ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ችሎት ቀርበው በቂሊንጦ ታስሮ ሚገኘው ማስተዋል ፈቃዱ ባለመቅረቡ የአቃቢ ህግ ይግባኝ ሳይታይ ቀርቶአል፡፡ ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬ እና ቤተለሄም አካለወርቅ ትናንት በዛቻ እና ማስፈራራት ክስ ቄራ ምድብ ችሎት ቀርበው በዋስ እንዲወጡ ቢታዘዝም ካሳንቺዝ ስድስተኛ ፖሊስ ግን ታሳሪዎቹን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ጠዋት በልደታ የይግባኝ ሰሚ ችሎት ነገ እንዲቀርቡ የተቀጠሩት እነወይንሸት ለፍርድ ቤቱ ስለእስራቸው ባስረዱበት ወቅት ዳኛዋ “እኔ ታስራችሁ ቅረቡ ብዬ አላዘዝኩም፡፡ በሌላ ክስ መታሰራችሁን ነው የማውቀው፡፡ በሌላ ክስ ዋስ ከተሰጣችሁ ነገ በራሳችሁ መቅረብ ትችላላችሁ፡፡” በማለት ነበር ያሰናበተቻቸው፡፡
No comments:
Post a Comment