ከርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትእዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን ያበሳጨ ነዉ ተብሎዋል።
በተያያዘ ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የወያኔ ንብረት የሆነዉን በጎንደርና በተለይም አዘዞ ላይ የሚገኘዉን ሱር ኮንስትራክሽን የደመሰሰና ያቃጤለ ሲሆን በቅርበት የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ በተዛማጅ ዜና አንድ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ እንዲገለጽ ያልተፈለገ ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ በወያኔ በኩል ከባድ እራስ ምታት ፈጥሯል። የእኚሁን ባለስልጣን ጉዳይ በተመለከተ የርበኞች ግንቦት 7 ምንም የሰጠዉ መግለጫ ባይኖርም በወያኔ በኩል ግን ያለዉ የደህንነት ክንፍ አጣርቻለዉ ብሎ መረጃዉን ማሳለፉን ለመረዳት ተችሏል።
No comments:
Post a Comment