የሜክሲኮው አደጋኛ የእጽ አዘዋዋሪ ከጥብቁ እስር ቤት እንዴት አመለጠ? በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱት
አደገኛው የእጽ ነጋዴ ጆአኪም ጉዝማን (ኤልቻፖ) ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት ከሜክሲኮ እስር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ማምለጡ አይዘነጋም፡፡
አደገኛው የእጽ ነጋዴ ጆአኪም ጉዝማን (ኤልቻፖ) ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት ከሜክሲኮ እስር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ማምለጡ አይዘነጋም፡፡
ይህ ሲናሎአ የተባለውን የእጽ ዝውውር ወንጀል መረብን የሚመራና በመላው አለም ግዙፍ መረብና የዘረጋ ወንጀለኛ በእስር ክፍሉ ሻወር ቤት አካባቢ በተከፈተ አነስተኛ ጉድጓድ በመጠቀም መሬት ለመሬት ተሸሎክሉኮ ማምለጡ እጅግ እያነጋገረ ነው የሚገኘው፡፡
በዚህ መሬት ለመሬት በተዘረጋ ዋሻ ውስጥ መብራት ተዘርግቶና የማምለጫ ሞተር ሳይክል ሳይቀር ተዘጋጅቶ ይጠብቀው የነበረው ሰው አሁን እየታደነ ሲሆን እርሱን ለጠቆመ 3.8 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ ለመስጠት ሁሉ ቃል ተገብቷል፡፡
ከአንድም ሁለቴ መሬት ሰርስሮ ከእስር ላመለጠውና የሀብት መጠኑ 1 ቢሊዮን ዶላር ለሚገመተው አደገኛ ወንጀለኛ አደን ይህቺ ጉርሻ ትበቃ ይሆን? መመለስ የሚያስቸግር ጥያቄ ቢሆንም የሜክሲኮ ባለስልጣናት በአደኑ ይቅናቸው እያልን ከማምለጡ በፊት ኤልቻፖ በእስር ቤት ውስጥ ምን ሲሰራ እንደነበር የሚያሳየውን ይህን ቪዲዮ እንጋብዛችኋለን፡፡
No comments:
Post a Comment