትኛውም ቦታ እንዲከበሩ በተጨማሪም ሰዶማውያን እራሳቸው በክርስትያኑ ማህበረሰብ እንዲከበሩ የሚደነግግ ህግ ያለበት ጭምር ሲሆን በተጨማሪም በ10ቱ ትእዛዝ ውስጥ የነበሩ ስለዝሙት የተጻፉ ህጎች ተሽረዋል:: እንዲሁም የዘመኑን ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂዎችን እንደ RFID maicrochips (666) ክርስቲያኖች መጠቀም እንዳለባቸው አዲሱ የእግዚያብሔር ህግ ያዛል:: ስለሆነም በአዲስ መልክ በሮማ ካቶሊክ በማስቀጠልም “የእግዚያብሔር ጸጋ ለሁሉም የአለም ህዝብ ልጆች ነው::” ይላሉ ጳጳስ ፍራንሲስ:: ይህ የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው 11ዱ የእግዚያብሔር ትእዛዝ በመባል ይታወቃሉ:: ጳጳስ ፍራንሲስ የእግዚያብሔርን ህግ የሆነውን 10ቱን ትእዛዝን መሻር እና መለወጥ አስመልክቶ ስለ መጨረሻው ዘመን ዋና ምልክት ሆኖ በነብዩ ዳንኤል የተጻፈው የትንቢት ቃል ተግባራዊ ይሆናል:: ለምሳሌ ጳጳስ ፍራንሲስ የአለም ሰአት ግዜ አቆጣጠር ስርአት እና የእግዚያብሔር ህግ ስርአትን እንደሚቀይሩ የተናገሩ ሲሆን ነብዩ ዳንኤልም በትንቢቱ እንዲህ ብሎት ጽፎታል “በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ። ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል። መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።” ዳን 7:25_27
“ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።” ማቴ 24:24_25
ሌላው የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ ከ10ቱ ትእዛዝ ውስጥ የሚገባው ሌላው አዲሱ ህግ የዘመኑን ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂዎችን ውጤቶች እንደ RFID maicrochips (666) ያሉትን ሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቀሙ የሚያዝ ህግ የደነገጉ ሲሆን የዚህ ህግ ትንቢት በራዕይ 13 ላይ የተጻፈው ትንቢት ቃል አሁን ይፈጸማል ማለት ነው:: “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር። በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል። እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል። በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል። የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው። ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።” ራዕ 13:11_18
ብዙዎቹ የእግዚያብሔር ሰዎች እንደሚመሰክሩት በራእይ 13 ላይ “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።” እንዲህ ተብሎ የተጻፈለት እራሱ የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ ነው ብለው ይመሰክራሉ::
ስለሆነም የእግዚያብሔር ቤተሰቦች ስለጌታ ፍቅር ብላችሁ እባካችሁ ንቁ! እባካችሁ ንቁ! እባካችሁ ንቁ! ታላቁ መከራ የእግዚያብሔር ቀን በፍጥነት እየመጣ ነው::
ጆሮ ያለው ይስማ !

No comments:

Post a Comment