ከኦባማ ቀጥሎ በአሜሪካ ከፍተኛው ደመወዝ ተከፋይ ነበሩ::ከ2ሺ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን አከናውነዋል ወንድሞቻቸው፡- ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን ይባላሉ :: ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኤሌክትሮን ክበበው፤ ለ33ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የ2015 “የዓመቱ የዓለማችን ልዩ ስም” ውድድር ላይ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በቀዳሚነት እየመሩ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ዘንድሮም የተለያዩ አገራት ዜጎችና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ 64 ግለሰቦች ያልተለመዱ ስሞች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ኤልክትሮን ክበበው፤ በ1ሺህ 132 ድምጽ፣ በ89.6 በመቶ ውጤት በቀዳሚነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢሜልና በተለያዩ መንገዶች ከቀረቡለት በርካታ ለየት ያሉ ስሞች 64 ያህሉን በመምረጥ፣ ለአንድ ሳምንት ያህል በድረ ገጽ አማካይነት ድምጽ እንዲሰጥባቸው የሚያደርገው የውድድር ኮሚቴው፤ የመጨረሻውን ውጤት ከጥቂት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ የሰማይ እንሽላሊት፣ ጣፋጭ ቡና፣ ዳላስ፣ ቶክዮ፣ ቴኒስ እና የመሳሰሉ የአገር፣ የቦታ፣ የእቃ፣ የሰብል ወዘተ መጠሪያዎችን የያዙ የተለያዩ አገራት ዜጎች በዘንድሮው ውድድር እንደተሳተፉ አወዳዳሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በመምራት ላይ ለሚገኙት የ47 አመቱ ዶ/ር ኤሌክትሮን ይህን ስም ያወጡላቸው፣ ኤሌክትሪካል ኢንጂነር የሆኑት ኢትዮጵያዊው አባታቸው አቶ ክበበው ነበሩ፡፡ አዲስ አድማስ

No comments:
Post a Comment