Thursday, April 16, 2015

ለወራት በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ የቆየው የኮምቦልቻው ወጣት ዘሪሁን ገሰሰ ተለቀቀ.


የጀስቲስ (ዘሪሁን) አድናቂ
የካቲት 13 ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ኮምቦልቻ በመጓዝ ላይ ሳለ ሸዋሮቢት ከተማ ላይ ከተሳፈረበት አውቶብስ ላይ በመንግስት ታፍኖ የተወሰደው የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የኮምቦልቻ የህዝብ ግንኙነትና የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ እንዲሁም የሚሊየኖች ድምፅ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የነበረው በአሁኑ ሰዓት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ ከወራት አፈና በኋላ ሰኞ በ 28/07 / 07 ምሽት ላይ ተለቋል. ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ እጅግ ጠንካራ ፖለቲካዊ አቋም ያለውና ሀገር ወዳድ ሰላማዊ ታጋይ የነበረ ሲሆን በሰላማዊ ትግሉ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችና በአካባቢው ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በስርአቱ የሚፈፀሙ በደሎችን በማህበራዊ ድህረ-ገፆችና የሚዲያ አ ውታሮች በመፃፍ በማጋለጡ ሁኔታው ያልተመቸው አንባገነናዊው መንግስት ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግበት ቆይቶ በህገወጥ መንገድ አፍኖት እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል. ምንም እንኳ ወጣት ዘሪሁን ዝርዝር መረጃዎችን በፓርቲው በኩል ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግና ውስን መረጃዎችን ብቻ የሰጠ ቢሆንም ከአሁን በፊት ሲገለገልባቸው የነበሩት የፌስቡክ አካውንትና ፔጆች እንዲሁም ዌብሳይቶችና የኢሜይል አካውንቶቹ በህገ-ወጥ መንገድ ከተለቀቀ በኋላም በመንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ አልሸሸገም.
ወጣት ዘሪሁን ገሠሠን ያነጋገሩት ምንጮቻችን እንደገለፁት << ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ ከፍተኛ ጥበቃና ምርመራ እየተደረገበት ባላታወቀ ድብቅ እስር ቤት እንደቆየና በቆይታውም የሀሰት ውንጀላን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመበት ያረጋገጠ ሲሆን አጠቃላይ ሁኔታውንና መንግስት በተለይ በሰማያዊ ፓርቲ ብሎም በሰላማዊ ታጋዮች ላይ ለመፈፀም እየተዘጋጀበት ስላለው የሀሰት ውንጀላ ሁኔታና ዝርዝር መረጃዎችን ለፓርቲው አሳውቆ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት ተናግሯል. ከዚሁ ጋር አያይዞም በወጣቱ ሰላማዊ ታጋይ መታሰር ከፍተኛ ቁጭት በማሳደርና ህገወጡን መንግስታዊ አፈና በማጋለጥ; በማውገዝ ከፍተኛ ተፅእኖ ሲያሳድሩ የነበሩ የሚዲያ ተቋማት; እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ-ገፃች መረጃዎችን ለህዝብ ሲያደርሱ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን; ድርጊቱን በቀጥታ በማውገዝ ለማስፈታት ጥረት ያደረጉ የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶችና በአጠቃላይ የህገ-ወጡን መንግስት ሽፍታዊ ተግባር በማውገዝ ስሜታቸውን ለገለፁ ዜጎች ብሎም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የትግል አጋሮቹ ከፍተኛ ምስጋናውን እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል. ወጣት ታጋይ ዘሪሁን ገሠሠ ለቀድሞው አንድነት ፓርቲ እጩ የነበረ ሲሆን ፓርቲው መፍረሱን ተከትሎ ለተለጣፊዎቹ እውቅና አልሰጥም በማለት ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል ለተወካዮች ም / ቤት እጩ የነበረ መሆኑና በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን << >> አንድነት ብለው የሚጠሩት የመንግስት ተለጣፊዎቹ << የእነ ትግስቱ ቡድን >> እና የምርጫ ቦርድ የተለመደ ተባባሪነት በተወሰደ ፖለቲካዊ ውሳኔ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በጣሰ መልኩ ከእጩነት መሰረዙ አይዘነጋም.Kattani Katti their image.

No comments:

Post a Comment