Tuesday, June 30, 2015

የቱርክ መንግስት የግብረሰዶማውያኑን ሰልፍ በውሃ ተኩስ በተነ


በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል የተሰባሰቡ ግብረሰዶማውያን ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የአገሪቱ መንግስት ህገወጥ ነው ሲል በውሃ መርጫ ካኖን መበተኑ ተሰምቷል።
ከሰሞኑ በዓለም ላይ እየተከበረ ያለውን የግብረሰዶማውያን ቀን ለማክበር ወጥተው የነበሩት እነዚህ ሰልፈኞች በታቅሲም አደባባይ አቅራቢያ በመሰባሰብ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን በስፍራው የነበረ የሮይተርስ ዘጋቢ ተናግሯል።
ፓሊሶች የሰልፉ መሪዎችን ካሰሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ መመለሷን የዘገበው ይኸው የሮይተርስ ዘጋቢ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖሊሶችን ጣልቃገብነት የሚቆጣጠር አዲስ ረቂቅ አዋጅ እንዲወጣ በመመካከር ላይ እንደሆኑም ጨምሮ ተናግሯል።
የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት (AFP) እንደዘገበው ደግሞ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የወሰዱት እርምጃ በተለያዩ የግብረሰዶም መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ዘንድ “ፋሽስት” የሚል ቅፅል አሰጥቶቷቸዋል።
ግብረሰዶማውያኑ ከዚህ በፊት ለ13 ዓመታት ያለምንም የመንግስት ጣልቃገብነት ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጉ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ኤርዶጋን በዚህ ዓመት የመጀመሪያውን እቀባ ማድረጋቸው ነው የተነገረው።
(ዜናው የአል-አረቢያ ቴቪ ነው)

Monday, June 29, 2015

እነ ቴዎድሮስ አስፋው ጥፋተኛ ተባሉ

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ጥፋተኛ ከተባሉት መካከል አንደኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ አስፋው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን ያሬድ ደመቀ እና አንዋር ከድር የፓርቲው አባል አይደሉም፡፡ እነ ቴዎድሮስ ጥፋተኛ የተባሉት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 486/ለ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተመሰረተብኝ ክስ የሀሰት ነው፡፡ የተሰማው ምስክርም የሀሰት ነው›› ሲል ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ አመልክቷል፡፡
ዳኛው አንዴ ጠፋተኛ መባሉን በመግለፅ ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ቅሬታ ማቅረብ እንደማይችል ገልጸው ማቅለያ እንዲያቀርብ በጠየቁበት ወቅትም ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተባለውን ወንጀል ፈጽመዋል ብንባል እንኳ የነበረው ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ 30 ኢትዮጵያውያን በጭካኔ የታረዱበት ወቅት ነው፡፡ በታሪካችን እንዲህ አይነት ውርደት አጋጥሞን አያውቅም፡፡ መንግስት የታረዱትን ወገኖቻችን ኢትዮጵያውይነት በሚክድ መልኩ ያወጣው መግለጫ ደግሞ የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን አለመሆናቸውን ላጣራ ከማለቱ በተጨማሪ ለሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን መቀጣጫ እንደሚሆን መግለፁ ደግሞ በጣም አሳፋሪ ነበር፡፡ ተፈፀመ የተባለውን ነገር እውነት ነው ቢባል እንኳ በዚህ ስሜታዊ በሚያደርግ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡
ወጣት ቴዎድሮስ አክሎም ‹‹እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ ተርጓሚው ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ በመታገል ህግ እንዲሰፍን የራሴን አስተዋጽኦ እያደረኩ እገኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገሉ ከሚገኙት ወጣቶች መካከል አንዱ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ሲል የክስ ማቅለያ አቅርቧል፡፡ ከቴዎድሮስ በተጨማሪ ያሬድ ደመቀና አንዋር ከድርም የክስ ማቅለያዎችን አቅርበዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ቴዎድሮስ ለክስ ማቅለያነት ያቀረባቸው የመንግስት መግለጫ፣ ህግ እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑና ቀሪዎቹ ተከሳሾች በማቅለያነት ያቀረቧቸው ጉዳዮችን በማስረጃ እንዲያቀርቡና በማቅለያነት የቀረቡት ጉዳዮችም ማቅለያ መሆን እንደሚችሉና እንደማይችሉ ለመወሰን ለሐምሌ 3/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Ethio Hagere's photo.Ethio Hagere's photo.Ethio Hagere's photo.

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደዕረቡ መዘዋወሩ ተሰማ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ እና ውጪ በርካታ የጸጥታ ሃይሎች ነበሩ


ዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ ተማም አባቡልጉ ጋር ተደዋውለን ተገናኝተን ነበር፡፡ ‹‹እነአቡበከርን ከቂሊንጦ አላመጧቸውም፤ ቀጠሮው ለዕረቡ መዘዋወሩን የሚጠቁም መረጃ ሰምቻለሁ፡፡›› አለኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳርማር አንበሳ ጫማ ቤት ፊትለፊት አንድ የፖሊስ አመራር አራት ሂጅብ የለበሱ ሴት ሙስሊሞችን ‹‹ከዚህ አካባቢ ሂዱ›› እያለ በመቆጣት ከአካባቢው እንዲርቁ ሲያደርጋቸው ተመልክቻለሁ፡፡
በርካታ የጸጥታ ሃይሎች በተሰበሰቡበት የፍርድ ቤት መግቢያ በር ጋር ተፈትሼ ወደውስጥ ዘለኩኝ፡፡ የኮሚቴዎቹ አንዷ ጠበቃ የሆነችውን ወ/ሮ አዲስን አገኘኋትና ስለጉዳዩ ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡ ‹‹መደበኛ ባልሆነ መንገድ ዕረቡ የሚል መረጃ አግኝቻለሁ፤ ዕረቡ ችሎቱ ይሰየም አይሰየም ግን በእርግጠኝነት አላወኩም›› የሚል መልስ ሰጥታኛለች፡፡
እኔም የፍርድ ቤት ቅጥር ግቢውን ለቅቴ ስወጣም፣ ከውስጥም ሆነ በውጪ (በፍርድ ቤቱ) በርካታ የጸጥታ ሃይሎች፣ ፖሊሶችና የፍርድ ጉዳዩን ለመታዘብ የመጡ ወንድ እና ሴት ሙስሊሞች ቆመው ተመልክቻለሁ፡፡

እነ ወይንሸት ሞላ ይግባኝ ተጠየቀባቸው


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ሰኔ 16/2007 ዓ.ም ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ዛሬ ሰኔ 22/2007 ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ቀደም ሲል ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል›› በሚል በተከሰሱበትና ከእስር በተለቀቁበት ክስ ላይ ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡
አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ የጠየቀ ቢሆንም ዳኛዋ ‹‹በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ ከእስር የተፈቱ በመሆናቸው ዋስትና ሊከለከሉ አይገባም፡፡›› ብለዋል፡፡ ዳኛዋ እነ ወይንሸት እንደተለቀቁ እንጅ በእስር ላይ መሆናቸውን እንደማያውቁ ገልጸው 3 ወር ተፈርዶበት ቂሊንጦ የሚገኘው ማስተዋል ፈቃዱ ባለመቅረቡ፣ ከእሱ ጋር ረቡዕ ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ቀርበው ክርክር እንዲጀምሩ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡ ሰኞ ሰኔ 29/2007 ዓ.ም ውሳኔ እንደሚሰጡም አሳውቀዋል፡፡
ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ኤርሚያስ ፀጋዬ በነፃ፣ እንዲሁም ወይንሸት ሞላና ዳንኤል ተስፋዬ ሁለት ወር እስር ተወስኖባቸው ሁለት ወር በመታሰራቸው እንዲፈቱ ተፈርዶላቸው ከእስር ሲለቀቁ እስር ቤት በር ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዛወራቸው ይታወቃል፡፡ ወይንሸት፣ ኤርሚያስና ዳንኤል ሰኔ 19/2007 ዓ.ም በቄራ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ‹‹ከእስ እንዲለቀቁ በተወሰነላቸው ወቅት ምስክሮችና የምስክሮቹ ጓደኞች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውብኛል›› የሚል አዲስ ክስ አቅርቦባቸው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡ በዚህ አዲስ ክስ ላይ የፖሊስን ምስክር ለመስማት ነገ ሰኔ 23/2007 ቄራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

ፖሊስና አቃቤ ህግ በኢህአዴግ ላይ ሰልፍ መውጣታቸውን ቀጥለዋል!



 

አይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው ሆኗል ማለት ይቻላል!
ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ (ሰልፍ እንበለው) ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከል፡-
• ኢህአዴግ ሌባ ነው!
• ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም
• ቴዎድሮስ ለህዝብ ሞተ፣ መለስ ደንግጦ ሞተ፣ ሀይለማሪያም በቁሙ ሞተ!
• እያዋረደን ያለው ወያኔ ነው!
• ወያኔ አሳረደን!
• ኢህአዴግ ቡሽቲ መንግስት ነው! (አሁን ይህም ክስ ላይ ይቀርባል! ዳንኤል ብርሃኔን መሰሉኝኮ)
• የወያኔ 24 አመት አገዛዝ ይበቃናል!
• የሀገር አበሳ የውጭ ሬሳ
• ኢህአዴግ….
• ኢህአዴግ….እና የመሳሰሉት ስድቦች (ማለቴ መፈክሮች) ይገኙበታል!
አንድ ጓደኛዬ በተደጋጋሚ ችሎት ላይ ተገኝቶ አቃቤ ህግና ፖሊስ ‹‹ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም!›› ብለዋል እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ያዳምጥና ‹‹በዚህ መፈክር የተከሰስኩት እኔ ብሆን መከላከያ ምስክር የማደርጋቸው ጠንካራ መሪ አይደሉም የሚባሉትን ሰው ነበር፡፡ ችሎት ላይ አቅርቤ እሺ ጠንካራ ናቸው ወይንስ…. እላቸው ነበር›› ብሏል፡፡
ዛሬ እነ ቴዎድሮስ አስፋው ላይ ደግሞ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው፣ መለስ ደንግጦ ነው የሞተው፣ ኃይለማሪያም በቁሙ ነው የሞተው›› ብላችኋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ መርዶ እኮነው ስንሰማው የዋልነው፡፡ ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ ደግሞ የብሶት መፈክር መሆኑ ነው! ሌላው ቀርቶ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው!›› የሚለውም የክስ መዝገብ ላይ መስፈሩ ያሳፍራል፡፡ ለማንኛውም በዚህ ክስ ላይም ያ ጓደኛዬ መቃወሚያ ቢጤ አቅርቧል፡፡
‹‹መለስ ደንግጦ አልሞተም ስትሉ፣ ኃይለማሪያም በቁሙ አልሞተም ስትሉ የሀኪም ማስረጃ አምጡ!›› እላቸው ነበር ብሏል! ያው የመለስን ገዳይ በቅርብ አላገኘውም ብሎ ይሆናል!
ጌታቸው ሺፈራው

Saturday, June 27, 2015

“ከሀገር ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጦች ላገሬ ያደረኩትን ዉለታ ዋጋ አልሰጡትም” ሼህ አላሙዲ (ገበየሁ ባልቻ)


ሼህ አላሙዲ
በተከታታይ በደቡብ አፍሪካና በአረብ ምድር ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉን እልቂት ከተመለከትኩ በሗላ የሀገራችንን ፖለቲካ መከታተል የበለጠ አሳዛኝ ዜና ያመጣብኝ ይሆናል በሚል ስጋት ኮምፒተሬን በእጅጉ ፈርቸዉ ከረምኩ አንዱ ሳይቋጭ ሌላ መከራ፡ በመከራ ላይ መከራ፡ መሪዎቻችን የመከራ አምካሪዎች፡ ምን ይበጀን ይሆን?። ባለፈዉ ስፈራ ስቸር በተለመደዉ በድር ጥንጥን ስተላለፍ ሼህ አላሙዲ በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች የእሳቸዉን ስራ ዋጋ ሰጥተዉት ለዉይይት ባለማቅረባቸዉ የተሰማቸዉን ሐዘን ፍንጭ የሰጡበት አጋጣሚ ቀልቤን ስቦት ሀሳቤን ልናኘዉ በማለት ወረቀትን ከብእር አገናኘሁ የዜናዉ ምንጭ ኢሳት ለኳሺ ኤልያስ ክፍሌ።
ሼህ አላሙዲ ከኢትዮጵያ አፈር ተበጥብጠዉ እንደዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያነሰ ወይም የጎደለ ኢትዮጵያዊነት ሳይኖራቸዉ እንደኔዉ በትንሿ መንደራቸዉ ተወልደዉ አድገዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር ዘር ሀይማኖት ሳይለዩ ከሰፈራቸዉ ልጆች ጋር ቡድን ተቧድነዉ  ኳስ አቃብለኝ ብለዉ ሲጮሁ፤ ላዘገየባቸዉ ወይም ላላቃበላቸዉ ደግሞ ቆይ ጠብቅ ባንተ ምክንያት ነዉ የተሸነፍነዉ ብለዉ ሲዝቱ፤ ጎል ጠባቂ ተረኛ ሁነዉ ደግሞ ብዙ ጎል ሲገባባቸዉ ሁለተኛ አንመርጥህም እንደዉም ከኛ ጋር አትጫወትም ሲባሉ ሆድ ሲብሳቸዉ። ከዛ ደግሞ አለፍ ብሎ ተማሪ ቤት አጠገባቸዉ የተቀመጠዉን ተማሪ ዞር ሲል ሲቆነጥጡ እሱም ባንኖ አንተነህ ሲላቸዉ እሳቸዉም እኔ አይደለሁም ብለዉ ሲክዱ፤ እሱም ጊዜ ጠብቆ ብድሩን ሲወጣ። እርሳሳቸዉ ሲጠፋባቸዉ አጠገባቸዉ ካለዉ ጓደኛቸዉ ነድፈዉ  አይኔን ግምባር ያድረገዉ ብለዉ ሲክዱ።እንዲህ አንዳንዴ ደግሞ ሾለክ ብለዉ ብይ ሲጫወቱ ፤ ወደ ሁዋላ ደግሞ አንድ ቀላ ድምቡሺቡሺ ያለች ልጅ ወድደዉ እንዳይጠይቁ ፍርሀት በሰራ አከላታቸዉ ገብቶ መላ አጥተዉ በልጅቱ አጠገብ ሲያለፉ እጃቸዉን ኪሳቸዉ ከትተዉ ድንጋይ በጫማቸዉ እየመቱ ልጅቱ እንደበደለቻቸዉ ሁሉ ቆይ ነገ ባላገኝሺ ብለዉ ፎክረዉ በቄንጥ ባጠገቧ ሲያልፉ። ለልጅቱ የላኩት የፍቅር ደብዳቤ ተጠልፎ ዲሊክተሩ ቢሮ ደርሰዉ የተግሳጽና የኩርኩም ናዳ ሲወርድባቸዉ እንዲያ እንዲያ እያሉ ከዛሬዉ ከዲታነታቸዉ ዘመን በላይ የልጅነት ጊዜያቸዉን  በምድረ ኢትዮጵያ እስከ መጨረሻዉ የማይረሳ ህልም ሁኖ የሚቀር የደስታ ኑሮ ኑረዉ እንደእኔዉ ኑሮን ለማቅናት በረሃዉን ተከትለዉ ልባቸዉ ወደመራቸዉ ቦታ ተጓዙ። ምድር በሰጠችህ በረከት ትኖራለህ ተብለዉ ነበርና የዛሬዉን አላሙዲን ሲሆኑ እኔም በላብህ ጥረህ ግረህ ትኖራለህ የሚለዉ የግድ ተግባራዊ እንዲሆን ከሳቸዉ በተቃራኒ ሂጄ  በአንድ የምእራብ ሀገር እኔን ሁኜ እኖራለሁ።
ከተረሳ ሁሉም ይረሳል የፖሊስ ጥፊ የባለስልጣን ግልምጫ ሳያየኝ አምላክን እያመሰገንሁ እኖራለሁ። ምርጫ ሲመጣ አንዴ አንዱን በሌላ ጊዛ ደግሞ የወደፊት እቅዴ ደሀን ሀብት በሀብት ማድረግ ነዉ ሲለኝ ብዙ ጊዜ ብታለልም እዉነት እየመሰለኝ መልሼ ያንኑ እመርጣለሁ። ደግነቱ ወረቀቴ በገባችበት ሳጥን ቆይታ ለመረጥኩት ተፎካካሪ ማንም ሳይነካት ትደርሳለች ክፉም አይነካትም። አደራ እፍረት ባጠገባችሁ ያላለፈ የስርአቱ ደጋፊዎች ኢትዮጵያም  እንዲሁ ነዉ ብላችሁ እንዳታስቁኝ። ይሄኛዉ ነገሩ ሌላ ነዉ እናንተም ታዉቁታላችሁ ብቻ ለማደናቆር ስትፈልጉ ዶሮዋን ቆቅ ታደርጓታላችሁ።
ስለልጂነት ዘመናቸዉ ይህን ካልኩ በሗላ በቀጣዩ ደግሞ እኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያዉያኑ መሀል የተለያየ ስምና ስብእና እየተሰጣቸዉ እኛም ከወሬዉ ብዛት ትክክለኛዉ እሳቸዉ የትኛዉ እንደሆኑ ማመን ተቸገርን እዚህ ደርሰናል። ኑሮ እንጨት እንጨት ሲለዉ ገመድ አዘጋጅቶ የመጨረሻ ትንፋሹን ሊዉጥ ሲል ገመዱን በብር ሺራፊ ቆረጡት ይላል በአይኔ በብረቱ አየሁ የሚል አዳናቂ፤ አይ ያንተ ነገር ይሄማ ምን አለዉ ይለዋል ሌላዉ አላሙዲን በአይኑ አይቶ የማያዉቅ ተራኪ። አየር ለመቀበል ወጣ ሲሉ አንዷ ደሀ በትካዜ ተዉጣ እድሌ ነዉ እንግዲህ ምን ይደረጋል እሱ ያዉቃል ብላ እምባዋን ጠራርጋ ስትነሳ አንች ሴት ከቅድም ጀምሮ ስመለከተሺ ነበር ምን ችግር ቢገጥምሺ ነዉ ቢሏት ማንነታቻዉን ያላወቀች አንዲት ያገሬ ሰዉ ልብ በሚሰብር አነጋገር ኑሮዋን ብታወጋቸዉ ልባቸዉ ተነክቶ 3 ልጆቿን ወደ ባህር ማዶ ልከዉ አስተማሩላት ይላል ሌላዉ። ሌላዉ ደግሞ ባለፈዉ አንድ የሰፈራችን ሰዉ የተሰጠዉ እድሜ አልቆ አትድንም አትልፋ ብሎ ሀኪም ቢነግረዉ ጆሮ ጠባቂያቸዉ ጉዳዩን ቢያደርስላቸዉ ባህር ማዶ ልከዉ አሳክመዉት ይባስ ብሎ ሩጫ ጀምሯል ይላል  ለሰዉ የተደረገለተ ወደሱ የሚጋባ የሚመስለዉ ምናበኛ።  ሌላዉ ደግሞ ተሰባስበን የሙዚቃ ክፍል ልናቋቋም ነዉ ብለዉ ወጣቶቹ አቤቱታ ቢያቀርቡ አይናቸዉ ሳያይ እጃቸዉ ብቻ ዘግኖ ያወጣዉን 30000 ዶላር ቢሰጧቸዉ ነገሩ ለዉሻ እንደ ተወረወረ ስጋ አይነት ነገር ሁኖ ተካክደዉ አንዱ ሌላዉ በደረሰበት አይደርስም ይላል። ቡና ቤት ከፈቱላት፤ መኪና ገዙላት፤ የወር ደሞዝተኛ አደረጉት፤ ወደ ትምህርት ተቋም ልከዉ አስተማሩት፤ አቋቋሙት፤ዳሩት የሚለዉ ነገር ችሮታዉ ከተደረገበት ቦታ እያለፈ ሲሄድ በከፍተኛ ፍጥነት እየተባዛና እየገዘፈ የሼህ አላሙዲን ነገር አንዴም እንደ ሮቢን ሁድ(Robin Hood) ለድሀ ተቆርቋሪ አይነት ሲያደርጋቸዉ ሌለዉ ደግሞ ከሰማዩና ከመንፈሳዉያን መሀል ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ያለ ነገር ከምድራዊ ሰዉ ሊሆን አይችልም ብሎ ነገሩን ይዘጋዋል።
እኚህ ሼህ በኢትዮጵያ አፈር በቅለዉ ለፍሬ መብቃታቸዉ ሀብታቸዉ ብቻ ሳይሆን መልካቸዉ እና ሌሎች አረቦች ላይ የማናየዉን  እሴቶች በሳቸዉ ላይ ተንጸባርቆ ይታያል። አንድ ቀን ስለ ሀብታም የማላዉቀዉ የለም የሚለዉ ፎርበስ (Forbus) መጽሄትም በኢትዮጵያ ባንድራ ጥለት በተንቆጠቆጠ እጀ ጠባብ እና ኩታ ያሳየን ይሆናል የሚል ተስፋም አለን። እንደዉ አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያዊ መሆን  ምኑ ያሳፍራል? ስለ ሰዉ ልጂ አፈጣጠር ንትርክ ሲነሳ ችግር መፍቻ እና ማነጻጸሪያ የሚሆነዉ ያዉ ኢትዮጵያ ነዉ ።  ነጻነት የጠማዉ የየሀገሩ ዜጋ በምናብ የሚያየዉ ይህችኑ የነጻነት ተምሳሌት ኢትዮጵያን ነዉ አረ ስንቱ መለስ ዘራዊ አዋርዶን ሄደ እንጂ ምን እሱ ቢሞት ሌሎች የማይሞቱትን ተክቷል እንደዉም እሱ ጥሩ ሰዉ ነዉ ቀድሞ መሞቱ። ያነጋገር፤ የባህል፤ ሰዉ የማክበር ምሳሌ ኢትዮጵያዊ ሁኖ እያለ በየምክንያቱ በኢትዮጵያዊነት እንዲታፈር የሚደረግበት ምክንያቱ ምን ይሆን?  ክቡር አቶ መለስ አንዱ ፓርላመንተኛ ደጋግሞ ኢትዮጵያን ብዙ ጊዜ  ፓርላማዉ ዉስጥ ቢያነሳባቸዉ ደማቸዉ ፈልቶ ምነዉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት አበዛህ ብለዉ ለህዝብ በሚተላለፍ ቴሌቨዢን ዉቃቢዉን ገፈዉት የለ? ዛሬ ሙት ወቃሺ አያድረገኝ እንጂ በዉነቱ በዛን ቀን እዚያ ምስኪን ላይ አቶ መለስ በብስጭት የጮሁት ጩኸት አበበ ከላዉም ከዛ በላይ እሳቸዉ ላይ አልጮኸም ነበር ሰበብ ሁነዉበት አረፉት እንጂ። ነገር ነገርን አስነስቶ ወዳልፈለግሁት አቅጣጫ ገፋኝ እንጂ ነገሬን ለማሳጠር  ዲታ አላሙዲ ገንዘቡን ከላያቸዉ ስናነሳ ኢትዮጵያዊ አንጂ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም ለማለት ፈልጌ ነዉ እንጂ አቶ መለስማ ወደ ማይመለሱበት ሂደዋል።
እንግዲህ ከዚሁ ተንደርድረን ጌታ አላሙዲ ለስራዬ እዉቅና ተነፈግሁ ከህዘቡ ጋር አላገናኙኝ አሉ የዜና ተቋሞችን መዉቀሳቸዉ የወዳጂነት እንጂ የክፋት ስላልሆነ እሳቸዉም በድፍረት ኢትዮጵያዉያን ሰፈር ቀርበዉ ኢትዮጵያዉያን ጋር የሆድ የሆዳቸዉን  ቢወያዩ መልካም ነዉ እላለሁ።  ከእነ አቦይ ስብሀት፤ በረከት ሰምኦን፤  ከመለስ ዘራዊ ጋር አንዴ ሲያጨበጭቡ አንዴ ሲፍነከነኩ ደስታ በደስታ ሁነዉ ሲዝናኑ ብዙ መረጃዎች ደርሰዉናል። ኢትዮጵያዉያን መሀል ግን በእንዲህ ሁኔታ ደፍረዉ የታዩበት አጋጣሚ ብዙም አናስታዉስም።
በነገራችን ላይ ሼህ አላሙዲ በዉጭ የሚኖሩ ኢንቨስተር እንጂ የህዝብ አደራ የተቀበሉ ባለስልጣንም አይደሉም አንዳንዶቻችንም ከአንድ መንግስትና ጥሩ ዜጋ የማይጠበቅ ሰብአዊ፤ልማታዊ፤በጎአድራጎታዊ ስራ ከሼህ አላሙዲ ስንጠብቅ እንታያለን። በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ነገሩን ስናየዉ ሼህ አላሙዲ ግለሰብ ብቻ አይደሉም እሳቸዉ የሚወስዱት የኢንቨስትመንት ዉሳኔ ጉዳቱና ጥቅሙ የሀገራችን ጥቅም እና ጉዳት በመሆኑ ዜጋ አይኑን ከፍቶ ሊመለከተዉ ይገባል። ስለዚህ ሼክ አላሙዲ የግል ሳይሆኑ የህዝብ በመሆናቸዉ የህዝብ የሆነ ደግሞ በሀገሩ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ በግልጽ መገምገም ስላለበት ሼህ አላሙዲም የዚህ ክስተት አንዱ መሆናቸዉን እሳቸዉም ሊገነዘቡልን ይገባል። ጥሩ ሲያደርጉ ጀግና፤ ከኢትዮጵያዊነት መስፈርት ሲወርዱ ደግሞ በህግ አምላክ ማለታችን ግድ ይላል ምንም እንኳን አሁን ህግ ባይኖርም የኢትዮጵያ ሊቃዉንት በየሀገሩ ስለተበተኑ መደበቂያ ጠፍቷል። ባለፈዉ ሼክስፒር ፈይሳ የወያኔን መሪዎች ከሀገር ወጥተዉ ሺቶ እንኳን እንዳይገዙ አስጨንቆ ይዟቸዉ መላ ጠፍቷቸዉ ነበር። ሼክ ሰፒር ፈይሳና ፕሮፌሰር አልማርያም እግር ላይ ወድቀዉ ምህረት ጠየቁ መሰል ዛሬ ፍርሀቱ ለቋቸዉ እየመጡ ሺቶ ነገር እየገዙ፤የቤት ክራይ እየተቀበሉ፤ ቱቦ እያስቀየሩ መመለስ ጀምረዋል።

እንግዲህ ሼህ አላሙዲ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍ ያለ ኢንቨስትመንት የሚያደርጉ ግለሰብ በመሆናቸዉ የሳቸዉ ኢንቨስትመንት ጥቅም እና ጉዳቱን ለመለካት ብቃት ያላቸዉ ባለሙያዎች ጉዳዩን አስመልከተዉ ማብራሪያ እንዲሰጡን ስለጉዳዩ እናዉቃለን የሚሉ ዜጎች ደግሞ የግል ሀሳባቸዉን፤መረጃቸዉን፤ጽሁፋቸዉን ወደ ጋዜጣዉ ቢሮ አከታትለዉ ቢልኩ ስለሳቸዉ ተጨባጭ ግንዛቤ እንይዘለን የሚል ግምት አለኝ።
እሳቸዉም ረቂቅ የሆነዉን የአማርኛ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ማብራሪያ እንዲሰጡ ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አለበለዚያ ከክፉ መሪዎች ጋር ተመሳጥረዉ የሀገርን ንብረት አባከኑ የሚለዉ ክስ ተከላካይ እስካልቀረበበት ድረስ እዉነት ሁኖ ሊቀር ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮየጵያ ላይ የሚያደርጉት የመዋእለ ንዋይ ፍሰት እሳቸዉም ተጠቅመዉ ህዝቡንና አገሪቱን ለመጠቀም ከሆነ እሳቸዉም ለዚህ ሀሳብ ትክክለኛነት ድፍረቱ ካላቸዉ የፖለቲካ ድርጅቱን እምነት ብቻ እንደ ፖለቲካ ሳይሆን እንደ ሀይማኖት አክርሮ በሚሰብክ የሚዲያ ተቋማት ሳይሆን ኢትዮጵያዉያን ክብር የሚሰጧቸዉና ተአማኒነት ባላቸዉ የዜና ተቋሞች ማብራሪያ እንዲሰጡ ይጠበቃሉ (አይጋ ፎረምን ማለቴ እንዳልሆነ ማስታወሻ ይያዝልኝ አስመሮም ለገሰንም የኢትዮጵያ ችግር ፈላጊ አድርጎ የሚያቀርብ ከክቡር ኢሳይያስ አፈወርቂ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚሰጠዉ በመሆኑ እሱም  አይመቸኝም)።
ሼህ አላሙዲ ላገራችን/ቸዉ ጥሩ ሰርተዉ በመረጃ እጥረት ስራቸዉን ካቃለልንባቸዉ በጣም ያሳዝናል በሌላ በኩል ደግሞ ሼህ አላሙዲ በዉጭ ሀገር እንደተመለከቱት ሁሉ በገለልተኝነት በኢንቨስትመንት ስራቸዉ ላይ ብቻ አተኩረዉ እጃቸዉን ሰብስበዉ ከመቀመጥ ይልቅ ከዚህ አፋኝ ስርአት ጋር እጅና ጓንት ሁነዉ ከሰሩም ኢትዮጵያዉያን የወያኔ መሪዎችን ባየንበት አይን የምንመለከታቸዉ መሆኑን በግልጽ ማስገንዘብም ያስፈልጋል።
ለማንኛዉም ይህንን ነገር ለማጥራት ሼክ አላሙዲ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ/ዶ/ር ጌታቸዉ በጋሻዉ ጋር በመሆን ፓናል ዉይይት ቢያደርጉልን ይህንን የጥርጣሬ ደመና ያጠራዋል የሚል እምነት አለኝ። እዚህ ላይ የወያኔ መሪዎች ሰዉን ለማሳሳት እንደ ሀዉዜዉ ድራማ ሁኔታ ጠብቀዉ በተቀረጸ ምስል ሰዉን ማሳሳት ልማዳቸዉ ስለሆነ አንባቢ የነዚህን ሰዎች ተንኮል ከነሱ ቀድሞ ሊገነዘብ ግድ ይላል ባለፈዉ ንብ ይሁን ዝንብ ያለበት ሸሚዝ እኝህን ሼህ አልበሰዋቸዉ በማየቴ ነዉ። ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ክርስቶስን በአካል አግኝቸዋለሁ ማለት የሚዳዳቸዉ፤ መጠጥ ወደዚህ አለም ከመጡ ጀምሮ ሸቷቸዉ የማያዉቅ  አፍሪካ መሪዎች ስብሰባ አቶ በረከት በጆሯቸዉ ምን እንዳላቸዉ አይታወቅም በእለቱ በሳቸዉ ሻምፓኝ ፍጆታ ምክንያት መሪዎቹ ሳይቃመሱ እንዳለቀ በትዝብት ተስተዉሏል። እንግዲህ እንዲህ ለነብሳቸዉ ያደሩትን መጠጥ የጋቱ ሼክ አላሙዲን ተናዳፊ ንብ ቢያለብሱም ብዙም ሊገርም አይገባም።
በእርግጥ ካፒታል ኢንቨስትመንት ከምእራብ አገሮች በላይ ወደ ታዳጊ አገሮች ቢፈስ በብዙ እጥፍ ትርፍ ሊያመጣ ቢችልም እኚህ ሼህ ግን ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ መዋእለ ንዋያቸዉን መሳባቸዉ ሊያስመሰግናቸዉ ሊያስከብራቸዉም ይገባል ለማንኛዉም ከሊቃዉንቱ ጋር የሚያድርጉት ዉይይት ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎችን ስለሚመለስልን በዚህ ነገር ትርፍ ለማምጣት የሚክለፈለፉ ወገኖች በጋዜጠኝነት ስም ወደዚህ አካባቢ ዝር ሳይሉ ጉዳዩ ክብርና እዉቅና ባላቸዉ ወገኖች እና ምሁራን ዉይይት ቢደረግበት ዜጋ ብዙ ጥቅም ሊያገኝበት ይችላል የሚል ጽኑ እምነት ሲኖረኝ ሼህ አላሙዲም በሄዱበት ሁሉ አጃቢያቸዉ ኢትዮጵያዉ ሁኖ ያለሃሳብ የኢትዮጵያዊነት ነጻነት የሚያስገኘዉን ጥቅም ተቋዳሺ ይሆናሉ የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።እንግዲህ እንደተለመደዉ ለእርምትና፤ለትንኮሳ በዚህ ድርሱኝ gebeyhubalcha@yahoo.com
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ገበየሁ ባልቻ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7950#sthash.Xx56su9G.dpuf

5 የመኢአድ አባሎች አንዳርጋቸው ፅጌን ይመስክርልን አሉ

በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት
እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር ስላለ ችሎቱ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ይዘዝልን እና ይመስክርልን ወይም ይመስክርብን ሲሉ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል አቶ አንዳርጋቸው ቀርቦ ምስክርነት ይሰጥ ይሆን ? አቃቤ ህግ በህይወት ይኑር አይኑር የማይታወቅ ሠው ይቅረብልን ማለት አግባብነት የለውም ብሏል ለማንኛው ቀጠሮው ሀምሌ 03/2007 ዓም ስንተኛ ችሎት እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ ፍርድ ቤቱ ግን ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው

እነ ወይንሸት ሞላ አዲስ ክስ ቀረበባቸው

                                                                            መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ከእስር ቤት ሲወጡ
እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ
አዲስ ክስ አቀረበ፡፡
እነ ወይንሸት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ
ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም ወስነናል፣ ከዚህ
በኋላ ይህን ጉዳይ አናይም›› በሚል መዝገቡን እንደማያዩ ገልጸው መመለሳቸው ይታወቃል፡፡
ይሁንና ዛሬ ሰኔ 19/2007 ዓ.ም በቄራ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ‹‹ምስክሮችና የምስክሮቹ ጓደኞች ላይ ዛቻና
ማስፈራሪያ አድርሰውብኛል›› ሲል ሌላ ክስ አቅርቧል፡፡ ፖሊስ እነ ወይንሸት ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው
ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ የነበሩትን ምስክሮችና የምስክሮች ጓደኞችን ‹‹ወያኔ
ለዘላለም አይኖርም፣ እንገናኛለን፣ ቤታችሁን እናውቀዋለን፣ የወያኔ ተላላኪዎች›› በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውብኛል ብሏል፡፡
ሆኖም እነ ወይንሸት በወቅቱ የመሰከሩባቸውን ሰዎች ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ እንዳላዩዋቸው፣ ዛቻና ማስፈራሪያም
እንዳላደረሱባቸውና ክሱ ሆን ተብሎ እስር ላይ ለማቆየት የተደረገ ነው ብለዋል፡፡
እነ ወይንሸት በአዲሱ ክስም የዋስትና መብት የተከለከሉ ሲሆን በምስክሮችና የምስክሮች ጓደኞች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ
አድርሰውብኛል ያለው ፖሊስ ምስክር ለማሰማት ለማክሰኞ ሰኔ  23/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡

Thursday, June 25, 2015

የወያኔ ሰላይ ስደተኞችን መግደሉ ተሰማ





ከሀገር ውጭም በስደት በሕውሓት ሰላዮች ክትትል ይደረግባቸው የነበሩ ኢትዮጵያውያኖች ከሰዳን ወደሊቢያ ገዞ ላይ እንዳሉ የሕውሓት ሰው ከሱዳን አቻው ጋር በመሆን በሱዳን ወታደራዊ ተሽከርካሪ ስደተኞቹ የተሳፈሩበትን ተሽከርካሪ በመግጨት አና እንዲገለበጥ በማድረግ አዳጋ ከደረሰባቸው መካከል የሥርዓቱ ሰው የነበረን ቁስለኛ ከሌሎች ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ፎቶ ከኪሱ በማውጣት ከፎቶው ካስተያየ በኋ በያዘው ሽጉጥ እንደረሸነው የአይን ምስክር ከሞት በተረፉት ሊጋለጥ ችሏል በወቅቱ በሕውሓቱ ሰው በሰሃራ ምድረ በዳ ያለቁት የሁሉም ሰዎች ሥም ያታወቃል ነገር ግር ለሟች ቤተ ሰሰባቸው ሲባል ስማቸውን ለጊዜው በሚዲያ ለማውጣት አልተፈለገም በፎቶ ግራፉ ላይ የምናየውን አሰቃቂ ድርጊት የፈፀመው ኢትዮጵያን የሚገዛው የትግራይ ነፃ አውጭ ሕውሓት ነው ።
— ኢትዮጵያውያን የገጠማቸው ፈተና በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆ በመላው ዓለም ተበትነን በምንገኘው ላይ የዕለት ተዕለት የግል ኑሮአችን ጣልቃ የሚገቡ በሥርዓቱ ቅጥረኞ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ በተገኘው አጋጣሚ ጥቃት እየተደረገብን ይገኛል በግል ሕይወትም ጭምር ።
ለምሳሌም :—
በትዳር ጓደኛ
በሥራ ቦታ ወዘተ

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ማስፈራራት የሚደርስባቸው ግለሰቦች ልሰደድ ቢሉም ሁሉም የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገራት በጣም አደገኛ እንደሆኑ እናያለን ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ ሞትን ፈርተው በስደት ያን የፈሩትን ያገኙታል ።
ኢትዮጵያውያንን ለጊዜውም ቢሆን ሕይወታቸውን የሚያድኑባት ሀገር ያለች አንዲት ኤርትራ ብቻ ናት ።
የኢትዮጵያን ወጣት በከፍተኛ አጣብቂኝ ላይ ይገኛል አህጉራዊ ራዕይ ያለቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በምንም ለምንም የማይፈለጉ ተደርገው በሀገራቸው ጉዳይ በሀገራቸው ላይ ባይተዋር ተደርገዋል የአማራጩ ቀዳዳ ሁሉ ተዘግቷል ።
አንድን ውሻ በፀቱን ዘግተህ እንደመግረፍ ያክል ነው ውሻ የፈለገ ይሁን መሮጫ ከለለው መልሶ ያሳደገውን ጌትዬ ነው ብሎ አያከብረውም አዙሮ የገጠጠ ጥርሱ በለጭ ያደርግና በማጉረጥረጥ ያስጠነቅቀዋል ያ ገራፊ ይህ መልዕክት ያልገባው ከሆነ ይፋለመዋል ።
የኢትዮጵያ ወጣት ይህ የውሻውን ዓይነት ለመብቱ የማይቆም ከሆነ ሀገሩን ተቀምቶ መብቱን ተነፍጎ የበይ ተመልካች ሁኖ ይቀጥላል ።
ለሟቾች ነፍስ ይማር ።

ዳዊት አስራደ በገጠመው ተደጋጋሚ እስርና እንግልት ምክንያት ሀገሩን ትቶ ተሰደደ!!


ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚእንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 ወራት ተኝቶ ከሞት ድኗል፡፡
በ97 ዓ.ም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን የጀመረው ዳዊት አስራደ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች አባልም ነበር፡፡ ዳዊት በፓርቲው የተለያዩ ሓላፊነቶች ላይ የሰራ ሲሆን ለአብነትም
– በወጣቶች የትምህርትና ስልጠና ዘረፍ
– የብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ አባል
– የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ጸሀፊ
– የኢኪኖሚ ጉዳዮች ሃላፊና በተለያዩ የአድሆክ ኮሚቴዎች ውስጥ በሀላፊነትና በአባልነት ሰርቷል፡፡
የአንድነትን የ5 አመት እቅድና ስትራቴጂ ከነደፉት ሰዎች መካከልም ዳዊት አለበት፡፡ በ2002 ምርጫ አንድነት መድረክን ወክሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ተወዳዳሪ ነበር፡፡ ሆኖም በ2007 የአንድነት ፓርቲ በምርጮ ቦርድ ለነ ትግስቱ አወል መሰጠቱን በመቃወም ከፓርቲው ሙሉ በሙሉ ቢገለልም በገጠመው ተደጋጋሚ እስርና እንግልት ምክንያት ሀገሩን ትቶ ሂዷል፡፡
መንግስት በሽብር ቡድኖች በሊቢያ የተቀጠፉ ኢትዮጵያውያንን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ቪዲዮ ቀርጻሃል›› በሚል ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በፖሊስ ተይዞ ቄራ ፖሊስ ጣቢያ ገባ፡፡ ሰልፉን በሞባይል በቀረጸበት የ25000.00 ብር ዋስ እንዲለቀቅ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት ወሰነ፡፡ ሆኖም አቃቢ ህግ ወዲያውኑ በ14 የተደረገውን ሰልፍ ለማወክ በ13 ከ200-300 የሚሆኑ ወጣቶችን አደራጅተሃል የሚል ተጨማሪ ክስ መሰረተበት፡፡ ይህን ክስ ደግሞ በ6000.00 ብር መያዣ ይፈታ ሲባል በእለቱ ስብሰባው ላይ ችግር ፈጥረሃል የሚል ክስ ታከለለት፡፡ ለዚህ ደግሞ 5000.00 ብር አስይዝ ተባለ፡፡
ሚያዚያ 14 በቄራ፣ ከሚያዚያ 15- 21 በፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስሮ ቆየ፡፡ ሚዚያ 21 ቀን ባስያዘው ገንዘብ ተፈቶ ሳይሰደድ ሲቀር ይምሰላል በግንቦት 3 ቀን ከፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ተደወለለት፡፡ ያስያዝከውን ንብረት ውሰድ ነጻ ነህ አሉት፡፡ ሲሄድ ግን ታሰረ፡፡ ሶስት ቀን ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ከቆየ በኋላ ወደ ማእከላዊ ተወሰደ፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዘያት እስከ ሰኔ 5 ቀን በማእከላዊ እስር ላይ ቆይቶ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት በእለቱ እንዲፈታ ወሰነ፡፡ እስካሁን ያዝያዘው 36000.00 ያልተመለሰለት ሲሆን ሰኔ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንዲገኘ ሌላ ቀጠሮ ተሰጠው፡፡
ዳዊት በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ባሉ መርማሪ ፖሊሶች ከኢህአዴግ ጋር እንዲሰራ ግብዣ ቀርቦለት ነበር፡፡
ዳዊት አስራደ በተለያዩ ባንኮች በተለያየ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሰርቷል፡፡ አገር ጥሎ በወጣበት ወቅትም በህብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የአንድ ክፍል ዋና ሓላፊ እና ጥሩ ደመዝ ተከፋይም ነበር፡፡ ዳዊት የአንድ ልጅ አባትና ባለትዳር ነው፡፡
ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስርዓቱ እግር ተወርች አስሮ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ በዚህ ሳምንት አገሩን ጥሎ መጥፋቱ ተገልጧል፡፡
(ዛሬ የሰማሁት መራር ዜና ነው- የዳዊት አስራደ ስደት፡፡ ይህን ቆራጥ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ታጋይ በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ የሚወደውን ልጁን፣ የሚያፈቅራትን ሚስቱን እና ሀገሩን ትቶ መሰደዱን ስሰማ ከልቤ አነባሁ፡፡ )

Wednesday, June 24, 2015

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ


June 23, 2015
def-thumbአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከሰነዓ አለም አቀፍ አውሮፓላን ጣቢያ ታፍነው ከተወሰዱ በዛሬው ዕለት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ. ም፣ አንድ ዓመት ይሞላቸዋል። የወያኔ አረመኔዎች ይህን ዓይነት የውንብድና ተግባር ሲፈጽሙ በከፍተኛ ደረጃ ያሰሉት፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን፣ ንቅናቄው ብሎም ሕዝቡ፣ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት፣ የሚያደርገውን ትግል ለማዳከምና ከተቻለም ደግሞ ለማጥፋት እንደሆነ፣ ምንም የማያጠራጥር ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ የወያኔዎች ስሌት በምን ያህል ትክክል ነበር ?
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ፣ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸመው የውንብድና አፈና ተግባር፣ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባለው ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ሌላው ቀርቶ ከአፈናው በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ንቅናቄያችንን በጥርጣሬ የሚመለከቱ ወገኖች በአደባባይ ወጥተው፣ ” እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” በማለት አቶ አንዳርጋቸውና ንቅናቄው ለሚታገሉለት ሕዝባዊና ሐገራዊ ዓላማ መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሐገር ውስጥ፣ በምድር ላይና በውጭ ሐገር የሚገኘውን የንቅናቄያችንን አካላት ተቀላቅለዋል። ቀደም ሲል በንቅናቄያችን በተለያዩ ደረጃዎች ይሰሩ የነበሩ ዓባላቶች ከአፈናው በኋላ ለትግሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምረዋል።
የአቶ አንዳርጋቸውን አፈና ተከትሎ፣ የንቅናቄው አመራር መሰረታዊ የትግል እንቅስቃሴዎቹን በስፋትና በጥልቀት በመፈተሽ አስፈላጊውን ማሻሻያዎችና ማስተካካያዎችን አድርጓል። ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸው ለረጅም ጊዜ የደከሙለትን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ የመታገለን ጥረት አሳክቶ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዓርበኞች ግንባር ጋር ሙሉ ለሙሉ ተዋህዷል። ከዚህም በተጨማሪ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ጨምሮ፣ ከሌሎች አምስት በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋራ በጥምረት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል።
በሌላ በኩል ያለፈው አንድ አመት የወያኔ የዘረኛ ዓምባገነን ቡድን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን የአፈና፣ የግድያ፣ የዕስርና የድብደባ ውንብድና ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት ዓመት ነበር ። ለዚህም ጸረ ሕዝብ ተግባሩ፣ በባህርዳር ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ፣ በሰላም እንታገላለን ብለው ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የአንድነትና የመኢሀድ ድርጅቶች ማፍረስ ብቻ ሳይሆን፣ ዓባሎቻቸው ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ የድብደባና የዕስር ወንጀል መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ በኦሮምያ፤ በአፋር፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ይህ ነው የማይባል አፈና፤ ግድያና የሕዝብ መፈናቀል በሰፊው አከናውኗል:: ከምርጫው ጋር ተያይዞም በአደረበት ስጋት የተነሳ በርካታ፣ በተለይ ወጣቶች ላይ፣ የመደብደብ፣የማዋከብ የዕስርና የግድያ ተግባር የፈጸመው በዚሁ አቶ አንዳርጋቸውን ከአፈነበት ቀን ጀምሮ በተቆጠረው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በጣም የሚገርመው ለራሱ አመቻችቶ ያዘጋጅውን ምርጫ እንኳን ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩ ብሎ ከአወጀም በኋላም፣ ከምርጫው በፊት በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ወንጀል አጠናክሮ መቀጠሉ ያለበትን የስጋትና ጭንቀት ደረጃ የሚያሳይ መረጃ ነው ።
የወያኔ በራስ የመተማመን ደረጃ ከመቼውም ወቅት ይልቅ እጅግ አሽቆልቁሎ የታየውም ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በሐገር ውስጥ ይነሳብኛል ብሎ በሚያስበው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስጋት ምክንያት ይህን ስጋት ለመቀነስ በአንድ መንገድም ይሁን በሌላ ይረዱኛል ብሎ ያሰባቸውን በአካባቢው የራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ያላቸውን ቀደም ሲል ወቀሳ ቢጤ እንደመሰንዘርም ዕልህም እንደመጋባትም ይዳዳቸው የነበሩትን መንግስታት ባለሥልጣኖች በመማጸንና ሐገር ውስጥ በመጋበዝ ማንነቱን አበጥሮ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአደባባይ ወጥተው ወያኔ ያልሆነውን ነው ብለው ምስክርነት እንዲሰጡለት ማድረጉ የወያኔ ስጋት የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ሌላው መረጃ ነው።
በዚህ አጋጣሚ ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸውን አፍነው ለወያኔ የሸጡትን የየመን ባለሥልጣኖች ድርጊት በሚመለከት በጊዜው በሰጠው መግለጫ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ “ጊዚያዊ ጥቅምን በማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት የሚያደርገውን ትግል ከወያኔ ጋር በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ በመተባበር ለማፋን መሞከር፣ ታሪካዊ ስህተት መስራት ነው!” እንዳለው ሁሉ፣ ዛሬም የሌሎች መንግስታት ባለ ሥልጣኖች እንደ ትላንትናዎቹ የየመን ባለሥልጣኖች ጊዚያዊ ጥቅምን ብቻ በማየት ሌላ ታሪካዊ ስህተት እንዳይደግሙ ከወዲሁ ለማሳሰብ ይወዳል።
በንቅናቂያችን እምነት ከዚህ በላይ በጥቂቱም ቢሆን ለማሳየት እንደተሞከረው ያለፈው አንድ ዓመት ያሉት መረጃዎች በሙሉ የሚያሳዩት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በማፈን ለማዳከም ያሰበው ትግል ይበልጥ ተጠናክሮና ተቀጣጥሎ በርካታ አንዳርጋቸውዎችን ከማፍራቱም በላይ ብዙዎች ለነጻነታቸው መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን እስከመስጠት የሚያደርስ ዕልህ ውስጥ ገብተዋል። ወያኔ እንዳሰበውና እንዳሰላው ትግሉ መዳከም ሳይሆን መሬት እያያዘና እየተጠናከረ በመምጣቱ የወያኔ ስጋት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እየጨመረ ሄዷል። ይህም ሁኔታ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ሲያፍን ያሰላው ስሌት እጅጉኑ የተሳሳተ እንደነበረ በግልጽ አረጋግጧል። የወያኔ የአፈና ተስፋ ገና በአፈናው ማግስት እንደ ጧዋት ጤዛ ተኗል። ከአለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በመላው ሀገሪቷ ተጠናክሮ የምናያቸው የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎች የሚያመለክቱት ይህንኑ ስጋትና ጭንቀት ነው። የወያኔ የቅዥትና የስጋት የዛፍ ላይ እንቅልፍ፣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሮና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ንቅናቄያችን፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ለዕኩልነት ለፍትህና ነጻነት የሚደረግ ትግል፣ በተለይ እንደወያኔ ባለ ዘረኛ አምባገነን ቡድን በበላይነት በሚዘወር ሐገራዊ ሁኔታ ውስጥ፣ ምን ያህል ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አስቀድሞ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህም ሆኖ ግን ባለፈው አንድ ዓመት፣ የትግል ጓዳችን የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን መከራና ስቃይ እንዲሁም ይህ ሁኔታ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያስጀመረውን የጭንቀት ዘመን፣ ለአንድ ሴኮንድም ቢሆን መዘንጋት አይችልም።
ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በአፈናው የተነሳ የደረሰው መከራና ስቃይ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ለፍትህ ለዕኩልነትና ለነጻነት በመቆማቸው በወያኔ አረመኔዎች ቁም ስቅላቸውን የሚያዩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሰቆቃ የሚያበቃው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ በሚያደርገው ሁለ ገብ ትግል በመሆኑ ማንኛችንም በአቶ አንዳርጋቸውም ሆነ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንደራሳችን ጥቃት አድርገን የሚሰማን ወገኖች በሙሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከታፈኑበት አንድ አመት ወዲህ የተጀመረውን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አጠናክረን ወደ ውጤት ደረጃ በማድረስ መጭው ዘመን የሕዝብ የፍትህ የእኩልነትና የነጻነት ተስፋ የሚለመልምበት ፣ የወያኔ አምባገነን ሥርዓት እድሜ የሚያጥርበት ዘመን እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ንቅናቄያን ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ክብር ለፍትህ ለእኩልነትና ነጻነት መስዋትዕነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ታጋዮች!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም.

ሃይ ባይ ያጣው የአለም ህዝቦች ስጋት!


አለም ዝም ያለው, ታላላቅ ሀያላን ሀገራት ሁሉ ፀጥ ብለው ተመልካች የሁኑበት አረመኔያዊው እውነተኛው ትርኢት በጭራሽ አላባራም. እንዲያውም ብሶበታል. ሶሪያ ደበነች, ኢራቅን ፈጁት, ሊቢያ ን አናወዟት, ግብፆችን አረዱ, ኢትዮጵያዊንኑ ወንድሞቻችን ደገሙ. ኮሪያ, አሜሪካ, ኤርትራ ብቻ ያልነካኩት የለም ግን ዝም ተብለዋል. ሀይ ባይ አልተገኘም.
አንድ ቡድን አለምን ሲያስጨነቅ አለም መሪዎች ያጣች ይመስላል. ነገሩ ግራ የገባ ነው. ልምምዳቸው በሜዳ ነው.ይባስ ብለው ለዚሁ ሽብር ተግባር የሚጠቅሙ ህፃናት እያሳደጉ ነው. አልተሸሸጉም. ሆኖም ዝም ተብሏል.
ይሄው እያደገ የሚሄደው አረመኔያዊ አገዳደል መልኩን ከእርድ ቀይሯል. በደማሚት, በእሳት, በውሃ መድፈቅ ጀምሯል.ደአሽ ሰውን ሲገድል ብዙ ልቦችን እንደሚገድል ያውቃል. ከሚሞተው ሰው በላይ ቀሪውን የአለም ህዝብ ለማቃጠል, ሁሌ እያሰብን እየዘገነን እንድንኖር እያደረገ ነው. ሀይ ባይ እስከሌለ ድረስ ገና ይቀጥላል. ፈጣሪ የበላዩ ጌታ ሀይ ይበልልን እንጂ.
ይሄው የትናንቱ ደግሞ ከመቸውም ጊዜ የከፋ ነው. 16 ኢራቃዊያንን በሶስት በተለያየ አይነት መንገድ የገደሏቸው አገዳደል. ምክኒያታቸው የኢራቅ መንግስት ሰላይ ናችው የሚል ሰበብ ነው ያቀረቡት. ባይሆኑስ ይተዋቸው ነበር?
* የመጀመሪያ አራቱን ሰዎች እጅና እግራቸውን አስረው በአንድ መኪና ውስጥ አስገብተው ቆልፈው መኪናውን በመሳሪያ አጋዩት, እየተቀጣጠሉ ጩኸታቸው እየተሰማ ደበኑ.
* ሁለተኛዎችን በብረት የተሰራ አጥር መሳይ አራት መአዘን ቤት ውስጥ እንደ ውሻ እያሰሩ ካስገቧቸው በሗላ በሚዘገንን ሁኔታ በውሃ ውስጥ ለቀቁዋቸው.
* ሶስተኛውና በጣም ዘግናኙ ደግሞ ሁሉንም በተቀጣጣይ የደማሚት ሽቦ አንገታቸውን አስረው ጠላልፈው ለኮሱ, በጫጨቋቸው. እንደው በእነዚህ ሰዎች ላይ ሁሉም አለም ተቆጥቶ እንዲነሳ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ግራ ይገባል. ምንም አላስቀሩ ሁሉንም ወንጀል ደስ እያላቸው ፈፅመውታል. ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም አልተዘመተባቸውም.የኢራቅን የሳዳምን ሀያል ጦር የፈረካከሰው, የጋዳፊን ግዛት በአንዴ ያሽመደመደው የአለም የተባበሩቱ ጦር እንዴት ደአሽ አቃተው? ISIS ምነው ከበደው? ሁሌም ጥያቄ ይጭራል.
ሰላሙን ያብዛልን

Tuesday, June 23, 2015

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ

ከያሬድ ኃይለማርያም
ሰኔ 16፣ 2007 ዓ.ም.
ከብራስልስ

Yared
Yared
‘የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል’ አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡ በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ ፍትሕን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ድጋፍ ለተራበ ሕዝብ ስንዴና ዘይትን እንደመርዳት ቀላል አይደለም፡፡ እህል ተርፏቸው ወደ ባሕር የሚጨምሩ አገሮች የተራበ ሲያገኙ የተረፋቸውን መወርወራቸው አንድም እርዳታ በመስጠትና ለጋሽ በመሆን የሚገኝው የመንፈስ እርካታና በዋነኝነት ደግሞ የተጠኑ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትርፎችም አሉት፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ላለፉት አስርት አመታት በርካታ የአፍሪቃ አገራት፤ የኛዋ አገር ደግሞ በግናባር ቀደምነትነት የዚህ የእህልና የገንዘብ ድጎማ ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች፡፡ በዚህ የቁስ እርዳታ ማን እንዳተረፈ በጥልቅ መመርመር የግድ ይላል፡፡ በእርግጠኝነት ግን መናገር የሚቻለው አገርንና ሕዝብን ለውርደት የዳረገና ክፉ የታሪክ ጠባሳም መሆኑን ነው፡፡ ዘንድሮ ስንዴና ዘይት የሚላክለት ድሃ ሕዝብ ያለችውን ቅሪት እየሸጠ በርሃና ባሕር አቋርጦ በራሱ ጥረት “ምና አደከማችሁ እኔ እዛው እምጣለሁ” ብሎ ለጋሾቹ ደጃፍ ደርሷል፡፡ ለዚህም በየአመቱ ከኢትዮጰያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሱማሌ የሚሰደደው ሕዝብ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ የምዕራቡ አለም እርዳታውን በመርከብ ከማጓጓዝ ሳይድን አልቀረም፡፡ ስንዴ የሚጭኑ መርከቦች ሽብርን ለመዋጋት በሚል ሽፋን የጦር መሳሪያ በማጓጓዝ ስራ የተጠመዱ ይመስለኛል፡፡
ዛሬ ላይ የቻይና ቢዝነስ ተኮር ወረራ ያስደነበራቸው የምዕራቡ አለም አገራት የአፍሪቃን አንባገነኖች ከነ ወንጀሎቻቸውና ስንክሳራቸው ተቀበለው አብረው ለመዝለቅ የተገደዱበትና መለማመጥ የጀመሩበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ “ልማት” እና “ደህንነት” (security) ብቸኛዎቹ የምዕራቡና የአፍሪቃ አንባገነኖች የመወያያና የመደራደሪያ አጀንዳዎች ሆነዋል፡፡ ሰብአዊ መብቶች፣ ዲሞክራሲንና የሕግ የበላይነትን በዋነኝነት ያነሱ የነበሩት አውሮፓዊያን ሳይቀሩ እነዚህን አጀንዳዎች ወደጎን የገፉዋቸው መሆኑን በግልጽ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም በኢትዮጵያ የ2007 ምርጫ ዙሪያ ያሳዩት የዳር ተመልካችነት ሚና እና ከምርጫውም በኋላ የሰጡዋቸው መግለጫዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ሁሉን ነገር ወደ ጎን ተትው “ሰላም” በሚለው አጀንዳ ላይ ብቻ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ከ”ልማታዊው” አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥብቁ ቁርኝት አድሰው እንደሚቀጥሉ በግልጽ የሚያሳየውን የአጋርነት መግለጫቸውን አንብበናል፡፡
በአገዛዝ ሥርዓቱና በአለም አቀፉ ማኅበረሰብ መካከል፤ የአፍሪቃ ኅብረቱንም ጨምሮ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ቀደም ብሎ የተደረሰበት አንድ አይነት ስምምነት እንዳለ የሚያሳየው የምርጫ ቦርድና ገዢውን ቡድን ጨምሮ ሁሉም መፈክራቸው “ምርጫዉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል” የሚል ነበር:: ይህ መሪ መፈክር ተደጋግሞ በሁሉም ሚዲያዎችም እነቪኦኤን ጨምሮ እስክንደነቁር ድረስ ሲነገርን ቆይቷል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ ቅድመ ሥራ የተሰራበት ነገር ስለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም፡፡ አንደኛ ሰላም ባለበት አገር ልክ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ ዳመና እንዳንጃበበ ተደርጎ የተሰራው ዘገባ ሁሉ ሕዝቡ ስጋት ውስጥ እንዲገባና እንዲሸበር አድርጎታል፡፡ ይህ ተንኮል ያልገባውና ቀላል ግምት የማይሰጠው ሕዝብም ሊመጣ ይችላል ከተባለው አደጋ እንኳን ወያኔ አንዳች ኃይል ያለው ሰይጣንም ቢያስጥለው አይጠላም፡፡ ይህም ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነገር ነው፡፡ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ ፈጥሮ ሕዝብን ማስጨነቅና ማስሸበር የተፈለገበት ዋነኛ አላማም የገዢውን ኃይል ብቸኛ የሰላም አስከባሪ አካል አድርጎ ሕዝብ እንዲያየውና ወያኔ ከሌለ ያልቅልናል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል:: ይህ ደግሞ ከአመታት በፊት ቀድሞ የተወሰነና የምዕራቡንም አለም ቅቡልነት ያገኘውን የገዢውን ቡድን በስልጣን የመቆየት እቅድና ሕዝብ ባይዋጥለትም ሳያንገራግር እንዲቀበል ለማደረግ ቀላሉና ብቸኛው መንገድ ነበር፡፡ ስለሆነም “ነጻና ፍትሐዊነት” በምንም መልኩ የዚህ ምርጫ መሪ መፈክር አልነበሩም፡፡ ወያኔም ይህን ለማሟላት ዝግጁ አይደለም፡፡ ስለዚህ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ አደጋ እንዳንጃበበ አድርጎ የማቅረቡ ፋይዳ ለወያኔም ሆነ ለምዕራቡ አለም ብቸኛው የማደናገሪያ ካርድና የመውጫ ቀዳዳ ነበር፡፡
ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት እንኳን በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ሲጉላሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩና አልፎም በአንዳንድ ቦታዎች ሲገደሉ የበርካታ ሚዲያዎች፣ የአፍሪቃ ሕብረት ታዛቢዎችና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ አንድ አይነት ነጠላ ዜማ ነበር የሚያዜሙት፤ “የምርጫው ሂደት ሰላማዊ ነው፡፡ … በሰላምም ተጠናቋል፣ ወዘተ…”፡፡ ይህ ከላይ እንዳልኩት አንድም የአገዛዝ ሥርአቱን ብቃትና ጥንካሬ ለማጉላት ያለው ብቸኛ መንገድ ስለሆነ በሌላ መልኩም ቀድሞ የተዶለተበትንና አለም አቀፍ ቅቡልነት ያገኘውን በምርጫ ስም የአንባገነን ሥርዓቱን የአገዛዝ ዘመን የማደስ ስልት ለመሸፈን የተደረገ የትብብር ዘመቻ ነው፡፡
ምርጫ የዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሚረጋገጡባቸው መንገዶቹ አንዱ ነው፡፡ ልማት ደግሞ የአንድ አገር ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መበቶች በተሟላ መልኩ እንዲረጋገጡ የሚያስችል ሌላው መንገድ ነው፡፡ ልማትና ዲሞክራሲ ተጣጥመው በሚሄዱበት ስፍራ ሁሉ ማህበራዊ ፍትሕም ይሰፍናል፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምም ይኖራል፡፡ ለዚህም ነው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ በሁለት ማዕቀፍ የተቀመጡት መብትና ነጻነቶች፤ የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባሕላዊ መበቶች ሳይነጣጠሉ መተርጎምና መከብር እንዳለባቸው የተደነገገው:: ይሁንና ለድሃ አገራት ስንዴና ዘይት እየረዳ ስለ ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር ካንገት በላይም ቢሆን ይሟገት የነበረው የምዕራቡ አለም ‘ድሃ በል’ በሆነው የገበያ መርህና በግሎባላይዜሽን ስም የዝርፊያ ጋሪውን አስቀድሞ ዜማውን በመቀየር ከ”ልማታዊ” አንባገነኖች ጋር ተስማምቶ የእጃዙር ቅኝ ግዛት መረቡን አፍሪቃ ላይ ጥሏል፡፡ እኛንም ከገዢዎቻችሁ የተራረፈውን ቀምሳችሁ ማደር ከቻላችሁ ዲሞክራሲንና ሰብአዊ መብቶችን ቀስ ብላችሁ በመቶ አመት ሂደት ትቀዳጃላችሁና ተረጋጉ እያሉን ነው፡፡ ለጊዜው አለማችን እኛው በፈጠርናቸው ሽብርተኞች ተወጥራለችና እጃቸው ከመውደቋ በፊት እነሱን ለማጥፋት እንተባበር እያሉን ነው፡፡ እንግዲህ የሚበጀንን እንምረጥ::
በቸር እንሰንብት!
ያሬድ ኃይለማርያም

ኢህአዴግ የምክር ቤትና የክልል ወንበሮችን ሙሉ ለሙሉ አሸነፍኩ አለ

ኢህአዴግ የምክር ቤትና የክልል ወንበሮችን ሙሉ ለሙሉ አሸነፍኩ አለ
ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት ወር በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በተቃዋሚ ስር የነበረን አንድ ወንበር መልሶ በመውስድ ሁሉንም የፓርላማ ወንበሮች በብቸኝነት ማሸነፍ መቻሉን ትናንት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ከዚህ በፊት በፓርላማ አንድ የተቃዋሚ እንዲሁም አንድ የግል ተወዳዳሪ ወንበሮችን ማግኘት ችለው የነበረ ሲሆን በዘንድሮው ምርጫ ኢህአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ መቶ በመቶ ማሸነፉን ይፋ አድርጓል።
የምርጫ ቦርድ ሰኞ ምሽት ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረትም ኢህአዴግ 500 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችን ሲያሸንፍ የፓርቲው አጋር ድርጅቶች ደግሞ 46 ወንበሮችን እንዳሸነፉ የቦርዱ ሀላፊዎች አስታውቋል።
በደቡብ ክልል በቦንጋ ጋዋት የተካሄደው ምርጫ ውጤት በቦርዱ ባለመጽደቁ ውጤቱ አለመካተቱን የቦርዱ ዋና ጸሀፊ ፐሮፌሰር መርጋ በቃና ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
በግንቦቱ መርጫ ከተመዘገበው 36 ሚሊዮን ህዝብ ከ 33 ሚሊዮን የሚበልጥ ድምጽ መሰጠቱን የቦርዱ ሀላፊ ፐሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግረዋል።
ለክልል ምክር ቤቶች በተካሄደው በዚሁ ምርጫ ገዢው ኢህአዴግ 1 ሺ 984 ማሸነፍ እንደቻለና በቦንጋ የሶስት ብቻ ወንበሮች ውጤት አለመታወቁን ብሉምበርግ የዜና ወኪል ዘግቧል።
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የምክር ቤትና የክልል ወንበሮችን በብቸኝነት ሙሉ ለሙሉ በማሸነፍ የተለመደ ድሉን ይፋ ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን በርካታ መገናኛ ብዙሀን በመዘገብ ላይ ናቸው ።
ምርጫውን በብቸኝነት የታዘበው የ አፍሪካ ህብረት ከታዘባቸው ከ300 በላይ ጣቢያዎች 21 በመቶ ኮሮጆዎች ባዶ ስለመሆናቸው ሊያረጋግጥ የነበረው እንቅስቃሴ በሀላፊዎች ክልከላ እንደተደረገበት መግለጹ ይታወሳል።
አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በበኩላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች የድምጽ አሰጣጡን ሂደት እንዳይታዘቡ መደረጉና በጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው ወከባ በምርጫው ሒደት ላይ ተጽእኖን አሳድሯል ሲሉ ስጋታቸወን መግለጻቸውን የታወሳል።

የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ * ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ


ማለዳ ወግ …የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ …
እንደ ሮመዳኑ መረጃ ግብአት …
* ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ
* “የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ናስር አል ቁሰቢ
ነቢዩ ሲራክ
ታዋቂው የሳውዲ የቴሌቪዥን ኮሜዲ ድራማ ተዋናይ ናስር አል ቁሰቢ በያዝነው ሮመዳን ባቀረበው አንድ አስተማሪ ኮሜዲ ከጽፈኛው የአይ ሲ አይ ኤስ ISIS ወይም ዳአሽ አሸባሪ ቡድን አባላትና ከደጋፊዎች ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረበት አስታውቋል ።
መቀመጫውን ዱባይ እንዳደረገ የሚነገረው ሳውዲው ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ በዘንድሮ ሮመዳን ባዘጋጀው ተከታታይ ” ሰለፊ ” በተባለ ፕሮግራም ላይ አሸባሪ ቡድኑን አስመልክቶ ባቀረበው ዝግጅት ነው ። በዚህ የሮመዳን የመጀመሪያ ሳምንት ዝግጅት ላይ ሶርያ ውስጥ የአሸባሪ ቡድን ጋር ያለውን ልጁን ለመፈለግ ወደ ሶርያ ያቀናውን አባት እስመልክቶ ያቀረበው አጭር ድራማ ነው። እንደ ቀልድ በተላለፈው እጅግ ተጽዕኖ መፍጠር መቻሉ የተሰደሰው ዝግጅት ሲጀምር ልጁን ሊፈልግ የሄደ አባት ወደ የአሸባሪዎችን መቀላቀሉንና በአሸባሪው ቡድን ውስጥ የሚካሔዱትን መረን የለቀቁ ሰብአዊ መብት ረገጣዎች ፣ የአሸባሪዎችን ጨካኔ በተገቢ መንገድ ያሳያል። ዝግጅቱ ሲጠናቀቅም አባት ልጁን ለመቅላት ስለት በአንገቱ ላይ በጭካኔ ቦታ መርጦ ሲያሳርፍና ልጅ አንገቱን ሰጥቶ የአሁን አራጅ አባቱ በልጅነት በፍቅር ያሳደገበትን ሁኔታ ከጎን በምናብ ጨረፍታ ያሳያል …
ስሜትን ፈንቅሎ መልዕክት በሚያስተላልፍ መንገድ ፣Saudi-Arabia
በቀልድ በታጀበው የናስር ዝግጅት አዲስ ነገር ባይቀርብም አለም ያወቀው እውነት የሮመዳን ታዳሚ ደጋግሞ ያጤነው ዘንድ ያመላከተ እንደነበር በመዘገብ ላይ ነው። ናስር በዚህ ዝግጅት የአሸባሪውን ISIS ቡድንን ልክ ያለፈ ጭካኔና ርክሰት የማይጨበጥ ጥልቅ የኪነ ጥበብ ውጤቱ አሳይ ቶበታል ። ለዚህ ድንቅ ተጽዕኖ ፈጣሪበለተባለ ስራው ክብርና ዝናን በአድናቂዎቹ ሲያሰጠው ፣ በጽንፈኛ ቡድን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስከትሎበታል !
ትወናውን በመሪነት አሳምሮና እያዋዛ በማቅረቡ የሚታወቀው ኮሜዲ ናስር በዘንድሮው የ”ሰለፊ ” ድንቅ ዝግጅት ጅማሬ ባቀረበው ISIS የተመለከተ ዝግጀት የግድያ ዛቻ ከላኩለት መካከል Julaybib Al-Jazrawi ከተባለ ሰው የደረሰው መካከል ” ፈጣሪ ምስክሬ ነው እኛ ሙጃህዲኖች ያንተን ጭንቅላት ከቀረው ገላህ ቀልተን ካልለያየን እረፍት አናገኝም ! … ” የሚል ከበድ ያለ ዛቻ ይገኝበታል !
የተሰነዘረበትን ሰሞነኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስመልክቶ ሲናገር ” የመጀመሪያውን ክፍል ከለቀቅኩ ጀምሮ በበርካታ ማስጠንቀቂያና ስድቦች የተሞሉ መልዕክቶች አጥለቅልቀ ውኛል ፣ ለሁሉም ተረጋጉ በማለት ረመዳን ከሪም የሚል ምላሽ ነው የሰጠኋቸው ” ብሎ በማሟረት በቲዊተር መልስ መስጠቱ ተጠቅሷል ! ታዋቂው ሳውዲ ኮሜዲ ይህን ምላሽ ከሰጠ በኋላ ዛቻ ማስፈራሪያውን በሚመለከ ት የአረብ መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰሞነኛ የሮመዳን መነጋገሪያ አርዕስት አድርገውታል ። ጉዳዩ በስፋት መሰራጩቱን ተከትሎ አርቲስት ናስር ከመገናኛ ብዙሀን በኩል ዛቻ ማስፈራሪያው ያሰጋው እንደሁ ተጠይቆ ሲመልስ ” የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ሲል እንቅጩን መመለሱ ተዘግቧል ! ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሜዲ ናስር ISIS አስመልክቶ ያስተላለፈው አጭር ዝግጅት ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ተሞካሽቷል ። አሸባሪውን ቡድን እርቃኑን የሚያወጣ እጥር ምጥን ያለ ዝግጅት ነው በሚልም ደስታቸውን የሚገልጹ ቁጥርም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቁሟል !
አርቲስት ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ ሮመዳን በመጣ ቁጥር ከሳውዲ አልፎ በመላ አለም የሚገኙ አረብ ተናጋሪ የቴሌቪዠን ተከራታታዮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል ። ” ጣሽ ማጣሽ ” ተብሎ በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ከጓደኛው አብደላ ሰርሃን ጋር ሮመዳን ተጀምሮ እስኪያልቅ በሚያቀርባቸው ልዩ ልዩ አጫጭር አስተማሪ ዝግጅቶች ዝነኝነትን ያተረፈ ኮሜዲ ነው ። ናስርና አብሮት ሲሰራ ባላቸው ውህደት አድናቆትን ያተረፈው ባልንጀራው አብደላ ድንበራቸው የማይደፈር የሳውዲ የሀይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት የሚታዩትን ችግሮች እየነቀሱ በማቅረቡ ተወዳጅነት አትርፈው ነበር ። ይህም ሲሆን ባልተለመደ መንገድ ለሮመዳን በሚቀርቡት ዝግጅቶች ዙሪያ በሳውዲ መንግስት ብቸኛ ፈቃድ ያለው ዝግጅት “ጣሽ ማጣሽ ” እንደ ነበር በስፋት ይታመናል !
የኮሜዲ ናስርና አብደላ ” ጣሽ ማጣሽ ” ካሳለፍናቸው ሁለት አመታት ወዲህ በባልንጀሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተወዳጁ ዝግጅት ሊቀጥል አልቻለም ። “ጣሽ ማጣሽ” የተባለው ዝነኛ በሮመዳን ዝግጅት በውስጥ ዝብሪት ከተዘጋ በኋላም ሳውዲው ኮሜዲ ናስር በ”አረብ ጎት ታለንት ” ዳኝነት ፈገግ በሚያሰኘው አስተያየቱ አፍቃሪዎቹን ሲያዝናና መክረሙ ይጠቀሳል !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓም

እነ ወይንሸት ሞላ ከእስር እንደተለቀቁ ታፈነው ታሰሩ

 
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 16/2007 ከእስር ተፈትተው ሲወጡ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍነው ታስረዋል፡፡
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩት ኤርሚያስ ፀጋዬና ዳንኤል ተስፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ጠብቀው ያፈኗቸው ሲሆን ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ወይንሸት ሞላንና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አፍነው መልሰው እንዳሰሯቸው ታውቋል፡፡
የቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር ፈርዶ፤ ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኖ ነበር፡፡ ኤርሚያስ ፀጋዬንም በነፃ እንዲለቀቅ ወስኖለት ነበር፡፡ ይሁንና ፖሊስና ደህንነቶች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ አፍነው እንደገና አስረዋቸዋል፡፡

Monday, June 22, 2015

ዛሬ ቤተ እስራኤላዊያን ሰላማዊ ስልፍ በቴል አቪብ ያደርጋሉ

ዛሬ ቤተ እስራኤላዊያን ሰላማዊ ስልፍ  በቴል አቪብ ያደርጋሉ
ምክንያቱም ባለፍው ቤተ እስራኤላዊ በፖሊስ ተመቶ ነበር ፖሊሱ እስር ቤት መግባት አለበት ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ መጀመሪያ የተማታው ቤተ እስራኤላዊ ነው ፖሊሱ አይድለም የሚል ነበር
ይህን ያስቆጣቸው ቤተ እስራኤላዊያን ዝም ብለው አልተመለከቱም በዛሬው እለት በአደባባይ ይወጣሉ 
አንድ ፍክራ አላቸው ይህም
አንድ ሰው ለሁሉም ነው
ሁሉም ለአንድ ሰው ነው የሚል ነው
የእኛን አንድ ሰው ነካችሁ ማለት ሁላችን ነካችሁ ነው የሚል ነው
በእውነት ሲታይ እንደዚህ አይነት አንድነት ታይቶ አይታወቅም አንድ ሰው ስለተነካ ሁሉም ለእኔ ብለው የሚወስዱት አንድነት
ፖሊሱ ፍርድ ቤት አይቀርብም እንደተባለ የእስራኤል መንግስት የቤተ እስራኤላዊያንን አንድ ነገር አላቸው
ኑ በንግግር እንፍታው እንደራደር ሰላማዊ ስልፍ አትውጡ
ከቤተ እስራኤላዊያን ለእስራኤል መንግስት የተሰጠው መልስ
የሸቀጥ ዕቃ ነው ለድርድር የሚቀርብ የእኛ ወገን የሸቀጥ ዕቃ አይድለም ምንም ንግግር አያስፈልግም የሚል ነው ፖሊስ በተጠንቀቅ ይገኛል
የዛሬውን ሰላማዊ ስልፍ ልዩ የሚያደርገው
የሀይማኖት አባቶች አንድነት ፈጥርው መገኝታቸው
የእስራኤል ጋዜጠኞች ወደ ቤተ እስራኤላዊያን መሆናቸው ብዙ ነጮች አብርው መሳተፋቸው ነው
ቤተ እስራኤላዊያን በእስራኤል ብዙ የተባሉት 190,000 ቢሆኑ ነው በጣም የሚያስደንቀው ግን አንድነት መፍጠራቸውና እስራኤልን የመሰለች ከባድ ሀገር ማስጨነቃቸው ነው
ከእነሱ ብዙ መማር ይቻላል
ይመቻችሁ ብያለሁ ጌቱ

Sunday, June 21, 2015

የአራት ኪሎ isis .ናይሮቢ ንፁሀንን ሊያውክ ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም በስደተኛው ትብብር እየተጋለጠ ነው
ህውሀት ኢህአዲግ ኬንያ ለስለላ ያሰማራቸው ግለሰቦች በስደተኛው ክትትል በመያዝ ላይ ቢገኝም የኢትዮጵያ ኤንባሲ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በላይ በመክፈልና ከኬንያ ፖሊስ ለኢትዮጵያ ኤንባሲ የሚሰሩ እንዳሉና ዳጎስ ያለ ክፍያ እንደሚያገኙ በዚህም የተነሳ ከእስር ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስት እራሱ ያሰማራቸውን አስወጥቶ በኤንባሲ ትእዛዝ ንፁሀንን ስደተኞች ቢያሳስርም በአካባቢ ያለ ስደተኛ ግን ሁሉም ዛሬ በጠዋት ወደ ፖሊስ ጣቢያው በማማምራት ወይ እኛን እሰሩን ወይ ፍቱልን በማለት በኤንባሲ ትዕዛዝ የታሰሩትን ንፁሀን ስደተኞች ወደ ሀገር ለመመለስ ጥረት ቢያረግም በስደተኛው አንድ መሆን ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ የታሰሩትን ሶስት ግለሰቦች አስፈቶታል ይህ በእንዴ እንዳለ ታስረው የነበሩ የህውሀት ኢህአዲግ የደህንነት ቡድን ተፈተው ከአካባቢ መሰወራቸወን የኮሜቴው አባላት ገልፀውልናል በተመሳሳይ በአሁኑ ሰአት በእነዚህ ደህንነቶች እጅ በርከት ያለ የስደተኛ ፎቶ ግራፍና የስደተኛ ስም ዝርዝር በእጃቸው ላይ መገኘቱን በማየት ማረጋገጥ ችለናል
በስተመጨረሻ በኬንያ ላይ በተለያየ ግዜ ታፍነው የተወሰዱ ንፁሀን ዜጎች የደረሱበት እንደማይታወቅና በስውር የተወሰዱ መገደላቸውን መረጃወች ያሳያሉ የስደተኛውን ትብብር በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግን ማለፍ አልፈልግም ሁሉም አንድ ሆነው በአንድ ድምፅ በመጮሀቸው ከጅብ ላይ ስጋ አስጥለዋል ወገንን አትርፈዋል
አንድነት ሀይል ነው ይበል ያስብላል




L

Saturday, June 20, 2015

በደቡብ ኢትዮጵያ የመድረክ አባል ተደብድበው መገደላቸውን ተገለፀ


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በደቡብ ክልል አንድ የምርጫ አስተባባሪው አርብለት ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲም በምርጫ 2007 ዙሪያ የዛሬውን ጨምሮ 4 አባላቱና ደጋፊዎቹ መገደላቸውን አስታውቋል።
በዚህ ሳምንት እንደተገደሉ ተቃዋሚዎች ከገለጿቸው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው አጠቃላይ ቁጥር ስድስት ደርሷል።
በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የተገደሉት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ በትናንትናውለት በሁለት ፖሊስ ባልደረቦች ከመኖሪያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ተደብድበው ህይወታቸው አልፎ ወንዝ ዳር መገኘታቸውን የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ምርጫ 2005 በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ወደ 46ሽህ የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ይገልጻሉ። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሂደቱ በወከባ እስራትና አልፎ አልፎ ግድያዎች የታዩበት ነው በሚል፤ ሂደቱንና ውጤቱን አንቀበለም በማለት መግለጫዎች አውጥተዋል።

ባህርዳር ስራ አጥ ምሩቃን በህወሃት ደህንነቶች ታፍነው እየተወሰዱ ነው


በባህርዳር ከተማ ትምህርታቸው ጨርሰው መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ወጣቶች ቦዞኔ እየተባሉ በጸጥታ አካላት ተገፈው ቤሻንጉል ወደሚገኘው የመንግስት እርሻ እንዲሰሩ መወሰዳቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ስራ ያላገኙት ወጣቶች እለታዊ ንሮአቸውን ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ስለተገኙ ብቻ በስርዓቱ ካድሬዎችና የፀጥታ ሃይሎች ቦዞኔ ተብለው እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ ምንም ዓይነት የምግብና የህክምና አቅርቦት ወዳልተዘጋጀለትና ቤንሻንጉል ውስጥ ወደ ሚገኘው የመንግስት የጥጥ እርሻ ተወስደው በግድ እንዲሰሩ መደረጉን ተገለፀ።
እነዚህ በግድ ተገፈው የተወሰዱት ወጣቶች መጀመርያውኑ ወደ ቦታው ሲሄዱ ስላልተቀበሉትና የሰሩትን ያህል በቂ ዋጋ ስለማይከፈላቸው ተማርረው ከካምብ እየሸሹ ወደ ጎረቤት አገሮች እየጠፉ ለመሄድ ሲሞክሩ በተለያየ መንገድ አደጋ እየደረሰባቸውና ህይወታቸው እያጡ መሆነቸውን ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማስከተል ከእርሻው ቦታ ጠፍተው ወደ ባህርዳር የተመለሱት አንዳንድ ግለሰዎች የመንግስት ንብረት ሰርቀው ነው የመጡት በሚል የሃሰት ውንጀላ ቢንያም ወርቁ፤ ፋንታሁን ይርሳው፤ ሙሉነህ ጥላሁን፤ ሙሉጌታ ታፈሰና ሌሎች ንፁሃን ወገኖች በፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።

የወያኔ መከላከያ ሰራዊት መካከል አለመግባባቱ ተባብሶ ቀጥላል


Shagiz Shagi's photo.
በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት ያልተፈለጉትን ለማሰናበት ተብሎ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ወታደሮች አገልግሎታችን ግዜ ያበቃ በመሆኑ መሰናበት አለብን በማለታቸው የተነሳ ስብሰባው እንደተቋረጠ ታወቀ።
ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት- በሰሜን እዝ በክፈለ ጦሩ አዛዦች ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለና ብርጋዴር ጀነራል ማዓሾ በየነ የተመራው ስብሰባ ግንቦት 21 2007 ዓ/ም የተካሄደ ሲሆን። እንደ አጀንዳ ያቀረቡት ደግሞ ከአስርና ከስባት አመት በላይ ካገለገሉት መካከል የተወሰኑትን ለማሰናበት በሚል ቢነጋገሩም ብዛት ያላቸው የሰራዊቱ አባላት ግን ከተባለው የአገልግሎት እድሜ በላይ ያገለገሉ ስለሆኑና። ላቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም“ ግዳጃችን ስለፈፀምን የሚገባንን ሰጥታችሁ ሸኙን” በሚል በአንድ ድምፅ ስለተቃወሙ ስብሰባውን እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማከል እንዳስረዳው- በአገልግሎት ስም የተወሰኑት ልንሸኝ ነው የሚለውን ሃሳብ እንደ ሽፋን እንጂ ዋናው አላማው ግን በወታደሩ ውስጥ በተካሄደው የግንቦት 16/ 2007ዓ/ም ምርጫ በረከት ያለ ድምፅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰጥቶ በመገኘቱ የተነሳ ይህ ደግሞ ለሰራዊቱ አዛዦች የራስ ምታት ስለሆነባቸው በምርጫ ጊዜ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መርጠው ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉት ወታደሮች ለመቀነስ የታለመ ሴራ ቢሆንም ነገር ግን ሳያስቡት ግርግር በመከሰቱ አጀንዳውን እንዳስቆሙት መረጃው ጨምሮ አስረድታል

Thursday, June 18, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 – ለሰማዕታቱ አደራ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው?


Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyኢትዮጵያ አንድ ተጨማሪ ወጣት ልጇን አጣች። ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም ማታ የደብረ ማርቆሱ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ኢሰብዓዊ በሆነ ድብደባ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ በጽናት ታግሏል። ለኢትዮጵያ ይበጃል ብሎ ባመነበት መንገድ ተጉዞ ለትግሉ ሕይወቱን ሰጥቷል። ሳሙኤል በሕይወቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በትክክል ያውቅ ነበር፤ ለህልፈት የዳረገው አደጋ በመድረሱ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሰውበታል፤ ሆኖም ግን ግንባሩን አላጠፈም። በሕይወቱ ላይ ያንዣንበበውን አደጋ ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ በመገመቱ “ከታሠሩኩም ህሊናዬ አይታሰርም፤ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ። በተለይ የኔ ትውልድ አደራ!”የሚል ኗሪውን እረፍት የሚነሳ ተማጽኖ በጽሁፍ አስቀምጦ የመጨረሻውን ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። ለዚህ የሙት አደራ ምላሻችን ምንድነው?
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በወጣት ሳሙኤል አወቀ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ይመኛል።
ዛሬን እየኖርን ያለነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከሀቅ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠናል። እንዴት ነው የሳሙኤል አወቀ እና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት አደራ መወጣት የምንችለው? እንዴት ነው ይህንን የህወሓት ፋሽስታዊ ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነበት፤ የአገር አንድነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መገንባት የምንችለው? እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለዚህ ትግል የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ማንን ነው የምንጠብቀው?
አርበኞች ግንቦት 7 መፍትሔው ሁለገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። ሁለገብ ትግል ደግሞ ሕዝባዊ አመጽንና ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አቀናጅቶና አስማምቶ ማራመድን ይጠይቃል። በሁለገብ ትግል እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ የሚያበረክተው ነገር አለ። ሁለገብ ትግልን የሆነ አካል የሆነ ቦታ እስኪጀምረው መጠበቅ አይገባም፤ እያንዳንዳንችን እንደሁኔታው በየአካባቢያችን ልንጀምረው የምንችለው የትግል ስትራቴጄ ነው። ሁለገብ ትግል በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት “እኔም ኃላፊነት አለብኝ” እንድንል የሚያደርግ አሳታፊ የሆነ የትግል ስትራቴጂ ነው። ሁለገብ ትግል ጥቂቶችን ሳይሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚያሳትፍ ሕዝባዊ ትግል ነው።
በየጊዜው በህወሓት ፋሽስቶች ለሚደርስብን በደል ምላሽ መስጠት የሚኖርብን በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት ለአምባገነን አገዛዝ ያለን ጥላቻ ስንገልጽ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከራሱ ይጀምር፤ ለህወሓት አምባገነን አገዛዝ ላለመንበርከክ ቃል ይግባ፤ ከሚመስለው ጋር ይቧደን፤ የትግሉን አቅም ይገንባ፤ በአቅሙ መጠን አምባገነኑን ሥርዓት ይገዳደር። ትግሉ እሆነ ቦታ እስኪጀመር መጠበቁን ትተን በሁሉም ከተሞችና በሁሉም የገጠር መንደሮች በአቅማችን መጠን ትግሉን እናፋፍም። እያንዳንችን ለነፃነታችን ኃላፊነት አለብን። የሰማዕታት አደራ የእያንዳንዳችን አዕምሮ እረፍት ሊነሳ ይገባል። ይህንን ስናደርግ ነው ለሰማዕታቱ አደራ ምላሽ ሰጠን ማለት የምንችለው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ሰበር ዜና ለቀስተኞቹ ታገቱ


የሳሙኤል አወቀ ስርዓተ ቀብር ላይ ደርሰው ወደ ደብረማርቆስ ሲመለሱ የነበሩት ለቀስተኞች ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ወደ ደብረማርቆስ እንዳይመለሱ መታገታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለቀስተኞቹ በመኪና እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ከቢቸና ወደ ደብረማርቆስ 80 ኪሎሜትር አካባቢ የምትገኝ የትመን የተባለች ቦታ ላይ ፖሊሶች ያስቆሟቸው ሲሆን ‹‹በዚህ ሰዓት መንቀሳቀስ አትችሉም›› በሚል የሾፌሩን መንጃ ፈቃድ ከቀሙ በኋላ ለሚሊሻ አስረክበዋቸው ሄደዋል፡፡ ለቀስተኞቹ የታገቱበት ቦታ ከመኖሪያ አካባቢ የራቀና ጫካ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ለቀስተኞቹ አሁንም ድረስ በበርካታ የሚሊሻ አባላት ተከበው ይገኛሉ፡፡

በሽብርተኝነት የተከሰሱ የአየር ኃይል አባላት ነገ ፍ/ቤት ይቀርባሉ


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣
1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡
በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Wednesday, June 17, 2015

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!


አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡
ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡
በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡
እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!
ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡
ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .
ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Michael Aboye's photo.Michael Aboye's photo.

በኬንያ ስደተኞችን ይሰልሉ ነበር የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ


ባሳለፍነው እሁድ ናይሮቢ ኢስሊ የተበለ ቦታ የከተሙ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰማራቸው ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡
በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ግለሰቦቹን በተመለከተ ሲያቀርቡት የነበረው ጥቆማ በመጨረሻ ሰሚ ጆሮ በማግኘቱ የኬንያ የጸረ ሽብር ግበረ ሀይል ግለሰቦቹን ከያሉበት ለቃቅሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ስደተኞቹን አስደስቷል፡፡ታሳሪዎቹ በቀጣዩቹ ቀናቶች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የሚጠበቅ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት በኢምባሲው አማካኝነት ከፖሊስ ሐላፊዎች ጋር ግኑኝነት መጀመሩ የፍርድ ሂደቱን እንዳያስተጓጉለው ብዙዎች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት ከኬንያ ተጠርንፈው ወደ አገር ቤት የተወሰዱ ሰዎችን የተመለከተ ሪፖርት ለመንግስት ያቀርቡ እንደነበርም ለመረጃው ቅርበት ያለቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡
በመጪዎቹ ቀናቶችም ጉዳዩን የተመለከተ ዘርዘር ያለ መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡

ጴትሮስ አሸናፊ
በቅዱስ መጽሐፍ በአለማችን ረጅሙን እድሜ ማቱሳላ( 969 ዓመት )መኖሩን አንብበናል። (ዘፍ 5፣27) ከዚያም ለጥፋት ውሃ ምክንያት በሆነው የሰው ኃጢአት ምክንያት 120 መድረሱን ብናነብም ይስሐቅ 180 ዓመት መኖር ችሏል። ከዚያም ወርዶ 70 ከበዛም 80 ዓመት ሲሆን ይህንን ካለፈ ትርፉ ድካምና መከራ እንደሆነ ነግሮናል።
«የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና» መዝ 90፣10
ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የጆሀንስበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወንጀለኛ ላይ ያሳለፈበት የ1535 አመት የእስር ውሳኔ ፍርድ የሚያስገርምና የሰው ልጅ እድሜ ቢበዛ ስንት ሆኖ ነው ይሄን ያህል አመት የተፈረደበት የሚል ጥያቄ የሚጭር ነው።
አልበርት ሞራኬ ይባላል ። የ35 አመት ጎልማሳ ነው። በምስራቃዊ ጆሃንስበርግ አይቮሪ ፓርክ ነዋሪ ነው።
በ175 የተለያዩ የወንጀል ክሶች ፍርድ ቤት ቀርቦ በ144 ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሏል ።
የተከሰሰባቸውን ወንጀሎች የተመለከትን እንደሆነ
* 30 የአስገድዶ መድፈር
* 41 የአፈና
* 24 የዘረፋና ሌሎች ተደራራቢ
* 3 የዘረፋ ሙከራ
* 1 የመግደል ሙከራ
እንዲሁም የጦር መሣሪያ ያለፈቃድ መያዝና ሌሎችም ወንጀሎች ናቸው ።
የጆሀንስበርግ ችሎት ያሳለፈበት የ1535 አመታት እስራት ሲተነትን እንደሚከተለው ይሆናል:
* በተደጋጋሚ ለመፈፀማቸው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ30 አመት ፅኑ እስራት፣
* በዘረፋ ወንጀል በቀረቡበት ክሶች በያንዳንዱ 15 አመት እስራት፣
* በመግደል ሙከራ 10 አመት እስራት፣
* በአፈና በቀረቡበት ክሶች በያንዳንዱ 5 አመት እስራት፣
* በሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በመያዝ 5 አመት እስራት
ጎልማሳው አልበርት ሞራኬ በተከሰሰባቸው 175 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሎ የተከራከረ ቢሆንም በአስገድዶ መድፈር ከቀረቡበት 30 ክሶች ብቻ በ29 ጥፋተኛ ሆኖ ከመገኘቱም በተጨማሪ በአጠቃላይ በ144 ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆኑን የመሐል ዳኛው ሪያን ስትሪደም ይናገራሉ ።
ከአስገድዶ መድፈር ሰለባዎቹ አንዷ ኪቤትስዌ ማዋሻ ላለፉት 2 አመታት የልደት ቀኗን እየጠበቀ 2 ጊዜ እንደደፈራትና ልደቷን ማክበር እንዳልቻለች ተናግራ አሁን ግን አልበርት ሞራኬ በመታሰሩ የፊታችን ሜይ 7ቀን 29ኛ አመት ልደቴን በሰላም አከብራለሁ ብላለች ( ሌላ እንዳያጋጥማቸው እየፀለይን) ።
ችሎቱን የመሩት ዳኛ ሪያን ስትሪደም ስለ ሞራኬ ሲናገሩ
“ሞራኬ በፈፀማቸው ወንጀሎች የማይፀፀት ከመሆኑም በላይ አንድም ወንጀል እንዳልፈፀመ አስረግጦ ሲናገር እንኳ ሃፍረት አይሰማውም ከዚያም አልፎ የአስገድዶ መደፈር ሰለባዎቹን ለወደፊቱ ራሳቸውን እንዴት ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ ለመምከር ይሞክራል ” ይላሉ።
የሞራኬ የ1535 አመት እስር በደቡብ አፍሪካ ክብረወሰን ነው ወይ ቢባል በፋፁም አይደለም። እኤአ በ2007 ዓ/ም ሞንጌዚ ጂንዜላ የተባለ የ39 አመት ጎልማሳም በ60 የአስገድዶ መድፈርና ተያያዥ ወንጀሎች ተከሶ የ55 አመት ፅኑ እስራትን ጨምሮ የ2461 አመት እስር ተፈርዶበታል።
እኤአ በ2013 ዓ/ም ምሉንጊሳ ምሻሊ የተባለ ሌላ ወንጀለኛ ደግሞ በ39 አስገድዶ መድፈር ክስ የ39 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል ።(አላነሰችም? )
ሞራኬ አሁን የ35 አመት ጎልማሳ ሲሆን የ1535 አመት እስሩን ሲጨርስ የ1570 አመት አዛውንት ይሆናል ማለት ነው። የሞራኬ የሙያ አጋር የ39 አመቱ ሞንጌዚ ጂንዜላ ደግሞ የ2461 አመት እስሩን ሲጨርስ የ2500 አመት የእድሜ ባለጸጋ ይሆናል ማለት ነው። ከሁለት ሚሊኒየም በላይ።
…………………………………….
ፎቶው የ35 አመቱ ሞራኬ ነው
ጴትሮስ አሸናፊ

አንድ የፌደራል ፖሊስ 3 ባልደረቦቹንና አንድ ቻይናዊ ገደለ

                         
የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ
በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል::
የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት እየገቡ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው።
ፖሊሶቹ ለሰበተ-ሚኤሶ ባቡር ስራ ቻይናዎችን እንዲጠብቁ የተመደቡ ናቸው። ቻይናዊው ሰራተኛና ሶስቱ ፖሊሶች ህዝቡን በተለይም የቀን ሰራተኞችን ያለ ክፍያ የሚያሰሩ እንዲሁም ለባቡሩ ካሳ ያልተከፈለበት እርሻን አስገድደዉ መንገድ እንዲሰራ እንደሚያደርጉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገዳዩ ፖሊስ ድርጊቱን ሲቃወም በመቆየቱ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ መሆኑንና ያለመያዙም ሚስጢር ከህዝብ መጠለያ በማግኘቱ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ድርጊቱ ከተፈጸመ በሁዋላ የባቡር ስራው መቆሙን ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት ቻይናውያን ሰራተኞች ስለሚፈጽሙት በደል ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ሲደርሱት ቆይቷል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። የቻይናዊውን ግድያ በተመለከተም መንግስት እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።            

Tuesday, June 16, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊ ሳሙኤል አወቀ በወያኔ ጭፍሮች ተገደለ

                                                     
የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡
ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡
ሳሙኤል አወቀ እስር፣ ድብደባ፣ ዛቻ እየተደረገበት ወደኋላ ሳይል ሲታገል የቆየ ወጣት ነው፡፡ በርካታ ምሁራን ቤታቸው ቁጭ ባሉበት ይህ ወጣት በድፍረት የምስኪኑን አርሶ አደር ስቃይ በየቀኑ ለሚዲያ ሲያጋልጥ ቆይቷል፡፡ ለዚህ ሁሉ ግን በቀል ተፈፅሞበታል፡፡ ለነገዋ ኢትዮጵያ፣ ለነፃነት ያለመው ወጣት በትናንትናው ዕለት ተገድሎ ተገኝቷል፡፡ ይህ ወጣት ከቀናት በፊት ይህን ፅፎ ነበር፡፡
የገዥዎቻችን የሥራና የመግባቢያ ቋንቋ
ሳሙኤል አወቀ
ሀገሬ፣ ታሪክ፣ ሐይማኖት፣ ባሕልና ሸማግሌዎች አሏት፡፡ ነገር ግን ምነው ትንፍሽ የሚል ጠፋ? በየቀበሌው ጠያቂ የሌለው ጥቃቅን ንጉስ ነግሶብናል:: በደል እና ግፍ ራሳቸው እየፈፀሙ ለራሳቸው እንድንሰግድ የሚያደርግሥርዓት ተበጅቷል:: የቀበሌ ካድሬ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንኳን አይገዛውም:: አላምንበትም አልተማከርሁበትም ይላል:: ወደየት ይደረሳል? ለማንስ ይነገራል? ከተመደበለት የቀበሌ ኮሚኒቲ ፖሊስ ጋር አብሮ ያስራል፡፡ ይገርፋል፡፡ ይደበድባል፡፡ ሲፈልግ የሀሠት ምሰክር አደራጅቶ እሰር ቤት ያሰወረውራል፡፡ የህዝብ ሮሮ ለነሱ ሙዚቃ ሆኗል፡፡ ሀይ ባይ፣ ገላጋይ፣ ገሳጭ አሥታራቂ ሽማግሌዎች እና የኃይማኖት መሪዎች በዓለማዊ ሕይወት ሕዝባቸውን ረስተዋል፡፡
ማተቤ፣ ኃይማኖቴና ክብሬ ያሉ በአውሬ ተግባር ግፍ ተፈፅሞባቸው፣ ቶርች ተደርገው ወኀኒ ተዘግቶባቸዋል፡፡ የፖለቲካና የነፃነት፣ የፍትሕ የእኩልነት፣ ጥያቄ ያነሱ ኢትዮጵያውያን እንዳለሰው ተደርገው ወሕኒ ወርደዋል፡፡ ተሰደዋል፡፡ ተገድለዋል፡፡ አካላቸው ጎድሏል፡፡ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን እንዲሁ ተመሳሳይ ግፍ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን አገራቸው አላስኖራቸው ብላ በስደት የበረሃ አወሬ የባሕር ዓሣ ቀለብ መሆናቸው ሳያንስ በፈላ ውሃ ተገሽረዋል፡፡ ከፎቅ ተወርውረዋል፡፡ የወሲብ ንግድ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በጅምላ ታፍነው አንገታቸውን ሲቀሉ አይተናል፡፡
ብሔራዊ ውርደት በዓለም የታሪክ መዝገብ ተፅፎብናል፡፡ በሙሰናና በብልሹ አሰተዳደር ታንቀናል፡፡ የከተማ ክፉ ችጋር ጠብሶናል፡፡ ወጣቶች ሥራአጥ ተደርገዋል፡፡ እህቶቻችን ጎዳና ላይ ናቸው፡፡ ስንቱ ጉድ ይፃፋል? ትላንት ኢህአፓ እንዲህ ተደረጉ ቀይ ሽብር ታውጆ ትውልድ እና እውቀት አለቀ ብለን በታሪካችን እያዘንን ነው፡፡ የአሁኑ ዘመን ግን እጅግ የከፋ እና የአስተሳሰብ እድገት የተቀጨበት ነው! እናም ሽማግሌዎች እና የኃይማኖት አባቶች ከወዴት ናችሁ? ሀገሬ ኢትዮጵያ እርቅ ያስፈልጋታል? የኢትጵያዊያን የሰቆቃ እና የጣር ጬኸታችንን እያቃሰተ ነው:: የግፍ ፅዋው ሞልቶ ገንፍሏል:: አስርሃለሁ፣ ትገደላለህ፣ ትታፈናለህ፣ ትባረረላህ የገዥዎቻችን የሥራና የመግባቢያ ቋንቋ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!