Friday, April 10, 2015

አዲስ አበባ የጦር ቀጠና መስላለች:: ፖሊስና መከላከያ ፈሰዋል ፡፡MINILIK SALSAWI


ፒያሳ አካባቢ ያየነው ትንሽ ለየት ይላል፡፡ መርካቶን አሊያም ከዛም አለፍ ያሉትን የአዲስ አበባ ክፍሎች በቁጥጥር ስራቸው አውለው ወደ አራት ኪሎ እየገሰገሱ የሚመስሉ ፈርጣማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፒያሳ ላይ ገዥ መሬት ይዘዋል፡፡ መኪና አይቀርባቸውም እንጅ መኪና መንገዱን ግማሹን እነሱ እየተንፈላሰሱበት ነው፡፡ ተቆጣጥረውታል! ደግሞ ኮዳና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሳቸውን ግጥም አድርገው ታጥቀዋል፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንዳለፉ የሚተኩሱ በሚመስል ሁኔታ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይዘውታል፡፡ በተጠንቀቅ! በቃ ፒያሳን የጦር ቀጠና አስመስለዋታል፡፡
ከሶስቱ መካከል አንዱ የሁለቱን ደህንነት ለመጠበቅ በሚመስል መልኩ ወደኋላ ይቀራል፡፡ ሰውንም፣ ወርቅ ቤቶቹንም፣ መኪናዎችንም ዘወር ዘወር ብሎ ያያል፡፡ እንደገና ፈጠን ፈጠን ብሎ ይቀላቀላቸውና በአንድ ላይ ወደቀኝና ግራ እያማተሩ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይነጉዳሉ፡፡
ሌላ ሶስት አባላት ያሉት ‹‹ጋንታ›› ይከተላል፡፡ እነዚህም በተመሳሳይ ሶማሊያ አሊያም ኤርትራ ድንበር ያሉ ነው የሚመስሉት፡፡ ቀኝና ግራ፣ ወደኋና ወደፊት ይቅበዘበዛሉ፡፡ የቆሙ መኪናዎችን ጠጋ ብለው ያያሉ፡፡ አላፊ አግዳሚው ላይ ያፈጣሉ፡፡ ከእነሱ በኋላ ደግሞ ጯፉ እሳት የተቆሰቀሰበት የሚመስለውን ዱላ ከአጋማሹ ላይ የያዙ አራት ‹‹ተራ አስከባሪዎች›› (ካልሲ አባራሪዎች) ይከተሏቸዋል፡፡ ደጀን ጦር መሆናቸውን ነው፡፡
በዛሬው እለት Getachew Shiferaw አዲስ አበባን እንዲህ ቃኛት::
ማሳሰቢያ፡- አብረውኝ ከነበሩት ሁለት ጓደኞቼ ጋር ፎቶ የማንሳት ፅኑ ፍላጎት የነበረን ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ፎቶ ማንሳት ሳይቻለን ቀርቷል!
Image

No comments:

Post a Comment