Tuesday, June 23, 2015

የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ * ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ


ማለዳ ወግ …የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ …
እንደ ሮመዳኑ መረጃ ግብአት …
* ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ
* “የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ናስር አል ቁሰቢ
ነቢዩ ሲራክ
ታዋቂው የሳውዲ የቴሌቪዥን ኮሜዲ ድራማ ተዋናይ ናስር አል ቁሰቢ በያዝነው ሮመዳን ባቀረበው አንድ አስተማሪ ኮሜዲ ከጽፈኛው የአይ ሲ አይ ኤስ ISIS ወይም ዳአሽ አሸባሪ ቡድን አባላትና ከደጋፊዎች ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረበት አስታውቋል ።
መቀመጫውን ዱባይ እንዳደረገ የሚነገረው ሳውዲው ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ በዘንድሮ ሮመዳን ባዘጋጀው ተከታታይ ” ሰለፊ ” በተባለ ፕሮግራም ላይ አሸባሪ ቡድኑን አስመልክቶ ባቀረበው ዝግጅት ነው ። በዚህ የሮመዳን የመጀመሪያ ሳምንት ዝግጅት ላይ ሶርያ ውስጥ የአሸባሪ ቡድን ጋር ያለውን ልጁን ለመፈለግ ወደ ሶርያ ያቀናውን አባት እስመልክቶ ያቀረበው አጭር ድራማ ነው። እንደ ቀልድ በተላለፈው እጅግ ተጽዕኖ መፍጠር መቻሉ የተሰደሰው ዝግጅት ሲጀምር ልጁን ሊፈልግ የሄደ አባት ወደ የአሸባሪዎችን መቀላቀሉንና በአሸባሪው ቡድን ውስጥ የሚካሔዱትን መረን የለቀቁ ሰብአዊ መብት ረገጣዎች ፣ የአሸባሪዎችን ጨካኔ በተገቢ መንገድ ያሳያል። ዝግጅቱ ሲጠናቀቅም አባት ልጁን ለመቅላት ስለት በአንገቱ ላይ በጭካኔ ቦታ መርጦ ሲያሳርፍና ልጅ አንገቱን ሰጥቶ የአሁን አራጅ አባቱ በልጅነት በፍቅር ያሳደገበትን ሁኔታ ከጎን በምናብ ጨረፍታ ያሳያል …
ስሜትን ፈንቅሎ መልዕክት በሚያስተላልፍ መንገድ ፣Saudi-Arabia
በቀልድ በታጀበው የናስር ዝግጅት አዲስ ነገር ባይቀርብም አለም ያወቀው እውነት የሮመዳን ታዳሚ ደጋግሞ ያጤነው ዘንድ ያመላከተ እንደነበር በመዘገብ ላይ ነው። ናስር በዚህ ዝግጅት የአሸባሪውን ISIS ቡድንን ልክ ያለፈ ጭካኔና ርክሰት የማይጨበጥ ጥልቅ የኪነ ጥበብ ውጤቱ አሳይ ቶበታል ። ለዚህ ድንቅ ተጽዕኖ ፈጣሪበለተባለ ስራው ክብርና ዝናን በአድናቂዎቹ ሲያሰጠው ፣ በጽንፈኛ ቡድን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስከትሎበታል !
ትወናውን በመሪነት አሳምሮና እያዋዛ በማቅረቡ የሚታወቀው ኮሜዲ ናስር በዘንድሮው የ”ሰለፊ ” ድንቅ ዝግጅት ጅማሬ ባቀረበው ISIS የተመለከተ ዝግጀት የግድያ ዛቻ ከላኩለት መካከል Julaybib Al-Jazrawi ከተባለ ሰው የደረሰው መካከል ” ፈጣሪ ምስክሬ ነው እኛ ሙጃህዲኖች ያንተን ጭንቅላት ከቀረው ገላህ ቀልተን ካልለያየን እረፍት አናገኝም ! … ” የሚል ከበድ ያለ ዛቻ ይገኝበታል !
የተሰነዘረበትን ሰሞነኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስመልክቶ ሲናገር ” የመጀመሪያውን ክፍል ከለቀቅኩ ጀምሮ በበርካታ ማስጠንቀቂያና ስድቦች የተሞሉ መልዕክቶች አጥለቅልቀ ውኛል ፣ ለሁሉም ተረጋጉ በማለት ረመዳን ከሪም የሚል ምላሽ ነው የሰጠኋቸው ” ብሎ በማሟረት በቲዊተር መልስ መስጠቱ ተጠቅሷል ! ታዋቂው ሳውዲ ኮሜዲ ይህን ምላሽ ከሰጠ በኋላ ዛቻ ማስፈራሪያውን በሚመለከ ት የአረብ መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰሞነኛ የሮመዳን መነጋገሪያ አርዕስት አድርገውታል ። ጉዳዩ በስፋት መሰራጩቱን ተከትሎ አርቲስት ናስር ከመገናኛ ብዙሀን በኩል ዛቻ ማስፈራሪያው ያሰጋው እንደሁ ተጠይቆ ሲመልስ ” የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ሲል እንቅጩን መመለሱ ተዘግቧል ! ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሜዲ ናስር ISIS አስመልክቶ ያስተላለፈው አጭር ዝግጅት ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ተሞካሽቷል ። አሸባሪውን ቡድን እርቃኑን የሚያወጣ እጥር ምጥን ያለ ዝግጅት ነው በሚልም ደስታቸውን የሚገልጹ ቁጥርም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቁሟል !
አርቲስት ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ ሮመዳን በመጣ ቁጥር ከሳውዲ አልፎ በመላ አለም የሚገኙ አረብ ተናጋሪ የቴሌቪዠን ተከራታታዮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል ። ” ጣሽ ማጣሽ ” ተብሎ በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ከጓደኛው አብደላ ሰርሃን ጋር ሮመዳን ተጀምሮ እስኪያልቅ በሚያቀርባቸው ልዩ ልዩ አጫጭር አስተማሪ ዝግጅቶች ዝነኝነትን ያተረፈ ኮሜዲ ነው ። ናስርና አብሮት ሲሰራ ባላቸው ውህደት አድናቆትን ያተረፈው ባልንጀራው አብደላ ድንበራቸው የማይደፈር የሳውዲ የሀይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት የሚታዩትን ችግሮች እየነቀሱ በማቅረቡ ተወዳጅነት አትርፈው ነበር ። ይህም ሲሆን ባልተለመደ መንገድ ለሮመዳን በሚቀርቡት ዝግጅቶች ዙሪያ በሳውዲ መንግስት ብቸኛ ፈቃድ ያለው ዝግጅት “ጣሽ ማጣሽ ” እንደ ነበር በስፋት ይታመናል !
የኮሜዲ ናስርና አብደላ ” ጣሽ ማጣሽ ” ካሳለፍናቸው ሁለት አመታት ወዲህ በባልንጀሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተወዳጁ ዝግጅት ሊቀጥል አልቻለም ። “ጣሽ ማጣሽ” የተባለው ዝነኛ በሮመዳን ዝግጅት በውስጥ ዝብሪት ከተዘጋ በኋላም ሳውዲው ኮሜዲ ናስር በ”አረብ ጎት ታለንት ” ዳኝነት ፈገግ በሚያሰኘው አስተያየቱ አፍቃሪዎቹን ሲያዝናና መክረሙ ይጠቀሳል !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓም

No comments:

Post a Comment